Thursday, April 4, 2013

ደኅና ሁኝ ቤተክርስቲያን

ሠዓሊ አምሳሉ /ኪዳን አርጋው

(አንድ አድርገን መጋቢት 26 2005 ዓ.ም)፡- የእርቅ ድርድሩ የአባ ጳውሎስ ሞትና ከዚያም ፓትርያርክሹመት ውዝግብ ጉዳይ ተዳፍነው የኖሩ ብዙ ጉዳዮች ሸፍጦችና የጥፋት የክሕደት ሥራዎች ግልጽ እንዲታዩ እንዲወጡ አድርጓል፡፡ በዚህ ጣጣና ሽኩታ ውስጥ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነበሩባትን ያሉባትንና የተጋረጡባትን አደጋዎች ማየት ችለናል፡፡ ይህ የቤተክርስቲያን ችግር ድንገት አሁን የተፈጠረ ሳሆን ሥራዬ ተብሎ ዝግጅት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እየተሠራ የመጣ እንደሆነ አብዛኛው ሕዝበ ክርስቲያን የሚያውቅ አይመስልም ፡፡ ምንም እንኳ ወደ ኋላ ቢተወውም ደርግ በነበረው ፀረ ሃይማኖት አቋም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ቀላል የማይባል ጉዳትና ኪሳራ ደርሶባት አልፏል፡፡ ደርግን በተካው ሕወሃት መራሹ መንግሥት ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከድጡ ወደ ማጡ ለመስጠም ግዴታ ሆኖባት ይሄው በከባድ ችግር ታንቃ እየተንፈራገጠች ትገኛለች፡፡ ይህ ችግር ብዙዎቹ እንደሚመስላቸው የዘር የደጋፊ ወይም የወገንተኝነት ጉዳይ አይደለም፡፡

በእርግጥ የዚህ ችግር ፈጣሪዎች ጉዳዩ የዘር ወይም የወገኝተኝነት ጉዳይ ብቻ እንደሆነ መስሎ እንዲታይ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የዚህ ችግር ትክክለኛና የተደበቀው ገጽታ ግን በፍጹም ይህ አይደለም፡፡ ይሄ በነበረ ምንኛ በታደልን ነበር፡፡ ችግሩ የሚወደድና ቀላል ሆኖ ሳይሆን ከመጥፎውና ከከባዱ ጥፋትና አደጋ ቀላሉን ጥፍትና አደጋ ከመምረጥ አንጻር እና ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ምን አልባትም ከሰው ልጅ ታሪክ ጋር ዘመድ ሆኖ አብሮ የኖረ የሰው ልጅ መገለጫ ወይም ችግር ስለሆነ እንጅ፡፡ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  ምንም አንኳ በእናታቸው በኩል ጎጃሜ ቢሆኑም አባ ጳውሎስን አስቀድሞ አጭቶ ቆይቶ ከወገኖቹ መርጦ እንዲሾሙ ማድረጉ ከቤተክርስቲያኗ ሕግና ቀኖና ውጭ መሆኑ ከፋ እንጅ የራሱን ወገን ማሾሙ በራሱ ብቻውን ግን ይህ ሰው በመሆን ዘወትር የምንፈጽመው ጥፋትና ደካማ ጎናችን ነውና ምንም ባልነበር ሕወሃት መራሹ መንግሥት በፊት የነበረው ደርግም ምንም እንኳ ደርግ የአማራ መንግሥት ነው የሚባል ባይሆንም ኮሎኔል መንግሥቱ /ማርያምም እራሳቸው በአባታቸው ኦሮሞ ናቸውና ይሁንና ግን መንግሥታቸው የራሴ የሚላቸውን ሰው እንዲሾሙ አድርጓልና፡፡

ከዚያም በፊት በነገሥታቱም ዘመን ጳጳሳቱ የእኛ ወገን ባይሆኑም ማለትም ግብጻዊያን ቢሆኑም ነገሥታቱ እስከወደዷቸውና እነሱን እስከመሰሉ ጊዜ ድረስ እንጅ ተጻራሪ አቋም ይዘው በአንድም በሌላም ምክንያት እንዲሠሩ ዕድል የሰጡበት አጋጣሚ አልነበረምና አዲስ ችግር ባለመሆኑ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  ይህንን ማድረጉ ምንም አልነበረም ለየት ያለው ሕወሃት መራሹ መንግሥት የፈጠረው የሚከፋው ችግር ግን በዓይነቱ አዲስና እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ይህ ችግር ቀድሞ ከነበሩት ነገሥታት ዘንድ በዐፄ ሱስኒዮስ ጊዜ የተከሰተና ቀላል የማይባል መሥዋዕትነት ቢያስከፍልም ችግሩ ወይም ስሕተቱ ወዲያውኑ ታርሟል፡፡ ይህ ችግር ምንድን ነው ይህ ችግር ነገሥታቱና መሪዎቹ በመሰላቸውና ባመኑበት ግላዊ አቋምና አቅጣጫ ቤተክርስቲያንን ያለ ሕግጋቷ፣ዶግማዋና ቀኖናዋ ባጠቃላይ አስተምህሮዋ አቅጣጫዋን ለማሳት የማስገደድ ሙከራዎች ናቸው፡፡ ዐፄ ሱስኒዮስ በፖርቹጋሎች አሳሳችነት ይሄንን ለማድረግ ሲሞክሩ ከባድ መሥዋዕትነት በጠየቀ የሕዝቡ ዐመፅ እንዲከሽፍ ተደርጓል፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም ያልነበረ ሥር ነቀል መንግሥታዊ ሥርዓት በመደንገጋቸው ካህናትን ቢያስቆጣም እሳቸው እራሳቸው የቤተክህነትን ትምህርት የተማሩና በዲቁናም ያገለገሉ ስለነበሩ የካህናቱን አግባብ ያልሆነ ጥቅምና በጉልበታቸውም አምራች እንዲሆኑ አስገደዱ እንጅ የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ ሕግና ሥርዓት በፍጹም አልነኩም ወይም ላለመጋፋት ወይም ላለመድፈር በጣም ጥንቃቄ አድርገው ነበር፡፡
ወደ ደርግ አገዛዝ ስንመጣ ደግሞ በግብታዊነት ሳይገባው ፈጽሞ ጭፍንና የደነቆረ ባዕዳዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወይም ርዕዮተ ዓለም ይዞ አባሎቹን የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ እንዳይሆኑ እስከማድረግና እንደውም ሃይማኖትን እስከ ማጥፍት የደረሰ ዓላማ በማንገብ የገጠር አብያተክርስቲያናትን የገበሬ ማኅበር /ቤት የከተሞችን ደግሞ ሙዚየም (ቤተ መዘክር) የማድረግ ከባድ የጥፋት ዓላማ ነበረው ወደ ኋላ ግን የሚከተለው ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ከመላው ዓለም እየደከመና እየኮሰመነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ያንን የጥፋት ዓላማ ለማስፈጸም ይዞት የነበረውንም ቁርጠኝነትና ትጋት ለመተው ተገዷል፡፡ በዚህ ወቅት ነበር አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ የሆኑት በእርግጥ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚያም በፊት የደርግ ሰው የነበሩ ቢሆኑም ደርግ እንደነበረው ዓላማ ፓትርያርኩን በቤተክርስቲያን ላይ ጥፍት እንዲሠሩ ለማድረጉ ወይም ደግሞ እርሳቸው የደርግ ሰው ስለነበሩ የደርግን ዓለማ ለማስፈጸም ሲሉ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከዶግማ እስከ ቀኖና ፈጸሙ የተባለ አንድም ጥሰት መቆነጻጸል ወይም ክሕደት ሲጠቀስ ሰምተን አናውቅም ከዚህ ይልቅ እንዲያውም አቡነ መርቆሬዎስ ከፕትርክናቸው ገና በፊት ቤተክርስቲያንን ወይም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሲሉ ያደርጉት የነበረውን ለምሳሌ የክርስቲያኖች ቁጥር አናሳ በሆነበት በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል በግራኝ መሐመድና በተለያዩ ምክንያቶች የጠፉና የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትን እያስተባበሩ ሲያሠሩና ሲያስገነቡ ደርግንም ድጋፍ ይጠይቁና ያገኙም ነበር፡፡

ወደ ሕወሃት መራሹ  ‹‹መንግሥት›› ስንመጣ ግን ነገሩ የተለያየ ችግሩና ጉዳቱም ከባድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በርዕዮተ ዓለም ደረጃ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  የሚከተለው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ከደርግ የተለየ አይደለም፡፡ የምከተለው የመንግሥት አስተዳደር ዓላማዊ(secular) ነው ስለሚል አመራሮ ሃይማኖተኛ እንዲሆኑ አይፈቅድም፡፡ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  ይህ አሁን በቤተክርስቲያኗ ላይ እያደረገ ያለውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ የጀመረው ገና ከድሮው በረሀ እያለ ጀምሮ እንደነበረ የትግሉ አካልና አመራር የነበሩ ሰዎች በጻፏቸው መጻሕፍትና በቃለ መጠይቆች ይናገራሉ፡፡ ሕወሃት መራሹ መንግሥት   አባ ጳውሎስን ፓትርያርክ ሌሎች ታጋዮችንም ጳጳሳት ያደረገው 1984 .ምና ከዚያም በኋላ ሳይሆን ገና በረሀ እያለ ጀምሮ ነበር፡፡ እነኝህን ሰዎችንም ለዚህ ተልእኮ የበቁ ይሆኑ ዘንድ ለማደናገሪያ ወይም መስሎ ለመታየት የሚያስችላቸውን ትምህርት በየገዳማቱ በማስረግ እንዲያገኙ እንዳደረገ ይህን ሥራ ይሠሩ የነበሩ አመራሮች በጻፏቸው መጽሐፎቻቸው ገልጸዋል፡፡

እኔ እንኳ በሆነ አጋጣሚ ታሪካቸውን የማውቅላቸው ከእነኝህ ታጋዮች አንዱ በደርግ ጊዜ ለዓመታት በገነት ሆቴል ሆነው ሲሰልሉ የነበሩ ዛሬ ግን ጳጳስ የሆኑ ሰው አውቃለሁ፡፡ እነኝህ አመራሮች ከጻፏቸው መጻሕፍት እንደምንረዳው አባ ጳውሎስ ጳጳስ አድርገው ከሾሟቸው 40 በላይ ጳጳስት አብዛኞቹ ወያኔ በረሀ እያለ ለጵጵስና ያዘጋጃቸው ታጋዮች እንደነበሩ ታውቋል፡፡

እንደኔ እንደ እኔ አሁንም ቢሆን እነኝህ ግለሰቦች ለጵጵስናም ይሁን ለፕትርክና የሚያበቃውን መስፈርት የሚያሟሉና ለቅድስት ቤተክርስቲያን (ለእግዚአብሔር) ታማኝ አገልጋይ ቢሆኑ ኖሮ እንዲህ መደረጉ በራሱ ችግር ነው ብየ አላስብም፡፡ ምክንያቱም ሀገራችን ኢትዮጵያ ወይም ቤተክርስቲያን እንኳንና የገዛ ዜጎቿን ይቅርና የማናውቃቸውን ግብጻዊያን፣ ሶርያዊያንና ሮማዊያን ጳጳሳትንና አባቶችን ተቀብለን በእነርሱ መንፈሳዊ አገልግሎት ስናገኝ ኖረናልና፡፡ ሐዋርያዊ ተልእኮና አገልግሎት በዘርና በድንበር የሚገደብ ባለመሆኑ፡፡ ችግሩ የሚፈጠረው ግለሰቦቹ ታማኝነታቸው ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለድርጅታቸው ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለመንግሥታቸው፣ የቤተክርስቲያንን እንጀራ አይበሉ ግን የሚያገለግሉት እግዚአብሔርን ሳይሆን ድርጅታቸውን የሆነ እንደሆነ ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የሆነው ነገርም ይሄው ነው ሕወሃት መራሹ መንግሥት   ለኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ የሚሰጠው ዋጋ ምን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀውና ግልጽ ነው፡፡ ምንም እንኳ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሀገሪቱ ያሉ ብሔረሰቦች ሁሉ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ማንነት የየራሳቸው አስተዋጽኦ እንዳለበት የታወቀ ቢሆንም በሕወሃት መራሹ መንግሥት  ዕይታ ግን 3 ሺህ ዓመታትን ያስቆጠረው ከቀዳማዊ ምኒልክ የሚጀምረው ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥትና ከዚያም በፊት በነበረው እናቱ የመጨረሻዋ በሆነችበት 52 በላይ ነገሥታት የነበሩበት ሥርዎ መንግሥት በበላይነት የተያዘውና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ የአንድ ዘር ብቻ ማለትም የአማራ እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  ይህንን ጉዳይ ለወዳጆቹ የውጭ መንግሥታት አንጀት በሚበላ ገለጻ አጅቦ ጭምር በማቅረብ ዘለዓለም ዓለማችን ስንጨቆን የነበር ነን እያለ ሲያባብልበትና ፈር የለቀቀ ድጋፍ ሲያገኝበት ቆይቷል፡፡ ከዚህ የተነሣ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  ስናውቀው ጊዜ ጀምሮ ለታሪካችንና ቅርሶቻችን ካለው ጥላቻ የተነሣ በሚገርምና በሚደንቅ ሁኔታ ህልውናቸውን ጨርሶ በመካድ የኢትዮጵያን ታሪክ 100 ዓመታት ብቻ ገድቦት እንደነበር ይታወሳል የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል እንዲሉ ምንም እንኳ አሁን ወደ መጨረሻ ለኢትዮጵያ ታሪክ የነበረውን 100ዓመታት አስተሳሰቡን የቀየረውና ያስተካከለው ቢሆንም፡፡ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  በዚህ ጤነኛ ባልሆነ ከባድ ጥላቻ እንደተሞላና እንደሰከረ ነበር ሥልጣን የተቆናጠጠው፡፡ በዚህ ጥላቻው ብቻም ሳይሆን ለራሳቸው ዓላማ ለእሱ ድጋፍ ይሰጡ ከነበሩ ከሀገራችን ጠላቶች የተሰጠው ተልእኮም በአጋጣሚ ከፍላጎቱም ጋር በመጣጣሙ ጭምር ነው ፡፡ እናም ሥልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ወደ ፊት ሊሠራው አስቦት የነበረው ሥራ ሁሉ በዚህ በሽተኛ አስተሳሰብ ማዕቀፍና መሠረትነት የተሰላና የተቀመረ ነበር፡፡ በመሆኑም ይህንን ከባድ ጥላቻ ያለበትን ታሪክና ቅርስ ስልታዊ መሆነ መንገድ ለማጥፍት ሲያስብ የዚህ ሁሉ ታሪክና ቅርስ ማኅደር የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዕይታው ውስጥ ጥልቅ አለች፡፡

ስለዚህ ይህንን የተወሳሰበ የጥፋት ሥራ በተሳካ መልኩ ለመሥራት ገና ከበረሀ ጀምሮ በአማካሪዎቹና ደጋፊዎቹ ጠላት ሀገራት እየታገዘ ዝግጅቱን ያጧጡፈው ያዘ፡፡ ሕወሃት መራሹ መንግሥት  የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን የሚያያት የአንድ ዘር ጠበቃና የህልውና መዋቅር አድርጎ ነው የሕወሃት መራሹ መንግሥት   ባለሥልጣናት ይህንን እኩይ አስተሳሰብ የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ንግግሮችን በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከፊደል እስከ ዜማ ከመድኃኒት ቅመማ እስከ ፍልስፍና ከዘመን አቆጣጠር ቀመር እስከ ሥነፈለክ ከአርበኝነት ነጻነታችን ተጠብቆ እንዲኖር እስከ ሀገር ፍቅር እነዚህን ሁሉና ሌሎችንም ከሀገራችንም አልፋ ለመላው ዓለም ያበረከተቻቸውን የማይተካ አስተዋጽኦ ሆን ተብሎ ለማየት ባለመፈለግ ልክ ለሀገር ተቆርቋሪ እንደሆኑና እንደሚያስቡ ሁሉ ሊሠራ የማይወድ አይብላ እያለች የፈጣሪን ቃል የምታስተጋባ ቤተክርስቲያንን በዓላትን በመጥቀስ ለዚህች ሀገር ድህነት ተጠያቂ ነች ሲሉ በአደባባይ ተደምጠዋል፡፡ የነፍጠኛ ሃይማኖት እያሰኙም ሲያዘልፏትና ሐዋርያዊ ተልእኮዋንም ሲያደናቅፉ ቆይተዋል፡፡ ለሕወሃት መራሹ መንግሥት  ባለሥልጣናት ሥራ ማለት ቁፋሮ፣ጉልጓሎ፣አጨዳ፣ፈለጣ የመሳሰሉት ነገሮች ናቸው፡፡ እንደ ኢትጵያ ቤተክርስቲያን አስተምህሮና አስተሳሰብ ግን ሥራ ማለት ቁፋሮ ጉልጓሎ ቆረጣና የመሳሰሉት ብቻ አይደሉም፡፡ በታም ውስን ቀናትን በዓል ብላ ከጉልበት ሥራዎች ነጻ እንዲሆኑ ብታደርግም በእነዚህ ቀናት ግን እንዲሠሩ የምታዛቸው ሥራዎች ደግሞ አሉ፡፡ ለምሳሌ የታመመ መጠየቅ፣የተጣላ ማስታረቅ፣ የታሠረ መጎብኘት፣ለአረጋያንና ለሕፃናት ባጠቃላይለቤተሰብ ጉዳይ ጊዜ መስጠት የመሳሰሉት ማኅበራዊ ክንውኖች ሁሉ በትዕዛዝ ጭምር እንዲሠሩ እንዲደረጉ ትመክራለች ታስተምራለች፡፡ ቤተክርስቲያን ይህንን ሥርዓት ለምን እንደደነገገች ባለ አእምሮ የሆነ ሰው ሁሉ በሚገባ ይረዳዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ነው በዚህ አስከፊ ድህነት ውስጥ ሆነንም እንኳ ጠንካራ የሆነ የማኅበራዊ ሕይዎት ትስስር ሊኖረን የቻለው ብዙ ጊዜ ምዕራባዊያኑ በዚህ የድህነት ዓይነት ውስጥ ሆነንም እንኳ እንዲህ ዓይነት ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስር ይዘን ሲያዩ የማይታመንና ተአምር ሆኖባቸው ሲገረሙ ይስተዋላሉ፡፡ እነሱ ይህንን እሴት በሥነ ልቡና ሊቃውንት(psychologists) እና በኅብረተሰብ መጣቅ (sociology) ባለሙያዎቻቸው ምክርና ትምህርት ሊያመጡት አልቻሉምና፡፡

የፈለገ ቢሆን ከዓመት 365ቱንም ቀናት ከወር 30ውንም ቀናት ከሳምን 7 ቱንም ቀናት በከባባድ የጉልበትና ተመሳሳይ ሥራዎች ላይ ማሳለፍ የሚችል ሰው ጨርሶ አይኖርም፡፡ ይህም ስለሆነ ነው ሁሉም ሀገራት በሳምንት ውስጥ 1-3 የሚሆኑ ቀናትን የዕረፍት ቀናት አድርገው የደነገጉት፡፡ ሕይወት ሥራ ብለን በምናስበው ነገር ብቻ አትቆምም ሰው እንደመሆናችንም ልንሠራቸው የሚገቡ ነገሮች ደግሞ ብዙ አሉ፡፡ ሀገራችንን ያደኸያት ይህ ሳይሆን ቀጠሮ እንዳለው የራሱን ጊዜ እየጠበቀ ከውጭና ከውስጥ በሚፈጠር ቀውስ የሚከሰተው ጦርነት ብቻ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ በረጅሙ ታሪኳ ከአንዱ ጦርነት ወደ ሌላው ጦርነት አንድትገባ ስትገደድ በአማካኝ 10 ዓመታት የበለጠ የሰላም ጊዜ ኖሩት አያውቅም፡፡ እንግዲህ ልብ በሉ እንኳንና ይሄ ሁሉ ጦርነት አንድ ጦርነት ብቻ እንኳ የአንዲትን ሀገር የሰው ኃይሏን ጨምሮ የሚበላው ሀብትና ጥሪት ከሥልጣኔዋ እስከ ቅርሷ የሚያደርሰውን ውድመት ልብ ላለ ሰው ሀገራችን ኢትዮጵያ ይሄንንም ያህል እንኳ በመኖሯ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው ብሎ ፈጣሪን ካላመሰገነ እራሱን ለትዝብት ይዳርጋል፡፡
ሀገራችንና ሕዝባችን ባለፉበት የፈተናና የመከራ ሕይወት ሌላ ማንም ሀገርና ሕዝብ ቢያልፍ ገና ከድሮው ድምጥማጡ ጠፍቷል፡፡ ሀገራችን ካለችበት ስትራቴጅካል (ስልታዊ) አቀማመጥ ወይም ሥፍራ፣ በረጅሙ ታሪካዊ ዳራችን ተከትሎን የመጣው ጣጣ፣ለብዙ አፍሪካ ሀገሮች ነጻነት የተጫወትነው ሚና በቅኝ ገዥዎች ያስከተለብን የበቀል እርምጃ በመሳሰሉት ምክንያቶች በዚህ መከራ ማለፍ ግዴታ ሆኖብናል፡፡

ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና ሕወሃት መራሹ መንግሥት  የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን የአንድ ብሔረሰብ ጠበቃና ውላጅ ናት የሚለው አስተሳሰቡ ቤተክርስቲያንን ለሰይጣናዊ ጥቃቱ አጋልጧታል፡፡ አባ ጳውሎስና መሰሎቻቸው በዚህ 20 ዓመታት ሥውርና በግልጽም የሚታዩ የጥፋት ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ ከዶግማ ዶክትሪኗ እስከ ቀኖናዋ የሊቃውንትና የሕዝበ ክርስቲያኑ ምላሽ እየታየ ለመሸራረፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ ለዚህ ትሩፋታቸው የበለጠም እንዲያጠፉ ለማትጋት ከአፅራረ ቤተክርስቲያን ሞገስን አሰጥቷቸው ከቤተክርስቲያናችን ፍላጎትና ከቃሉ ትዕዛዝ ውጭ የዓለም አብያተክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዘዳንትነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ አንዳንድ የኔ ቢጤ የዋህ አባ ጳውሎስ የነገረ ሃይማኖት ምሁር ሆነው በዓለም ካሉ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ዐዋቂዎች(theologian) የላቀ ወይም ተመራጭ ዕውቀትና ብቃት ኖሯቸው ያንን ቦታ የያዙት የሚመስለው አይጠፋም፡፡ ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ ብቻ ሳይሆን ብዙ የማይተኩ ብርቅና ድንቅ ቅርሶቿም በረቀቀ ዘዴ እንዲሰወሩ ወይም የገቡበት ሳይታወቅ እንዲጠፍ ተደርጓል መጻሕፍቶቿም ተቆነጻጽለው እንዲታተሙ ተደርጓል ወዘተ፡፡ በተለይ በተለይ ደግሞ ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ 6 አእላፋት(ሚሊዮን) ልጆቿን እንድታጣ ተደርጓል ይህ ቁጥር ከብዙ የአውሮፓ ሀገራት ሕዝብ ቁጥር የላቀ ቁጥር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ሕዝብና ቤት ቆጠራ /ቤት ኦፊሴላዊ ይፋዊ መረጃ መሠረት 1989 . በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ላይ 53 ሚሊዮኑ (አእላፋቱ) የኢትዮጵያ ሕዝብ 27 ሚሊዮኑ ወይም 50.6% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ ነበር፡፡ 1999 . በተደረገው ቆጠራ ግን 73 አእላፋቱ (ሚሊየኑ) የኢትዮጵያ ሕዝብ 38 ሚሊዮን መሆን ሲኖርበት 32 ሚሊየኑ (አእላፍቱ)ማለትም 50.6% ወደ 43% ወርዶ 7.6% ልጆቿን ማለትም 6 ሚሊየን ምእመናን እንዲበሉባት ተደርጓል፡፡ ልብ በሉ ይህ የሆነው 1989 – 1999 . ባለው 10ዓመታት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በፊት የነበረውንና 1999.. በኋላ እስከ አሁን ያለውን ብናስብ ደግሞ ምን ያህል መንጋ እንደተበላባት መገመት ይቻላል፡፡ ይህንን ኪሳራ ያደረሱት የበግ ለምድ ለብሰው የገቡ ተኩሎች ወይም መናፍቃን እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ እነኝህ ግለሰቦችና ቡድኖች ሳይታወቁ ቀርተው አልነበረም ነገር ግን ከቤተክርስቲያኗ የበላይ አካላት ከፓትርያርኩ /ቤት ድጋፍ ስለሚደረግላቸው እንጅ፡፡ አምና ‹‹ሲኖዶስ›› በእነኝህ ተኩላት ግለሰቦችና ቡድኖች ጉዳይ ሲነጋገሩና ሰዎቹም ሲመረመሩ የእንቅስቃሴው ሥር አባ ጳውሎስ ሆነው በመገኘታቸው የሲኖዶስ አባላት አባ ጶውሎስን ሃይማኖትዎ ምንድን ነው? ብለው እንደጠየቁና በማግስቱ በሚቀጥለው የሲኖዶስ ስብሰባ ይህንን እንዲመልሱ ተቀጥሮ እንደነበርና በማግስቱ ሳይገኙ እንደቀሩ የሚታወቅ ጉዳይና የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

አባ ጳውሎስ ለወያኔ ይሄንን እመርታ አስመዝግበው አልፈዋል፡፡ ‹‹ፓትርያርክ›› ተብየ ሲመጣም አይበለውና
ሌላ ቀጣይ 10–15 ዓመታት ቢሠራና ቆጠራ ቢደረግ የቤተክርስቲያኗ አባላት ወይም ክርስቲያኖች በመላው ሀገሪቱ ሲቆጠሩ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ያነሰ ወይም ቤተክርስቲያኗ አለች ተብሎ ለመናገር የማያስደፍር ይሆናል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የሚጠፋው መንጋ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር አባላቷ ባዶ ላይ ለመድረስ የሚጠይቀው ጊዜ ዝጅግ እየተፋጠነ ይሄዳልና፡፡ ይህች ከሕገ ልቦና ጀምራ በየኪዳናቱ ስሟ እየተቀያየረ ለዚህች ሀገርና ለዚህ ሕዝብ ህልውናና ልዕልና ውድ ልጆቿን እየገበረች እየደማች እየቆሰለች ያልከፈለችው የመሥዋዕትነት ዓይነት ሳይኖር ለሽዎች ዓመታት የቆየችው ቤተክርስቲያን በጣት ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ ነበረች ተብሎ ሊነገርባት ነው፡፡ ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ሃይማኖት ሲባል በአብርሃም ፣በሙሴ ወይም ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ዘመን የተጀመረ ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት የነበረው ከአዳም ጀምሮ ነው፡፡ ሃይማኖት ማለት ‹‹ማንነቱን በትክክል በተረዳ መልኩ እግዚአብሔር የሚባል አምላክ መኖሩን ዐውቆና አምኖ ማምለክ ለእርሱ መገዛት›› ማለት ነው፡፡

ይሁዲነት ወይም ክርስትና ሃይማኖቶች አይደሉም ከአዳም ጀምሮ በነበረችው በአንዲቷ ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ኪዳናት ናቸው እንጅ፡፡ ለዚህም ነው የአግዚአብሔር ቃል በኤፌ. 4÷5 ላይ አንድ ሃይማኖት ብቻ መኖሩን የሚናገረው እናም ይህች ቤተክርስቲያን ከአዳም ወደ ሕገ ልቡና ማለትም የተጻፈ ሕግ ሳይኖር በውርርስ ከዛ ወደ ኦሪት አሁን ደግሞ በመጨረሻ ወደ ክርስትና ስሟ እየተቀያየረ ህልውናዋ ሳይቋረጥ በኢትዮጵያ ሰዎች ዘንድ ቆይታ ነበር፡፡ ይህንን መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር መረዳት ይቻላል፡፡
እናም ይሄንን ያህል ታሪክና መሠረት ያላት ቤተክርስቲያን አጋንንት ግብዓት መሬቷን ፈጽመው ሊፋንኑ ጥቂት ዓመታት ብቻ ተቀጥሮላታል ቢባል ማን ያምናል? ለአንድ ኢትዮጵያዊስ ከዚህ የከበደና የከፋ አስደንጋጭ መርዶ ሊኖር ይችላልን?

ለሚሰማኝ ሁሉ ልናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር የሕወሃት መራሹ መንግሥት  (የጎግ ወማጎግ) ደጋፊ ወይም አባል ሆኖ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ሰው ካለ ለነገሩ ይኖራል ብየ አልገምትም ሁሉም እውነቱን ልቡናው ያውቀዋል ነገር ግን ሕወሃት መራሹ መንግሥት  ለዚህ እንዲረዳው በፈጠረው የኑሮ ውድነትና ሌሎች ነገሮች ታንቆ ስለተያዘ እንጅ ወያኔ የሱ ደጋፊ ካልሆኑ በስተቀር መኖር እንዳይቻል ስላደረገ አይ ካለ ከሥራው ይፈናቀላል፣ቤቱ ይፈርሳል ፣ገንዘቡ ይወረሳል ምክንያት ተፈልጎለት ወይም ተፈጥሮለት ወደ እስር ቤት ይወረወራል፣የመማር ዕድልእንዳያገኝ ይደረጋል፣ በግሉም እንኳን ቢሆን ሠርቶ መኖር እንዳይችል ይደረጋል በእነዚህ ምክንያቶች ግድ ሆዱን ብቻ እንዲያስብ ኅሊናውን ከጭንቅላቱ አውጥቶ እንዲጥል አድርገውታል፡፡፡ አስቀድሞም የእግዚአብሔር ቃል ‹‹የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል›› ተብሎ ተጽፏልና ራዕ 13÷17፡፡ ነገር ግን ምናልባት አንዳንድ የዋሀን አይጠፉምና የሕወሃት መራሹ መንግሥት   ደጋፊ አቀንቃኝ ወይም አባል ሆናቹህ እግዚአብሔርን የምታመልኩ የሚመስላቹህ ወይም ማምለክ የምትችሉ የሚመስላቹህ ካላቹህ እራሳቹህን እያታለላቹህ እየሸነገላቹህ ፈጣሪን ለማታለል እየሞከራቹህ እንደሆነ ላረጋግጥላቹህ እወዳለሁ፡፡ የሕወሃት መራሹ መንግሥት   ደጋፊ ወይም አቀንቃኝ ስትሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቹህ ግንኙነት ያኔውኑ ተቋርጧል፡፡ ምክንያቱም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በቅድስት ቤተክርስቲያን (በእግዚአብሔር) ላይ ለሚሠራው ጥፋትና ውድመት ወይም ጠላትነት አባሪ ተባባሪ ሆናቹሀልና፡፡ በመሆኑም ሕወሃት መራሹ መንግሥት  አባል ሆኖ ክርስቲያን መሆን አይቻልም ‹‹ምን እናርግ›› ብሎ ክርስትና የለም አባት አናቶቻችን ‹‹ምን እናድርግ›› ብለው እጅና እግራቸውን አጣምረው በመቀመጥና የአላዊያን ነገሥታትንና የመናፍቃን ጳጳሳትን ግፍና ጥፋት በዝምታ በመመልከት አይደለም ቤተክርስቲያንን ከእኛ አድርሰዋት የነበረው ማቄን ጨርቄን ሳይሉ አስፈላጊውን መሥዋዕትነት በመክፈል እንጅ፡፡

ክርስቶስ ከእኔ ይልቅ ሌላ ምንም ነገርን የሚወድ ለኔ ሊሆን አይገባም ብሏልና፡፡ ልጆቸን፣ወላጆቸን ፣ኑሮዬን በሚል ‹‹ምን ላድርግ›› የሚል ምክንያት ከክርስቶስ ፊት አይሠራም፡፡ ነገር ግን በጽናት በስሙ መከራ መቀበል ብቻ ነው የክርስቶስ የሚያሰኘው በፊቱም ሞገስን የሚያሰጠው፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ተገዶ ለወያኔ ያደረ ሰው ከደሙ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ቢያንስ ቢያንስ ዕለት ዕለት ስለዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያንና ስለዚህች ቅድስት ሀገር በእግዚአብሔር ፊት ተግቶ ማዘን ፈጣሪን መማፀን ይኖርበታል፡፡ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?
 
የጸሃፊው አድራሻ፡ ሠዓሊ አምሳሉ /ኪዳን አርጋው

7 comments:

  1. የወፍ በረር ቅኝት ለሚባለው የጽሑፍ ዘየ ጥሩ ምሳሌ ነው:: ከምንም በላይ ግን እሪ በከንቱ የሆነ መፍትሄ አልባ ድካም ሆኗል:: ምንም አዲስ ነገር የለውም ወሬ ሲጻፍ ነው:: ለለውጥ የሚያግዝ መፍትሄ ቀርቶ ችግሩን ማሳየት ያልቻለ አድርባይ ብእር ነው ያልዎ ውድ ጸሐፊ:: ያልነኩት የለም የነገሩንም የለም:: ከቻሉ በድጋሚ ጽፈው ችግሩን በቀጥታ አመልክተው መፍትሄ ነው ያሉትን ይንገሩን:: ካልሆነ ግን ከልቤ ልነግሮ የምፈልገው ጥላቻ መዝራት ይሆንብዎታል::

    ReplyDelete
  2. ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ

    ReplyDelete
  3. ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን ቃለህይወት ያሰማልን። ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  4. ፖለቲከኞች እባካችሁ ከቤ/ክ እጃችሁ አንሱ ስንቃወምም ህዝብ የሚያዉቀዉን እዉነት እየተናገርን እንቃወም የአቡነ ጳዉሎስ ምንኩስና ታሪክ በትክክል ያዉቃሉ መጨረሻቸዉ ጥሩ አልነበረም ማለት መልካም ከገዳም ፎርጅድ አስርተዋል ማለት በማያዉቁት ነገር መቦጫረቅ ነዉ ሚሆንቦት እንትና እንትን ብሎ የሚል ቁምነገር የሌለዉ ሃላፊነት የጎደለዉ አንዱን አንዱን እንዲጠላ የሚታገል የጥላቻ ጽሁፍ እግዚያብሄር ልብ ይስጣችሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሰላም ጤናይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
      መድኃኔዓለም ይመስገን።

      ወንድሜ ሆይ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን የፖለቲካ ጽሁፍ አላቀረበም። ያቀረበው በሙሉ ስለኃይማኖቱና ስለ ክርስቶስ ነው። የፖለቲካ አኪያሄድ ያየሁት እርስዎ ላይ ነው። አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች በሃይማኖታችን ታሪካዊ ጠላቶች እየተደገፉ ኃይማኖታችን እያጠፏት እንደሆነ አያውቁም እንዴ? ኃይማኖታችን ትጥፋ ዝም በሉ ነው የሚሉት?

      ኃይለሚካኤል።

      Delete
  5. ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
    ይኸው ዛሬ አገር አፍቃሪው የአማራ ሕዝብ በሀገሩ ወደ ሀገሩ እየተሰደደ ነው በራሱ ወገን ላይ በሀዘን ተጠመደ። እንግዲህ ምን አይነት እናት ትሆን (ትግሬ: አማራ: ኦሮሞ: ጉራጌ ) ምኒልክን እንደገና የምትወልደው።

    ReplyDelete
  6. ante lerasehe kalehbet tige weta

    ReplyDelete