Wednesday, October 15, 2014

‹‹የቤተክርስቲያን መሪዎች መንግሥት እንዳይነቀፍ ብለው ቤተክርስቲያኒቱና ክርስትያኖች መብታቸው ሲነካ ዝም ብለው ካዩ የእግዚአብሔርን አደራ አልጠበቁም ማለት ነው›› አቡነ ጢሞቲዎስ

   

 አንድ አድርገን  ጥቅምት 5 2007 ዓ.ም ፡- 

ህዳር 8 1992 ዓ.ም አቡነ ጢሞቴዎስ ከ”ምኒልክ መጽሔት ጋር ካደረጉትን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

ጥያቄ፡- በስልጣን ላይ በተቀመጠ መንግሥት በአደባባይ የሚሰራቸውን ስህተቶች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፓትርያርኳና ከጳጳሶቿ የነቀፈችበትና የእርምት እርምጃ የወሰደችበት ጊዜ የለም ይባላል፡፡ በዚህ መሰረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፓትርያርክነት የሚገኙትና ሌሎቻችሁም ጳጳሶች ቀደም ብለው ከነበሩት ጳጳሶች የተለየ ነገር አልሰራችሁም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በዚህ ላይ የእርስዎን አስተያየት ቢያካፍሉን?


አቡነ ጢሞቲዎስ፡ በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት የሚሰራቸውን ስህተቶች ምን ዓይነት መሆናቸው ባይገለጹም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክና በጳጳሶቿ የነቀፈችበትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀችበት ጊዜ የለም የሚባለው ትክክል ነው፡፡ ለምን ቢሉ ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በስተቀር ማንም ፓትርያርክና ጳጳስ መንግስትን አጥፍተሀል ተመለስ ያለ አልነበረም፡፡ አሁንም የለም፡፡ ምክንያቱም የቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በሩ ሲታጠር ማንም የተነፈሰ አልነበረም፡፡ አሁንም የቤተ ክርስቲያኒቱ  መብት በተለየ ቦታ ጊዜ ሲደፈር ማንም የቤተ ክርስቲያን መሪ የተነፈሰ የለም፡፡ ይልቁንም መንግስት ለራሱ ጸጥታ ሲል በእያንዳንዱ ቦታ ጣልቃ ሲገባ ይታያል፡፡ ታዲያ እንዲህ ያለ ዝምታ ለመንግስት የሚመች አይመስልም፡፡ እንዲያውም የቤተክርስቲያኒቱን መብት ከተጠበቀ ጸጥታ ይሰፍና መንግሥትም በሰላም ይገዛል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መንግሥት እንዳይነቀፍ ብለው ቤተ ክርስትያኒቱና ክርስትያኖች መብታቸው ሲነካ ዝም ብለው ካዩ የእግዚአብሔርን አደራ አልጠበቁም ፤ መንግሥትንም ባለመምከራቸው ጎዱት እንጂ አልጠቀሙትም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከነበሩት ጳጳሳት የባሰ እንጂ የተለየ ሥራ አልሰራንም ሥራችን ይመሰክራል፡፡


2 comments:

  1. ምነው ፖትርያርክ ቴዎፍሎስ ተረሱ የደርግን መንግስት አልተቃውም እንዴ?

    ReplyDelete
  2. አባ ቴዎፍሎስን ለደርግ አሳልፎ የሰጠ ጳጳስ ማነው?

    ReplyDelete