Thursday, March 5, 2015

ስለ ‹‹ዝቋላ ደብረ ከዋክብት›› ቤተ ክርስቲያን ትጣራለች ‹5›







1.  ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ችግር እስኪቀረፍ እና ቋሚ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ ለችግሩ የሚፋጠን ቡድን በማቋቋም እሳቱን ለማጥፋት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከሚመለከታው አካላት ጋር በአስቸኳይ በመነጋገር በግዥ እና በውሰት የሚሟሉትን በፍጥነት ማሟላት ቢችል ፤ ከአቅም በላይ የሆኑትን ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግሮ ማቅረብ ቢችል
2.  አልፎ እንዳይቆጨን ዛሬ ላይ አቅሙ የፈቀደ ምዕመን  የውኃ ቦቴ ይዞ በአስቸኳይ ቢንቀሳቀስ፡፡ ቦቴ መኪና ያላቸውን የሚያውቅ ሰው በእርዳታ ወይም በክፍያ መኪናዎችን ወደ ቦታው  በማንቀሳቀስ  እያስተባበረ ቢፋጠን
3.   በመኪና መንቀሳቀስ የሚችል ደግሞ ውኃ ለማጥፋት ወደስፍራው ላመራው ሕዝብ የሚጠጣ ውኃ እና የሚቀመስ እኅል ይዞ ቢቻኮል፣
4.  በተለያዩ ግላዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ወደ ቦታው ማምራት የማይችሉ ምዕመናን በያሉበት የአቅማቸውን በማስተባበር ለዚህ አስቸኳይ ተግባር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ መላክ ቢችሉ
5.   ከእሳቱ አደገኛነት የተነሣ አንዳንድ ጉዳቶች ሊከሰቱ ስለሚችሉ የሕክምና ባለሙያዎች የመጀመሪያ እርዳታ ሳጥናቸውን አንግበው ቢነጉዱ፣
6.    ጉልበት ያለው በጉልበቱ እቦታው ድረስ ሄዶ እሳቱን ለመቋቋም እየተጠራራ ቢንቀሳቀስ፣ በሞባይል፣ በኢሜይል፣ በፌስቡክበተቻለው ሁሉ፣ ይሕንን መልእክት በማስተላለፍ ላልሰማ ብናሰማ


  • ባቶች በየጊዜው በገዳማት ላይ የሚነሱ እሳቶችን ትውልዱ እሳት አጥፊ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ቋሚ የመፍትሄ አቅጣጫ ቢያመላክቱ


በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ የምትገኙ ወጣቶች ፤ ቤተክርስቲያን የምታውቃችሁም ማኅበራት ፤ ስለ ቤተክርስቲያን ግድ የሚላችሁ ምዕመናን ፤ ሰዎችን የማስተባበር ልምድ ያላችሁ ሰዎች ይህን ችግር ለመፍታት እና እሳቱ በትውልዳችን የባሰ ጉዳት እንዳያስከትል ለዚህ ችግር ፈጥናችሁ ትደርሱ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ትጠየቃላችሁ፡፡
በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የምትገኙ ምዕመናን ችግሩን ለመፍታት በቅርበት የማትገኙ ምዕመናን እሳቱ የባሰ ጉዳት ሳያደርስ ይቆም ዘንድ  በጸሎት ታስቡ ዘንድ ትለመናላችሁ፡፡

  ነገ እንዳይቆጨን ዛሬ ላይ እንንቀሳቀስ

1 comment:

  1. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

    ለመሆኑ ግን በየገዳማቱ የሚነሳው ቃጠሎ ለምንጣሮ ወይም የእርሻ መሬት ለማዘጋጀት ነው እየተባለ እስከመቼ እንታለላለን? ደግሞስ ለምንጣሮ የተያያዘ እሳት ሁሉ ለምን በገዳም አባቶች የተለማውን ደን ብቻ ያቃጥላል? መንጣሰሪዎቹ አይጠነቀቁም ወይ? ሁሉም መንጣሪዎች ዝንጉዎች ናቸው ወይ? በገዳማትና በቤተክርስቲያናት ብቻ ለምን እሳት ይያያዛል? የኸ ነገር አረ ብዙም አያስኬድም እግዚአብሔርም እኮ ያጋልጣል። እስከመቼ አንዱ ያለማውን አንዱ እያወደመና እያቃጠለ አንዱ የገነባውን አንዱ እያፈረሰ ይህች አገር ስትደቅ ትኖራለች? በቅኝ ግዛት ተገዝተናል ወይ? ደንና ታሪክ ይኼን ያህል የሚያወድመው ማነው በቅኝ ግዛት የገዛን? ጠላታችንን ሳናውቅ አኮ ጋዳማት እና ደኖች የያዟቸው ሀብቶቻችን መውደም ከጀመሩ አመታት ተቆጠሩ። እንስሳትና አእዋፋት እጽዋት በሰው ምክንያት ሠላም አጡ። ለምን ህዘብ በየአብያተ ክርስቲያናት ምህላ አንዲያደርግ አይደረግም ቀልድ ነው ወይ የተያዘው የተፈጥሮ ሀብትና ታሪክ ሲወድም።የውጭ ታሪክ ፀሐፎዎችና ተመራማሪዎች መጥተው ለምን ይህን መሰለ ታሪካችሁንና ሀብታችሁን ታወድማላችሁ ብለው ይንገሩን ወይ? እነሱማ የኢትዮጵያ ታሪክና የተፈጥሮ ሀብት የዓለም ሀብት ነው ብለው ያምናሉ እኛ ነን እንጂ አይምሮ ያጣነው። ስለሚወድመው ሀብት ምንም ደንታ የሌለን።
    አባካችሁ ምህላ ፀሎጽ ይያዝና አምላካችንን እንማፀን። ትዕቢት ለኢትይጵያ አገራችን አያዋጣትም። ከአምላኳ ሸሽታ መኖር አትችልም። እጆቿን ትዘርጋና ተማፀን። እንላለን።

    ReplyDelete