Friday, October 17, 2014

የቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረትን ከ‹‹ድምጻችን ይሰማ ›› አይነት ኦርቶዶክሳዊ ካልሆነ አካሄድ መጠበቅ የሁላችን ሃላፊነትና ግዴታ ነው፡፡

  • “ ተግዳሮቶቼን የምፈታው በምክክርና በጸሎት ነው፡፡” – ማኅበረ ቅዱሳን (አዲስ አድማስ፤ ሚያዝያ ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
አንድ አድርገን ጥቅምት 8 2007 ዓ.ም
በቅርቡ ፓትርያርኩ እና አጋሮቼ የሚሏቸው ሰዎች የፈጠሩት ስም ማጥፋትን በተመለከተ ብዙ የእምነቱ ተከታዮች ስሜታቸው እንደተነካ እና ፓትርያርኩ እየሰሩት ያለው ስራ አግባብነት እንደሌለው ከበታች ምዕመን ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ድረስ ተቃውሞ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ስሜ ያለ አግባብ ጠፍቷል ያለው ማኅበረ ቅዱሳንም ጉዳዩን አገልግሎቱን በቤተክርስቲያኒቱ ጥላ ሥር ሆኖ እንዲያካሂድ ለፈቀደለት ለቅዱስ ሲኖዶስ በማቅረብ ምላሹን እየተጠባበቀ መሆኑን ከመግለጹም በተጨማሪ በቀጣይ ያለ ምንም ማስረጃ ይሁን መረጃ ጆሮ ስላገኙና አጨብጫቢ ስለከበባቸው ብቻ በማኅበሩ ላይ ለሚደረግበት ስም ማጥፋት በሕግ እንደሚጠይቅም ለቅዱስ ሲኖዶስ በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ይህን የወቅቱን አጀንዳ ከድጥ ወደ ማጥ ለመቀየር የሚፈልጉ መቀመጫቸውን ከሀገር ውጪ ያደረጉ ፤ ላያቸው መንፈሳዊ ሲፍቋቸው ፖለቲካዊ ርዕዮትን የሚያራምዱ ሰዎች ‹ማኅበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው።›› የሚል ጽሑፍ በ facebook ፤ በ twitter እና በሞባይል sms መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ እና ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በጎ ሥራ ለመመስከር እንዲቻል ይህ መልዕክት ለሁሉም ማዳረስ ሐይማኖታዊ ግዴታችን ነው ፡፡›› በማለት ከላይ ሲመለከቱት ሐይማኖታዊ ውስጠ ፖለቲካዊ የሆነ መረጃ በማስተላለፍ ላይም ይገኛሉ፡፡ ማኅበሩም ይህን በመመልከት ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንዳልጠራ ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶስ በማቅረብ ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን በድረ-ገጹ አሳውቋል፡፡

መልዕክቱ እንዲህ ይላል፡-
የኢሕአዴግ መንግስት እና በቤተክህነት ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የተዋህዶ እምነትን የፖለቲካ አሽከር ለማድረግ የጀመሩትን ሴራ እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም በድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ እና በእኔም ለእምነቴ በብስለት እና ብልሃት በተሞላበት ሁኔታ በጋራ የተዘጋጀ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ሊካሄድ እንደሆነ እና ምእመናን ለዚሁ ንቅናቄ እንዲዘጋጁ ጥሪው ተላልፏል።

ስለዚህም የፊታችን እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ/ ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ፤ ማኅበረ ቅዱሳን የሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ ‹‹የቤተክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አለመሆኑ የምንመሰክርበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡በዕለቱም ምእመናን ምን ማድረግ እንዳለብን በቀጣይ ቀናት የሚገለፅ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ እና ስለ ማኅበረቅዱሳን በጎ ሥራ ለመመስከር እንዲቻል ይህ መልዕክት ለሁልም ማዳረስ ሐይማኖታዊ ግዴታችን ነው ፡፡

‹አንድ አድርገን›  ይህን ጥሪ አጥብቃ ትቃወማለች ፤ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የማይበጅ ፤ የተፈጠረውን ችግር የሚያባብስ ፤ የተከሰተውን ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ የሚወስድ ሕገ ወጥ ጥሪ በመሆኑ ፤ ‹‹ድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ›› የሚለው ጥሪ ምዕመኑን ለማያስፈልግ ሁካታ እና ብጥብጥ የሚዳርግ በመሆኑ ‹አንድ አድርገን› ዳግም አጥብቃ ትቃወማለች፡፡

ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝው የማንኛውም እምነት ተከታይ ፤ የፖለቲካ ድርጅት ፤ የተደራጁም ሆኑ ያልተደራጁ ማኅበራት በሚፈልጉት ጉዳይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዳላቸው ሕገ መንግሥቱ ይጠቅሳል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግም ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ጥያቄ በማቅረብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደሚችሉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን ወደ መሬት የሚያወርዱ መመሪያ እና ደንቦች እንዳሉም ይታወቃል፡፡ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ የሕዝብ መሰብሰቢያ በአላትን እየጠበቁ ስውር አጀንዳ እየቀረጹ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድን ባሳለፍናቸው ሦስት ዓመታት በአይናችን ለመመልከት ችለናል፡፡ ስለዚህ ይህን የመሰለ ሕገ ወጥ ጥሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተገን በማድረግ መጥራት ሕገ ወጥ አካሄድ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

ችግራችን የሚፈታው በጸሎት እንጂ በሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ነው የሚል እምነት የለንም፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ  የሥም ማጥፋት የተካሄደው በፓትርያርኩ ሰብሳቢነት በተመራ ስብሰባ እንጂ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ስብሰባ ስላልሆነ እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ፤ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ የሚያሳውጅ እና የሚያስወጣ ስም ማጥፋት ነው ብለንም አናምንም፡፡

በመጨረሻም እሁድ ጥቅምት 9 2007 ዓ.ም በቅድሥት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚካሄደው ብፁዓን ሊቃነጳጳሳትን በሥጋ ሞት የተለዩትን ፀሎት የማሰብ እና የፍትሐት ስነ-ስርዓት  ፤ የአቡነ ጳውሎስ ሀውልት ምርቃት ያለምንም ችግር እንደሚከናወን ‹አንድ አድርገን› ሙሉ እምነት አላት፡፡ ምዕመኑም ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ከሚል ፖለቲካዊ ከሆነ አካሄድ ራሱን እንዲጠብቅ ተባባሪም ሆኖ እንዳይገኝ በዚህ አጋጣሚ መልዕክት ለማስተላለፍ ትወዳለች፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አውደ ምህረትን ከዚህ አይነት ኢ-ክርስቲያናዊ ከሆነ አካሄድ የመጠበቅ ኃላፊነት የሁላችንም መሆኑን መዘንጋትም የለብንም፡፡

እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን ጠላቶችን ያስታግስልን ፤
 የአባቶቻችንን ጉባኤ ይባርክልን፡፡ 

አሜን

8 comments:

  1. some times, u give matured views. Keep that up.

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው አይዞአችሁ ያው ፈተና አለ አይደለም።የሚገርመን ባንፈተን ነበር ያለ ነው ፈተናውን የምናልፍበት ጉልበት ሃይል ጥበብ እውቀት እግዚአብሄር ይሰጠናል።ቤተ ክርስቲያን መከራና ፈተና አጥቷት አያውቅም።የእግዚአብሄር ረደኤት አለየን!!!!

    ReplyDelete
  3. የቤተ ክርስቲያንን አውደ ምህረትን ከዚህ አይነት ኢ-ክርስቲያናዊ ከሆነ አካሄድ የመጠበቅ ኃላፊነት የሁላችንም መሆኑን መዘንጋትም የለብንም፡፡

    ReplyDelete
  4. Ene gin mahiberun wede lela telefelofosh lemasegebat ena wede wetemedachew lemasegebat yetaleme program yemeselegnal silezih. kom belen enasebebet....bekiyewo ele tafekirewo le Kidist Betekirestian we leele Maheberene Mahibere kidusan...

    ReplyDelete
  5. ችግራችን የሚፈታው በጸሎት እንጂ በሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ነው የሚል እምነት የለንም፡፡

    ReplyDelete
  6. "ይህ በእንዲህ እያለ በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ይህን የወቅቱን አጀንዳ ከድጥ ወደ ማጥ ለመቀየር የሚፈልጉ መቀመጫቸውን ከሀገር ውጪ ያደረጉ ፤ ላያቸው መንፈሳዊ ሲፍቋቸው ፖለቲካዊ ርዕዮትን የሚያራምዱ ሰዎች ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው።›"

    Andadrgen, you mentioned the above statement in the above post. How do you know it is organized by Diaspora? Have you ever think that it might be organized by Woyane to dismantle MK? Please look things from different angle.

    ReplyDelete
  7. ውድ አንድ አድርገን በርግጥ ይህን ያህል ደግሞ ሊያስፈራን የሚችል ነገር መሆን የለበትም ብዬ ነው ያማምነው፥ ምክንያንቱም እኛ ኦርቶዶክሳዊያን እስከ ዛሬ ድረድ የተለያዩ የውስጥ ካድሬዎች በሚነግሩን ተቀብለን ነው እየሄድን ያለንው ለዚህም ይመስለኛል እምነታችን በእጅጉ እየተሸረሸረች ያለችው።
    ውድ አንድ አድርገን፡-
    እውነት አንተ እንዳልከው ከሆነ በዘመናችን ሰማዕታት የሚባሉትን ልናገኝ ቀርቶ ገድላቸውንም ልንሰማ እንደማንችል ነው፡ የቀደሙት አባቶቻችን ከአላውያን መንግሥታት ጋር፣ እምነት ከሌላቸው መሳፍንት ጋር ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ይህቺን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ለእኛ በምንም ለእኛ እንዳላስረከቡን ትረዳላችሁ ብዬ እገምታለው፣ አባቶቻን ማራራ የሞትን ጽዋ የተጎነጩት ስለእምነታቸው ነው ስለ ሃይማኖታቸው ነው ነገር ግን ግድ የለም የዛሬን እናሳልፈው ቢሉ ኖሮ ዛሬ እኔና አንተ አንገታችንን ቀና አድርገን የምናምናትን ተዋሕዶ ሃይማኖት ባልኖረች ነበር። ስለዚህ ስለሃይማኖቴ ስለምን አልቆምም ምናልባት ማኅበሩ የራሱ ለዘብተኛ አካሄድ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ዛሬ ስለማኅበሩ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ እየተደረገ ያለውን ግፍና አፈና በምንም ይሁን በምን የምንገልጽበት መድረክ መኖሩ በእጅጉ ተፈላጊ ነው። ትላንት እኮ በርካታ ካህናቶች ዓይናቸውን ተስረው ወደ ገደል ተወርውረዋል፣ ቤተክርስቲያን ምዕመናኗን በውስጧ እንደያዘች ተቃጥላለች፣ ገዳማት ተመዝብረዋል፣ ገዳማውያን ቆባቸውን በማውለቅ ተደብድበዋል ተገርፈዋል፣ ሊቃነ ጳጳሳት ከቤታቸው ተሰብሮ ተደብድበዋል ለሞትም ተዳርገዋል ታዲያ እኛ ምኑን እምነት አማኞች ነን?
    ፖሊ ካርፐስ የሚባል የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብሞት የጽድቅ አክሊል አገኛለው በማለት በድፍረት ዓላውያን በሰለጠኑበት ዘመን ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ይመሰክር ነበር። አንድ ቀን ግን የሮማ ወታደሮች ይሄንን ሰው አምጥታችሁ ስቀሉት ተብለው ተላኩ፣ እርሱ ጋር ሲደርሱ ተዘጋጅቻለው የጽድቅ አክሊል ወደምቀዳጅበት ወሰዱኝ በማለት እጁን ሰጣቸው ነገር ግን የእርሱ ተከታዮች "አባታችን እኛ እናውቅሃለን የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆንክ" " ለዛሬ እግዚአብሔር የለም በል እና ከሞት ትረፍልን" ብለውት ነበር ነገር ግን ፖሊ ካርፐስ ይሄን ያህል ዘመን ስኖር አንድ ቀንም ክዶኝ የማያውቀኝን አምላኬን እንዴት ላንድ ቀን ብዬ እክደዋለሁ ይልቁንም ወደ እርሱ ለመሄድ ናፍቂያለሁ እና እባካችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ አምላኬን መቼም ቢሆን አልከዳውም ብሎ ነበር በክብር መራራውን የሞት ጽዋ የጠጣው።
    እኛስ ዛሬን እናሳልፋት ምክንያቱን አሳሪዎች እና ገዳዮች ስላሉ . . .

    ReplyDelete
  8. ውድ አንድ አድርገን በርግጥ ይህን ያህል ደግሞ ሊያስፈራን የሚችል ነገር መሆን የለበትም ብዬ ነው ያማምነው፥ ምክንያንቱም እኛ ኦርቶዶክሳዊያን እስከ ዛሬ ድረድ የተለያዩ የውስጥ ካድሬዎች በሚነግሩን ተቀብለን ነው እየሄድን ያለንው ለዚህም ይመስለኛል እምነታችን በእጅጉ እየተሸረሸረች ያለችው።