አንድ አድርገን ጥቅምት 01 2007 ዓ.ም
በካሌብ ብርሃኑ /ግላዊ እይታ/
ማኅበረ ቅዱሳን ምንድን ነው ?
ይህን ለመመለስ ከተመሰረተ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰራ የለውን ሥራ በተጨባጭ መረጃ መገምገም ቀላሉ መፍትሔ ነው፡፡ በብዙ ቦታዎች እንደተገለፀው ማኅበሩ ሲቋቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ተማሪዎችን በመንፈሳዊ ህይወት አንፆ ማሳደግ በዓለማዊውም ትምህርታቸው ጠንካራ ኦርቶዶክሶችን ማፍራት በዚህም በስነ ምግባር የታነፁ ዜጎችን ለ ኢትዮጵያና ለ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ማበርከት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተማሩ ሰዎች ስብስብ እንደመሆኑም መጠን ቤተ-ክርስቲያኗ በተለይም ገዳማቶቿ የእውቀት እና የነገ ቤተ-ክርስቲያን መሪዎች መፍለቂያ እንደመሆናቸው መጠን ከ እርዳታ እና ከ ጥገኝነት ተላቀው እራሳቸውን የሚችሉባቸውን ፕሮጀክቶች በመንደፍ እና ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም የተዘጉና የተዳከሙ የ አብነት ትምህርት ቤቶችን በማጠናገር እና በማስከፈት መምህራንና ተማሪዎችንም ስፓንሰር በማድረግ ለተፈለገው የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት እንዲበቁ የማድረግን ስራ መስራት ነው፡፡ ማኅበሩ ሲቋቋም እንደ ሌሎች ማኅበራት በሰዎች ስምምነት ብቻ ሳይሆን በቤተ-ክርስቲያኗን ከ አምላክ ቀጥሎ የመጨረሻ አዛዥ በሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ደንብ እና ቡራኬ የተሠጠው ፤ ለዚህ አገልግሎቱም ከቤተ-ክርስቲያኗ መዋቅር ስር ሆኖ የሚያገለግል የ አገልጋዮች ማኅበር ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ግን ይህ ከላይ የተገለፀው ብቻ አይደለም ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ እንደመሆኑ አንፃር በብዙ አባቶች እንዲሁም አገልግሎቱን ቀና እንነት በተገነዘቡ ሰዎች “የቤተ-ክርስቲያን የችግር ጊዜ ልጅ” የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል፡፡ ይህ የተባለበት ምክንያት ደሞ አጽራረ ቤተ-ክርስቲያኖች የመነኩሴ ቆብ ለብሰው ህዝቡን ሊያወናብዱ “ቤተ-ክርስቲያኗ አርጅታለች እናድሳታለን” እያሉ በየአዳራሹ በሚበጠብጡበት ጊዜ ተከታትሎ ጉዳዩን ለቤተ-ክርስቲያኗ የበላይ አካላት (ቅዱስ ሴኖዶስ) በማስረጃ በማቅረብ አባቶች ውሳኔ እንዲሰጡ በማድረጉ እና አለማዊውን ትምህርት በከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያጠናቀቁ ክህናት ምሁራንን ለ ቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎት በማቅረቡ ነው ፡፡ ይህ ደሞ ኢንጅነሮቻችን በነፃ ዲዛይን በሚያደርጓቸው ቤተ-ክርስቲያኖች ፤ ምሁራኖቻችን በሚያቀርቧ ቸው የጥናት እና ምርምር ስራዎች ውስጥ የሚታይ መሬት ላይ የወረደ እውነት ነው፡፡
በአሁኑ ስዓት ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ይህ ማለት ብቻ አይደለም ምክንያቱ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ከ አገልጋዮች ስብስብነት ወደ እሳቤ (ideology) አዊነት ስለተሸጋገረ ነው፡፡ ይህን ስል ምን ለማለት ፈልጌ እንደሆነ በምሳሌ ልግለፅ ፡-
ከጥቂት ወራቶች በፊት እንዲህ ሆነ በአውሮፓ ሀገር የምትኖር እህት በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ከኦርቶዶክሳዊ ስርአት ውጪ የሆነ ስራ ሲሰራ አይታ “ለምንድነው እንደዚህ ሚሰራው ከአባቶች ያልወረስነው በመፅሐፍም ያልተፃፈ ከቤተ-ክርስቲያናችንም ትውፊት ውጪ የሆነ ሥራ ለምን ይሰራል?” ብላ ትጠይቃለች በዚህ ሰዓት ይህቺ እህት አንቺ እማ ማኅበረ ቅዱሳን ነሽ ሚል ታፔላ ይለጥፉባታል ፤ ማኅበሩ ከነመፈጠሩ የማታውቀው እህት ይህ የተሰደብኩበት ማኅበር ማን ነው ብላ ማፈላለግ ትጀምራለች በመጨረሻም ወደ ኢትዮጵያ በምትመጣበት ወቅት ብዙ ጥናቶችን በማኅበሩ ላይ ካደረገች በኋላ ወደ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቀርባ የታማሁባችሁ እናንተ የቤተ-ክርስቲያን ተስፋ ናችሁ በማለት ቤተ-ክርስቲያን ሥርዓት ሚፈፀምባቸውን መንገዶች እንድ ማሳያ ፕሮጀክት በመንደፍ የፕሮጀክቱን ማስፈፀሚያም አስተዋፅኦ በማድረግ ወደ አገልግሎቱ ገባች፡፡ ከዚህ ታሪክ የምንረዳው ነገር ስርዓት ሲጣስ የሚጠይቅ ፤ ስለቤተ-ክርስቲያን ፍቅር ልቡ የሚነድ እና ሲለሚፈፀምባት በደል የሚታመም መፍትሄም የሚፈልግ ሰው እሱ ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነው ወደሚል መደምደሚያ እየተዞረ መሆኑን ማሳየት ነው ይህ ደሞ በማኅበሩ አባላቶች የተገለፀ ሳይሆን ፤ በግልባጩ ቤተ-ክርስቲያኒቷን ለማውደም ከሚንቀሳቀሱ አካላት የመጣ እውነታ ነው፡፡
የማኅበሩ የመጨረሻ ግብ
የማኅበሩ የመጨረሻ ግብ ምንድነው ወደሚለው ጥያቄ እንዙር ፤ ማኅበሩ በግልፅ እንዳስቀመጠው “ቤተ-ክርስቲያን የመሪነት ቦታዋን ማስመለስ” ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው ብዙ ሰዎች ይህን ሲሰሙ ሊደናገጡ ይችላሉ ፤ አንዳንዶችም በስልጣናቸው የተመጣባቸው ሰለሚመስላቸው ማኅበሩን ለማጥፋት ጉድጓድ ሲቆፍሩ ይታያሉ (አጥልቃችሁ አትቆፍሩት ….) ፤ ቤተ-ክርስቲያንን የመሪነት ቦታዋን ማስመለስ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባጭሩ ላቅርብ፡፡
ቤተ-ክርስቲያን በቀደምት ዘመናት የነበራት ቦታ አለ ይህም የተሰሚነት ፤ አገርን የማገልገል ፤ “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጓቸው” የሚለውን የአምላኳን ትእዛዝ መፈፀም ፤ በልማትና እርዳታ ከፍተኛ ቦታ ላይ መድረስ ወደምትችልበት ቦታ ማድረስ መቻል ማለት ነው፡፡
ታዲያ ይህን ማኅበር ሚገዳደሩት እነማን ናቸው ?
1. መንግሥት ፡- መንግሥት እንደ አስተዳዳሪነቱ ሁሉም ነገሮች (በተለይም የምሁራን ስብስብ) ያስፈራዋል በተለይ ደግሞ ብሔር ተኮር ለሆነ የገዢ ስርዓት ስለ አንድነት የምታስተምር ቤተ-ክርስቲያን ፈተናው ነች፡፡ ለዚህም ማሳያው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእስራኤላውያን ዘር ቢመጣም በፊቱ ቀለም ሳይሆን ባፈሰሰው ደም አለምን አድኗል፡፡ መልካችን ቢለያይም ደማችን ግን አንድ ነው ብላ ማስተማሯ መንግስት ከበረሃ ጀምሮ ጥርሱ ውስጥ እንድትገባ አደርጓታል፡፡ ይህን አስተምህሮቷን ለማዳከም በሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ ደሞ ቤተ-ክርስቲያኒቷን ሊያጠናክሩ የሚችሉ አካላትን ማጥፋት ካልተቻለ ማዳከም ሁነኛ መፍትሔው ነው፡፡
2. አፅራረ ቤተ-ክርስቲያናት፡- እነዚህ አካላት ደሞ ቤተ-ክርስቲያኗን ለማፍረስ ምእመናኖቿንም ለመረከብ ብዙ የሚለፉ የእምነት ድርጅቶች ናቸው፡፡ በተለይም በቤተ-ክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ በመግባት ተሐድሶን እናደርጋለን የሚሉ ቅጥር ፕሮቴስታንቶች ሲሆኑ በኦርቶዶክስ ማልያ ለሌላ ቡድን ሚጫወቱ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት የሉም እያሉ በየቦታው ቢያስነግሩም በየእጆቻችን ያሉት መረጃዎች ይህን አያመላክቱም፡፡ ይባስ ብለው እነዚህ ሰዎች መፃህፍትን እና ቪዲዮችን በመልቀቅ አለን እናድሳታለንም እያሉ ሲፎክሩ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደነበራቸው እቅድ በ ሚሊኒየሙ (2000 ዓ.ም) ሙሉ በሙሉ ቤተ ክርስቲያኗን እንረከባታለን ብለው እቅድ ቢያወጡም ሊሳካላቸው አልቻለም ፡፡ የዚህን ምክንያትም ሲናገሩ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል የወጣት ምሁራኖች ስብስብ እንቅፋት እንደሆነባቸው ያስረዳሉ በመሆኑም በሚቀጥለው ስትራቴጂያቸው በቻሉት አቅም ቤተ-ክርስቲያኗን ለመረከብ ማኅበሩን ማጥፋት ካልቻሉ ደግሞ ማዳከም ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡
3. ጥቅማቸው የተነካ የቤተ-ክርስቲያኒቷ አካላት ፡- እነዚህ አካላት ቤተ-ክርስቲያኒቷ ላይ ኑራቸውን ጥገኛ ያደረጉ ነገር ግን ከሚገባቸው በላይ የቤተ-ክርስቲያኒቷን ንብረት ለመቀራመት የሚተጉ ፤ ምንኩስናን እና ቅስናን ክፍት የስሥራ ማስታወቂያ ያደረጉ የቤተ-ክርስቲያኗ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ከሰበካ ጉባኤ አባልነት እስከ ቤተ-ክርስቲያኗ ከፍተኛ የስራ አመራር ደረስ የተሰገሰጉ ቡድኖች ሲሆኑ ፤ ማኅበሩ እያደረገ ያለው አገልግሎት የነሱን ጥቅም የነካ (የሚነካ) የመሰላቸው (የነካባቸው) አካላት ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የማኅበሩን አገልጋዮች ባዩ ቁጥር “ባለ ድግሪው ሊቀድስ መጣ” እያሉ ሚጨነቁት ምክንያቱ ደሞ የማኅበሩ አገልግሎት መርህ ቤተ-ክርስቲያንን በገንዘብ በጉልበት እና በእውቀት ማገልገል በመሆኑ ሚሰራቸው እያንዳንዳቸው አገልግሎቶች ለቤተ-ክርስቲያን በነፃ ሚደረጉ ሲሆን እነዚህ አካላት ደሞ በቤተ-ክርስቲያኗ ተከፋይ (ሊያውም ከሚገባቸው በላይ) በመሆናቸው ነው፡፡ ተከፋይ ስል በቤተ-ክርስቲያን በአገልግሎት ለሚሳተፉ መደበኛ አገልጋዮች ሚከፈላቸውን ደሞዝተኞች አለመሆኑ ይተወቅልኝ፡፡ ይልቅስ አንዲት ፕሮጀክት ለመተግበር የአስር ፕሮጀክት ብር የሚበሉትን ለማጠየቅ ነው፡፡ እናም እነዚህ አካላት ተደላድለው የቤተ-ክርስቲያኒቷን ሃብት ለመብላት ማኅበሩን ማጥፋት ካልቻሉ ደግሞ ማዳከም ሁነኛ መፍትሔአቸው ነው፡፡
4. ማኅበሩን ባለማወቅ እንቅፋት የሚሆኑ፡- እነዚህ አካላት ስለማኅበሩ ምንም ባለማወቅ ወይም ከላይ የተገለፁትን አካላት እንደ መረጃ ምንጭ በመውስድ ለማኅበሩ እንቅፋት የሚሆኑ አካላት ናቸው፤ በዚህ ምክንያትም አንዳንዶች ማኅበሩን የተሐድሶ መነሻና መድረሻ አድርገው የሚያስቡ ሆነዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ማኅበሩ ከ ሰንበት ት/ቤቶች ጋር ፉክክር የገባ የሰንበት ት/ቤቶችን ለመብለጥ (ለማዘዝ) የተቋቋመ እየመሰላቸው ማኅበሩን ለመጣል ብዙ ሲለፉ እናያቸዋለን፡፡ እነዚህ ወገኖች ሁላችንም አንዲት ቤተ-ክርስቲያን ለመገንባት የምንጥር መሆናችንን አልተረዱም፡፡ ይልቅም ማኅበሩ ከብዙ ሰንበት ት/ቤቶች ጋር በ ጋራ ስለሚሰራቸው ስራዎችም እንዲሁም ሰንበት ት/ቤቶችን ለማጠናከር የሚሰራውን ስራ አልተገነዘቡም፡፡ የዚህም ማሳያው የሰንበት ት/ቤቶችን መጠናከር ሲመለከቱ “እሰይ ከማኅበሩ ቅዱሳን እየበለጡ ነው” እያሉ በየመድረኩ የሚሰጡት ያላዋቂ አስተያየት ነው፡፡
ይህን ያህል ማኅበሩን ሊያጠፉት (በማወቅም ሆነ ባለማወቅ) ስለሚጥሩት አካላት ከገለፅን እውን ማኅበሩን ማጥፋት ይችላሉ ወይ? ወደሚለው የመጨረሻ ጉዳይ እንሂድ፡፡
ማኅበሩን ሊያጠፉት አይችሉም!!!፡፡ እንደምን እንደማይችሉ በትንሹ ልግለፅ ፤ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ማኅበሩ አሁን የአገልጋዮች ስብስብ ብቻ ከመሆን ዘሎ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤ (ideology) ወደ መሆን ተሻግሯል፡፡ እነዚህ ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳናውያን ብለው ሚያስቡት በአባልነት የተመዘገቡትን ከ 60,000 በላይ አባላት ሊሆን ይችል ይሆናል ነገር ግን አሁን ከዛም አልፏል ፤ ማኅበረ ቅዱሳናዊነት በያንዳንዱ ለቤተ-ክርስቲያን ይገባኛል በሚል ኦርቶዶክሳዊ ውስጥ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ቤተ-ክርስቲያኔን ባለኝ ነገር ሁሉ ላገልግል በሚል ኦርቶዶክሳዊ ውስጥ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህን ደሞ ተቋሙን በማፍረስ ማጥፋት የሚቻል አይደለም ፤ ብዙዎች ማኅበሩ አሁን ካለበት የአደረጃጀት ስርአት ቢበተን የልባቸው ሚሳካ ይመስላቸዋል፡፡ በጣም ትልቅ ስህተት ነው ፤ ምክንያቱም አሁን እንደሚታየው ማኅበሩ ላይ ያሉት አባላት በአንድ መዋቅር ስር የተሰበሰቡ ናቸው ይህ ደሞ ተወደደም ተጠላም ለነዚህ አገልጋዮች የሚያስቀምጥባቸው ድንበር (limitation)
አለ፤ ይህን መዋቅር መበተን ግን እነዛን ሰዎች ያለ ምንም ድንበር አገልግሎት ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ሌላ ትልቅ የአገልግሎት በር መክፈት ነው፤ ይህ ደሞ እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ወደ ቤተ-ክርስቲያን እንዲመለስ እና በትጋት እንዲያገለግል የሚያደርግ ጥይት መተኮስ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ሊፈፀም የሚችለው አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው እያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት እና ሰበካ ጉባኤ ማኅበረ ቅዱሳናዊ እሳቤን ወደመያዝ ይዞራል ያኔ “በተንን” የሚሉት መዋቅር ሺ ጊዜ ጠንክሮ እና አብቦ ይመጣል፡፡ (it’s just a win win scenario)
በመጨረሻም ፡- ከዚህ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በማኅበሩ ላይ የሚደረገውን “የማጥፋት” (ማጥፋት ካልነው) እንቅስቃሴ በመመርኮዝ በስሜታዊነት ወይም በዓላማ የራሳቸውን የግል አጀንዳ ማስፈፀሚያ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ አካላት ከዚህ ሥራቸው እንዲቆጠቡ እጠይቃለሁ፡፡ ማኅበሩ ያሉትን አባላት በማየት መሬትን አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ የምትጠይቁ ወገኖችን ማኅበሩ ከሚገዛባቸው መተዳደሪያ ደንቦቹ መካከል በማንኛውም አይነት ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አለመሳተፍ መሆኑን ተረድታችሁ ማኅበሩን ለቀቅ ብታደርጉት እላለሁ፡፡
Thank you it's Nice observation
ReplyDeleteማኅበሩ አሁን የአገልጋዮች ስብስብ ብቻ ከመሆን ዘሎ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤ (ideology) ሆኖል የምትለው አስተሳሰብ 1997 ቅንጅት መንፈስ ሆኗል ከሚለው አስተሳሰብ ጋር ይዛማዳል ከእግዚአብሄር ከሆናችሁ ማንም አያጣፋችሁም ካላሆናቸኁ ግን ትጣፋላቸሁ
ReplyDeleteየማጥፋት ሙከራው በአንተ ይጀመራል ማለት ነው? ሞክረው እና ማን እንደሚጠፋ እናያለን።ለሥጋዊ ኑሩየ እኔ እየሮጥኩሁ ማህበሩ ሥለኔ ብዙ እያሰራ መቸ ይሆን እንደነሱ ለመልካም ነገር እኔም የምተጋው እያልኩ ነበር። አሁን ጊዜው መድረሱን ተገነዘብኩ። ለራሴም ለሌላውም ህይወት መልካምነት ማህበሩን አሁን ለመቀላቀል ወሰንኩ። አምላካችሁ ያድናችሁ ከተባሉት ጋር ህበረት መፋጠረ ጊዜው አሁን ነው።
DeleteEgziabehar mehabern ytebk
ReplyDeletemalefiya new. egziabher yistlin
ReplyDeleteማኅበሩ ቤተ-ክርስቲያኔን ባለኝ ነገር ሁሉ ላገልግል በሚል ኦርቶዶክሳዊ ውስጥ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡
ReplyDeleteማኅበሩን እንደ ተቋም፣ እንደ ጽ/ቤትና እንደ ድርጅት ማፍረስ ቀላል ነው፤ እንደ አስተሳሰብ፣ እንደ አመለካከት፣ እንደ የአገልግሎት መሥመርና አተያይ ግን ማፍረስ አይቻልም፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በማፍረስ የሚጀመረው አጥር ንቅነቃ ግን መጨረሻው ሲኖዶሱን በማደንበሽ እንዳይጠናቀቅ ያሰጋል፡፡ ባለቤቱን ካልናቁ ነውና፡፡
ReplyDeleteማኅበሩ ያሉትን አባላት በማየት መሬትን አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ የምትጠይቁ ወገኖችን ማኅበሩ ከሚገዛባቸው መተዳደሪያ ደንቦቹ መካከል በማንኛውም አይነት ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አለመሳተፍ መሆኑን ተረድታችሁ ማኅበሩን ለቀቅ ብታደርጉት እላለሁ፡፡
ReplyDeleteይህ ጉዳይ የማህበሩ ጉዱይ አይደለም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው የቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆንን ሁሉ መከፈል ያለበትን መስዋእት እንከፍላለን እግዚአብሄር ይርዳን አሜን
ReplyDeleteOh, great! God bless you!!
ReplyDeleteEgziabeher mahiberun yetbiklen
ReplyDeletemahberu wusit yetesegesegu poletikegnoch alu.mengistin bemekawem kechalum mengistin lemenad alama yalachew.enezih wegenoch kehaymanotegnoch meleyet alebachew wanaw chigir yih yimeslegnal
ReplyDelete……….ስጋህን የሚገድለውን አትፍራ ነፍስህን የሚገለውን ፍራ…….ተብለናልና አንፈራም አንረበሽምም የሚመጣውን ለማየት ያብቃን… ….. …… ……..
ReplyDelete.....tseleyu beneteselame betekeresetiyan...
ReplyDeleteHULUM LEBEGO NEW
ReplyDeletebeseferut kuna mesefer ayikerim
ReplyDeleteእናቴ ማርያም የጠላትን አይነ ልቦናውን አሳውሪ፡፡
ReplyDelete