Thursday, March 5, 2015

ስለ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት ‹2›


 ከዲ/ን አባይነህ ካሴ
ንዑ ተጋባእክሙ
በደብረ ከዋክብት ሀገርክሙ
ክተት! ወደ ደብረከዋክብት

ጀግናን ቀን ይወልደዋል፡፡ ቀን ማለት ጭንቅ ሰዓት፡፡ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ ገድል የሚፈጽም፡፡ አሁን ብዙ ጀግኖች ደብረ ከዋክብት ገብተዋል፡፡ ክንዳቸው እስኪዝል ከእሰቱ ጋር ግብግብ ገትመ አድረዋል፡፡ ተተኪ ደጀን ግን የግድ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንድረስላቸው እና እኛም ከበረከቱ እንሳተፍ፡፡

እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች የሚገኙት ከእልፍ አንድ ቀን ነው፡፡ እንዳያመልጡን እና እንዳያስቆጩን ያስፈልጋል፡፡ በቅርብ ያላችሁ እቦታው ድረስ በመግባት አግዙ፡፡ ከየሥራ ገበታችሁ አስፈቅዳችሁ ግቡ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እዚያው ትፈልጋችኋለች፡፡ ባለመኪኖች በተለይ ፍጥነት የተመላበት ርምጃ ትወስዱ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡

በሩቅ ያላችሁ ደግሞ ቢያንስ በገንዘብ ተራዱ፡፡ የሚጠጣ ውኃ ለጀግኖቻችን ያስፈልጋቸዋል፡፡ የሚበላ እኅል ካፋቸው ሳይደርስ ይኸው ሌሊቱን አድረው አሁንም በእሳት እየተንገበገቡ ነው፡፡ ለእነርሱ ማስተናገጃ ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም እሳቱን ለማጥፋት ከተለያየ አቅጣጫ ውኃ ተሞሉ ቦቴዎች መንቀሳቀስ ይገባቸዋል፡፡ ይኽን ለማድረግ ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ በሚከተለው አድራሻ ገንዘብ በማስገባት ትተባበሩ ዘንድ ትጠየቃላችሁ፡፡

ብዙዎችችሁ እንዴት ልናግዝ እንችላለን ባላችሁት መሠረት ከዚህ ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ ልታደርጉ እንደምትችሉ እንጠቁማለን፡፡
ዝቋላ ደብረ ከዋክብት  አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ገዳም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ደብረዘይት ቅርንጫፍ
ሂሳብ ቁጥር 216s01014885


Zequala Debre Kewakibt Abune Gebre Menfes Kidus Monastery
Commercial Bank of Ethiopia
Debrezeit Branch
Ac No 216s01014885

SWIFT code is CBETETAA

No comments:

Post a Comment