Thursday, April 18, 2013

በሕግ አምላክ 5 ሳይባል 6 አይባልም!!


  ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
 amsalugkidan@gmail.com        
ይህ ጽሑፍ በዕንቁ መጽሔት የወጣው በጥር ወር መጨረሻ ነበር ፡፡ ከዚህ ጽሑፍ ቀደም ሲል የወጣውን የጸሐፊውን ጽሑፍ ‹‹ጉባኤ ኬልቄዶን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደ መልካም አርዓያ ሊወሰድ ይገባልን ?›› በሚል ርእስ የጻፈውን ጽሑፍ በእኛ ብሎግ መለጠፋችንና አንባብያንም በርካታ ጥያቄዎችን ማንሣታቸው ይታወሳል ይሄኛው ጽሑፍ ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሚሰጥ ስለሆነ ከወጣ የቆየ ቢሆንም የተለያዩ ሃሳቦችን ከማንሸራሸር  ፤ የተለያዩ የሰዎችን እይታ ከማስተላለፍ አኳያ ይረዳል ብለን ስላሰብን እነሆ ለጥፈነዋል መልካም ንባብ፡፡ (ይህ የአንድ ሰው ሃሳብ ነው)

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 10 2005 ዓ.ም)፡- የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል እንዲሉ የ4ኪሎዎቹ ግራ ክንፍ አባቶች ቡድን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበረ ፕትርክናቸው እንደማይመልሱ ይፋ አደረጉ፡፡ ምክንያቱም አሉና ከ20 ዓመታት በፊት በሕመም ምክንያት ሥራውን መሥራት አልችልም በሚል ደብዳቤ አስገብተው ትተውት ስለሄዱ በቦታቸው ሌላ ፓትርያርክ ተክተን ቆይተናል አሁን ለ20 ዓመታት ምንም እንዳልተሠራ ቆጥረን ወደኋላ መመለስ አንችልም ፡፡ በማለት የሚያውቁትን እውነት ሳይሆን የሚኖሩትን እብለት በይፋ ተናገሩ ፡፡ ለዚህ ለዚህማ ድርድሩና እርቁስ ለምን አስፈለገ? ፡፡ሰዎቹ በመግለጫቸው ብፁዕነታቸው ልሂድ ሲሉ አሉ «ቅዱስ አባታችን ለማን ትተውን ይሄዳሉ? ማንስ ይሰበስበናል?» ብለን ለምነናቸው ነበር፡፡ ከሄዱም በኋላ ለ10 ወራት ያህል ጠብቀን ሕመማቸውም ተሽሏቸው ከሆነ እንዲመለሱልን ጠይቀናቸው ነበር ብለዋል፡፡ ታዲያ መሄዳቸው ይህንን ያህል ያስጨነቃቸው ያስከፋቸውም ከሆነና እንዳሉትም መመለሳቸውን  የሚፈልጉና የሚናፍቁ ከሆነ ምነዋ ታዲያ አሁን ልመለስ ሲሉ ምን ሲደረግ ዘራፍ ማለታቸው? በቀል መሆኑ ነው ወይስ ውሸት?፡፡ እውነቱን ግን ማለትም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ማን እንዴት አድርጎ እንዲሰደዱ እንዳደረጋቸው አይደለም እነሱ ሕዝበ ክርስቲያኑም በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሚገባ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ይህንንም እያወቁ ለአፍታ እንኳን እግዚአብሔርን ባለማሰብ ፤ ባለመፍራትና ባለማፈር ማበላቸው ለገዛ ራሳቸው ያላቸውንና የሚሰጡትን ዝቅተኛና እርካሽ ዋጋ ሊያሳይ ቢችል እንጂ ሌላ የሚፈጥርላቸው እርባና እንደሌለ ኅሊናቸው ያውቀዋል፡፡
እንበልና ያሉት እንኳ ልክ ቢሆን ማለትም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በሕመም ምክንያት ሥራዬን መሥራት አልችልም ቢሉ ኖሮም እንኳ እርሳቸው ስለታመሙ ሥራው ግን መሠራት ይኖርበታልና ፕትርክናቸው ሳይነካ ምክንያቱም በሕይወት እያሉ ሊነካ አይችልምና እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን ሥራውን የሚሠራ ምስለኔ ወይም እንደራሴ ተሠይሞ ሥራው እንዲሠራ ይደረጋል እንጂ የትኛው ሕገቤተክርስቲያን ነው ፓትርያርክ ከታመመ ፣ ካረጀ ፣ ከተሰደደ ፣ ሥራውን መሥራት ካልቻለ ወዘተ በቦታው በመንበሩ ሌላ ፓትርያርክ ይሾማል የሚለው?፡፡ አሁንም የ4 ኪሎዎቹ የግራ ክንፍ ቡድን አባቶች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ፣ ምእመናንን የሚያከብሩ ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያፈቅሩ ፣ እውነትን የሚናገሩ ፣ ስለ ሃይማኖት የሚኖሩ ከሆነ ይህንን ጥያቄ በትክክል ያስኬደናል የሚሉትን ሕገ ቤተክርስቲያን በመጥቀስ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በይፋ ሊመልሱልን ይገባል፡፡ እንዲሁ ዝም ተብሎ ቀኖና ቤተክርስቲያን የምትል ቃል በመጥቀስ በሌለ ቀኖና  ተሸሽጎ ወይም አምታቶ ማምለጥ አይቻልም፡፡ ስለተሰቀለው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ብላችሁ መልሱልን ፡፡ይህንን ጥያቄ ሳትመልሱ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሕጋዊነት የለውም ክሕደት ነው ፤ እብለት ነው እግዚአብሔርን እንዳልሰማችሁት ረግጣችሁ እንዳለፋችሁት ቁጠሩት፡፡ ምክንያቱም እሱ በየዕለቱ ሊደረግ ሊፈጸም የሚገባውን ነገር ሁሉ በቤተክርስቲያኗ የሕግ የሥርዓት የቀኖና መጻሕፍት እየተናገራቹህ እየገሠጻቹህ እየመሰከረባቹህ ነውና ፡፡
እውነት እንነጋገር ከተባለ እንደ ቤተክርስቲያኗ ሕግና ሥርዓት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ ነበራትን ? 5 ሳይባልስ 6 ሊባል ይቻላልን ? ቢባል ካላበልን ካልቀጠፍን ካልተዳፈርን በስተቀር እውነቱን ከተናገርን በርግጠኝነት 5ኛ ፓትርያርክ እንዳልነበራትና 6ኛም ብሎ መሾም እንደማይቻል እንናገራለን እንመሰክራለን፡፡ አባ ጳውሎስ እንደሚታሙት ሁሉ ፓትርያርክ ለመሆን የሚያበቃቸውን መስፈርት ጨርሶ አያሟሉም የሚለውን እንኳ ለፈጣሪ ትተን አባ ጳውሎስ 5ኛ ፓትርያርክ እንዳልነበሩ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያኗ ሕግ (እግዚአብሔር) ቁልጭ አድርጎ በማያሻማ መልኩ መልሶታልና፡፡እዛው ላይ በግልጽ ከተቀመጡት ምክንያቶች በስተቀር ፓትርያርክ ሳይሞት በሕይወት እያለ በምንም ተአምር ፓትርያርክ ሊሾም እንደማይቻል ተናግሯልና፡፡በመሆኑም ከዚህ ሕግ ውጪ በሆነ መንገድ የሆነ ቡድን ሾምን ቢሉ ያ ሹመት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም ድርጊቱም አመፃ ነው ያስኮንናል፡፡ በመሆኑም በግልጽ አማርኛ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ አልነበራትም 6ኛም አይኖራትም ማለት ነው ፡፡ እስካሁንም ድረስ እንደ ቤተክርስቲያኗ ሕግና ሥርዓት ቤተክርስቲያን የምታውቀውና እየተገለገለችም ያለችው በ4ኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ነው፡፡ 5ኛ 6ኛ 7ኛ እያለ ሊቀጥል የሚችለው ልዑል እግዚአብሔር ብፁዕነታቸውን በሞት ከወሰደ በኋላ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ታዲያ እውነቱ እንዲህ ከሆነ ይህንንም ፓትርያርክ ሾምን የሚሉቱ የ4 ኪሎዎቹ የግራ ክንፍ ቡድን አባቶች የሚያውቁት ከሆነ ይሄንን ሁሉ ትርምስ ምን አመጣው? ከተባለ መልሱ ቀላልና ግልጽ       ነው፡፡ የ4 ኪሎዎቹ የግራ ክንፍ ቡድን አባቶች የሠሩትና ሊሠሩት ያሰቡት ነገር እግዚአብሔርን እንደሚያስቆጣና እንደሚያስቀይም ቢያውቁም ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ከንቱና ፋይዳ ቢስ መሆኑን ቢያውቁም ያሳሰባቸውና እንዲሠራ የፈለጉት ሥራ ምድራዊው እንጂ ሰማያዊው ባለመሆኑ ፣ የሌላውን እንጂ የቤተክርስቲያኗን ባለመሆኑ ፣የግለሰቦች እንጂ የእግዚአብሔር ባለመሆኑ እነሱን በምቾት እስካኖረ ጊዜ ድረስ የሠሩት ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለመኖሩና ፈጣሪን ማስቀየሙ አላሳሰባቸውም አላስጨነቃቸውም አያስጨንቃቸውምም፡፡ እንዲህ ዓይነት ስብእና ለመያዝ ማመንና መንፈሳዊነትን ይጠይቃልና፡፡ ምንም እንኳ እናምነዋለን የሚሉት ቅዱስ መጽሐፍ «ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል» ቢልባቸውም ቅሉ የሐ.5÷29 ቅዱስ ቃሉ «ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቁንም ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ» ቢልባቸውም ማቴ. 10÷28 ሰዎቹ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን በመፍራታቸው፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ለሰው በመታዘዛቸው ፣ እንደራሴነታቸው ለእግዚአብሔር መሆኑን ረስተው ወይም አሽቀንጥረው ለምድራዊያን በማድረጋቸው ይህ ችግር ሊፈጠር ቻለ፡፡
የ4 ኪሎዎቹ የግራ ክንፍ አባቶች ቡድን ምን ነበር ያሉት? 5 ብለን 6 እንላለን እንጅ እንደገና ተመልሰን 4 አንልም ለታሪክ አዘጋገብ አይመችም አሉ፡፡ «ብፁዓን» አባቶች ሆይ ! አሁንም እባካቹህ ስለ ወላዲተ አምላክ ብላቹህ ትመልሱልን ዘንድ እንማፀናለን ፡፡ ይበላሻል የተባለው ታሪክ የትኛው ታሪክ ነው? የትኛውስ ቀኖና ነው የሚጣሰው? ከማንም በላይ በዚህ 20 ዓመታት ውስጥ በዚህች ቤተክርስቲያን ምን እንደተሠራ ልቡናቹህ ያውቀዋል ምስክሮችም ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ዛሬ በሚገርም ሁኔታ ተለውጠው የግራ ክንፍ አባቶች ቡድን በመሆን ተሰልፈው መግለጫ ሰጪ ሁሉ የሆኑ ቢኖሩም ቀደም ሲል ግን በአባ ጳውሎስ ላይ በቤተክርስቲያኗ ግፍ አበዙ፣ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ተቆነጻጸለ ተፋለሰ ወዘተ በማለት በተለያየ ጊዜ ከባድና ጠንካራ አመፅ ቀመስ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው ይሄ እንደምን ተዘነጋቸው? ሥራ የተባለው ምኑ ነው? ተደርጎ በማያውቅ አረማዊ ድፍረት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቦታ በሰው መወረሱ ?፣ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ከዶግማ እስከ ቀኖና መፍረሱ መጣሱ?  ፣ የአስተዳደር መዋቅሯ በየጊዜው ለድርጅታዊ አሠራር ሲባል ያለ አግባብ እና ያለ ሥርዓት መናጥ መቃወሱ? ፣ ሀብት ንብረቷ ያለ ማሠለስ ያለ ሃይ ባይ መዘረፍ መከስከሱ? ፣ ዘረኝነት መንገሡ? ፣ የምዕመናን ኅብረትና አንድነት ሆኖ በማያውቅ ደረጃ መፈረካከሱ ይሄ ነው ሥራ የተባለው? ታሪክ የተባለውስ የትኛው ታሪክ ነው? እርግጥ ነው ታሪክ ሲባል መልካም መልካሙ ብቻ አይደለም መጥፎ መጥፎውም እንደ መጥፎነቱ የታሪክ አካል መሆኑ አይቀርም ፡፡ነገር ግን መጥፎውን ታሪክ ያመለጠ ካልሆነና አሁንም የማረም የማስተካከል ዕድሉ ካለ ያለፈውን ምዕራፉን በማስተማሪያነት ይዞ ያላመለጠውንና ያላለፈውን የመጥፎን ታሪክ አካል ያርሙታል ያቀኑታል ያስተካክሉታል እንጂ ሊገልጹት በሚያሳፍር ምክንያት ዳግም እንደገና በመሳሳት በጥፋት ላይ ጥፋት በመጨመር በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላይ መጫወት መቀለድ ይገባልን?፡፡
ታሪክ ይበላሻል ቀኖና ይጣሳል አላቹህ? ታሪክንና ቀኖናንማ ምሳቹህ ቀበራችሁት እኮ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ዳግመኛ ስሕተት በቤተክርስቲያን ላይ አንፈጽምም በማለት ተቃውሞ ላሰማችሁትና ላልተስማማቹህት ብፁዓን አባቶች በግል አድናቆቴና ምስጋናዬ ? ይድረሳችሁ ፡፡ ነገር ግን ሥራቹህ ገና ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም ያበርታቹህ፡፡ ተቃውሟቹህ በስማቹህ ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ስም የወጣውን መግለጫና የታቀደውን ስሑት የጥፋት ሥራ ሕጋዊ እንዳልሆነና ሊተገበር እንዳይችል በመታገል ለሕዝበ ክርስቲያኑ እስከ ማስተጋባትና ካስፈለገም መከራ እስከመቀበል ድረስ ካልዘለቀ ተቃውሟችሁ የይስሙላ ይሆናል፡፡ ቤተክርስቲያንንም ለተኩላት አሳልፋችሁ እንደሰጣቹሃት ቁጠሩት ፡፡በዝምታ ራስን ማግለልም ከተባባሪነት ተለይቶ የሚታይ አይደለም ቤተክርስቲያንን ከአደጋ በጎችንም ከተኩላ ለመታደግ የሚያበቃ ሥራ አይደለም ዝምታቹህ ለአጥፊዎች እንጅ ለቤተክርስቲያን አይጠቅምም፡፡ በእግዚአብሔርም ዘንድ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ ነገር ግን በተቃውሟቹህ ብትቀጥሉ እኛ ምእመናን ከጎናቹህ ነን የቤተክርስቲያን በዚህ ደረጃ መቀለጃና መጫወቻ መሆን አስቆጥቶናል ፡፡ተቃውሟችንን ማሰማት እንፈልጋለን ቤተክርስቲያናችንን ለማንም ጥቅመኛና ምንደኛ መረካረኪያ አሳልፈን በመስጠት ባለዕዳ መሆን አንፈልግም፡፡ ተቃውሟችንን እንድትመሩልን እንፈልጋለን ይህንን ስታደርጉ ብቻ ነው ተጋድሏቹህ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ሊያሰጣቹህ የሚችለው ታማኝ እረኝነታቹህ የሚረጋገጠው አባትነታቹህ የሚታወቀው ፡፡ቤተክርስቲያን እስከዚህ ዘመን ድረስ መቆየት የቻለችውና ከትውልድ ወደ ትውልድ አስተምህሮዋን ጠብቃ ለመሸጋገር የበቃችው የአላዊያን ነገሥታትንና የመናፍቃን ጳጳሳትን የጥፋትና የክሕደት ሥራ አባቶችና ምእመናን በመቃወማቸው አይሆንም አይቻልም በማለታቸውና እነዚያን የጥፋት አካላትንም ከቤተክርስቲያናችን በማራቃቸው በማስወገዳቸው ሰማዕትነት እስከመቀበል ድረስ በመፅናታቸው ነው ፡፡ ይህ ክርስቲያናዊ ግዴታ እና ኃላፊነት በሁሉም ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ በስሙ ከተጠመቅንበትና ልጅነትን ካገኘንበት ቀን ጀምሮ የተጫነብን አምላካዊ አደራ እና ግዴታ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይህንን አምላካዊ አደራና ግዴታ መወጣት እንፈልጋለን ምሩን አሰማሩን፡፡
ሲኖዶስ ማለት በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ፣ የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ የሚፈጽሙ፣ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ጥቅም የሚያስቀድሙ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ማለት እንጂ የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ የሚፃረሩ፣ ለቤተክርስቲያን መከራ የሚደግሱ፣ ሕግጋቷን የሚያፈርሱ የሚጥሱ ሰሐትያን ሊቃነ ጳጳሳት ዱለታ ማለት አይደለም፡፡ ይሄ የድፍረት ድፍረት ነው፡፡ ሰዎቹ በመግለጫቸው መንበረ ፓትርያርክና ቅዱስ ሲኖዶስ አይሰደዱም ይህ በታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅ በማለት የተሰደዱ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጠቅሰው መንበሩና ሲኖዶሱ ግን እንዳልተሰደዱ ነባራዊ ሁኔታዎችን ባላገናዘበ መልኩ ምሳሌ ጠቅሰው ለማስረዳት ሞክረዋል፡፡ እንደዛ ከሆነማ መንበረ ማርቆስ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ማለት ነዋ? ምክንያቱም እንደነሱ አባባል የቅዱስ ማርቆስ መንበር ያለው እስክንድርያ (ግብጽ) በመሆኑ ከእስክንድርያ መውጣት ስለማይችል፡፡ ግብጾችም እንዲህ እያሉ እኛስ እራሳችን እንዴት የተገባን ሆን ሳይሉ፣ በከንቱ ያገኛችሁትን በከንቱ ስጡ የሚለውን አምላካዊ ቃል እረስተው፣ እግዚአብሔርን በማምለክ ይቀድሙናል ሳይሉ፣ ለወንጌል መስፋፋት እንቅፋት እየሆኑ እንደሆነ ሳይረዱ ለ1600 ዓመታት ያህል ጵጵስናንም ፕትርክናንም ከልክለውን ቆይተው ነበር፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓይነት አሠራርማ ቢሆን ኖሮ ክርስትና ከኢየሩሳሌም ባልወጣም ነበር፡፡ ወንጌልም በመላው ዓለም ባልተስፋፋ ወይም እንዲስፋፋ ባልተፈልገም ነበር፡፡ ክርስትና የርሥትና የጉልት ጉዳይ አይደለም ያመነ ሁሉ የሚዋጅበት ክርስቶሳዊ ሕይወት እንጅ፡፡ ሲኖዶስ ማለት ቅድስት ቤተክርስቲያንን የሚመሩ ብቁ ሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ማለት ከሆነና ከመሬት ጋር የተጣበቀ ግዑዝ ነገር ማለት ካልሆነ እንዴት ነው ሊቃነ ጳጳሳቱ ተሰደው ካሉበት የሚያደርጉት የቤተክርስቲያን ጉባኤ ሲኖዶስ ሊባል(ሊሆን) የማይችለው፡፡ የቤተክርስቲያን  ሦስቱ ዐበይት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባዎች ማለትም ጉባኤ ኒቅያ፣ጉባኤ ቁስጥንጥንያ፣ጉባኤ ኤፌሶን(በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያ፣ በኤፌሶን የተደረጉ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባዎች) ኢትዮጵያ ውስጥ ወይም እስክንድርያ የተደረጉ ይመስላቸዋልን?፡፡ ጥያቄው እሱ አይደለም ጥያቄው እንደቃሉ ሁሉ በሰው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ ተጠያቂነቱ ለሰው ሳይሆን ለመንፈስ ቅዱስ የሆነው፣የቅድስት ቤተክርስቲያንን ዶግማ ቀኖናና ሥርዓት የሚጠብቀው ወይም እየጠበቀ ያለው የብቁአን ሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ የትኛው ነው?የሚለው ነው እንጂ ቦታ አይደለም፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የትኛው ነው የውጭው ነው ወይስ የሀገር ቤቱ የሚለውን ጥያቄ በሚገባ ይመልሳል፡፡
 ከሰዎቹ መግለጫ ላይ ሌላው ያስገረመኝ ነገር ስደተኞቹን አባቶች በድርድሩ ወቅት ከቤተክርስቲያን ጋር  ተያያዥነት የሌላቸውን ጉዳዮች በማንሣታቸው ያሉት ነገር ነው፡፡ ጉዳዩን በግልጽ ቢናገሩት ምንኛ በተመቸ ነበር ይሁንና በሌሎች መድረኮችም ይህ ተያያዥነት ይሌለው ያሉትን ጉዳይ ምንነት ገልጸውታል፡፡ ስደተኞቹን አባቶች ፖለቲከኞች ናቸው ብለዋቸዋል፡፡ አሁንም ግን  ጉዳዩን ፖለቲካ ነው አሉ እንጅ ዝርዝር ጉዳዩን መናገር አልፈለጉም፡፡ ይሁንና እነኛ አባቶች የሀገርና የሕዝብ ጉዳይ በማንሣታቸው ከሆነ ፖለቲከኛ ያሏቸው እነሱን ብቻ ሳይሆን ከስንክሳር እስከ ገድላገድላት ያሉትንም እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉ ቅዱሳን አባቶቻችንንም እየዘለፉ ነው፡፡ «ድሃ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ» ብሎ ማለት ከሐዋርያዊ ተልእኮ ውስጥ ዋነኛው ሥራ ነው፡፡ ሐዋርያት ያ ሁሉ መከራ የደረሰባቸው ምን ስላደረጉ ይመስላቸዋል? ክርስቶስን(ወንጌልን) መስበክ ማለት  እውነትን ፍትሕን መስበክ ስለእነሱም መጋደል ማለት እንደሆነ አያውቁምን?  እነ ዮሐንስ አፈወርቅ መከራ የተቀበሉት ምን ስላደረጉ ይመስላቸዋል? ስለ እውነት ስለ ፍትሕ መጋፈጥ መከራ መቀበል ሐዋርያዊ ግዴታ ነው፡፡ አብሶ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዚህች ሀገር ባለአደራ ናትና ለዚህች ሀገር ህልውናና ነፃነት ታቦት ተሸክማ ለጦርነት እስከ መሰለፍና የማይተካ መስዋዕትነት እስከመክፈል ድረስ ያላደረገችው ነገር የለምና ስንት የሆነችበትን የደከመችበትን ዋጋ የትም በትና እንደ እንግዳ ልትሆን ፈጽሞ አይገባትም ያገባታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ሀገሪቱንና ሃይማኖቷን ወይም አማኖቿን ነጣጥሎ የጠራበት አንድም ጊዜ እንኳን የለም፡፡ ባለ አደራ ናት፡፡ ምነው የአራት ኪሎዎቹ አባቶች የማን የፖለቲካ ቡድን አባል ሆናቹህ ያውም ቤተክርስቲያንን በሚጎዳ መልኩ የማንን ሥራ እንደምትሠሩ የማናውቅ ይመስላቹሀልን? ይሄን ካደረጋቹህ ላይቀር ይህችን ሀገረ እግዚአብሔር የቃልኪዳን ምድር በሚጠቅም መልኩ ለሀገሪቱ አንድነት ፣ ለሕዝቡ ደኅንነት ለታሪክ ሕያውነት በሚበጅ መልኩ በመሰማራት የአባቶቻችንን ፈለግ በመከተል አደራ ብትወጡ ምንኛ በታደላቹህ ነበር፡፡
ከ4 ኪሎዎቹ ግራ ክንፍ የአባቶች ቡድን ውስጥ ከሞላ ጎደል በአባ ጳውሎስ የተሾሙ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አባ ጳውሎስ ፓትርያርክ አልነበሩም ከተባለ የእኛም በእሳቸው የተሰጠን ጵጵስናም አይኖርም ማለት ነው በሚል ሥጋዊ ስሌት የተነሣ ነው፡፡ ነገር ግን ጵጵስናን በመመረጥ እንጂ በጉልበት ሊያገኙት እንደሚችሉ ያስባሉን? ከእግዚአብሔር ካልተሰጠ ከሰው ማግኘት ይቻላልን? ከእግዚአብሔር ያላገኙትን ያልተሰጣቸውን እንዳገኙ እንደያዙ መስለው ለሰው ቢታዩ ለነሱ ምን ይጠቅማቸዋል? እራስን ማታለል እራስን መሸንገል አይሆንባቸውምን?፡፡ ባንፃሩ ግን ለጵጵስና የተገቡ ከሆኑ እንደ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት ማለትም ገድላትንና ተአምራትን ጨምሮ ስለ እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ሲናገሩ ባልተገባቸው ሰዎች የተደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንደተደረገላቸው ሰዎች እምነትና ንጽሕና ምንም እንኳጉዳዩ ባልተገባቸው ሰዎች ቢፈጸምም በእግዚአብሔር ዘንድም ግን እንደተፈጸመላቸውና እንደሚጸድቅላቸው መጻሕፍቱ ይናገራሉ ይመሰክራሉ፡፡ የእነኝህ ጳጳሳት ሹመትም በዚሁ መልኩ የሚታይና የማያሳስብ ነገር ነበር ፡፡ ለነገሩ እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጂ ለእነዚህ አባቶች ከስደተኛው ሲኖዶስ ዘንድ በጵጵስናቸው እንደሚሾሙ ተነግሯቸው እንደነበር ይነገራል፡፡ ሰዎቹ ግን ባልታወቀ ምክንያት እንደልባቸውና ኅሊናቸው ማደር ሳይፈልጉ ቀርተዋል ፡፡
እንግዲህ እነኝህ ሰዎች ይህንን በማድረጋቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን የሚጋረጥባትንና የሚደርስባትን አደጋ ከምንም ሳይቆጥሩ ይህንን አድርገዋልና ቤተክርስቲያን ለሚደርስባት ችግር ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳሉ በሥጋም በነፍስም ተጠያቂ ይሆኑበታል፡፡ይህ ሁኔታ ቤተክርስቲያን በምኖች እጅ እንዳለች ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ስደተኛውም ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኗ ሕግ እንደሚፈቅድላቸው ሁሉ እነሱም እንደተናገሩት የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የመመሥረትና የመምራት መብት ያለን የቤተክርስቲያኗን ሕግ ሥርዓትና ቀኖና ጠብቀን አክብረን ያለነው እኛ እንጂ ለሕገ ቤተክርስቲያን ደንታ የሌላቸው ሥርዓትና ቀኖና አፍራሾች የ4 ኪሎዎቹ የግራ ክንፍ አባቶች ቡድን አይደለም ፡፡ በመሆኑም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሲያርፉ በቦታቸው ሥርዓቱን ጠብቀን ቀጣዩን ፓትርያርክ እንሾማለን ብለዋልና የ4 ኪሎዎቹ የግራ ክንፍ አባቶች ቡድን በሠሩት እጂግ ብስለትና ኃላፊነት የጎደለው ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ስሕተት ወይም ጥፋት ውጤቱ ቤተክርስቲያን ለሁለት መከፈሏ እርግጥ ሆኗል ማለት ነው፡፡ የዚህ መዘዝ ደግሞ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን በገጠማት ተመሳሳይ ችግር  ከደረሰው ጉዳት የተለየ አይሆንም፡፡ቅዱሳን አባቶችንም ያሳሰባቸው ይሄው ነው ይህ ዛሬ የገባው የክሕደትና የድፍረት መንፈስ  ዛሬ ያላደረገውን ነገ የሚያደርገው መሆኑ፡፡ ማለትም ዛሬ ሥርዓትንና ቀኖናን  እንዳስጣሰ እንዳስፈረሰ አለመቅረቱ ይህ ክፉ መንፈስ አንዴ ገብቶ ቦታ ይዟልና ነግሣôልና ነገ ደግሞ እሱ በፈለገ ጊዜ የቤተክርስቲያኗን ዶግማ በይፋ ማስጣሱ ማስፈረሱ የማይቀር መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ወይም መንገድ ነው ዛሬ ከ30ሽህ በላይ ዓይነት የክርስትና ሃይማኖት ነን የሚሉ ተቋማት ሊፈጠሩ የቻሉት፡፡ የቤተክርስቲያን ታሪክ የሚያሳየን ይህንን ነው፡፡ በመሆኑም የቤተክርስቲያኗ ሐዋርያዊ አስተምህሮና ርትዕትነት ዘላቂ መሆኑ ከባድ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ድረስ የከፋና የከበደ ስሕተት ነው የተፈጸመው ለነገሩ እነዚህ  የግራ ክንፎቹ አባቶች  ቡድን እንደ ግንዛቤአቸው እምነታቸውና ዓላማቸው የሚበልጥባቸው ስለበለጠባቸው እንጂ ይሄንን አደጋ አተውት አይመስለኝም «ላልምልን ሰርቄአለሁ?» ነበር ያለው ሰውዬው?፡፡ታዲያ እንግዲህ ይህ ሁሉ ሲሆን እጅና እግራችንን አጣምረን ዝም ብለን ነው የምናየው? ቀን የማይመሽብህ አምላክ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ ለአንዲቷ ሃይማኖት ሲሉ በስምህ መከራን ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ቅዱሳን የገባኸውን ቃልኪዳን አስበህ ድረስልን ታደገን አሜን፡፡                


9 comments:

  1. oh man where are you you did god job . an interesting document.

    ReplyDelete
  2. Lebete Kiristyan Yembej Neger Post Btadergu Melkam Ymeslenal Miknyatum Hulum Yeyerasu Budin Wokllo Yefelegewun Mesdeb Ena Mekonen Yetm Ayadersim Ende Ewunetu Kehone Le Ethiopia Betekiristyan Yederesebat Fetena Meteyeq Yemgebachew Bewuch Yalu Abatoch nachew. Zerengnet Gotengnet Tebab Astesaseb Beagerachin Lay Yasefenut Enesu Nachew Qedmew Hulum Amechachtew Ye Kobelelut. Qenona Tetase Dogma Ferese Ketebale KEne Abba Melke Tsedek Yebelete Asafary Drget Bebete Kiristyan Lay Yefeseme Alewy? Amara Silehonu Menekat Yelebachewum Malet new wys Ye Poltica Agarachin Sile honu Esu Menkat Yelebnim new. Enesu Besltan Lay Eyalu Kedebre Tawor Beqer Lela sew Be Addis Abeba Tlaliq Adbarat Bota Yagengne Neber way? Edetew Ewunet Tenageru Sewoch

    ReplyDelete
  3. ደህና ሁኚ ብለው የተሰናበቷትን ቤተ ክርስቲያን በነገር መርዝዎ መውጋቶ ምን ይባላል? ያለፈው ጊዜ ያሉትን ረስተውት ይሆን? የሆነ ሆኖ በማስረጃና ምክንያታዊ ሁኖ መጻፍ ያለብዎም መሆንዎን አይርሱ:: እንደ ሥዕሉ በመገልበጥ ብቻ የሚሳካልዎ አይመስለኝም::

    ReplyDelete
  4. እኔ የምለው ይህች ቤተ ክርስቲያን የማን ናት? ሰው ያጣች ከመሰለን ይሁን:: እረ ተዉ የሚዋቀስ አምላክ አላት:: አሁን እውነት ይህ የተቆርቋሪነት ስሜት ነው? እውነት እጸድቅ ብለው የጻፉት ነው? እሺ ምን ይደረግ ነው እያሉ ያሉት? እኛ ምእመናን እንግዲ አንሰደድ ለንግሥ ሆነ ለቁርባን መቼም ከአገረ አሜሪካ ኢየሩሳሌም ይቀላል:: እረ አግዙን ለጽድቅ የሚረዳንን ለትሩፋት የሚጠቅመንን ማድረግ ባትችሉ ዝም እንድል ለምን አትፈቅዱልንም? የእርሱን ጊዜ እየጠበቅን ነው እረ እንግባባ??? ከፍ እያሉ ክህነቱን ቆቡን ካባውን መስቀሉን መያዛቸውን ዘንግቶ መዛለፍ አይከብድም? ኃጢአት ሰርተው ባይመለሱ ለማን ይብሳል? እርሶ ሊያስታውሷቸው የፈለጉት ምንድን ነው? በዚያውስ ላይ ከነአናዊ ተግባርዎ ፈጣሪን የሚያስደስት ይመስልዋታል? እረ እንደማመጥ???????? መሐሪ አምላክ ሆይ ማረን!

    ReplyDelete
  5. I was one of a live witness that my job at the Church was taken away and given to another person who is from Gonder during the Aba Merkorewos zemen.

    Guys, unless you are just hiding it, everyone knows that Aba Merkorewos was not really appointed by God or Church's willingness. Ato Sealiw, if you truly believe that we do not have 5th patriarch because he was nominated while the 4th is alive, why don't you apply the same mechanism to the 3rd & 4th patriarch who are both enthroned while The 2nd Patriarch Aba Tewoflos was not officially deceased?

    In fact by your own logic, we didn't have 3rd & 4th patriarch. Aba Pawlos should be considered as the 3rd after Aba Tewoflos because it was only by then that the Church for sure announced the death of the 2nd patriarch. Do you know that for that same reason our Egoptian sister Church didn't recognize the 3rd & the 4th??

    Don't be hypocrite & please speak the truth!!!

    ReplyDelete
  6. ሰላም ጤናይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።

    መድኃኔዓለም ይመስገን።

    ይህ ሰዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው የተባለ ሰው ለካ በሺተኛ ነው። ባለፈው አንድ ሰው ፖለቲከኛ ነው ሲለው ለካ አውቆት ኖሯል። እኔ እኮ ምንም የእውቀት ችግር እንደነበረበት ባውቅም ከልቡ ለቤተክርስቲያን የሚያስብ ሰው መስሎኝ ነበር። በመጀመሪያ ባለፈው ጊዜ አምሳሉ ፓለቲከኛ ነው ሲል የተቃወምኩትን ሰው ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከዛ በተረፈ ግን የአንድ አድርገን ብሎግ አዘጋጆች ከዚህ በታች ያለውን አስተያየት ለሰዓሊ አምሳሉ ታደርሱልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ።

    ሰዓሊ አምሳሉ ሆይ፥

    ፩ኛ - ካህናትን መሳደብን እግዚብሔር እንደከለከለ አታውቅምን? ኃይማኖትን ሲቀይሩ ወይም ሲያጎድፉ ስታይ ፊት ለፊት ኃይማኖቴን አትንኩ ብሎ መናገር መልካም ነው፤ ነገር ግን ማስረጃ ሳይኖርህ ካህናትን በጅምላ የግራ ክንፍ እያልክ መሳደብ አጸያፊ ነው። ከነሱ ውስጥ ድጎችም ሊኖሩ ይችላሉ፣ ሰርገው የገቡ አስመሳዮችም ሊኖሩ ይችላሉ። ሆኖም ግን በጅምላ ስድብ እንኩ ማለት መልካም አይደለም። ወይም እገሌ ኃይማኖትን እንዲህ አጓድሏልና ኃይማኖቴን ለመጠበቅ ይህን ማድረግ አለብኝ ብለህ የሚታይ፣ የሚጨበጥ ነገር ማቅረብ አንድ ነገር ነው። አንተ ግን የምታወራው ነገር ምን እንደሆነ እንኳን በትክክል የማታውቅ ሆነህ በዛ ላይ ስድብ ስታክልበት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

    ፪ኛ - አቡነ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን ብዙ በድለዋል። ኃይማኖታችን ሊያጎድፉ ከካቶሊኮች፣ ከኃሳውያነ መሢሕ ፕሮቴስታንቶችና፡ ከእምነተቢስ ህዝባዊ ወያን ሓርነት ትግራይ ወንበዴዎች ጋር ተባብረው ቤተክርስቲያናችን ለማጥፋት የወሰዷቸው እርምጃዎች የሚረሱ አይደሉም። በተለይ ደግሞ ከእምነተቢሶች ጋር እጅና ጓንት ሆነው የተቀደሰውን የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ ያደረጉት ዘመቻ ለዘመናት የሚዘነጋ አይደለም። በዚህም ሥራቸው ከጥፋት መሪያቸው ከመለስ ዜናዊ ጋር ሁላችንም ዓይናችን እያየ ኃያሉ አምላክ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ እንደ ፈርኦንና እንደ ግብጽ በኩሮች እንደቀሰፋቸው በቅርቡ ያየነው ተዓምር ነው። ሆኖም ግን የአቡነ ጳውሎስ ጥፋት በውጭ የሚገኙትን በአሜሪካን ሴኩላር ህግ የተመሠረተ የተለየ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉትን ንጹሕ አያደርጋቸውም። አሜሪካን የሚገኙት የውጭ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉት ከአቡነ ጳውሎስ የባሱ፥ ሃይማኖትን ጭራሽ የቀየሩ፣ ኃይማኖትንም የሚሳደቡና ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሰዎች መሆናቸውን ሰዓሊው አምሳሉ አታውቅም የምታውቅ ከሆነ ደግሞ እንደሚመስለኝ ፎቶህንም የለጠፍከው አሜሪካ የመምጣት ተስፈኛ ሆነህ በዚህ አስተያየትህ ስፖንሰር የሚያደርጉህ መስሎህ ሊሆን ይችላል። ተሞኝተሃል። አንተን ከኢትዮጵያ ማስወጣት ይቅርና አያገኙትም እንጅ እነሱ ወደ ኢትዮጵያ መመለስን የሚለምኑበት ቀን እሩቅ አይደለም።

    ፫ኛ - በፓትርያርክ ላይ ፓትሪያርክ አይሾምም የሚለው ሕግ የሠፈረው በፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ነው። እኒህ አንተ ይገባቸዋል የምትላቸው የውጭ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉት ፍትሐ ነገሥትን አንቀበልም የሚል አስተያየት ከዚህ ቀደም ethiopianorthodox በሚባለው ድህረ ገጻቸው ላይ አውጥተውት ነበር። ፍትሐ ነገሥትን አንቀበልም ካሉ የሠሩት የአሸዋ ግንብ እንደሚፈራርስባቸው ሲገነዘቡ በኋላ ጽሁፏን አነሷት። ማን እንደሆኑ ለማወቅ ያ በቂ ነው። ፍትሐ ነገሥትን ሳያምኑበት በፍትሐ ነገሥት ሕግ መሠረት ሥልጣን የኛ መሆን አለበት የሚባል አቤቱታ አለ ወይ? ይህን እግዚአብሔር ይቀበለዋል ወይ?

    ፬ኛ - በአሜሪካን አገር ያሉ የውጭ ሲኖዶስ ሠርተናል የሚሉት ሴቶች በግዳጃቸው ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡ አድርገዋል፣ ግቡ ብለውም በየስቴቱ አስተምረዋል። ፍትሐ ነግሥት በነሱ ላይ የሰጠውን ፍርድ እነሆ ተመልከት።

    ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ወገን አንዱስ እንኳ ተደፋፍሮ ከግዳጅዋ (ከደሟ) ያልነጻችውን ሴት ወደቤተክርስቲያን ያስገባ :- በደሟም ወራት ሥጋውንና ደሙን ያቀበላት ቢኖር ከሹመቱ ይሻር :: ምንም ከነገሥታት ሴቶች ወገን ብትሆን :: ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፮ ቁጥር ፪፻፴፭

    እንግዲህ እንደምታየው ያንተን ካህናቶች ፍትሐ ነገስት ሽሯቸዋል። ፍትሐ ነገስት የሻራቸው ፍትሃ ነገስትን ጠቅሰው ስልጣን ይገባናል ሊሉ ይችላሉ ወይ?

    ፭ኛ - እነዚህ ያንተ የውጭ ሲኖዶሶች ዋልድባ በተደፈረ ማግሥት የሲኖዶስ ስብሰባ አደረግን ብለው በስብሰባው መደምደሚያ የዋልድባ ጉዳይ ሳይቆጫቸው እስላሞችን በመደገፍ መግለጫ አውጥተዋል። የዋልድባን ገዳም ለማዳን ሎሳንጀለስ ላይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ በመሰብሰቢያቸው ጥሪውን እንዳይነገር ከልክለዋል። ከነሱ መካከል አንድም ሰው አልተገኜም። የውጭ ሲኖዶስ የሚባለው መንገዱ ውጭ አገር ባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀየስ በመሆኑ ምክንያት የፖለቲካ ሰዎቹ ለፖለቲካ ሲሉ አንዳንዶቹን ገፋፍተው ያስወጧቸው ቢሆንም ውጭ አገር ሲኖዶስ መስርተናል የሚሉት የማያምኑት በፍትሐ ነገሥት ብቻ ሳይሆን በገዳምም አያምኑም። የገዳምን ነገርም ሆነ የፍትሐ ነገስትን (የቅዳሴንም ጭምር) ለፖለቲካ አኪያሄድ ስለመቻቸው እንጂ እኛ ውች አገር ያለን ሰዎች በአንዱም እንደማያምኑ እናውቃለን።

    ፮ኛ - ፭ኛ ሳኡባል ፮ኛ አይባልም ያልከው ከሁለተኛ በኋላ ሥራአት እንደፈረሰ አታውቅምን? ሦስተኛ ሳይባል አራተኛም እኮ የለም። ያለ ተርጥር ምንም ሦስተኛ ቅዱስ መሆናቸውን ብናውቅም በደርግ ሥርአት እንደተጣሰ እኮ መዘንጋት የለብህም።

    ፯ኛ - ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፭ ቁጥር ፻፺፱ - ረስጠጅ ፸፯ ። ኤጲስቆጶስ እራሱን ከክርስቶስ አገልጋይ አውጥቶ ለንጉሥ ከሚሠሩ ሥራዎች በማናቸውም ሥፍራ መሾም አይገባውም። በዚህ ጸንቶ ቢኖር ከሹመቱ ይሻር። ጌታችን አንድ ባሪያ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻለውም አለዛም ግን አንዱን ያሳዝነዋል ሌላውንም ደስ ያሰኘዋል ብሏልና (ማቴ ፮፡ ፳፬) - ይላል። አሁን የውጭ ሲኖዶስ መሥራች አባ መልከጸዴቅ የጻፉትን የቋሚ ምስክርነት የሚለውን መጽሐፍ አንብብና እንደገናም በደርግ ሸንጎ ውስጥ የያኔው ኤጲስቆጶሳት የነበራቸውን ተሳትፎ መርምርና ውጭ አገር እንኳን ሲኖዶስ ካህን እንኳን እንደሌለ ትረዳለህ። ሁለቱ በውጭ አገር ያሉ የውጭ ሲኖዶስ መሠረትን የሚሉትን ክህነት ሰው ሳይሆን ፍትሐ ነገሥት እራሱ ሽሮባቸዋል። መጽሐፍ የሻረውን አንተ ወደ መንበር ልታመጣ ትደክማለህ። እኔ ራሴ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ አቡነ መርቆሬዎስን ፓትርያርክ ያደርጋሉ ብየ ተስፋ አድርጌ ነበረ። ይህን የፈለኩት ትክክል ነው ብየ ሳይሆን በውጭ አገር ብዙ የተዋህዶ ልጆች በዚህ የውጭ ሲኖዶስ በሚባለው ትምህርት እምነታቸው ወደ ፕሮቴስታንትነት እየተለወጠ ስለመጣ እነሱን በተኹላ ከመበለት ለማዳን መንገድ ይገኝበታል ብየ ስላሰብኩ ነበረ። ወንድሜ ሆይ፥ ይልቁንስ የቤተክርስቲያን ቅንአት ካለህ ዋልድባን ሄደህ ተመልከትና ስለዋልድባ ጻፍ። አለቃ አያሌው የተናገሩትን ሁሉ ደግሞ ፈላልገህ አድምጥ። ብዙ ትምህርት ታገኝበታለህ።

    እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. Egziabher Hasabon Yasakalot!!!Kidus Pawlos Endalew"Endenezi Aynetun Afachewn Mezgat Yasfelgal"Andadregen,You have to post this kind of thouthful comments on the front pabge.Egziabher lehulum Abatoch fikirina andinetin yistlin.yedabilosin sirra keigrachew sir ketikito yitalilin.

      Delete
  7. ኃይለሚካ ኤል ጡሩ ብለሃል

    ReplyDelete
  8. ኃይለሚካኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን እውነቱ ይሄ ነበር እነሱ ግን ህዝቡን ያታልሉታል እግዚአብሔር ይፍረድ

    ReplyDelete