Monday, October 20, 2014

ዝክረ አበው


አንድ አድርገን ጥቅምት 10 2007 ዓ.ም
ቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የመሩ ከአጸደ ሥጋ ዓለም በሞት ተለይተው በአጸደ ነፍስ የሚገኙ ቅዱሳን ፓትርያኮችና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎላቸዋል፡፡  ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንዲሁም ለብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በጊዜው ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎላቸዋል፡፡ ያለፉትን አባቶቻችንን እንዲህ ለማስታወስ ሞከርን፡፡

1.     ቀዳማዊ አቡነ ባስልዮስ (፲፰፻፹፬ዓ/ም (ሚዳ ሚካኤል) - ፲፱፻፷፫ ዓ/ም (አዲስ አበባ)) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበሩ።የመናገሻ አምባ ማርያምን ገዳም እያስተዳደሩ ሳሉ፤ ከዚህ ሥልጣናቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ተሰጣቸው። ከዚያም ቀጥሎ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፭ዓ/ም በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በመንፈሳዊ መሪነት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደአገራቸው ተመለሱ። የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የጵጵስና ማዕርግ የመስጠትን ልምዳዊ መብቷን ለኢትዮጵያውያን አልለቅም በማለቷ ድርድር ከተደረገ በኋላ፤ በቀድሞው ሥልጣናቸው ሲያገለግሉ የቆዩት ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ፥ አቡነ ባስልዮስ ተብለው ከአቡነ ቴዎፍልስ፤ አቡነ ሚካኤል፤ አቡነ ያዕቆብ እና አቡነ ጢሞቴዎስ ጋር በእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ እጅ ተቀቡ፡፡


ግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ብዙ ጊዜ የወሰደ ድርድር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ተደርጎ፥ እሑድሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም፤ ንጉሠ ነገሥቱም በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ፓፓው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ላይ የሢመቱን ሥርዓተ-ጸሎት አድርሰው፤ የፓትርያርክነቱን ዘውድ ባርከው ደፉላቸው። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ በግብጽ ፓትርያርክ እጅ በዚህ ማዕርግ ሲቀቡ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው።

የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበር፥ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ 
መንበረ ተክለ ሃይማኖት ተብለው፥ አምሣ-ዘጠነኛው ዕጨጌ ሆነውተሾሙ። በዚሁ በዕጨጌነታቸው ዘመን የፋሺስት ወረራ ኢትዮጵያን ባጠቃ ጊዜ፣ በጦርነቱ ግምባር ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተሰልፈው ‹‹አብያተ ክርስቲያናትንና መጻሕፍትን የሚያቃጥል የምእመናንን ዘር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና በሃይማኖት፤ በጸሎት፣ በምህላ በርታ›› እያሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያጽናኑ ቆዩ። በጦርነቱም ጊዜ የተቀመጡበት በቅሎ በአረር ተመቶ እስኪወድቅና የለበሱትም ካባ አምስት ቦታ ላይ በጥይት እስኪበሳሳ ድረስ ከንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ ሀገራቸውን እምነታቸውን አሳልፈው ላለመስጠት ከወታደር እኩል የቆራጥነት ሥራ ሠርተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ እስከ ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ድስ አርባ ሁለት አብያተ-ክርስቲያነትንና አስራ ሁለት ትምህርት ቤቶችን አሰርተዋል፡፡ ፓትርያርኩ በተወለዱ በ፸፱ ዓመት ዕድሜያቸው ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ/ም አርፈው ጥቅምት ፬ ቀን በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ። አቡነ ቴዎፍሎስ ተተክተው ሁለተኛው ፓትርያርክ ሆኑ።

2.    አቡነ ቴዌፍሎስ(፲፱፻፪ -፲፱፻፷፹) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ፡፡ ጎጃም በሚገኝው በዝነኛው ደብረ ኤሊያስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ማርያም ውቤ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘርትሁን አደላሁ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፪ ዓ/ም ተወለዱ። ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም መልእክቱ ወልደ ማርያም ነበር።


ቀደም ብሎ በኢትዮጵያና በግብጽ በተደረገው ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ጳጳሶች ሲሾሙ ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ ወልደ ማርያም ለሹመት ከተመረጡት አምስት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ወደግብጽ ተጉዘው በእስክንድርያፓትርያርክ ዳግማዊ አቡነ ዮሳብ እጅ በካይሮ በትረ ካና ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እሑድ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፵ ዓ/ም ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ “ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ” ተብለው የሐረርጌ ጳጳስ ሆኑ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ባላቸው ከፍተኛ እውቀት ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ሰፊ አገልግሎት የሰጡት  ቀዳሚያቸው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ ካረፉ በኋላ ተከታዩን ፓትርያርክ ለመሾም መጋቢት 29 ቀን 1963 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ በተደረገው ምርጫ በዕለቱ ተገኝተው የመረጡት ፻፵፮ አባላት ሲሆኑ  አቡነ ቴዎፍሎስ  - በ፻፳፫ ድምጽ  አግኝተው አሸንፈዋል። በዚህም መሠረት ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር  በኢትዮጵያውያን ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ካህናትና ምዕመናን  ጸሎት 2ተኛው  የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የፓትርያርኩ ስርዓተ ሲመት ተከናውኗል።በደርግ መንግሥት ያለ ሕግና ያለ ፍትህ ከስልጣናቸው ወርደው እንዲታሰሩ እስከተደረገበት እስከ የካቲት 9 1968 ዓ.ም ድረስ በፓትርያርክነት ስልጣን ላየ ቆይተዋል፡፡

 ሐምሌ ቀን ፲፱፻፸፩ ዓ/ም እኒህ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ርዕሰ ሊቃና ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ በደርግ እጅ ተገደሉ። ቀደም ሲል “የተቀባ ፓትርያርክን ሞት ብቻ ነው የሚሽረው” የሚለውን እምነት በሚቃረን ሁኔታ ከሥልጣን አውርደው “የተቀባ ፓትርያርክ ሳይሞት በላዩ ላይ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም” የሚለውን ሁለተኛውን እምነት ጥሰው ሰኔ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሦስተኛው ፓትርያርክ እንዲሾሙ አደረጉ።


ከበርካታ ዓመታት በኋላ የአቡነ ቴዎፍሎስ አጽም ደርግ ከቀበረበት ቦታ በማውጣት  ሐምሌ 4 ቀን 1984 .. በክብር አረፈ፡፡  ሐምሌ 5 ቀን 1984 . የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሲመት ተፈጸመ፡፡

3.    ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ሦስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ተክለሃይማኖት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በታሠሩ በ5 ወራት ከ2 ቀናቸው ሐምሌ 11ቀን ኤጲስ ቆጶስ ፤ ከአንድ ወር ከ12 ቀናት በኋላ ነሐሴ 23 ቀን ዕሁድ 1968 ዓ/ም ደግሞ 3ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አገልግሎት በመቀጠል በዘመናቸው የአብነት ትምህርት ቤቶችን ፤ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትንና የሰንበት ትምህርት ቤት እንቅስቃሴን በበለጠ አስፋፍተዋል ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ለ1 ወር ከ12 ቀናት በኤጲስ ቆጶስነት ፤ ለ11 ዓመታት ከ9 ወራትና ከ10 ቀናት በፓትርያርክነት ካገለገሉ በኋላ ግንቦት 28 ቀን 1980 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፡፡ 


የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖትን ርእሰ አበውነት ከሌሎቹ አራት አርእስተ አበው ለየት የሚያደርጉት ሁለት አበይት ነጥቦች አሉ ፡፡ እነዚህም 1ኛ. በኤጲስቆጶስነት ተሹመው ሳያገለግሉ ፓትርያርክ እንዲሆኑ ሲፈለግ በቀጥታ ከብሕትውና በአታቸው እንዳሉ በካህናትና በምእመናን እንዲመረጡ ተደረገና ሐምሌ 11ቀን 1968 ዓ/ም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሾሙ ፡፡ ወዲያውኑ ኤጲስ ቆጶስ በሆኑ በ42 ቀናቸው ነሐሴ 23 ቀን 1968 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው ተሰየሙ ፡፡ 2ኛ. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በእሥር ቤት እያሉ  ቋሚ ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ነው ፡፡
በወቅቱ አቡነ ተክለሃይማኖት 28 ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙ እንደነበረ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ትሁትና እጅግ ጸሎተኛ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡


4.    አቡነ ጳውሎስ (1928 .ም-2004 ዓ.ም). በዘመነ ዮሐንስ በዓድዋ ከተማ በመደራ አባ ገሪማ ገዳም አካባቢ ከካህን ቤተሰብ፣ ከአባታቸው ከአፈ መምህር ገብረ ዮሐንስ ወልደ ሥላሴና ከእናታቸው ከወ/ አራደች ተድላ ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም ገ/መድህን ነበር፡፡ አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት ቤተክርስቲያኒቱን ለ20 ዓመት ካስተዳደሩ በኋላ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከንጋቱ 11:00 ሰአት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለዩ።6 comments:

 1. Abet abet abet bewunu egizeabihar ayayimin? Lemin ewunetegnaw tarik ayinegerim? Yeabune paulos ashoshum endet nebe? Lemin tezelele? Abune tekilehayimanot kemotu behuala abune Merikorios teshome. Bewekitu yeneberew menigist yihunta neberebet sishomu minigizeam benegesitatum zemen endemideregew. Gin yebetekiristian sireat teshoro ahun besilitan lay yalew mengist beketita talikagebinet abarerachew. Yerasunim sew ashome. Abune merkoriowosim esikahum behiwot betena alu. Yih Lemin tezelele? Beabune tewofilos gize yefetsemew sihitet meteqesu yeahunin yemenigist sihitet tikikil ayaderigewum. Bewokitu yeneberew tiwulid yan tifat sileteqebele zarem yeteserawun tifat eniqebelew lemat kehone ayasikedim. Yetefalesew mesitekakel alebet. Beanis besimiminet eriq mefeter alebet enji endet tifatin befitim tefetsimualina ahunim enikebelew yibalal? Wedefitim befetsem enikebelew malet new yih akahed. We need to stand for the respect and preservation of law and order of our church. We need to teach our kids respect for the law, not disobeying the law and lawlessness. And also we need to write truth. If we fear, we better not write at all.

  ReplyDelete
 2. Yemotutin newu eko yanesau:: tsehafiwu degimo qaliti mehed yefera yimeselegna:: ewunetun bi nager nege yemnanebewu anagegnim

  ReplyDelete
 3. why you didn't wrote about abune Merkorious?

  ReplyDelete
 4. Abune merkorios is still alive. If you haven't read the title above.ቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የመሩ ከአጸደ ሥጋ ዓለም በሞት ተለይተው በአጸደ ነፍስ የሚገኙ ቅዱሳን ፓትርያኮችና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ peopel have not differentiate d politics from religion, perhaps if we seperate our political views from our religious view even if we dont agree on something we might come up with a common understanding. That is why we have blogs we different views these days.

  That was on thw firat paragraph.

  ReplyDelete
 5. aba merkorios is not bishop but he is the solijer of mengistuhailemaria

  ReplyDelete