Sunday, April 14, 2013

በግዕዝ ቋንቋ ዘፈን


(አንድ አድርገን ሚያዚያ 4 2005 .)- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለተለያዩ አገልግሎቶች የምትጠቀምባቸው ቀዳሚ ቋንቋ ግዕዝ መሆኑ ይታወቃል እኛ ግዕዝን የምናውቀው አባቶች ቅኔ ሲቀኙበት ውዳሴ አምላክ ሲያደርሱበት ሰዓታትን በመቆም በተለያዩ የቤተክርስያኒቱ ያሬዳዊ ዜማዎች ጋር በማስማማት ለአምላክ ምስጋና ሲያቀርቡበት ነበር ፡፡ አሁን በእኛ ዘመን ደግሞ አዲስ እይታ ነው በማለት ከተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች ጋር በማቆራኝት በግዕዝ ቋንቋ አዲስ ዘፈን ተሰርቶበታል፡፡

4 comments:

  1. The Angry EthiopianApril 16, 2013 at 1:16 AM

    More info please ? where is the song ?

    ReplyDelete
  2. ኃጢአቱ የቱ ጋር ነው? በግእዝ መዘፈኑ ነው ወይስ መዘፈኑ? ቋንቋው መግባቢያ እንጅ ሌላ ምንድን ነው? ሲዘፈንበት፣ ሲሸለልበት፣ ሲፎከርበት፣ ሲሰደብበትና ሲሞገስበት የኖረ አይደለም? እኔ እንኳን ስንት የግእዝ ዘፈኖችን አውቃለሁ:: በጥቅሉ ደሞ "የማኅሌተ ገንቦ" ግጥሞችን አስታውሷቸው:: ቤተ ክርስቲያናችን ግን እንኳን ሰውን ወደ እርሷ የገባውን ቋንቋ ሳይቀር ትቀድሳለችና ለይታ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ትጠቀምበታለች:: ሌሎች ግን ምንም ቢያደርጉበት ለቋንቋው እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ካልጎላ በቀር ጥፋቱ አልታየኝም:: የዘገባው መንገድም ስህተት ይመስለኛል:: "እኛ ግዕዝን የምናውቀው" ብለው ማቅረብ የነበረብዎ አይመስለኝም:: በናንተ እውቀት ድምዳሜ ላይ መድረስ የለብንም:: ባስተያየት መልኩ ቢቀርብ ኖሮ አወያይና አስተማሪ አቀራረብ ይመስለኛል:: ምሉእ ዘገባ ለማድረግም በማን የትና ምን እንደሚመስልም ማቅረብ ነበረባችሁ:: ለኛ ለማድረስ መፍጠኑ መላክም ነው:: ሆኖም ግን ተሟልቶ ይቅረብ ብለን የምንመራው ዓይነት ዜና ባታቀርቡ እላለሁ:: አዘጋጆች ሆይ ደጀ ሰላም የዝምታ ጊዜዋን እስክታበቃ በቤተ ክህነት ጉዳይ ላይ የመረጃ የምትሰጠን አንድ ገጽ የናንተው ናትና ከልብ ሁኑና ሥሩ የሚል መልእክትም አለኝ::

    ReplyDelete
    Replies
    1. Could you please mention one Geez Zefen you proclaimed to have known from the past times? Thanks!

      Delete
  3. geez is one of language in the world but limited in e.ot.c spoken by only some church people , not greater not less from other langugaes using for prasing God and some selected kings, bishops etc. so what is the fault for using for zefen ?

    ReplyDelete