Monday, March 9, 2015

የእምነት ተቋማትንና የአምልኮ ቦታን የሚመለከት ሕግ ሊወጣ ነው


 * በግለሰብ ቤት አምልኮን መፈጸም አይፈቀድም፡

(አንድ አድርገን የካቲት 30 2007 ዓ.ም)፡- ባሰላፍናቸው ሃያ አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ በርካታ የእምነት ተቋማት የተቋቋሙበት ዓመታት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ወደ መንግስት ተጠሪ ቢሮ ያቀረበው(በጊዜው አቶ ጌታቸው እና ወ/ሮ ሮማን ገሥላሴ በተጠሪነት ሲያገለግሉት የነበረው )ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከአንድ ሺህ በላይ አዲስ እምነት ለማቋቋም ጥያቄዎች ለፌደራል ጉዳዮች እንደቀረቡ እና  ከነዚህ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት የእምት ተቋም ለማቋቋም የጠየቁ ቡድኖች ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሊያሟሉ ይገባሉ ያላቸውን መስፈርቶች ማሟላት በመቻላቸው ፍቃድ እንደተሰጣቸው ያትታል፡፡

በአሁኑ ወቅት ባለፉት ሃያ ዓመታት ፍቃድ የተሰጣቸው በእምነት ተቋምት የማምለኪያ ቦታቸው የህብረተሰቡን ሰላም እያሳጡ በመሆናቸው ፌደራል ጉዳዮች እና በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ለአዲስ የእምነት ተቋም ፍቃድ በሚሰጥበት ጊዜ የአምልኮ ስፍራ ምን ምን መምሰል እንዳለበት ፤ ዝቅተኛ የቦታው መጠን ፤ ከትምህርት ቤቶች እና ከሕዝባዊ መገልገያ ቦታዎች ሊኖራቸው የሚገባ የርቀት መጠን ፤ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከቦታው ሊወጣ የሚችለው የድምጽ መጠን ፤ ቦታው በማኅበረሰቡ የቀን ተቀን አኗኗር ላይ የሚያመጣው ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ተጽህኖዎችና መሰል ጉዳዮችን መፍትሔ የሚሰጥ እና መስመር የሚያስይዝ ረቂቅ ሕግ በመውጣት ላይ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ይህን እና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በኤፍ ኤም 96.3 ላይ ቀርበው በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ይህ ሕግ ወጥቶ ወደ ሥራ ሲገባ በየስርቻው የእምነት ተቋም ስም የያዙ ፤ በግለሰብ ቤቶችን በመከራየት አገልግሎት የሚሰጡ ፤ ከአንድ በላይ የእምነት ተቋማት ያቋቋሙ  ፤ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው የእምነት ተቋማት ፤ አንዴ ፍቃድ አውጥተው የእምነት ማካሄጃ ስፍራ ሳይኖራቸው በየጊዜው የተለያዩ አዳራሾችን ለሚከራዩ (ብሔራዊ ተያትር ጀርባ የመምህራን ማኅበር ጽ/ቤት አዳራሽ ቀን ቀን ሌላ ሥራ ሲያከናውን ቆይቶ በሳምንት አራት ቀን ማታ ማታ እና ቅዳሜና እሁድ ለሁለት የእምነትተቋማት እንዲጠቀሙበት ማከራየቱ ይታወቃል) ተቋማት አሰራራቸውን በሕግ አግባብ መስመር የሚያስይዝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

3 comments:

  1. የዘገየ ቢመስለኝም በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ምክንያቱም በተለይ በየሰፈሩ ውስጥ ያለው የድምጽ ብክለት ሰብአዊ መብትን ሁሉ የሚጥስ ነው ለምሳሌ መተኛት/ማረፍ / የማይቻልበት ሁኔታ አለ፡፡ ነገር ግን ሆቴሎችን ነገር ግን ሆቴሎችን ፡ ጭፈራ ቤቶችን መልካም ነው፡፡

    ReplyDelete
  2. I think this is good but what is motive behind?

    ReplyDelete