- አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ከግሪሳዎች ቅርሻት መጽዳት ጀመረ።
- በአሰግድ የተጀመረው በበግ ዋሻውም ይቀጥላል።
- በቅዱስ ዮሴፍ የተጀመረውም በሌሎች አብያተክርስቲያናትም ይቀጥላል።
ፓስተር አሰግድ ባለፈው አርብ ከግብር አበሮቹ ጋር እመቤታችንን፣ቅዱሳኑንም በገዛ ዐውደ ምህረታቸው ለመስደብ አርብ አርብ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የያዘውን መርሀ ግብር እንደተለመደው የክህደት መርዙን ለመርጨት ቢመጣም ፣ ቄስ ሙሴ በተባሉ ካህን አማካኝነት ማስተማር እንደማይችል ተነግሮት መመለስ ችሏል።
ፓስተር አሰግድ ቀሲስ ሙሴን "እባክዎን የዛሬን አስተምሬ ልውረድ። ሁለተኛ አልመጣም፣አያሳፍሩኝ? " ቢልም ፣ ካህኑ ሙሴ ግን አይቻልም ማስተማር አትችልም ፣ አርፈህ ተቀመጥ በማለት በትህትና እርሳቸው ኦርቶዶክሳዊ ስብከታቸውን ሰብከው የእለቱን መርሀ ግብር በሰላም አጠናቅቀዋል።
በዕለቱ አጅበውት መጥተው የነበሩት ግሪሳዎች እንደወትሮው የስብከተ ወንጌሉ ናሁሰናይ ያድነናል ብለው ተስፋ ያደረጉ የነበረ ቢሆንም እሱ ለራሱ መጻኢው ጊዜ የዓለም ፍጻሜ ሆኖበት በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ተጠቅልሎ ለራሱ ይመጣበት ካለው መከራ ያመልጥበት ዘዴ በመፈለግ ላይ መሆኑን በማየታቸው ፣ እንዲሁም የተዋህዶ ልጆችም ጠንከር ብለው በመታየታቸው ድንጋጤና ፍርሃት ውጧቸው ትንፍሽ ሳይሉ ድመት እንዳየች አይጥ መግቢያ አጥተው ፍጥጥ እንዳሉ አምሽተው ወደ ማረፊያቸው አቶ አሰግድን አጅበው ተመልሰዋል ።
ተሃድሶ ላይ እሳት እየነደደ ነው ። ከላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ፣ ከታች ሰንበት ተማሪዎች ፣ ከጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ፣ ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮችና ምእመናን እንዲሁም አሁን አሁን እንደ ካህኑ ሙሴ አይነት አባቶች ካህናት ጠንክረው መነሳታቸው ተሃድሶ የገና ዳቦ ሆኖ እንደሚያርፍ አንጠራጠርም፡፡
እናም ውድ የተዋህዶ ልጆች ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው " በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ
እንድታሳዩ እንመኛለን።" ዕብ 6:11-12 እንዳለ እኛም የተሀድሶያውያንን ሳናስወጣ እረፍት ልናገኝ አይገባንም፡፡
በ2008 ዓም የተሃድሶ ፀሐይ ጠልቃ የተዋህዶ ፀሐይ ፏ ብላ የምትወጣበት ዘመን ይሁንልን፡፡
ዘመድኩን በቀለ
-----//----
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
(መጽሐፈ ሚስጢር)
በ2008 ዓ/ም የተሃድሶ ፀሐይ ጠልቃ የተዋህዶ ፀሐይ ፏ ብላ የምትወጣበት ዘመን ይሁንልን፡፡ አሜን አሜን አሜን፣ በዚህ ጉዳይ ብቻ አንስተን እንጹም፣ እንጸልይ፣ እንስገድ፣ ለመስራት እንነሳ፣ በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መረጃዎችን እንበትን እንደጋገፍ አንድ እንሆን ከዚያ ስራውን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሚሆን ይሰራል ከሁሉም የሚበልጠውን ፍቅርና አንድነት ይኑረን፡፡
ReplyDeletethdeso tofeto ewntgawa twedo orthodox ementachen tenkera sytan afrow ytofwetm wganewchacenm nesh gabtaw and ement and temeket yzan endmenegaz ydengl Maryam yasrat legowch hulw tsff new Amam!!
ReplyDeleteለጊዜው እንጂ የሚያተራምሱት መሰረት ስለሌላቸው የትም አይደርሱም ግን ነቃ ብሎ መጠበቅ ግዴታችን ነው፡፡
ReplyDelete