Monday, November 2, 2015

ሲኖዶሱ በዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ከመንግስት ጎን በመሆን ለመደገፍ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 2008 (ኤፍ..) የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ከመንግስት ጎን በመሆን ለመደገፍ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ። የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ 11 ቀናት ተካሂዶ ዛሬ የተጠናቀቀውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አጠቃላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ 20 ያህል የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳላፈ ሲሆን፥ በተለይ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ቅኝት አድርጎ ቤተክርስቲያኒቱ የበኩሏን ድጋፍ ለማድረግ አብይ ኮሚቴ አቋቁማለች። ከዚህ ውጪ ስርአተ ቤተክርስቲያንን ከማስጠበቅ ባለፈ ሃገራዊ ልማቶች ላይ ተሳትፏዋን ይብልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል ነው ያሉት።

የመልካም አስተዳደር ዕጦትንና የሙስና መስፋፋትን አስመልክቶ ቤተክርስቲያን በተገኘው አጋጣሚ አጥብቃ እንድታስተምር ሲኖዶስ ወስኗል። ቤተክርሰቲያኗ የራሷን ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ሌሎች መልእክቶች ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማስተማር የሚያስችል ፕሮጀክትም መንደፏን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።
ሲኖዶሱ 159 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት አጽድቋል።

No comments:

Post a Comment