Thursday, November 5, 2015

‹‹መምህር›› ግርማ ተጨማሪ የተጠረጠሩበት ወንጀል ይፋ ሆነ

  •  ቤታቸው ላይ በተደረገው ብርበራ ስምንት ሲም ካርዶች ተገኙ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ከሲምካርዶቹ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች እየተጠበቁ ይገኛሉ
  •  ቤተክህነት አቶ ግርማ ሕገ ወጥ አጥማቂ መሆናቸውን የሚያስረዳ ማስረጃዎቿን ለአዲስ አበባ ፖሊስ አቅርባለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 2008 (ኤፍ..)

‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙ አዲስ የተጠረጠሩበት ወንጀል ይፋ ሆነ። ይህ የተጠረጠሩበት ወንጀል ሀሰተኛ ሰነድ መገልገል የሚል ነው ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።
ጥቅምት 23 2008 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ባልሰጠኋቸው የስብከት እና የማጥመቅ ፈቃድ እንደሰጠኋቸው በማስመሰል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በቤተክርስቲያኒቱ ስም ሲያስተምሩ እና ሲያጠምቁ ቆይተዋል በማለት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ይህንን በተመለከተም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያለ ቤተክርስቲያኒቱ እውቅና በህገ ወጥ መንገድ በሀሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ሲያገለግሉ ነበር በማለት ‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙ የተፃፉ ሰባት ቅፅ ደብዳቤዎችን ጠቅላይ ቤተክህነት ለፖሊስ በመሸኛ ደብዳቤ ልኳል። በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ይህንን ምርመራ ለማከናወን 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።


ተጠርጣሪው ‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙ በበኩላቸው ደቡብ ወሎን ጨምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ቤተክህነት ደብዳቤ እየፃፈልኝ ነው ሳገለግል የሰነበትኩት ብለዋል። ጠበቆቻቸውም እንዲሁ ሌላው ቢቀር እሳቸው በቋሚነት በሚያገለግሉባቸው የረር ስላሴ እና ጀሞ ሚካኤል እንኳን ህገ ወጥ ናቸው የሚል በቤተክህነት  የተላከ አንዳችም ደብዳቤ ያለመኖሩን እንዲሁም መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ወንጀል ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ አድርጎ ደንበኛችን የዋስትና መብታቸው ይከበርላቸው ሲል ጠይቋል።

የምርመራ ቡድኑ በበኩሉ የተጠረጠሩበት ወንጀል ሀሰተኛ ሰነድ መገልገል በመሆኑ ችሎቱ የጠበቆቹን ጥያቄ እንዳይቀበል ሲል አመልክቷል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት 1 የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን 7 ቀኑን ፈቅዷል። ውጤቱን ለመጠባበቅ ለህዳር 3 ቀን 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በሌላ በኩል ‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙ ባለፈው ሳምንት ከተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ጋር በተያያዘ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ስራ አለኝ በማለት ከጠየቀው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ አምስት ቀን ብቻ ነው የፈቀደው።

ፖሊስ ድጋሚ ቀነ ቀጠሮ ለመጠየቅ ካቀረበው ምክንያት መካከል ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች አሉ፤ ከቤት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪው ከሚኖሩበት ወረዳ የሰነድ ማስረጃ አልቀረበልኝም፤ ቤታቸው ላይ በተደረገው ብርበራ ስምንት ሲም ካርዶች የተገኙ በመሆኑ ሲም ካርዶቹ በማን ስም የወጡ ናቸው? እና በስልኩ ውስጥ የሚገኙ መረጃዎችን ኢትዮ ቴሌኮም አጥርቶ እንዲልክልን ደብዳቤ ፅፈን ውጤቱን እየተጠባበቅን ነው የሚሉት ይገኙበታል።

በዚህም ላይ የተጠርጣሪው ጠበቆች ሰው ታስሮ ሌላ ሰው ለመያዝ በሚል ተጨማሪ ቀን ሊጠየቅ አይገባም፤ ህጉም አይፈቅድም፤ እና ፖሊስ ምርመራውን ቀደም ሲል ያጠናቀቀ በመሆኑ ባለፈው በተሰጠው 7 ቀን የተጠርጣሪውን ቃል ተቀብሎ ክስ መመስረት ሲገባው ደንበኛችን ያለአግባብ እየታሰሩ ነው ብለዋል። ችሎቱ ከኢትዮ ቴሌኮም የሚመጣውን መረጃ ለመጠባበቅ ከተጠየቀው 14 ቀን 5 ቀን ብቻ ፈቅዷል።

የዚህንም ውጤት ለመጠባበቅ ለጥቅምት 30 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

4 comments:

  1. ይገርማል፡፡ አይ ፖሊስ 8 ሲም ካርድ አወጣ ተብሎ ክስ አለ? ከዚያ በላይ ያላቸው ስንት የሀገራችን ደላሎች እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ አሁን ሲም ካርድ መኖር እሷቸው ከተከሰሱበት ጉዳይ ጋር ምን ያገናኘዋል? ደግሞ የሚገርመው የቤተክህነት ክስ ነው፡፡ እኔ ስለቤተክህነት ጉዳይ መናገር አልፈልግም፡፡ ቤተክህነት እራሱ ችግር በሆነበት ጊዜና ብዙ ወንጀለኞችን ተሸክማ ያለች ተቋም አንድ ሰው ያውም ለቤተክርስቲያኗ ያደረጉት የልማት ስራዎችን ወደ ኋላ አድርጋ ይህንን አገልግሎት በእርግጥ በትክክል ይህንን የሚወራው ወሬ እውነት ከሆነ ጥሩ አይደለም፡፡ የምናውቀው ነገር ግን የለም፡፡ አልሰማንም፣ አላየንም የሰማነው ተባለ፣ ሊሆን ይችላል በሚለው የሀገራችን ቢል ብዙ የሰውን ልጅ እየገደለና እያጠፋ ያለን ነገር ተቀብለን የምንወስነው ነገር እኔ አሁንም ይህ የሚያሳያው ምን ያህል ለውሸትና ሰውን ለመወንጀል ያለንን ቅርበት ነው የሚያሳየው፡፡ ጥላቻችንን ለምን በእንደዚህ መልክ እንገልፃለን???????????????????? ማስተዋል ይስጠን፡፡ ጓደኛህ ሲትማ ለእኔ ብለህ ስማ የሚለውን አባባል በዚህ ጉዳይ ተማርኩበት፡፡ ቤተክህነት ለመሆኑ ዛሬ ወኔ ያገኘችው በእኚህ አባት ነው??????????????? አህያውን ፈርቶ ዳውላውን!!!! አሁን እኔ ስለቤተክህነት ባወራ የአደባባይ ሚስጢር ቢሆንም የቤቴን ገበና በእኔ አፍ መጉደፉን ውስጤ አልተቀበለውም እንጂ ብዙ በተናገርኩኝ፡፡ ስለዚህ ቤተክህነት አያምርባትም ዝም ብትል የሚያዋጣት ይመስለኛል፡፡ ሌላው ቢቀር በግልጽ የረር ስላሴ ቤተክርስቲያንና ጀሞ ቅዱስ ኢራኤል ቤተክርስቲያን የሚያገለግሉትን ሳትሰማ ከቀረች ወይም ቤተክርስቲያኖችን ካላመነችበት ሲጀመር መክሰስ አትችልም፡፡ አለበለዚያ እንደዚህ የሚባል ክስ የለምና የተሸከመችውን ለምጽ ብታጠፋ ይሻላታል፡፡ እርግጠኛ ነኝ የቤተክህነት ከሳሾች ቢጣሩ ወይ ደፍተራ ጠንቋይ ናቸው ወይ ደግሞ መናፍቃን ተሀድሶ ናቸው፤ ወይ ደግሞ በእሷቸው በብዙ ምእመን ዘንድ ተቀባይነት በማግኘታቸው ቅናት ይዟቸዋል፡፡ ከዚህ አያልፍም፡፡ ለቤተክርሲያኗ ደህንነት ግን ታስባ ቢሆን ኖር መጀመሪያ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ፡፡ ወደዳችሁም፣ ጠላችሁም፣ እሷቸው በልጣዋችኋል፡፡ ምክንያቱም ጠንቋይም፣መተተኛም ይሁኑ አይሁን እኔ መረጃው ባይኖረኝም፡፡ ስንት ሚሊየን የሚከተል የአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ምእመን አንድም ጻድቅ በመጥፋቱ መቅደሳችሁን አርክሳችኋል፡፡ ተበልጣችኋል፡፡ ለ38 ዓመት ይህንን አገልግሎት ሰጥቻለሁ ሲሉ ሰምቻለሁኝ፡፡ ማፈሪያ ናችሁ፡፡ አንድም ሰው ግን በእውነት ቆሙ እኚህ ሰው ሊያውቃቸው አልቻለም፡፡ አሁንም ቢሆን በሀሰት፣ በአህዛብ መንገድ ተጉዘው የምንከሰው ነገር ያሳፍራል፡፡ እግዚአብሔርን እንዳናሳዝን፤ አሁንም ቢሆን እየቀረበ ያለው ክስ ምን ያህል ሀሰትን እውነት ለማስመሰል እየተደከመ መሆኑን የሚገልጽ እንጂ እውነታውን ለማግኘት እየተሰራ አይደለም፡፡ ለአረም ደግሞ አይደለም ተንከባክበነው እንዲሁ ይበቅላል እኮ አለ ወንድሜ ዲ. ዳንኤል ክብረት፡፡

    ReplyDelete
  2. ትውልዱን ለምን ሰበሰቡ ነው ?

    ReplyDelete
  3. betekihinet is full of robbers and criminals i the name of theholy Church.Unfortunately, we can't take the leading of the church.Since they are already ordained to serve the church and don't take their responsibility

    ReplyDelete
  4. አንተ ራስህ የዳቢሎስ መልዕክተኛ ነህ አጭበርባሪ፣ማፈሪያ የሰው ድኅነት የሚያበሳጭህ

    ReplyDelete