Friday, March 6, 2015

መንግሥት ‹‹የእሬቻ በዓል እና የሐውልት ተከላ ሥነ ሥርዐት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የጠበል ስፍራ ይከናወናል ተብሎ በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ መተላለፉን አላውቅም›› አለ

  • ‹‹በመንግሥት ብዙኃን ስለመተላለፉ ማረጋገጥ ከፈለጋችው ሲተላለፍ የተቀረጽው በእጃችን ስላላ ልንሰጣችሁ እንችላለን ፤›› የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት
  •   ‹‹ በሥልጣን ያላግባብ ሃይማኖታቸውን መጥቀም የሚፈልጉ አንዳንድ የክልሉ ባለሥልጣናት ያደረጉት ሊሆን ይችላል እንጂ መንግሥት በፍጹም ሊያደርገው እንደማይችል ልናረጋግጥላችው እንወዳለን ፤›› የመንግሥት ባለሥልጣናቱ
መንግሥት ‹‹የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ከክልሉ የገዳ ሥርዐት ጽ/ቤት ጋራ በመቀናጀት የእሬቻ በዓልና የሐውልት ተከላ ሥነ ሥርዐት መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የጠበል ስፍራ አከናውናለ ›› ብሎ መስከረም 15 ቀን 2007 ዓ.ም በመንግሥት ብዙኃን የሰጠውን መግለጫ እንደማያውቀው አስታወቀ ፡፡


ትላንት፣ የካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ሞፈር ቤት ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ እሰከ 10 ፡00 በዘለቀው ስብሰባ ከፌደራል መንግሥት ፣ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፣ከምሥራቅ ሸዋ ዞንና ከሊበን ዝቋላ ወረዳ መስተዳድር የመጡ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፤ በስብሰባውም ላይ እነዚህ ባለሥልጣናት ‹‹ መንግሥት የዚህን ታሪካዊ ገዳም ቦታ ነጥቁ ለሌላ አካል የሚሰጥበት ምንም ምክንያት የለውም ፡፡ የእሬቻ በዓልና የሐውልት ተከላ ሥነ ሥርዐት በገዳሙ ይከናወናል ተብሎ የተላለፈውንም ዘገባ መንግሥት አያውቀውም ፡፡ ››ሲሉ በስብሰባው ላይ ለተገኙት ገዳማውያን አስታውቀዋል ፡፡

ገዳማውያኑም በበኩላቸው በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ የተላለፈውን ዘገባ ጨርሶ አናውቀውም ተብሎ ከመድረክ የተገለጸውን ለመቀበል እንደሚቸገሩ ገልጠው‹‹በመንግሥት ብዙኃን ስለመተላለፉ ማረጋገጥ ከፈለጋችው ግን ሲተላለፍ የተቀረጽው በእጃችን ስላላ ልንሰጣችሁ እንችላለን ፤›› እንዳሏቸው ምንጫችን በዘገባው ተመልክቷል ፡፡ የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ማስረጃን መሠረት ባደረገውና ጥብዐት በተመላበት ሙግት አላላውስ ያላቸው ባለሥልጣናቱ በመጨረሻ በታሪካዊው ገዳማችን የእሬቻ በዓልም ሆነ የሐውልት ተከላ ሥነ ሥርዐት ሲከናወን መንግሥት ዝም ብሎ እንደማይመለከት፤ የገልጠው ‹‹በሥልጣን ያላግባብ ሃይማኖታቸውን መጥቀም የሚፈልጉ አንዳንድ የክልሉ ባለሥልጣናት ያደረጉት ሊሆን ይችላል እንጂ መንግሥት በፍጹም ሊያደርገው እንደማይችል ልናረጋግጥላችው እንወዳለን ፤›› እንዳሏቸው ምንጫችን ዘግቧል ፡፡

ስብሰባውን ለመሩት ባለሥልጣናት እጅግ ልብን በሚናካና በተማጽኖ ጭምር ‹‹ እኛም እንደሌላው ኢትዮጵያውያን ነን ፤አባትነታችን ባይከበር እንኳን ኢትዮጵያዊነታችን ሊከበር ይገባ ነበር፤ ኢትዮጵያዊ መሆናችን ተዘንግቶ እንደ ባዕድ ውጡ መባለችን እጅግ ያስቆጫል ፡፡ዉጡ ከሚሉን ወገኖቻችን ጋራ ለመግባባት ኢትዮጵያዊ መሆናችን ብቻ በቂ ነበር ፡፡ለእነርሱ ግን ሌላ አስፈለጋቸው፡፡እኛጥቃት ሰልችቶናል፤ በየጊዜው ይዛትብናል፣እንደበደባል፣ገዳማችን ይቃጠላል ››ያሉት ገዳማውያኑ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለአገሪቱ የዋለችውን ውለታ የሚመጥን ክብር ሊሰጠን ይገባል፤ በሕገ መንግሥቱ መሠረትነት ሕጋዊ ከለላና ጥበቃ እንድታደርጉልን እንጠይቃልን ››ማለታቸውን የስብሰባው ምንጫችን በዘገባው ተመልክቷል፡፡ባሥልጣናቱም እንዲህ ዐይነቱን አስተሳሰብ እንደሚዋጉ ገልጠው፤‹‹እኛ ከጎናችሁ ነን፤ በአጥፊዎቹም ላይ አጣርተን ርምጃ እንወስዳለን ፡፡ምንም ዐይነት ሥጋት አይግባችሁ ››ብለዋቸዋል ፡፡

ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሓላፊ ጋር በመሆን የእሬቻ በዓልና የሐውልት ተከላ ሥነ ሥርዐት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የጠበል ስፍራ እንደሚከናውን በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ መግለጫ የሰጡት የገዳ ሥርዐት ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ ለገሠ ነገዋ በስብሰባው የተገኙ ሲሆኑ፤ስብሰባው ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ አንዳች ቃል አለመተንፈሳቸው በገዳማውያኑ ዘንድ አግራሞትን እንደ አጫረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ተመልክቷል ፡፡

Source :- Abelak

2 comments:

  1. cherwere yaseman temesgen

    ReplyDelete
  2. እግዜአብሔር ይስጥልን ቃል ህይወት ያሰማችሁ

    ReplyDelete