Thursday, October 9, 2014

‹‹ሊበላኝ የፈለገን አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው›› ሀገርኛ ብሒል

Click here በቤተክህነት የተደረገው ስብሰባ ሙሉ ቪዲዮ ከሙሉ መግለጫ ጋር 

አንድ አድርገን መስከረም 30 2007 ዓ.ም
በስብሰባ ላይ የተባሉ
  • በሩ ለመንግስትም ስጋት ነው:: አልሸባብ ከማበረ ቅዱሳን  የተለየ አላደረገም
  • የሚያካብተው ገንዘብ ለመንግስት መገልበጫ ቢውልስ?
  • በምርጫ 97 በማበሩ ገንዘብ እየተሰጣቸው ጸበል ረጭተው ሌላ ቅስቀሳ ያካሂዱ ነበር
  • አሜሪካ ውስጥ የማበሩ ቤተ ክርስትያን ተመስርቷል:: ( የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስትያን ሲያትል):: ማን ባረከው? ቅዱስ ሲኖዶስ እንዴት ቆሞ ይመለከተዋል?::
  • እያንዳንዱ ፕሮፌሰር የሚያመሸው በረ ቅዱሳን ሕንጻ ውስጥ ነው? ምን ፈልጎ ነው? 
አዎ ይችህ ቤተ ክርስቲያን በርካታ መንጋውን ለመምራት በእግዚአብሔር የተመረጡ አባቶችን አፍርታለች፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ለእምነታቸው ፤ ለሀገራቸው ፤ ለሚመሩት ሕዝባቸው ፤ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ስም ተሰይመው ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚመሯት ቀጣይ አባቶች አርዓያነታውን አሳይተው ወደ ማይቀረው አለም ሄደዋል፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስ(ሁለተኛው ፓትርያርክ) የመሰሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  ካፈራቻቸው እና ለዚህ ታላቅ ክብር ከሾመቻቸው ፓትርያርኮች ውስጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ  የማይተካ የሚመስል አሻራቸውን በሚታይ በሚዳሰስ መልኩ ካስቀመጡ የላቀ ስብዕናና ታላቅ የሀገር ወዳድነት መንፈስ ካላቸው ገዢዎች በያዙት ‹ረግጬ ልግዛህ› መንገድ በአቋማቸው ምክንያት ብዙዎች  የማይደፍሩትን የሞት ጽዋ እስከመጎንጨት የደረሱ ፓትርያርክ ቤተክርስቲያቱን አስተዳድረዋታል፡፡


ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ቀርበው ታሪካቸውን ሲያጫውቱ በእሳቸው የተማሪነት ዘመን ተማሪዎች አጥፍተው ንጉሡ ‹ይገረፉ› የሚል ትዕዛዝ ሲያወርዱ በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ትዕዛዝ የተቃወት የወቅቱ የእምነት አባት ቀዳሚ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ መሆናቸውን አውግተውናል፡፡ ቀደምት ከቤተ መንግሥት የሚመጣ ኢ-ፍትሐዊ ለሆነ ትዕዛዝ የመጀመሪያ ተቃዋሚዎች የእምነት አባቶቻችን ነበሩ፡፡ አሁን ግን ‹ይገረፉ› ሲባል ልምጭ አቀባይ አባቶችን አፍርተናል፡፡አሁን ላይ ነገሮች ሁሉ ተገላቢጦሽ ሆኑና ፤ የእምነት አባቶች የምንላቸውም ተላልፈው የተሰጡትን ፤ ፍትህ  ለተጓደለባቸው ፤ ‹አቤት› ከማለት ይልቅ የይሁዳን ምግባር በመከተል ለቤተ መንግሥት ሹመኞች አሳልፎ ሰጪ መሆናቸውንና ለጭቃ ጅራፍ የሚያዘጋጁ መሆናቸውን ስንመለከት ያለንበት የመንፈስ ልዕልና ዝቅጠትን ያመላክተናል፡፡


ከቀናት በፊት መንግሥት አደራጅቶ ባሰባሰባቸው ‹‹የገዳማትና አድባራት ተወካዮች›› ነን በሚሉ አንድ ማኅበርን ለመተናኮል ተሰብስበው ተራ በሆነ ውንጀላ ሲወያዬ ቆይተዋል፡፡ ትላንት ስለማዕተብ› ሰው እውነተኛ እምነቱን ሲገልጥ እነሱ በማይገባ  ነገር ሲዶልቱ ታይተዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ የሰጠውንና እንዲሰራ የተፈቀደለትን ማኅበር አንድ ፓትርያሪክ መሰሎቻቸውን ሰብስበው አልባሌ ነገር መነጋገራቸው ምን ያክል ህገ-ወጥ ስራ ፓትርያሪኩ እየሰሩ እንደሆነ ያሳያል፡፡ይህ አሰራራቸው መንግሥት እጁን ማስገባት ያቃተው አካል ላይ እሳቸው እና ግብረ አበሮቻቸው ለመንግሥት ሀሳብ መሳካት  መንገዱን እየጠረጉለት እንደሚገኙ ያመላታል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን አካሄዳቸውን ዝም ብሎ እንደማያልፈው ተስፋ አለን፡፡ ፓትርያርኩ ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን የዘነጉትም ይመስላሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሌላው አሁን ያልታያቸው ነገር ይህ የስብሰባ ሂደት መንግሥት ሊመታ ያሰበውን አካል ለፊልም መስሪያ(እንደ አኬልዳማ) ግብአትነት እንደሚጠቀምበት ለማወቅ አለመፍቀዳቸው ወይም አለማወቅ መቻላቸው ነው፡፡  

አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ሳሉ እንኳን የአቡነ ማቲያስን ያህል ኢህአዴግ መስለው አልታዩም ነበር፡፡ አቡነ ጳውሎስ ፖለቲካው በአግባቡ የገባቸው ሰው ነበሩ አቡነ ማቲያስ ግን የቀደመ ኑሯቸው በሀገ እስራኤል እና በሀገረ አሜሪካ ስለነበረ የመንግሥትን አካሄድ በአግባቡ የተረዱ ሰው አይደሉም፡፡ አቡነ ማቲያስ ዛሬ አንድ ማኅበር ላይ የተነሳውን መንግሥት ነገ የቤተክርስቲያኒቱን ህልውና ላይ እንደማይመለስ የተገነዘቡ አይመስሉም፡፡  የተቀመጡበትን ወንበር መርሳት ከታሪክ ተጠያቂነት እና ተወቃሽነት አያድንም ፤ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ሕይወታቸውን ያጡበት አንዱ ምክንያት የደርግ መንግሥት ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ማድረግ የሚፈልገውን ነገር ‹አይሆንም› በማለታቸው ብቻ ነበር፡፡

 በቅዱስ ሲኖዶስ ለማኅበረ ቅዱሳን በሰጠውት መመሪያ መሰረት እየሰራ አይደለም ካለ አሰራሩን መፈተሽ ፤ ካጠፋም መቅጣት ፤ መመሪያውን ማሻሻልና መከለስ ያለበት ቅዱስ ሲኖዶሱ ሆኖ ሳለ ፓትርያርኩ ከአሰራር ውጪ ደስ ያላቸውን አካል እየጠሩ ለሰሚ በማይመች ስብሰባ የሂሳብ አሰራር ተግባራዊ እንዳሆን ከሚታገሉ  ፤ ስርአቱ ቢዘረጋ ነገ የሚቀርባቸውን ገቢ ከሚያሳስባቸው ፤ የቤተክርስቲያኒቱ መበዝበዝ ከማያሳስባቸው  ጋር ስብሰባ  ማካሄድ ተገቢ መስሎ አይታየንም፡፡ ፓትርያርኩም ምክክራቸው ከማን ጋር መሆን እንዳለበት ቅዱሳን አባቶች ቢነግሯቸውም ሰሚ ጆሮም አላገኙም ፤ ራስን ለማዳን ሌላውን ለማስመታት መንገድ መጥረግ ተገቢም አይደለም፡፡

መልዕክታችን አሁን ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያገለግሉኛል በጎቼንም ከተኩላ ይጠብቁልኛል ብላ በሙሉ እምነት ባለ ሙሉ ስልጣን አድርጋ የሾመቻቸው ከቤተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ጀምሮ እስከ ብጹአን አባቶች ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ዋጋ ከፍለው እዚህ ደረጃ ያደረሷትን የእልፍ አባቶች አጥንትና ደም ያለበት በመሆኑ ካሉበት የቀንድ አውጣ ኑሮ በመውጣት አባትነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ነው፡፡ አሁን ያሉት አባቶችና ቅዱስነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀድሞ አባቶች  የወንጌል አርበኝነት ፤ የተዋህዶ ዓይን ፤ የመአዘን ድንጋይ ፤ የጎጆ ምሰሶ ሆኑው ያለፉትን  ስራቸውንና ታሪካቸውን አውቀው ራሳቸውን ለተሻለ አገልግሎትና ቀንበር ለመሸከም ማዘጋጀት ይገባቸዋል፡፡ የዛኔ አባት ስናገኝ እኛም ልጆች እንሆናለን፡፡ያለበለዚያ ቅዱስነታቸው በዚህ አካሄዳቸው ‹‹ሊበላኝ የፈለገን አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው›› የሚለውን ተረት ትዝ እንዲለን እያደረጉ መሆንዎትን አይዘንጉ፡፡

ለማንኛውም ስብሰባው ላይ ምን ሲባል እንደነበር ከዚህ በታች ያለውን የቪዲዮ ምስል ይመልከቱ
Click here በቤተክህነት የተደረገው ስብሰባ ሙሉ ቪዲዮ ከሙሉ መግለጫ ጋር 





    6 comments:

    1. ጐበዝ አሁን ነውይ የአቡነ ቴዎፍሎስ ና አቡነ ጳውሎስ ነገር ትዝ ያላችሁ

      ReplyDelete
    2. Bogochin kelakilo yete sebesebe yetekulawochi sibsib habt nibret habit nibret eyalu mahibere kidusan layi ejachewun kemikesru berasachew ena bebete sebochachew sim yakabetutin habit masmezgeb yalebachew yilikun ye debr astedadai ena tsehafiwochi nache kemudaye mitsiwat yegelebetutin

      ReplyDelete
    3. Fathers are saying the right thing.

      ReplyDelete
    4. our fathers are on the right track!

      ReplyDelete
    5. እኔ ስለማህበሩ የተባለውን ምንም ማለት አልሻም ማህበሩ ለቤተክርስቲያን የቆመለትን አላማ ከመደገፍ በስተቀር ።
      ነገር ግን ሰለተናገሩት አባቶች ግን ማለት ፈለኩኝ ወደፖለቲካቸው ንግግር መግባትም አልፈልግም ስራው ያውጣው ይላል የሰፋሬ ልጅ።
      ሁለተኛው ምስል ላይ የተናገሩት አበት እውነት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸውን? የሚል ጥያቄ ስለፈጥረብኝ ነው።
      እንዲህ አሉን
      በስሬ 100 ሰራተኞች አሉኝ ብለው ጀመሩ የእግዚአብሄር አገልጋይ ካህናት ሳይሆኑ የእሳቸውን እጅ የሚጥብቁ ተስፈኛ ሰራተኞቻቸው እንደሆኑ አድርገው ።
      እውነት ከልብዎ ይሆን? ከእርሶ ውጭ ተስፋ የላቸውም?
      ወረድ ይሉና ደግሞ በአርአያ ስላሴ መፈጠራቸውን ይነግሩናል። ግን በፈጥራቸው ሳይሆ ን በእርሳቸው ንግግር ተስፋ የሚኖሩ?
      ቤተክርስቲያንን ሊያገለግሉ ሳይሆን ቁጥ ብለው የቤተክርስቲያንን ገንዘብ እንዲያገኙ ያሰቡላቸው ሰራተኞቻቸው እንደሆኑ ከእርሳቸው በቀር የሚያስብላቸው / የፈጠረውን ፍጡር የማይረሳ የሰማይ አእዋፍን የሚመግብ አምላክ የማያውቃቸው ምስኪኖች እንዳሉዋቸው አስረዱላቸው ሰበኩላቸው
      ቀጥል አድርገው እነዚህ ውጭ ሀገር ሄደው መኖር አለባቸው እንጂ እንዴት ጎንደር ቤተክርስቲያን ሄደው ዝቅ ተደርገው ይሰራሉ ይሉናል።
      እውነትም ቅዱስ አባታችን አትወያዩ ይሉናል ቤተክርስቲያኗን ለመናፍቃን መዘባበቻ እናደርጋታለን ይሉናል እኔ ግን በዘ ህ አልስማማም እናዳሉት እውነት ብለዋል እላለሁ አለመነጋገር እንዲህ ያለው አስተዳዳሪ እና ሰባኪ እንዳይታይ ያደርግ ነበር።
      ግን ቤተክርስቲያናችን አምላኴ ከእርሷ ጋር ስላለ ጎደሎውን እየሞላ በቅድስናዋ ትኖራለች
      እግዚአብሄር ያአባቶቻችንን ልቦና ይመልስልን እያልን ወደእርሱ እንጮሀለን ወዴት እንሄዳለን።

      ReplyDelete
    6. wow Sorry.BEALEBETUN KALAWOKU ATIRUN AINEKENIKU.




      ReplyDelete