Saturday, November 14, 2015

በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለማየት የታሰበ የመጀመሪያ ጉዞ(አንድ አድርገን ህዳር 4 2008 ዓ.ም)፡- ከድርቅ እና ከርሀብ ጋር የተቆራኝ ታሪካችን አሁንም በእኛው ዘመን ተከስቶ ማየት እጅግ ያሳዝናል ፤ ቀድሞ የነበሩት ሁለት ክፉ ጊዜያት በእኛ ዘመን ራሳቸውን ሊደግሙ በመንገድ ላይ ይገኛሉ ፤ የ66 እና የ77 ርሃብ ተብሎ በታሪክ የምናውቀው ጊዜ ራሱን ሊደግም እያኮበኮበ ይገኛል ፤ ከ15 ሚሊየን በላይ ወገን የርሃብ ደመና አደምኖበታል ፤ መንግሥት 8.2 ሚሊየን ሕዝብ አደጋ እንደተጋረጠበት እማኝነቱን ሰጥቷል ፤  አሁን እጅግ አስቸጋሪውን ነገር መንግሥት ‹‹ርሃቡን ከአቅሜ በላይ አይደለም›› በማለት በሚያስተላልፈው ዜና ብዙዎች ብዙ ረድኤት ሰጭዎችን እና በሀገር ውስጥ ያሉትን ሰዎች እያዘናጋ ይገኛል ፤ መርዳት የምንችልበት እውቀት ፤ ጉልበት እና ገንዘብ እያለን መንግሥት በርሃብ የተጎዱ ዜጎችን ራሴ እደርስላችኋለሁ ብሎ መነሳቱ ተጎጂዎቹ ዘንድ እርዳታ በሌላ እሳቤ እና መንገድ እንዳይደርስ አንቅፋት የሆነ ይመስለናል ፡፡ ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ አልጀዚራ እና ቢቢሲ ከመንግሥት ፍቃድ አግኝተው በተለያዩ ቦታዎች ላይ ደርሰው ያቀረቡት ዘገባ ዝናብ እጥረቱ ወደ ድርቅ ፤ ድርቁም ወደ ርሃብ መሸጋገሩን  ፤ እንስሳት በየቦታው በርሃብ ምክንያት እያለቁ መሆኑን ፤ ሰዎችም እየተጎዱ የሚበሉትና የሚጠጡት እስከማጣት እንደደረሱ አመላክተውናል፡፡ 


አሁን ትልቁ ጥያቄ በምን መንገድ የተጎዱ ዜጎች ጋር እንድረስ? የሚለው ነው  ፤ ከቀናት በፊት ከዚህ በፊት በግል ጋዜጦች ላይ የምናውቃቸው ሰዎች ተሰባስበው ለተጎዱ ወገኖች ዘንድ ለመድረስ የባንክ አካውንት ከፍተው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፤ ይህ አይነት አካሄድ ይበል የሚያስብል ነው ፤ ለሌሎችም በየአካባቢው ለሚገኙ ሰዎች መነሳሳት የሚፈጥር ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ 


‹‹አንድ አድርገን›› blog በቅርብ የምናውቃቸውን ሰዎች በማሰባሰብ አሁን የተከሰተውን ችግር ጥልቀት ለመረዳት እና ሕዝቡም እንዲውቀው ለማድረግ ያስችለን ዘንድ አምስት ሰዎችን ያካተተ ቡድን ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ለመሄድና ጉዳቱን ለመመልከት እቅድ የያዝን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ፤ የመጀመሪያው ጉዞ ከሳምንት በኋላ ከህዳር 11 - ሕዳር 19 ለስምንት ቀን ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጉዞ የምናደርግ  መሆኑን በየቦታው ያየነውን የታዘብነውን ፤ በድምጽና በምስል ይዘን የምንቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡  


ራሳችን ራሳችን እንድረስ ….      

6 comments:

 1. እግዚአብሔር ያግዛችው በርቱ መረጃው ግን በተቻለ መጠን ቶሎ ቢፈጥን መልካም ነው

  ReplyDelete
 2. Selam Endemen alechu Egezabehr yerdachu!
  Bamen malku merdate endamenechle asewkun adera

  ReplyDelete
 3. Betam yibel yemiyasegn wegenawi tegbar new.. gin wede misrakum bik maletun atizengu.. Afar ana Harerge betam yetegodu botawoch nachew!

  ReplyDelete
 4. በጣም ጥሩ ነው እግዚአብሔር ያበርታችሁ፤ እኛም የምንረዳበት መንገድ ቢመቻችም መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. እኔ ግን በጣም ያሳዘነኝ የመንግስት መሸፋፈን ነው፡፡ ድርቁ ብዙም እንዳልሆነ ነው እየዘገበ ያለው፡፡ የእኛ ሀገር ጋዜጠኞች የሚያገለግለው ለፖለቲካና ለውጪ ሀገር ዘገባ ነው እንዴ?????????? ለዚህ መንግስትና ለእኛ ሀገር ጋዜጠኞች ምን ይባላል እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋል ይስጣቸው፡፡

  ReplyDelete
 6. ይገርማል፡፡ መንግስት ግን ከህዝብ ይልቅ ፖለቲካውን ያስቀድማል!!!!!!!!!!! አሁን የምንትስዮ በዓል እያለ ቁርጥና ክትፎውን ለፖለቲካ ደጋፊዎቹ አሸሸገዳሜዬ እያለ ልባችንን እያደከመው ነው፡፡ ወገን እየተራበ የእኛ መንግስት ዳንኪራውን ያካሄዳል፡፡ ይህንን ታሪክ ምን ይለው ይሁን????????????? አንድ ወቅት ህዝቡ በርሃ እየሞተ እሳቸው ልደታቸውን አከበሩ ተብሎ ሀይለስላሴ የሚባሉት መንግስት እራሱ ይህ መንግስት ሲወቅስ ነበር፡፡ ይህም መንግስት ከሀይለስላሴ በተማረው መሰረት ህዝብ እየተራበ እርሱ ደግሞ ድግስ በድግስ እያደረገ ከተማውን ሁሉ አናወጠው፡፡ የዚህ መንግስት ጉድ ደግሞ ቀጣይ ትውልድ ይናገረዋል፡፡ መቼም አይቀር፡፡ አባቶቻችን በተረታቸው ከተራበ ለጠገበ ያሳዝናል እንዳሉት ለጥጋበኛው ማብረጃውን ይስጥልን ለረሀብተኞቹ ደግሞ እግዚአብሔር አምላክ ይድረስላቸው፡፡ እናንተን እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ በርቱ፣ ክርስትና ለጠገበ ማብላት ሳይሆን ለተራበ ማብላት ነውና በርቱ፡፡

  ReplyDelete