Sunday, November 10, 2013

የወ/ሮ ዘርፌ ቃለ መጠይቅ


(አንድ አድርገን ህዳር 1 2006 ዓ.ም) ወ/ሮ ዘር ከበደ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጋ ነበር ፡፡ ቃለ መጠይቁን አለፍ አለፍ ብለን እንዲህ ለማየት ወደድን…

ወ/ሮ ዘርፌ፡- ብዙ ዘማሪዎች ግጥምና ዜማ ራሳቸው ናቸው የሚሰሩት... እንደ ዓለማዊ ዘፈን ከሰው ብዙ አይቀበሉም… የስጦታ ጉዳይ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ አንድ ሰው ካልተሰጠው ምንም ነገር መስራት አይችልም። ጌታ ቢፈቅድ ብዙ ልሰራቸው ያቀድኳቸው ነገሮች አሉ፡፡ በእኛ አገር በተለያዩ ቋንቋዎች መዝሙሮች መሰራት አለባቸው፡፡ እዚህ አሜሪካ ብዙ የአበሻ ልጆች አማርኛ መስማት አይችሉም፡፡ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ፤ ግን ለማምለክ ብዙ ይቸገራሉ፡፡
ቃለ መጠይቁ ቃናው ከመናፍቃኑ አልለይ አለ ፤ አባቶቻችን ሲናገሩ እጅጉን ሲጠነቀቁ ነው የምናውቀው ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ውዴ›› ፤ ‹‹ፍቅሬ›› እያሉ ሲናገሩ አንሰማም ሰምተንም አናውቅም፡፡ የአምላክን ስም አንጠልጥለው ሲጠሩን አንሰማም ፡፡ እነዚህ ፕሮቴስታንታዊ ዘይቤ ያላቸው አነጋገሮች ‹‹ማምለክ›› ፤‹‹ስጦታ›› ፤ ‹‹ሙላት›› …… ከየት የመጡ ናቸው…? ለነገሩ ‹‹ስለ እመቤታችን መዝሙር መዘመር አልችልም፤ አንድ መዝሙርም ሲበዛባት ነው፡፡ እኔ የኢየሱስን ክብር መግለጥ ነው የምፈልገው›› ብላ ከአንደበቷ የተናገረች ቃሏ እንዴት እኛን ይመስል?
ወ/ሮ ዘርፌ ፡- ‹‹እዚህ አሜሪካ ብዙ የአበሻ ልጆች አማርኛ መስማት አይችሉም፡፡ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ፤ ግን ለማምለክ ብዙ ይቸገራሉ፡፡ በእንግሊዝኛ የተዘመረ መዝሙር የለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ነው እየዘመሩ ያሉት፡፡ለእነሱ በእንግሊዝኛ መዝሙር የመስራት ሀሳብ አለኝ፡፡››


አሁን ያሉት ከተሀድሶያውያን ጋር የሚንቀሳቀሱት ‹‹ዘማሪ›› ነን ባዮች ግዕዝ Nuclear Physics የሆነባቸው ይመስላል፡፡ የቡድኑ ‹‹ሰባኪ›› ተብዬውም ቢሆን ጆሮው ግዕዝን መስማት አንደበቱ ግዕዝን መናገር አይችልም ፤ ታዲያ የቤተክርስቲያን መሰረቷ ግዕዙን ትቶ እንግሊዝኛ ቋንቋ ላይ መንጠልጠል ምን ይባላል ?    

ወ/ሮ ዘርፌ  ፡- ከዚህ በተረፈ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብቼ፣ በዩኒቨርስቲ ደረጃ ያለኝን ተሰጥኦና ችሎታ ለማሳደግ እየተዘጋጀሁ ነው፡ በቤቴ ውስጥ የሙዚቃ መሳሪያዎች አሉኝ..ባህላዊም ዘመናዊም፡፡ እነሱንም እያጠናሁ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያኖች ነጮችን ቤተክርስቲያን ይዘዋቸው ይመጣሉ--. አማርኛ አይሰሙም፤ ነገር ግን ዜማውንና የድምፄን ቅላፄ ሲሰሙ ይደነቃሉ፡ለራሴም መጥተው ይነግሩኛል--.‹‹የሚያምር ድምፅ ነው ያለሽ›› ይሉኛል፡፡ አይሰሙትም ግን እንዴት ነው የሚያደንቁት--.እላለሁ፡፡ ሙዚቃ አለማቀፍ ቋንቋ ስለሆነ ይመስለኛል፡፡ አንዳንዴ በማይገባን ቋንቋ ሙዚቃውን ብቻ ሰምተን ‹‹ቅላፄው ደስ ሲል…ሙዚቃው ደስ ሲል›› የምንልበት ሁኔታ አለ አይደል፡፡ ወደነው የምንቃትትበት ጊዜ አለ--.ምን ማለት እንደፈለጉ ይገባናል እኮ››

ከጊዜ በኋላ በፒያኖ እና በጊታር ተመልሳ ለመምጣት ያሰበች ትመስላለች ፤ ‹‹ሙዚቃ አለማቀፍ ቋንቋ ነው›› የሚሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ናቸው ፤ መጀመሪያም እኮ መቼ መዝሙር አወጣች ሙዚቃ እንጂ ፤  ከመናፍቃን ካሴት ላይ አቶ በጋሻው ደሳለኝ የለቃቀመውን ግጥም እንጂ ፤ አቶ በጋሻው በመጀመሪያ ካሴት ላይ ካሉት ግጥሞች ከመናፍቃን ካሴት ላይ ሳያስፈቅድ በመውሰዱ እና ለወ/ሮ ዘርፌ በመስጠቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት ነበር ፤(የቀጠሮ ቀን ክሱን ከሳሽ በማንሳቱ ክሱ ተዘግቷል)፡፡  


“ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” መዝ .74:14 ለኢትዮጵያ ከተሰጡት ታላላቅ ሀብቶች መካከል አንዱ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልት ነው፡፡የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልት ግዕዝ ዕዝልና አራራይ በሚባሉ ሦስት የዜማ መደቦች ይመደባሉ፡፡በቤተ ክርስቲያን የሚቀርበው ምስጋና በሙሉ በሦስቱ የዜማ  ዓይነቶች አማካኝነት ነው፡፡ማንኛውም አገልጋይ  በቤተክርስቲያናችን  መዝሙር የሚያቀርበው  የቅዱስ ያሬድን የዜማ ምልክቶችና ዓይነቶች /ስልቶች/ ተከትሎና መሰረት አድርጎ ነው፡፡ ታዲያ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብቶ የነ ቢትሆቨንን ሙዚቃ ከመማር ከሁሉ የቀደመውን የቅዱስ ያሬድን ዜማ ከአባቶች እግር ስር ሆኖ መማር አይሻልምን ?  

አዲስ አድማስ ፡- በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተሸ ገጠር ገጠሩን ብቻ አገልግለሽ ነው የተመለስሺው፡፡ ለምንድነው?
ወ/ሮ ዘርፌ፡-  የገጠሩ ሰው ቶሎ ቶሎ ይጠራኝ ነበር፡፡ ወንጌልን የተጠማ ህዝብ ነው፡፡ እኛ ጥሪ በቀረበልን ቦታ ነው የምንሄደው። ‹‹እዚህ ቦታ ካልሰበክን፣ እዚህ ቦታ ካልዘመርን›› የሚል ሃሳብ የለንም፡፡ ሊሰበክለት፣ ሊዘመርለት ፈቃደኛ ሲሆን ብቻ ነው ልንሄድ የምንችለው። ፈቃደኛ ሆነው የጠሩን ቦታ ሁሉ እየሄድን እናገለግላለን፡፡ ከተማም ቢሆን…በአዲስ አበባ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን አገልግዬአለሁ፡፡

አንባቢ እዚህ ጋር መገንዘብ ያለበት ነገር በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ ውስጥ ከሚገኙ ከ150 ከሚበልጡ አብያተክርስቲያናት ውስጥ አሁንም ከእነ አቶ በጋሻው ቡድን ያልጠራው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ብቻ ነው ፡፡ ስለዚህ አሁንም ቤተክህነቱ ጉዳያቸው እስኪጣራ እንዳያገለግሉ ያገዳቸው ሰዎች ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ሲመላለሱ ይታያሉ ፡፡ ወ/ሮ ዘርፌን አገልግይን ብሎ የሚጠራ አዲስ አበባ ውስጥ አንድም ደብር የለም ፡፡ ለዛ ነው አገለግላለሁ በሚል መንፈስ ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያንን የጠራችው …. 

19 comments:

  1. hi guys which kind of mezemur is right I think you will say mk mezemur . Jesus was a singing a gospel song mathew 26:20-26 is it yaredawi zema ?
    I do not think so

    ReplyDelete
  2. hi guys which kind of mezemur is right I think you will say mk mezemur . Jesus was a singing a gospel song mathew 26:20-26 is it yaredawi zema ?
    I do not think so

    ReplyDelete
  3. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውNovember 10, 2013 at 3:34 PM

    ቃለ መጠየቁን አነበብኩት ይኽቺ ነገርም ትኩረቴን ሳበችው - "...በቤቴ ውስጥ የሙዚቃ መሳሪያዎች አሉኝ..ባህላዊም ዘመናዊም፡፡ እነሱንም እያጠናሁ ነው፡፡...."
    ተሃድሶዎችን ከቤተክርስትያን ለማስታረቅ ፋንቱ በጓሮ ቤት ዘው ዘው እያለች ነው የሚል ዜና በተነገረበት ጊዜ ያልኩትን ድጋሚ ለማስፈር እፈልጋለሁ - "...ማዕከላዊነት፣ኢትዮጵያዊነት እና ትውፊታዊ ቆፍጣናነት ቤተክርስትያንዋን ያድናታል። ለዚህ ነው ጠላትዎችዋ ሊከፋፍሏት፣የህዝቡንም ሀሳብ ሊበታትኑት የሚፈልጉት። ለዘመናት የውጭ ሃይሎች ከውጭ ሊያፈርስዋት ያልቻሉትን፣ በአሁኑ ዘመናችን - በዘመነ ወያኔ/ዘመነ ዓረብ፤ ውስጥዋ ፈልፍሎ የመግባትና መረባቸውን የመዘርጋት እድል አግኝተው ሲያምስዋት ነበር። ሲኖዶሱ ተሰደድኩ/አልተሰደድኩም ብሎ መዘበራረቁ ራሱ ቤተክርስትያኒቱን ክፉኛ አቁስሏታል። ይኼ ቁስል ተሃድሶ ነኝ ባዮቹን ብዙኛ ጠቅሟል።እንዚ ሰዎች ይቅርታ ከተባሉም፣መደረግ ያለበት በአደባባይ ነው እንጂ በግል ጥቅምና በጓደኝነት በተያያዙ ግለሰቦች እጅ በጓሮ በር መሆን የለበትም።
    የማንም ግለሰብ ማንነትና ዝና ከቤተክርስቲያኒቱ ህልውና እና ክብር ቀድሞ ሊታይና ትኩረት ሊያገኝ አይገባም። ይቅርታ ጠያቂዎቹ በጉባዔ ፊት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው፣ተንበርክከው እና ድንጋይ በትካሻቸው ላይ ተሸክመው፤ተሃድሶ የተባሉበትን ነጥቦች ሁሉ በዝርዝር ጥፋተኝነታቸውን አምነውበት ነው ይቅርታ መባል ያለባቸው። ከዛም ከመስበክ ስራቸው ለተወሰኑ ጊዜያት መገለል አለባቸው። ከዚያም በሂደት እየታየ ቀስ በቀስ ወደ ስብከቱ ጎራ ሊቀላቀሉ ይችላሉ። ማዕከላዊነት፣ኢትዮጵያዊነት እና ትውፊታዊ ቆፍጣናነት ቤተክርስትያንዋን ይጠብቃታል። እንደውም ለወደፊቱ ቤተክርስትያኒቱ አንድ ትውፊታዊ የስነ-ጥበብ ማዕከል ቢኖራት፤ ይኼም መዓከል ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የስነ ስዕል፣ የስነ መዝሙር፣ የስነ ፅሁፍ፣ የተግባረ ዕድ ወዘተርፈ መምሪያዎች ቢኖሩት፤ ቢያንስ ቢያንስ በመዝሙር ረገድ
    እንኳን ማንም ህገ ወጥ እየተባባለ እጅ ሊቀሳሰር አይችልም። ምክናያቱም ሁሉም ዘማሪዎች በዚህ መዓከል ስር የሚተዳደሩ ስለሚሆን።..."
    ከፀሎትና ፆም ሌላ ማዕከላዊነትን በቤተክርስትያናችን ላይ መልሶ የሚያነግስ ተጋድሎ፣ ቤተክርስትያናችንን ለወደፊቱ ከብዙ ንትርክና ጉዳት ያድናታል። የኛም በየቦታው መሰደድ እና በአልባሌ ፀባዮች መበረዝ፤ በተጨማሪም ይኼ ግሎባሊዝም የሚባለው ወሰን አልባ አለም-ዓቀፍ እንቅስቃሴም " ማዕከላዊነትን፣ኢትዮጵያዊነትን እና ትውፊታዊ ቆፍጣናነትን " በማስፈን ረገድ ተቃራኒውን ሚና የሚጫወት ቢሆንም፤ ሌላ አማራጭ ስለሌለ "ማ.ኢ.ት" ን መሠረት፣ መነሻና መድረሻ አድርጎ መነቃነቅ ለቤትክርስትያን ጠባቂዎችም ሆነ ለምዕመናኑ ተገቢ ተግባር ነው።



    ReplyDelete
    Replies
    1. It does not make sense. Our church is not like apolitical party. It should based on BIBLE,BIBLE and BIBLE principles. I ll tell you one thing before you say something read ,read and read. Are you really read bible? Do you know about love? No No No No

      Delete
  4. Andd adrgen- bizu gize befikr egobegnew neber.. Simm bicha honachubgn, andd awde mihret yemilut tomar neber andd meselachugn, yeteleyyau andnetoch bizu alu... Kidus sinodosn, bete kihinetun hiliwnachew behasabachu tiake wusst zewetr bandm belela yemitasgebu nachu. Enante endih aynetun gudayoch sititsifu yemtakerrbubet ye tilacha qalatoch hizbu wust sigeba ena ende enantem enderasu sigeltsew Agelegelin tilalachu mechem...ebakachu tinkake adrgu... Be politcawi ena be Egziabhearawi agelalets liunetu..... Lelaw andin hassab asteyayet kemestetachu befit Metshafun bilut...tiinkake....ewnet neaw enantem tinkake adrgu ebakachu..... Gid kalachu. Awo ye abatoch lijoch nean! Neger ke pente antsarawi nuro/ were abaze yezon mastawkiam degagmen kemnseralachew Silerasachin abziten binsera minale?????? Minale abztachu Le Geez denkoro yehonewn qidasem diram yemimeslewn bizu mastawekia eyeserachu eyetsafachu bitdersulet(saymot,saynetek,amlakun saytela,....) ehitochem wendmoche "alen!" Eyalu hedu wustachew bado neberna.... Ende enantem aynnetu sile Egziabhear neaw eyale gira yagabachewal... Demo pente..menafk....tehadiso...maq....yeZerfe... Bilachhu tasbugn yehonal.. Ebakachu! Yalewn endenebere le hizb quch adrgut...tsihufachu ye kekomite enkwan bihon dimdamew lehzb litew yegebal...be tsehafiw eyeta endeyay memenu enndet endeminamnte tikotralchu? Yehe eko haymanot neaw.. Nefs neaw..!?

    ReplyDelete
  5. You will hear a lot of gospel mezmur in our church that are preasing lord Jesus. What is your problem with her?

    ReplyDelete
  6. Yesew gudef setayu ersachehu lay yalewen zenedo yemiyakel sehetet sataremu geta edaymetabachu ebakachu asetewelu. Geta masetewalen yesetachu

    ReplyDelete
  7. ስማችሁ አንድአድርገን ወይስ አለያየን። ምነው ስለጌታችን ብትዘምር ተሰሚነትም ብታገኝ ችግሩ ምን ላይ ነው።የተዋጀነው ከነገድ ከዘር ከቋንቋ አይደለም ወይ? ስለዚህ በእግሊዘኛ ብትዘምር ምኑ ላይ ነው ሐጥያቱ? እንግሊዘኛን በያሬዳዊ ዜማ ትዘምረው በባሕላዊ መሳሪያ ትጠቀም እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ።

    ReplyDelete
  8. wey gud betame betame eko new yemigermew lebona yestachehu koy beged Orthodox athunu new endi yemeteluwachw? enate yewnte esuwan interview adergachehu endzihe enkuwan betel enate menme malet alnberbachehum mebtuwa new degmome atlem zem belachu seltemedachehuwachw new yensun haymanot lensu letmertu yefelgachehuwal megmerya enate manchehu derom selswe yemiyawera selrasu enkuwan aywekem be zihe seltani gezi enat website kefatachu sewen yalhatiyatu tewenegelalchu lebona yestachu lela menem aybalem

    ReplyDelete
  9. hulum yemenafkina yetehadso asteyayet new. inante gin merejan bemezegebna bemastelalef ketlubet.

    ReplyDelete
  10. how about refering her as Zemarit Zerfie? you guys make me sick.

    ReplyDelete
  11. Zerfie Tebareki Good job. Berechi yeseyetenan hasab anesetewem yegeta sime setera yamewal anechi gen yadaneshen awekeshalena leweletaw zemeri. tebareki .............

    ReplyDelete
  12. "...በቤቴ ውስጥ የሙዚቃ መሳሪያዎች አሉኝ..ባህላዊም ዘመናዊም፡፡ እነሱንም እያጠናሁ ነው፡፡...." ENA NEGE BE KIBOARD MINAMEN CHURCH WUST ASHESHEW GEDAM LENEL NEW ENDE ? Ere ebakachehu yichen betekeresetian atebetebetu ....ye betekerestian sereatu endenebere meketel alebet ,yihe yeged new

    ReplyDelete
  13. አንዴት ያሳዝናል የሰውን ስም በውሸት ማጥፋት። ክርስትናችሁ የት ነው? ክርስቶስ ለኔ ጌታ ብቻ አይደለም፣ የጌቶች ጌታ፣ የነጉሶች ንጉስ፣ የአምላኮች አምላክ ነው። ጌታን ማክበር፣ ማወደስ፣ ስሙን መጥራት ኦርቶዶስነተን ይገልትፃል አንጂ ተሃድሶነት አይደለም። አየሱስ የሚለው ስም:---- በማትለይ ምክር ከአባቱ ጋር ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፣ ለመላአክት አለቆች ኃይላቸው፣ የኃያላን ፈቃዳቸው፣ የዓጋአዝት ርቀታቸው፣ የቅዱሳን ገዢአቸው ነው።
    አየሱስ : -- የድህነታቺን መገኛ፣ የሚሰውር፣ የሚረዳ፣ ዋጋ የሚሰጥ መምህር፣ የምከራከርልን ፣ በረድኤት የሚቀበለን፣ አረኛችን፣ አዳኛችን ነው። ስለዚህ ክርስቲያዊ ሕይወትን የምንኖረው ክርስቶስን ስንገልጥ ነው። ታላቁ ክርስቶስን የሚገልጠው ባሕርይ ወይም ክርስቶስ በዚህ ዓለም ላይ ራሱን የገለጠበት ባሕርይ ቢኖር ትህትና ነው። ስለዚህ ትሕትናን ገንዘብ ታደርጉት ዘንድ በየሱስ ክርስቶስ ስም አግዚአብሔርን አለምንላችሃለሁ።

    አህቴ ዘርፌ የሰውን ነገር ትተሽ ጌታን አምስገግኚ ። 99% ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አንወድሻለን። መድሃኒ ዓለም ክርስቶስ ይባርክሽ፣ ይጠብቅሽ።

    ReplyDelete
  14. እዉነቱን እግዚአብሄር ብቻ ነዉ የሚያዉቀዉ ስለዚህ እግዚአብሄር እዉነቱን እንድናዉቅ ይርዳን.አሜን

    ReplyDelete