Thursday, October 31, 2013

የተሀድሶ ርዝራዥ በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን


  • ቅዳሴን በ45 ደቂቃ እንዲያልቅ አድርገዋል፡፡
  • ‹‹ሥላሴ ግቢ ውስጥ እሾህ ተከላችሁብኝ ፤ ማህበረ ቅዱሳንን የሚያጠፋልኝ ካለ ደሜን እለግሳለሁ፡፡››
  • የራሳቸውን ደመወዝ 5000 ብር አድርሰዋል ፤ ድርሳናት ገድላት እና ተዓምራት በጸበል ቤት እንዳይነበብ ከልክለዋል፡፡
  • በአስተዳዳሪነት ዓመታቸው በቦታው ታይቶ አና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መብረቅ ከሰማይ በመውረድ ረዥም እድሜ ያላቸውን ጽዶችን አቃጥሏል ፡፡(በአጼ ዘርዓያቆብ ዘመነ መንግሥት ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከሰማይ ብርሃን የወረደበት ቤተክርስቲያን ነው፡፡ )
  • ‹‹የማርያም ስም ሲጠራላችሁ ደስ ይላችኋል ፤ ኢየሱስን ስሰብክላችሁ ግን ቦታ አትሰጡትም ፤ ማርያም እኮ ከእግዲህ ዋጋ የላትም ፤ የኛ ጌታ ሁሉን ፈጽሞልናል›› አባ ማርቆስ በአውደ ምህረት ከተናገሩት የተወሰደ
  • ‹‹መጽሀፍ ቅዱስን በደንብ የተመራመረው ፕሮቴስታንት ሆነ ፤ ከታቦት ወንጌል ይቀድማል ፤ ኪዳን ከምትመጡና ቅዳሴ ከምታስቀድሱ መጽሐፍ ቅዱስ ብታነቡ ይሻላል›› የአባ ማርቆስ የጠርዝ ምንፍቅና አስተምህሮ


(አንድ አድርገን ጥቅምት 21 2005 ዓ.ም)፡-  ተሀድሶያውያን አውደ ምህረቱን ካጡ  አመት አልፏቸዋል ፡፡ የዛሬ ዓመት  ጉዳያቸው በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሊታይ የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል በዚህ አስተምህሮ ፊት አውራሪዎቹ አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በመላ ሀገሪቱ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ተቀባይነትን ስላጡ አይናቸውን ከሀገር ውጪ አብያተ ክርስቲያናት ላይ አድርገዋል በቅርቡም በአንዱ የአረብ ሀገር የሶስት ቀን ጉባኤ አካሂደዋል ከዚህ ቀደም በጉባኤ ብር ኪሳቸውን ሲሞሉ የነበሩት ሰዎች አሁን ላይ የገቢ ምንጫቸው መሟጠጡን ተገንዝበት በሌላ ሙያ በመሰማራት ከሀገር ውጪ የወጡም ይገኛሉ በዚህ መንገድ ላይ የሚገኙት አውራዎቹ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ያጡትን ተቀባይነት ለማደስ ያስችላቸው ዘንድ በዘመሪት ፋንቱ አማካኝነት የይቅርታ እና የመታረቅ ጥያቄ ማቅረብ መፈለጋቸው ይታወቃል እንደ እኛ እምነት ለመታረቅ ያሰቡት ከአስተምህሯቸው ጋር ቢሆን መልካም ነበር የእነዚህ ሰዎች ርዝራዦቻቸው ግን አሁንም በየቦታው በግለሰብ ደረጃ በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ተቀምጠው አመቺ ቀን እየጠበቁ ይገኛሉ ከእነዚህም መካከል የደብረ ብርሃኑ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አስተዳዳር አባ ማርቆር ብርሃኑ አንዱ ናቸው፡፡

አባ ማርቆስ ቀደም ሲል በናዝሬት/ በአዳማ /ደብረ ጸሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን በነበሩበት ወቅት የተሃድሶን አላማ ማራመድ የጀመሩት አባ ማርቆስ ብርሃኑ አላማቸውን ለማሳካት ህዝቡን አማራና ኦሮሞ ብለው ከከፋፈሉ በኋላ ኑፋቄአቸውን ለማስረጽ ቢሞክሩም ህዝቡ ስለነቃባቸው ወደ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ሄደው በመቀጠር ናዝሬትና አዲስ አበባ በሚገኙ የተሀድሶ ፕሮቴስታንት ማሰልጠኛ ገብተው በመሰልጠን ውስጥ ውስጡን ኑፋቄያቸውን በመስበክና የተሀድሶ ዘማርያንና ሰባክያንን በማሰማራት ስራቸውን ሲሰሩ ባለባቸው ችግር ምክንያት ከሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ከምዕመናን በመጋጨታቸው እንዲሁም በቤተክርስቲያን እድሳት ሰበብ በርካታ ብር በመዝረፋቸው ህዝቡ ሲነሳባቸው በወቅቱ ወደ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በመሄድ በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በአስተዳዳሪነት ሊቀጠሩ ችለዋል፡፡


በደ/ብርሃን ቅድሥት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ምን ሰሩ?
  1. ደብረ ብርሃን ከመጡ በኋላ ምዕመናን ለወንጌል ያላቸውን ፍቅር አጥንተው በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነትና እውቅና ለማግኘት ሳምንቱን ሙሉ አውደ ምህረቱን በመቆጣጠር ምዕመናን ምንም አይነት የሃይማኖት መሰረታዊ ዕውቀት እንዳይኖራቸው በማኅበራዊ ጉዳይ /በትዳር ላይ / ብቻ በማስተማር ተከታዮችን በማፍራት ስራ ሲሰሩ ነበር፡፡
  2. ከመናፍቁ አሰግድ ሳህሉ ጋር ጥብቅ ግንኑነት ያላቸው እኝሁ ግለሰብ በተሀድሶ ጉባኤ ያልተደፈረውን አህጉረ ስብከት በተሀድሶ ዘማርያንና ሰባክያን ለማጥለቅለቅ ከግብረ አበሮቻቸው ከእነ አሰግድ ሳህሉ ሀብታሙ ሽብሩ እና ዘማሪ ታምራት ጋር በመመሳጠር ያለ ሀገረ ስብከቱ ፈቃድ ህገወጥ ገባኤ ከሚያዚያ 5-7/2005 ማካሄድ ችለው ነበር ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሀብታሙ ሽብሩ ሲማርበት የነበረው /ትቤት በደ/ብርሃን /ሥላሴ በመሆኑ ቀደም ሲል እንዳያገለግል ስለታገደ አባ ማርቆስ አስታራቂ ሆነው በመቅረብ ወደ /ትቤቱ አገልግሎት እንዲመለስ ከፍተኛ የማግባባት ስራ ሲሰሩ ነበር፡፡ ሀብታሙ ሽብሩም በተናጠል /ብርሃን በሰራው መኖሪያ ቤቱ በመውሰድ ለሰንበት ተማሪዎቹ ኑፋቄውን በመዝራት ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነበር፡፡
  3.  አባ ማርቆስ ብርሃኑ አስካሁን በተሀድሶ ያልተበረዘውን የደ/ብርሃን /ስላሴ /ት ቤት ለመከፋፈልና የተሀድሶ ኑፈቄን ለማስገባት በስነ ምግባር ምክንያት የተባረሩትን በማሰባሰብ እርስ በርሳቸው እንዲከፋፈሉ ካደረጉ በኋላ የሰ//ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ አድርገው የሰንበት ት/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ‹‹ሕጋችሁ ቀጥቃጭ ነው ይህንን ሕጋችሁን ወደዚያ ጣሉ ሱሪ መልበስና ማገልገል ይቻላል ጥፍር ቀለም መቀባት ይቻላል ‹‹ኮርስ ያልተከታተለ አገልግሎት ላይ አይመደብም›› የምትሉትን ሕግ አስተካክሉ ማንም ለማገልገግ ፈቃደኛ ሆኖ የመጣ ሁሉ ተመድቦ ማገልገል ይችላል ፤ ኮርስ መማር አይጠበቅበትም›› በማለት /ትቤት ተሀድሶ እንዲገቡ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሥራ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ሰ/ት ቤቱን በመከፋፈል በወቅቱ የነበረው አመራር እንዲወርድ አድርገዋል፡፡ በየሳምንቱ በአገልግሎት ሰበብ ለሰ/ትቤቱ አባላት ትምህርት ሲሰጡ ነበር፡፡
  4. ሚያዚያ 12 እና 13 /2005 በተከሄደው ጉባኤ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ‹‹በጾመ ሁዳዴ በአባቶች ስርአት መሰረት ጭብጨባና እልልታ አይፈቀድም›› ብለው አስተምረው ከወረዱ በኋላ ‹‹ጭብጨባና እልልታ ምስጋና ነው ይፈቀዳል›› ማለት ለምዕመኑ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
  5.  ምልጃን በተመለከተ፡-  በቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ‹‹ቀጥታ ልመናችንን ለጌታ ማቅረብ እንችላለን ይህንን ብናደርግ ሚካኤልና ገብርኤል አይጣሉንም› በማለት አስተምረዋል፡፡ይህም ትምህርታቸው በምዕመናን ዘንድ ቁጣን ስለቀሰቀሰባቸው ለጊዜው ተደናግጠው ከቦታው ዘወር ለማለት ተገደዋል፡፡
  6.  በቢሮአቸው ለባለሀብቶችና ለባለሀብት ልጆች በየሳምንቱ ልዩ ልዩ ትምህርቶችን በመስጠት፡- ‹‹ጊታር ጌታን ማመስገኛ ነው ፤ሱሪ ለብሶ መቁረብ ይቻላል፤ጥፍር ቀለም መቀባት ይፈቀዳል፤ መጽሀፍ ቅዱስን በደንብ የተመራመረው ፕሮቴስታንት ሆነ ፤ ከታቦት ወንጌል ይቀድማል ፤ ኪዳን ከምትመጡና ቅዳሴ ከምታስቀድሱ መጽሐፍ ቅዱስ ብታነቡ ይሻላል›› በማለት የሚያስተምሩ ሲሆን ተጨማሪ ትምህርት የምታገኙበትን ‹‹ኤልሻዳ የቴሌቪዥን ጣቢያ›› ተከታተሉ በማለት ኤልሻዳይ የፕሮቴስታንት የቴሌቭዥን ጣቢያ እንዲከታተሉ ለምዕመኑ ውስጥ ውስጡን  ሲጋብዙ ኖረዋል፡፡
  7. ኑፈቄአቸውን እንደፈለጋቸው ለማራመድ እንቅፋት የሆናችውን ማኀበረ ቅዱሳንን ‹‹ሥላሴ ግቢ ውስጥ እሾህ ተከላችሁብኝ ፤ ማህበረ ቅዱሳንን የሚያጠፋልኝ ካለ ደሜን እለግሳለሁ እነ በጋሻው ችግር የለባቸውም ፤ ችግር ያለበት ማኅበረ ቅዱሳን ነው›› በማለት ውስጥ ውስጡን  ህዝቡ ማኅበሩ ላይ እንዲነሳ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
  8. ለአላማቸው መሳከት እንዱ እንቅፋት የሆኑአቸው ብጹዕ አቡነ አፍሬም በመሆናቸው ‹‹እርሳቸው አርጅተወል ጃጅተዋል ፤ የቃለ የወንጌል እንቅፋት ናቸው መነሳት አለባቸው›› በማለት ብጹእነታቸው በሕዝብ እንዲጠሉ ሰፊ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር፡፡
  9. ጵጵስና ለመሾም ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ሲሆን ‹‹ጵጵስና ለመሸም 60 ሺህ ብር ያስፈልጋል ፤ ይህን ብር ክፈሉልኝ›› የሚል ቅስቀሳ ላይ ተሰማርተው ጥቂት ብሮችን መሰብሰብ ችለውም ነበር፡፡
  10.  በወንጌል ሰበብ በየቤቱ በመሄድ ያለ ደረሰኝ በርካታ ገንዘብ ያሰባሰቡና ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ ሲሆን የታወቀባቸውና ገቢ የተደረገውንም ገንዘብ ከስብከተ ወንጌሉ እውቅና ውጭ በርካታ ገንዘብ ስነ ምግባርና ሃይማኖት ለሌላቸው ዘማርያንና ሰባክያን በመስጠታቸው 4 የስብከተ ወንጌል አባላት ድርጊታቸውን በመቃወም አገልግሎቱን በማቋረጣቸው የስብከተ ወንጌሉ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር አድርገዋል፡፡
  11. ለጉባኤ በሚሰቀሉ ፖስተሮች ላይ ‹‹መንፈሳዊ ጉባኤ›› መባል የለበትም ‹‹የወንጌል ጉባኤ›› ነው ተብሎ መሰቀል ያለበት በማለት ቤተክርስቲያን ለልጆቿ የምታደርገውን መንፈሳዊ ጥሪ  የፕሮቴስታንት ይዘት እንዲላበስ አድርገዋል፡፡
  12. በሕገ ወጥ መልኩ የቤተ ክርስቲያኑን ቤት እና የመቃብር ቦታ በመሸጥ እንዲሁም ለሁለገብ ህንጻው ከሚሰባሰበው ብር ላይ ለግል ጥቅማቸው ቤተ ክርስቲያኑን በመመዘበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ጠንካራ አደረጃጀትና ሰፊ የአገልግሎት አድማስ እንዳለው የሚነገርለት የማኅበረ ቅዱሳን /ብርሃን ማዕከልም ጉዳዩን በዝምታ ሲያስተውለውም ነበር፡፡

አባ ማርቆስ ቀድሞ በደብረዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት በሰበካ ጉባኤ ስር የሚተዳደረውን የመንፈሳዊ የጉዞ ኮሚቴ ለምን ራሳችሁን ችላችሁ አትወጡም? ለምንስ በሰበካ ጉባኤ ስር ትሆናላችሁ? በማለት ያነሱትን የመከፋፈል ስራ ተሳክቶላቸው ሰበካ ጉባኤውን ከመንፈሳዊ የጉዞ ማኅበሩ ጋር መነጠል ችለው ነበር :: ይህ የፈረሰው መንፈሳዊ የጉዞ ማኅበር እስከ አሁን ድረስ ለመሰባበስ እና ወደ ቀደመ ስራቸው ለመመለስ አለመቻሉን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እኝህ ግለሰብ ደብረዘይት ላይ የሰሩትን ስራዎች ዳግም ደብረ ብርሃን ላይ እንዳይደግሙት ስለ ቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ ወጣቶች ከደብረ ዘይት እኝህ ሰው የተመደቡበት ደብረ ብርሃ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ድረስ በመሄድ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ለሚባሉት ሰዎች ስለ ቀደመ ተግባራቸው መረጃ ከመስጠትም በተጨማሪ እኝህን ሰው እጅጉን አደገኛ ስለሆኑ በየዋህነት እንዳይመለከቷቸው ወንድማዊ ምክራቸውን ሰጥተዋቸው ነበር፡፡(መረጃውን ባጠቀሙበትም)

እኚህ ሰው ደብረዘይት በነበሩበት ጊዜ በእለተ ሰንበት ቅዳሴውን ካህናት በለሊት ያለ ሰዓት እንዲገቡ በማድረግ ከሰዓት ውጪ እጅግ በማለዳ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ቅዳሴው እንዲጠናቀቅ በማድረግ ለማስቀደስ ለመቁረብ እና ለማስቆረብ የሚመጣውን ምዕመን አዝኖ እንዲመለስ አድርገዋል፡፡ በደብረዘይት ቅዳሴውን እጅግ በማሳጠር ከአንድ ሰዓት በታች በ50 ደቂቃዎች ውስጥ እንዲያልቅ በማድረግ የስብከቱን ሰዓት ለቅዳሴው በማስበለጥ ለህገ ወጥ ሰባኪዎቻቸው አውደ ምህረቱን እንዲፈነጩበት አድርገዋል፡፡ በቅርቡ በደብረ ብርሃን ከቀኑ 6 ሰዓት ቅዳሴ በመግባት ከ45 ደቂቃዎች በኋላ ቅዳሴ እንዲጠናቀቅ አድርገዋል ፤ ምዕመኑም እጅጉን ግራ በመጋባት ስሜት ይህ ለምን እንደሆነ እና በማን አማካኝነት እንደተደረገ ጥያቄ ቢያቀርብም ለጥያቄው መልስ በጊዜው ማግኝት አልቻለም ነበር፡፡

 ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን በአጼ ዘርዓያቆብ ዘመን በቤተክርስቲያን ፍትህ ሲጓደል ድሃ ሲበደል አንድ ቀን ሙሉ በጨለማ የተዋጠ እንደነበር ታሪክ ይናገራል ፤ በዚያው ወቅት አጼ ዘርዓያቆብ የተበደለውን እና የተጓደለውን ፍትህ በማስካከል ያልሆነ ፍርድ ያስተላለፉት ላይ በቅን ልቦና እና በፈሪሃ እግዚአብሔር በፈረዱበት ቀን በቤተክርስቲያኑ በቀሳውስት መግቢያ በር በኩል ብርሃን ከሰማይ ወርዶ ነበር ፤ በአሁኑ በእኛ ዘመን የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በዓላትን ሲሽሩ ፤ስርዓትን ሲያፋልሱ መብረቅ ከሰማይ በመውረድ እድሜ ጠገብ ጽዶችን ለሁለት ሲሰነጥቅ ተመልተናል፡፡

ይህን የመሰለ ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን እጅጉን ያፈነገጠ ተግባራቸውን ቆሞ መመልከት ያልቻለው የደብረ ብርሃን አካባቢ ምዕመን ፤ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና በቤተክርስቲያኑ የሚያገለግሉ ካህናት በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብ የአስተዳዳሪነት ቦታውን ከያዙ ጀምሮ የሆነውንና የተደረገውን የደረሰውን በደል እና ኢ-ፍትሃዊ አካሄድ በቀጥታ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በግልባጭ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ይህን ደብዳቤ በመጻፍ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ጥቅምት 14 2006 ዓ.ም ጠይቀዋል፡፡(ዋናው ደብዳቤ ከጽሁፉ በታች አስቀምጠነዋል፡፡)


ቀን ፡- 14/02/2006 ዓ.ም

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ለ፡- ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም የሰ/ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሲኖዶስ አባል
ደብረ ብርሃን

ጉዳዩ፡-  የተሃድሶ እንቅስቃሴን ፈጥነው እንዲያስወግዱ ስለመጠየቅ

.......

ብጹእ አባታችን የተሀድሶ እምነት አራማጆች ስርጭት በአራቱም ማዕዘናት መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ ይህም ማለት በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ በኮታ ሲስተም በዘንዘሪጥነት እስከ ቤተመቅደስ አስተዳዳሪነት ቦታውን ይዘው የመርዝ ምላሳቸውን አሹለው መርዝ ሲያነበንቡና ሲረጩ ይገኛሉ፡፡ እኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ማንነታቸውንና እነማንስ አንደሆኑ እያወቅን በውስጣቸው ሆነው እምነታችንን ለመበረዝ ብሎም ለማጥፋት ሲሯሯጡ በአድር ባይነት አልያም በግዴለሽነት ወይም በመጠጋት ዝም ብለን የምናልፈው ሊሆን አይችልም፡፡

ማንም ሰው የራሱን እምነት የመምረጥና የመከተል ነጻነት ሕገ-መንግስታችን መብት የሰጠ እና የዚህ ጽሁፍም አዘጋጆች የምንቀበለውና የምናከብረው እንዲሁም ለተግባራዊነቱ የምንቆም ሲሆን ነገር ግን በውስጣችን እየተሸሎከሎኩ በቤተ ክርስቲያናችን ሀብት እና ንብረት  ስጋ ሕይወታቸውን በማንደላቀቅ እየመሩ እምነታችንን እና ቅርሶቻችንን ሲነጥቁን ሲመዘብሩን ስርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲጋፉ በትዕግስት አይን ማየት የሚቻል አይሆንም ፡፡ እነኚህ ሰዎች ቤተክርስቲያናችንን ለቀው(ትተው) በቅጽ ግቢዋ መመላለሳቸውን አቁመው በራሳቸው መኖር ግድ ይላቸዋል፡፡

….
ብጹዕ አባታችን የአስተዳዳሪውን ማንነትና ምንነትን ለማወቅ የተፈለገበት ምክንያት ከአስተሳሰባቸው ፤ ከእምነታውና ከተግባራቸው (ከስከቶቻቸው ጭምር) ሲሆን ይህም በመሆኑ ለመከታተልና ጥናትም ለማድረግ ጊዜያት ተወስደዋል፡፡ በመሆኑም አስተዳዳሪው የተሐድሶ እምነት ተከታይ(አራማጅ) መሆናቸውን ተረጋግጧ፡፡ የተወሰኑ መገለጫዎች

  1.  መስከረም 13/2004ዓ.ም ፡- ተዓምረ ማርያም በመንበረ ብርሃን አንሳስ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እየተነበበ ሳለ ተአምሩ ተነቦ ሳያልቅ በማስቆም የሰንበት ተማሪዎች መዝሙር እንዲዘምሩ ትዕዛዝ በመስጠታቸው ሕዝቡ የቅድስት ድንግል ማርያምን ተአምር እንዳይሰማ አድርገውታል፡፡
  2.  ነሐሴ 7 2004 ዓ.ም ‹‹እመቤታችን እንኳን ዋጋ የላትም ፤ የማርያም ስም ሲጠራላችሁ ደስ ይላችኋል ፤ ኢየሱስን ስሰብክላችሁ ግን ቦታ አትሰጡትም ፤ ማርያም እኮ ከእግዲህ ዋጋ የላትም የኛ ጌታ ሁሉን ፈጽሞልናል›› ማለታቸው
  3.   ነሐሴ 29 2004 ዓ.ም ፡- ‹‹ኢየሱስ አምላካችን ነው ሁሉን ነገር ፈጽልናል ጾም ጸሎት አያሻንም›› ማለታቸው
  4. ታህሳስ 16 2005 ዓ.ም ‹‹ወደ መስሪያ ቤት ሲኬድ ከዘበኛ ጀምሮ እስከ ሃላፊ ድረስ ብዙ ችግር አለ ፤ ወደ ጌታ ዘንድ ለመድረስ አማላጅ አያስፈልግም ፤ የኛ ጌታ ሁሉንም ፈጽሟልና›› ማለታቸው፡፡
  5. ጳግሜ 3 2005 ዓ.ም እና መስከረም 7 2006 ዓ.ም ‹‹ንስሃ አባታችሁ ጸበል ለመርጨት ሲመጡ መርዝ እንዳይረጯችሁ ተጠንቀቁ›› ማለታቸው
  6.  ነሐሴ 12 2005 ዓ.ም አንዲት ሴት በእሳቸው ፍቅር ወድቃ ተገቢውን መልስ እንደሰጧት  በአውደ ምህረት ላይ ገልጸዋል፡፡ ይህ ለጾታዊ ትንኮሳ ወጣቱን ለማነሳሳት ይህን መሰሉን ነገር አውደ ምህረትን  ያህል ክቡር ቦታ ላይ በድፍረት ተናግረዋል፡፡
  7.    የተለያዩ አስተዳደራዊ በደሎችን ፈጽመዋል
  8. ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ የደመወዝ ጭማሪ ለራሳቸው በማድረግ ብር 5000 የወር ደመወዝ ተከፋይ ራሳቸውን በማድግ ፍትሃዊ ያልሆነ የደመወዝ ጭማሪ አድርገዋል፡፡
  9. ዘመናዊ አስተዳደር ስልትን እከተላለሁ የሚሉት አስተዳዳሪው በካህናቱ መካከል ግጭትና የእርስ በእርስ ጥላቻ እንዲሰፍን አድርገዋል….ለአብነት ያህል
    •         በ23/08/05 በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቅኔ ማህሌት
    •        21/10/05 ዓ.ም በመንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
    •        በ3/01/06 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ካህናቱን አጋጭተው አሰዳድበዋል
  10. 10.   ለባለሀብትና ለህጻናት የተለየ ጉባኤ በማዘጋጀት የኑፋቄ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
  11. በቤተክርስቲያን የተለመዱ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ፤ እንዲቀሩ እና እንዲደበዝዙ አድርገዋል  ስርዓተ ቤተክርስቲያንን አፋልሰዋል፡፡
  12. በጠበል ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተዓምረ ማርያም ፤ ተዓምረ ኢየሱስ ፤ ድርሳናትና ገድላት ይነበቡ ይሰሙ የነበሩ ቢሆንም አነኚህ አገልግሎቶች በአስተዳዳሪው ትዕዛዝ ተቋርጠዋል፡፡
  13. የደብረ ብርሃን ሕዝብ የሚከተለው የአዋጅ ሃይማኖት ነው፡፡(አጼ ዘርዓያዕቆብ ያወጀላችሁን ነው) ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
  14.  የግዝት በዓላትን በመሻር ሐምሌ 5 2005 ዓ.ም በቅድሥት ሥላሴ ቅጽረ ግቢ መብረቅ ወርዶ እድሜ ጠገብ ጽዶችን አቃጥሏል ሌሎች እጽዋትንም አውድሟል፡፡
  15. .    
  16. .    
  17. .    
  18. .    
  19. .    
  20.   ንጽህናቸው የተጓደለ ፤ ትዳራቸውን የፈቱ ፤ በሕብረተሰቡ ዘንድ የወረደ ስነ ምግባር ያላቸው ሰዎች የቅዳሴን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡ በአጠቃላይ በቤተክርስቲያናችን ተዘርዝረው የማያልቁ የእመነትና የአስተዳደር በደሎችን ፈጽመዋል፡፡


ብጹእ አባታችን ከላይ የተገለጸው ቤተክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉባት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በተለይ ከእምነትና ከቤተክርስቲያን ስርዓት ጋር ተያይዘው የሚገኙ ችግሮች ለአንድ አፍታ እንኳን ቸል የማይባሉ በመሆኑ መልአከ ብርሃናት ማርቆስ ብርሃኑ የችግሮቹ ዋና ተዋናይ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች የሚታዩ ስለሆነ በአስቸኳይ ከአስተዳዳሪነት ስራቸው እንዲነሱ እንዲደረግ እየጠየቅን መንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤ/ክ/ጽ/ቤቶች የጉዳዩን አሳሳቢነት ተመልክተው ጥያቄውን ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍና ውሳኔ እንዲሰጡ እናሳስባለን፡፡
ከካህናትና ከምዕመናን

ግልባጭ፡-
·        ለቅዱስ ፓትርያርክ ጽ/ቤት
·        ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት
አዲስ አበባ


















2 comments:

  1. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውNovember 2, 2013 at 7:27 PM

    ስእንደዚህ አይነት ጉዶች ስንሰማ ስስለቤተክርስትያናችንና ስለአገራችን ምን ያስረዳናል - ከዚህ በፊት TheAngryEthiopian/ቆሽቱ የበገነው እንደጠቀሰው "....ከዚህ በፊት እንዳልኩት ወያኔ የሚባለው የአውሬ ቡድን አገሪቱ ላይ ዕቃ ዕቃ መጫወት ከጀመረ ወዲህ፣ ገዢዎቻችን ጴንጤና እስላሞች ሆነዋል። ቤተክርስትያናችንን ደግሞ ከውስጥም ከውጭም ሆነው የገዛ መሪዎችዋም ይገዘግዝዋታል፣ ያቆረቁዝዋታል፤ ህዝቡንም በአቦ-ሰጥ ፈረስ እያስጋለቡ ጉልበቱ እንዲበክን ያደርጋሉ። በቤተክርስትያን ውስጥ የተለያዩ አሳሳች ትርኢቶች እንዲከናውን በመፍቀድ፤ ምዕመኑን በስነልቦናዊ ጨዋታ ያዋዥቁታል። በየትኛው የአንጎል ክፍል እያሰቡ እንደሆነ ለማወቅ በጣም ያዳግታል።..."
    ባለቤትነትና ኀላፊነት የሚሰማው የመሪ አካል ቢኖር ኖሮ እንደዚህ ዓይነት ዜናዎች አንሰማም ነበር። በቅርቡ ያዳመጥነው የቤተክርስትያን መሪዎች በመንጎቻቸው ላይ እና በቤተክርስትያኒቱ ላይ በሚደርሰው በድል ላይ ተቃውሞ የማሰማታቸው ዜና፤ እንደው የይስሙላና "እንደዚህ አድርገን ነበር" ለማለት ነው እንጂ ምንም ፋይዳ የሚያመጣ አይደለም። ምናልባት እጆቻቸው በተለያዩ ማነቆዎች ስለተበተቡ ነው ብለን ልናስብ እንችል ይሆናል። ያ ግን የእሩቡን ያህል ምክንያት እንኳን አይሆንም።
    በተረፈ ደብረብርሃን በውጭ ngo ለሚመሩት ተሐድሶ/ቤንጤ ቡድኖች ዋንኛ ኢላማ ነች። ታላቁና ገናናው ንጉሰ ነገስታችን
    ዓፄ ዘርዓያዕቆብ፤ እነሱ፣ ፈረንጆች፣ አይሁዶችና የዘንድሮ እስላም ታሪክ ፀሃፊዎች ደግሞ ሁሌ ሊያንቋሽሹት የሚፈልጉት ቆራጥ መሪ የከተመባት ከተማ ስለነበረች ነው።

    ReplyDelete
  2. የድንግል ማርያም ልጅ ! እባክህ ዘመኑን በምህረትህ በቸርነትሕ ዋጀው ። አሜን !

    ReplyDelete