Friday, November 8, 2013

በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚኖሩትን አጥቢያዎች ቁጥር በአንድ እንደሚቀንስ ይጠበቃል

  • ‹‹እግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ  ሆኖ ወደ ህብረትና አንድነታችን አንደምንመለስ ትልቅ ተስፋ ነው ያለኝ፡፡›› ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከ12 ዓመት በፊት ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

(አንድ አድርገን ጥቅምት 29 2006 ዓ.ም)፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ለሁለት አስርተ ዓመታት ወደኖሩበት አሜሪካ ጥቅምት 27 2006 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመነ ፕትርክናቸው እንደሚሄዱ ሰሞኑን ከተለያዩ ዜና ማሰራጫዎች ለመረዳት ችለናል። በመረጃው መሰረት ብፁዕነታቸው 6ተኛ ፓትርያርክ ተብለው ከተሸሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅምት 27 2006 ዓ.ም ወደ አሜሪካ አቅንተዋል ፡፡ ከብፁዕነታቸው ጋር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ አብረዋቸው እንደተጓዙ ታውቋል ፡፡አካሄዳቸው በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የመድኅኒዓለም ቤተክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

እንደሚታወቀው ይህ አጥቢያ በብፁዕነታቸው ከተመሰረተ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ” ገለልተኛ “ በሚባልአስተዳደር መቆየቱም ይታወሳል። በዚህ ታሪካዊ የብፁዕነታቸው ጉዞም ይህንን አጥቢያ ወደ እናትቤተክርስቲያን አስተዳደር እንደሚመልሱት እና በቀጥታ በቅዱስ ሲኖዶስ በሚሾመው ሊቀ ጳጳስእንደሚተዳደር ይጠበቃል። በዚህም በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚኖሩትንአጥቢያዎች ቁጥር በአንድ እንደሚቀንስ እና መልካም እርምጃ እንደሚሆን ይጠበቃል። ሌሎችስ በአሜሪካ እና በተለያዩ የአውሮፓ ምድር ራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የሚገኙ የአብያ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ምን ይማሩይሆንከዚች ከአንዲት ቤተክርስቲያን ተገሎ እስከመቼ ይኖራልእንደ ብዙዎች ምዕመናን አስተያየት ወደፊት እግዚአብሔር በፈቀደው ቀን በውጭ ሀገር የተመሰረተው ሲኖዶስ ከአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እንደሚቀላቀል እና አንድ እንደሚሆን እምነታው ነው ፤ የዛኔ ደግሞ አሁን ላይ ራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የተቀመጡት ሌላ ፈተና ይሆናሉ ብለው ሃሳባቸውን ይገልጻሉ ፡፡ ዛሬም በነ አቶ ወይም ዶክተር እከሌ መመራትወይስ ቀደምት አባቶቻችን በሰሩልን ሥርዓት መቀጠልእኛ እኮ አባቶቻችን የሰሩልን የእምነት ስርዓት አስቀጣይ እንጂ እንደ አዲስ ጀማሪ መሆን መቻል የለብንም………ይህ መልካም ጅምር ነው ቸር ያሰማን

4 comments:

  1. አባታችንን ምኞታቸውን ቅዱስ እግዚአብሔር ይፈጽምላቸው፤ የእድሜ ባለጸጋ ያድርጋቸው። ወደ አሜሪካ ከሄዱ ዘንድ እግረመንገዳቸውን አሜሪካ ውስጥ አንድ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጸበል ያለበት ብዙ ምእመናን ታምሩን እየመሰከሩለት ነው፤ አንዲት ምእመን ለረጅም ጊዜ መክና ኖራ እዚያ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ ተስላ እና ጸበሉን ከተጠመቀች በኋላ መንታ ልጆች ወለደች ይማላል። ብጹነታቸው ቤተ ክርሲያኑን ባርከው ቢመለሱ ለብዙዎች ምእመናን መልካም ይሆን ነበር። ይህንን ማድረግ ደግሞ ለኢኦተቤተ ክርስቲያን ጥንካሬን በውጭው አለም ይሰጣታል።

    ReplyDelete
  2. አባታችን እድሜያቸውን ያርዝምልን።

    ReplyDelete
  3. አባታችን እድሜያቸውን ያርዝምልን።

    ReplyDelete
  4. I think you guys are becoming very divisive. Please do not insult the victims of all the division that was created at the top and I do not think you deserve the name that you have written on top of your site.

    ReplyDelete