Sunday, March 8, 2015

በሐውልቱ ላይ ለሚደረጉ ማናቸውም ተግባራት ያገባናል!


(አንድ አድርገን የካቲት 29 2007 ዓ.ም)፡- የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከመነሳቱ እንስቶ ያለው ሂደት በውዝግብ በጥያቄዎች የተሞሉ ነበሩ ፤ መንግሥት የባቡሩን ፕሮጀክት በሚቀርጽበት ጊዜ አማራጭ የባቡር መስመሮችን ሳይመለከት ቀጥታ ወደ ስራ ከገባ በኋላ የመጣ ክስተት በመሆኑ ብዙዎችን ሲያነታርክ ሲያነጋግር ሰንብቷል ፤ ሐውልቱ ከመነሳቱ እና ከተነሳ በኋላ ብዙ ጥያቄዎች መልስ ባያገኙም በማኅረሰቡ ዘንድ ሲጠየቅ  ነበር ፤ ሀውልቱ በሚነሳበት ወቅትም ረብሻ እና ብጥብጥ እንዳይነሳ በማለት በርካታ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊሶች ሐውልቱ በሚነሳበት ጊዜ ከፍተኛ ጥበቃ ሲያደርጉም ነበር፡፡

 ቅዱስ ሲኖዶስ እኚህን ታላቅ አባት የሰሩትን ሥራ እና ያደረጉትን ተጋድሎ አይቶ የወሰነው ውሳኔ እጅጉን ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም  አቡነ ጴጥሮስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምን ማለት እንደሆኑ ቤተ ክህነቱ የተረዳ አይመስለንም  ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዛን የሚደፉ ተግባራት እንዲያከናውኑ በቤተ ክህነቱ የተቀመጡ ሰዎች ይህን ሃውልት በተመለከተ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ መቻል አለባቸው ብለን እናምናለን፡፡ መንግሥታችን በዚህ ሐውልት ላይ እናንተ(ኦርቶዶክሳውያን) የባለቤትነትም ሆነ ሌላ ጥያቄ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለየ መልኩ መጠየቅ አትችሉም ? ብሎ ነገሮችን ሲያከናውን ቤተ ክህነቱም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ዝም ብሎ መመልከት ያለበት አይመስለንም፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ መብቷን ከሌሎች የምታገኝው ሳይሆን ራሷ የምታስከብረው መሆን መቻል አለበት፡፡  መብታችንን የምናስከብረው እኛው ራሰችን እንጂ በሌሎች አካላት የሚሰጠንና የምንነፈገወ መሆን መቻል የለበትም ፡፡ በዚህ ሐውልት ላይ የሚደረጉ ተግባራት ይመለከተናል የሚለውን መብታችንን የሚመለከተው አካል ድረስ  ሄደን መጠየቅና ማስከበርም ያለብን እኛው ራሳችን መሆን መቻል አለብን፡፡

አሁንም ሐውልቱ እንዴት ባለ ሁኔታ እንደሚመለስ ፤ መቼ እንደሚመለስ ፤ ሐውልቱ ወደ ቦታው ከተመለሰ በኋላ ሊመጡ የሚችሉ ስጋቶች ፤ ስጋቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመፍትሔ አቅጣጫዎችና መሰል ጉዳዮችን በመመካከር የአቡኑን ሐውልት ወደ ቦታው የሚያስመልሰው ኮሚቴ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የራሱ ስፍራ እና የራሷ ድምጽ ሊኖራት ይገባል የሚል እምነተ አለን፡፡


መንግሥት ከቀድሞ ‹‹አያገባችሁም›› መንፈስ በማላቀቅ በቀና መንፈስ ሐውልቱን ወደ ቀደመ ቦታው ለመመለስ ያዋቀረው ኮሚቴ   መስሪያ ቤቶች (የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንና የአዲስ አበባ ከተሞች መንገዶች ባለሥልጣን ) በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ይጨምር ዘንድ መልዕክታችን ነው፡፡

No comments:

Post a Comment