Sunday, November 8, 2015

ቅዱስ ሲኖዶስ ያለፈቃድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም በሚዲያ የሚያስተምሩትን በሕግ እጠይቃለሁ አለ

(አዲስ አድማስ ጥቅምት 27 2008ዓ.ም)፡- ቤተ ክርስቲያኒቱ በማታውቀው ሁኔታ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈቃድ ሳያገኙ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ትምህርታዊ ስብከት የሚያስተላልፉ፤ ዝማሬ የሚያሰሙ፤ ጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ ጋዜጦችና ልዩ ልዩ በራሪ  ወረቀቶችን የሚያሳትሙ በአገሪቱ ሕግ እንዲጠየቁ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፤ የሚመለከታቸው የሚዲያ አካላትም ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፤ ብሏል፡፡ 

ሲኖዶሱ ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2008 . 12 ቀናት ሲያካሒድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ 20 ነጥቦች ያሉት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ከሚዲያ ጋር በተገናኘ ሁለት ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ 

የመጀመሪያው፣ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ በስሟ ትምህርታዊ ስብከት ሲያስተላልፉና ዝማሬ የሚያሰሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ያሳለፈው ውሳኔ ሲሆን፤ መግለጫው እኒህን አካላት ለይቶ ባይጠቅሳቸው ምልዓተ ጉባኤው በተወያየበት ወቅት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሃይማኖታዊ ዝግጅት የሚያቀርቡ አካላት በስም መነሳታቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ የቴሌቪዥኑ የፕሮግራሚንግ ኮሚቴ ከጣቢያው ጋር ውል ገብተው በሳምንት አንድ ጊዜ ሃይማኖታዊ ትምህርት ለሚያቀርቡት ለማኅበረ ቅዱሳን፣ ለቃለ ዐዋዲ፣ ለታዖሎጎስ እና ለኤንሼንት ዊዝደም ፕሮግራም ክፍሎች አገልግሎታቸውን የሚደግፍ የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ ከሚመለከተው የመንግስትም ሆነ የሃይማኖት አካል እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡


3 comments:

  1. በቃ ሲኖዶሱ ውሳኔ ቢሰጥ ይመረጣል ግን አንዳንዶች
    ጥላቻን እና ስድብ አስተማሪዎችንም ይገሥፁልን ዘንድ ምኞታችን ነው። እምነታችን ስለማትፈቅድልን።
    ፍቅርን አስተምሩን ስድብና ንቀትን ጥላቻንም ያይደለ።

    ReplyDelete
  2. በቃ ሲኖዶሱ ውሳኔ ቢሰጥ ይመረጣል ግን አንዳንዶች
    ጥላቻን እና ስድብ አስተማሪዎችንም ይገሥፁልን ዘንድ ምኞታችን ነው። እምነታችን ስለማትፈቅድልን።
    ፍቅርን አስተምሩን ስድብና ንቀትን ጥላቻንም ያይደለ።

    ReplyDelete
  3. mlkam zana new !! egzabher amlak yabtochacnn edmna yagalglot gza kmulw tennet gar ystelen !! mcherashawe ysamerlen sntabkw ynber yabtochacen talak wesan ydengle mar yam yasrat legwech bnafkwet sentebekaw ynber new aman!!

    ReplyDelete