Tuesday, April 2, 2013

‹‹የኤልያስ አምላክ›› አዲስ ቪሲዲ በቅርብ ቀን


(አንድ አድርገን መጋቢት 24 2005 ዓ.ም)፡- ራሳቸውን ኤልያሳውያን የ‹‹ተዋሕዶ›› ልጆች በማለት በመጥራት በመንቀሳቀስ ላይ ያሉት ወገኖች አስተምህሯቸውን በሰዎች ጭንቅላት ላይ መጫን ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ ቤተክህነቷ በመሀል 4 ኪሎ እየተገኝች አነሱ እዛው አጠገቧ ስራቸውን ሲሰሩ አልሰማውም አላየሁም በማለት ዝምታዋ ተስማምቷት መቀመጧ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ኤልያስ ወርዷል የሚሉትን ሰዎች መንገድ ትክክል አለመሆኑን ምዕመኑ ያውቀው ዘንድ ሰባኪያን በተለያዩ አውደ ምህረቶች አስተምህሮው የገባቸውን ያህል ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ ፤ በዚህም ሳምንት መርሀ ግብር የያዙም ሰባኪያንም ይገኛሉ ፤ ነገር ግን ይህ አካሄድ ያልተመቻቸው ጥቂት ምዕመናን ለምን ሰባኪያን ከማስተማራቸው በፊት ቤተክርስቲያኒቱ በኤልያስ ላይ ያለውን አስምህሮ ለምዕመኑ አታሳውቅም ? እነዚህ ቡድኖች የቤተክርስቲያኒቱን ስም በመጠቀም ምዕመኑን ግራ እንዳያጋቡት ለቤተክርስቲያኒቱ አማኞች መልዕክቷን ለምን አታስተላልፍም ? ኤልያሳውያን ተለጥፈው የሚሰሩት ስራ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ መሆኑን ለምን አትናገር ? በማለት ቀድሞ ቤተክርስቲያኒቱ በሊቃውን ጉባኤ መልስ መስጠት አለባት የሚል ሃሳባቸውን ይሰጣሉ ::  
አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ‹‹የኤልያስ አምላክ›› የሚል አርዕስ ያለው ቪሲዲ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት አዘጋጅነትና በጌልጌላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት አዘጋጅነት ስራው ተጠናቅቆ በቀጣይ ሳምንት ለማድረስ የህትመት ስራው እየተሰራ መሆኑን መረጃ ደርሶናል ፡፡ ሌሎች ሰባኪያንም የስብከት መርሀ ግብራቸውን በቪሲዲ በማሳተም ለመልቀቅ ማሰባቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡ 

ስብከቱ ገበያ ላይ እንደዋለ ከሀገር ውጪ ላሉ ምዕመናን ብሎጋችን ላይ ለመለጠፍ እንሞክራለን፡

No comments:

Post a Comment