Wednesday, October 8, 2014

ፓትርያርኩ ማኅበሩን ለጅብ ሊያስበሉት ነው

                                                              አንድ አድርገን መስከረም 30 2007 ዓ.ም
  
  • ‹‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው›› አቡነ ማትያስ
  • ከገዳማትና ከአድባራት የተወከሉ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ግን ሕንፃውን ጭምር እየገለጹ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን በመጥቀስ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል
  • በአድባራትና ገዳማት የመልካም አስተዳደር እጦት መንገሡ ተገለጸ  ባለፉት አሥርት ዓመታት የምዕመናን ቁጥር ቀንሷል ተብሏል

ቤተ ክርስቲያን ግልጽ የሆነ መዋቅር ያላት ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራት፣ ከመዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ በመንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት ያከማቹና እያከማቹ በመሆናቸው፣ ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠራቸው ከሆነ አሸባሪ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስታወቁ፡፡ 

ፓትርያርኩ ይህንን ያስታወቁት ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 .. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡ 

በቤተ ክርስቲያን ስም የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ከቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት ማካበት የተከለከለና በከባድ ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ ድርጊት እየተስፋፋ መሆኑን የጠቆሙት ፓትርያርኩ፣ እየታየ ያለው የማኅበራት ዝንባሌ ሀብት ማካበት፣ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ የተፈቀደውን ‹‹አሥራት በኩራት›› ለራሳቸው መሰብሰብ፣ ከቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ውጪ የአገር ውስጥና የውጭ ሥራዎችን በሌላቸው ሥልጣን እየሠሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ 

ፓትርያርኩ እንዳብራሩት፣ ማኅበራቱ በሰበሰቡት ሕገወጥ ሀብት አባቶችን ይከፋፍላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ያሾማሉ፣ ያሽራሉ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን የማይፈጽሙትን እያስፈራሩ በመሆናቸው፣ አካሄዳቸው ለቤተ ክርስቲያኗ ጥንካሬና ህልውና ፍጹም አደጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

በቤተ ክርስቲያን ስም ያለአግባብ ሀብትና ንብረት ያካበተ ማንኛውም ኃይል ባስፈለገ ጊዜ እንቢተኛ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍል ስለሚችልና በዓለም ላይ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ንፁኃንን እየጎዳ ያለውን ትዕይንት ሊያስከትል ስለሚችል፣ ሁሉም የሃይማኖቱ መሪና ተከታይ መታገልና መቃወም እንዳለበት ፓትርያርኩ አሳስበዋል፡፡ 

ሌላው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያነሱት ነጥብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ቁጥር ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ መቀነሱን ነው፡፡ ለምሳሌ ያህልም በአዲስ አበባ ሰባት በመቶ፣ በኦሮሚያ አሥር በመቶና በደቡብ 7.8 በመቶ የቀነሰ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የተጠቀሰው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሆኑን የገለጹት ፓትርያርኩ፣ የምዕመናኑ ቁጥር መቀነስ በአሉታዊ ጎኑ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ለውጥ እንደሚያስከትል ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ሃይማኖታዊ ተልዕኮአችንን መሠረት አድርገን ብንመለከት ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የምናቀርበው ሕዝብ እያጣን መሆኑን ያሳያል፤›› ብለዋል፡፡ ምዕመናን ሲቀንሱ የቤተ ክርስቲያን ሀብት እየቀነሰ ስለሚሄድም፣ የሚዘጉ አብያተ ቤተ ክርስቲያናትም እየበዙ እንደሚሃዱ አክለዋል፡፡ 

የቤተ ክርስቲያንና ጥንታዊ እሴቶችም በአገር ደረጃ የነበራቸው ጠቀሜታ እየቀነሰ ከሄደ፣ የሃይማኖቱና የአገሪቱ መሠረታዊና ማኅበራዊ እሴቶች እንደሚጎዱ የጠቆሙት ፓትርያርኩ ባህሉ ከተጎዳ ጭካኔ፣ ስግብግብነት፣ ስንፍናና ወንጀል እንደሚበዙ ገልጸዋል፡፡ ፈሪኃ እግዚአብሔር ከመቀነሱና ከመጥፋቱም በተጨማሪ የትውልዱ ሥነ ምግባር ተጎድቶ የተለየ አደጋ እንደሚያስከትልም አክለዋል፡፡ 

አንዳንድ ሰዎች ችግሮችን ግልጽ በማድረግ ውይይት ለማድረግ ሲጠየቁ፣ ‹‹ሌሎች ሃይማኖቶች በእኛ ላይ ሊዘባበቱ ይችላሉና ዝም ይሻላል ብለው ይመክራሉ፤›› ያሉት ፓትርያርኩ፣ ዝም ማለት በመመካከር ሊገኝ የሚችለውን መፍትሔ እንደሚያሳጣ፣ ለምዕመናንና ለሕዝብ የሚሰጠው የተሻሻለ አገልግሎት እንዳይኖር እንደሚያደርግ፣ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደራዊ ሥራ በዘመኑ ሥልት እንዳይመራና ሃይማኖቱ እንዳይስፋፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ በማከልም በዚህ ዘመን ማናቸውም የሚደረግ ነገር ሁሉ ለሕዝብ ያልተደበቀና ምዕመናን በየቀኑ እያዩት ያለ ጉዳይ በመሆኑ፣ ‹‹ዝም እንድንል የሚመክሩን የቤተ ክርስቲያኗን መሻሻልና መጠናከር የማይፈልጉ ወይም የችግሩን አሳሳቢነት ያልተረዱ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡ 

በአድባራት፣ በገዳማትና በቤተ ክህነት ጭምር ብልሹ አሠራር መስፈኑን የሚያሳይ በሁለት ሳምንት ብቻ ከአምስት በላይ ከሚሆኑ አድባራትና ገዳማት የተውጣጡ ምዕመናንና ካህናት በሠልፍ ወደሳቸው መምጣታቸው ማሳያ መሆናቸውን የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ መደለያ (ጉቦ) በመስጠት ፍትሕ እንዲጓደል ማድረግ፣ በዘር፣ በአካባቢ በመደራጀት ንፁኃንን መበደልና ያልደከሙበትን ሀብት ያለአግባብ ማባከን ትምህርተ ወንጌልን የሚፃረር ተግባር መፈጸም በመሆኑ፣ ሁሉም ሊዋጋው የሚገባ ተግባር መሆኑን አሳስበዋል፡፡ 

በቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተጠቅመው ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በአንዳንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በመዋቅር ውስጥ እንደ ሰንሰለት ተያይዘው ለራሳቸው ጥቅም የሚሠሩ ግለሰቦች መበራከታቸው፣ የላቀ መንፈሳዊ ተግባር ለሚጠብቁ ምዕመናን ክፉኛ የመንፈስ ስብራት እየደረሰባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህንንና ሌሎች ችግሮችንም ከምዕመናኑ ጋር በመተባበር በተለይ ከቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች ጋር ዓመቱን ሙሉ በሚኖረው ውይይትና ምክክር ችግሩ ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ስለማኅበራት በጎ ያልሆነ አሠራርን ሲናገሩ ‹‹ማኅበራት›› እያሉ በወል ስም ከመጥራት ባለፈ ሙሉ ስም ባይጠቅሱም፣ ከገዳማትና ከአድባራት የተወከሉ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ግን ሕንፃውን ጭምር እየገለጹ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን በመጥቀስ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ ማንኛውም ገቢ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር በአንድ ቋት ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት እንዲመራ ጠይቀዋል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቀድሞ ቤታቸው እንዲመለሱም እንዲሁ ጠይቀዋል፡፡ 

Source :-  http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/7513

12 comments:

  1. መዝሙረ ዳዊት 27:1-14
    እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው? ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ። ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ። እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና። እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ። ማረኝና አድምጠኝ። አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ። አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ። ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ። አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ። አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ። የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ። የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ። እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ፥ ልብህም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

    ReplyDelete
  2. jeb kehede....wesha Chohe>> ባለፉት አሥርት ዓመታት የምዕመናን ቁጥር ቀንሷል ተብሏል

    ReplyDelete
  3. መሳይ ተክሉOctober 9, 2014 at 3:02 AM

    ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንንና ማኅበረችንን ይጠብቅልን!!
    አሜን አሜን አሜን!

    ReplyDelete
  4. Well done our beloved father!

    ReplyDelete
  5. Mulu lemulu yemidegef hasab new yaqerebut bego hilina lalew ena ye betekrsteanituan chigir yale simet lteredaw. qum negerachu mkidusanin yeneka... Hulem silehone new enji. Egziabhear gin sirawn yeseral egnam libona yesten

    ReplyDelete
  6. Egziabher amlak ye misanew neger yelem ena betekrstiyanachinin ena mahiberachinin yitebkilin lebochi kesashe honew tenestewal ena firdun lemedhane alem erasachewn yemiteyiku bihon noro kekifatachew betemelesu nebe ye betekrstiyan astedadari hono bale mekina ena bale hintsa yehonebat betekrstiyan sertewu ena belabachew betekrstiyanin yemiredu mahiberatin lemafres tenesu egziabher yayal firdun yisetal

    ReplyDelete
  7. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  8. tadeya yememnu mekense teteyakwe manwe bewesetachwe beguyachwe yakefewachwe erasune Tehadeso belo yemetrawe ye protasetanet ketregna (buchela) nachwe ;;

    ReplyDelete
  9. እግዚአብሔር ምን አለ????

    ReplyDelete
  10. እግዚአብሔር ምን አለ??

    ReplyDelete
  11. ✔ፓትርያርኩ ለሾማቸው ኢሓዲግ ማህበረ ቅዱሳንን በማፋረስ ውለታ ሊመልሱ ይሆን.....???
    ★※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※★
    እኔ የማህበረ ቅዱሳን አባል አይለሁም ስለ ማህበሩ ድንቅና መልካም ሥራ ግን ምስክር ነኝ !ስለ ማህበሩ ሕያውና ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ለመመስከር ደግሞ ኦርቶዶክስ መሆን ብቻ በቂ ነው...........
    ሰሞኑን ቀጠን ባለ የኢሓዲግ ትዕዛዝ ከቅ/ሲኖዶስ እውቅና ውጭ መዋቅሩን ባልጠበቀና ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ ብፁዕ ወቅዱስ አብነ ማቲያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋር ባደረጉ ስብሰባ ባልተለመደ መልኩ ግልፅ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻና አስነዋሪ ከአባቶች የማይጠበቅ በፀያፍ ንግግር የተሞላ አንገታችንን ያስደፋን አሳፋሪ አስተያየቶችን ቁጭ ብለው አንገታቸውን እየነቀነቁ ሲያስተናግዱ አረፈዱ......የሚገርመው ነገር ተናጋሪዎቹ በመንግስት ካድሬ አይዞ የተባሉ በሥነ ምግባር የዘቀጡ በሙስናና በስርቆት የደለቡ በልማት ስም የተሰሩ የአድባራቱን ህንፃዎች ለመናፍቅና እስላም እያከራዩ ኪሳቸውን የሞሉ ባዶ እጃቸውን መጥተው ቤ/ያኒቱን ዘርፈው ቪላ ቤት መኪና ገዝተው ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ያጣበቡ ውስኪ እየተራጩ የሚዳሩ በእንጦንስና በመቃርስ ቆብ የሚያላግጡ እግዚያብሄርን የማያውቁ የእግዛብሄር ሰዎች የቤ/ያን ዳር ድንበር መስፋት የቀኖናና ዶግማ መፋለስ የተሐድሶ ዘመቻ የመንጋው መበተን የማይደንቃቸው ስለሆዳቸው ብቻ የሚያስቡ ነውረኞች እነዚህ ነው እንግዲ ፓትርያርኩ ሰብስበው ማህበረ ቅዱሣን ለማፍረስ ሲዶልቱ የዋሉት.....እኔ የምለው ለመሆኑ የአሸባሪነት ጉዳይ የመንግስት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አጀንዳ ነው እንዴ? እረ ብዙ አንገብጋቢ የቤ/ያቱ አስቸኩዋይ ጉዳዮች እያሉ አክራሪነት፣ አሸባሪነት፣የትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ህዳሴ ግድብ ፓትርያርኩን ምን አገባቸው ? ነው ወይስ ወደ ፕትርክና መንበር ያመጣቸውን ኢሓዲግ ታማኝነታቸውንና ታዛዥነታቸውን ለማሳየት ነው? ለነገሩ ከስልጣኑ ጋር የተቀበሉትን ማሕበረ ቅዱሳንን የማፍረስ ተልዕኮአቸውን በይፋ መጀመራቸው ነው፣ ለነገሩ ማህበሩ በመንግስት ይሁንታና በፖትርያርኩ ፈቃድ ሳይሆን በፈቃደ እግዚአብሄር በቅዱሳን ፀሎት በፃድቃን ሰማዕታት ተራዳይነት በድንግል ማርያም ምልጃ ነው የተመሰረተው ነገም በእግዚያብሄር ጥበቃ ወደፊት መጓዙን ይቀጥላል!........አባታችን ይልቅ ማህበሩን ተጠግተው እርቃናቸውን ቢሸፍኑ መልካም ነበር ሲኖዶሱም እንደራሴ ሾሞላቸው ቅዱስነታቸው ከተጠናወታቸው የአልዛይመር (የመርሳት ችግር)በሽታ በጊዜ ቢያገግሙ መልካም ነው ያለዚያ የዚህን ግራ የገባው መንግስት ምክር እየተቀበሉ ጉድ እንዳያደርጉን..........የተዋህዶ ልጆ ንቁ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ነው ያገባናል የመናፍቃንና የአህዛብ ብሎም የተሐድሶች የጎን ውጋት የህገወጥ መነኮሳት ቀበኛ የሆነ ማህበር ለነ ሆዶና ከርሶ አልመች ስላለ ማህበሩን አፍርሰው ቤ/ያኒቱን ወረው ሊቀራመቷት ነውና አንድ ሆነን ለማህበሩ ህልውና እንፀልይ ከውስጥና ከውጭ ጠላት እንከላከለው በቅዱሳን ምልጃና ፀሎት ተዋህዶ እስካለች ማህበሩ ለዘላለም ይኖራል !!!
    ✔በዲ/ን አብርሃም ወርቁ ወ/ሰንበት
    ✔ጥቅምት ፳፻፯
    ✔ፓትርያርኩ ለሾማቸው ኢሓዲግ ማህበረ ቅዱሳንን በማፋረስ ውለታ ሊመልሱ ይሆን.....???

  12. እግዚአብሄር አምላክ ቅዱሳን አባቶቻችንን ይጠብቅልን: የማህበሩ አባላትን አይነ ልቦናቸውን ያብራልን።
    ማህበረ ቅዱሳን ሳይሆኑ ማህበረ ርኩሳን ናቸው።

    ReplyDelete