Tuesday, April 9, 2013

መምህር ምህረተአብ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለኤልያሳውያን የሰጠው መልስ(አንድ አድርገን መጋቢት 01 2005 ዓ.ም)፡- የኤልያሳውያን ጉዳይ ሁሉም ዝም ባለበት ሰዓት መምህር ምህረት አብ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ባሳለፍነው ሳምንት መጋቢት 25 2005 ዓ.ም ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቅሰን መጻፋችን ይታወቃል ፡፡ ይህን ትምህርት በቅርብ ሆነው መከታተል ላልቻሉ እህትና ወንድሞቻችን መልሱን ማድመጥ ይችሉ ዘንድ የትምህርቱን አድራሻ እንዲህ አስቀምጠንልዎታል፡፡ ትምህርቱን ይድምጡ ራስዎን ፤ ቤተሰብዎንና ቤተክርስቲያንን ከእንዲህ አይነቱ ትምህርት ነቅተው  ይጠብቁ ዘንድ መልዕክታችን ነው፡፡

7 comments:

 1. መልሱ በቂ ቢሆንም ያለቦታ የማይመጥኑ ምሳሌዎች ግን በዝተዋል::

  ReplyDelete
 2. sebek hoye resehen anetsa. neseha geba

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን
  ሰላም ለሁሉም።

  የመምህር ምህረተአብ ሃሳቡ ጥሩ ነው። ለመምህር ምህረተአብ ያሉኝ ጥቂት ምክሮች የሚከተሉት ናቸው።

  ፩ኛ - ትኩረት የሚያስፈልገው ነጥቦቹ ላይ ነው። ለምሳሌ እሁድ ይቅርና ቅዳሜን ብቻ ነው ሰንበት ብለን ማክበር ያለብን ያሉትን እሁድ ለምን እንደሆነ ማስረዳት። እንዲሁም መስቀል ምን እንደሆነ፣ አባቶቻችን ከመስቀል ውጭ እንደመስቀል የምንጠቀምበት ምልክት እንዳልስጡን ማስረዳት። እነዚህ ትምህርቶችን ማስተማር በመንገዳችን ላይ እንድንጸና ይመክሩናል።

  ፪ኛ - ሐሳዊ መሢሕ ትርጉሙ ምን እንደሆነ የቤተክርስቲያን ትምህርት አለ። የሌሎችን ምሳሌዎች ከመውሰድ የራሳችን የቤተክርስቲያናችን ትርጉም በቂ ነው። በሐሳዊ መሢሕ ተከታዮች በግንባራቸውና በቀኝ እጃቸው የሚጻፈው የአውሬው ቁጥር በዕብራይስጥ መርምያዋዖስ በግእዝ ደግሞ ፀራዊ የሚል ነው ::

  መርምያዋዖስ የሚለው ንባብ ሜም አርባ፣ ሬስ ሁለት መቶ፣ ሜም አርባ፣ ዮድ አሥር፣ ዋው ስድስት፣ ዖ ሰባ፣ ሳን ሦስት መቶ። ድምር ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት።

  ፀራዊ የሚለው ንባብ ፀ ስድስት መቶ ፣ ረ ስድስት፣ ወ ስልሳ። ድምር ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት።
  ይህ ትርጉም የሚያሳየን ነቢዩ ዳንኤልም በትንቢቱ አራተኛው አውሬ ብሎ እንደነገረን የእግዚአብሔር መልአክም እንደተረጎመለት ሐሳዊ መሢሕ ሰው ነው። አንድ ሰው ሳይሆን ብዙ ሰው የሚከተለው፡ አንድ ነገድ፣ አንድ ሃገር፣ በአንድ ዘመን እሱም በመጨረሻው ዘመን የሚመጣ፣ አንድ አስተሳሰብ እሱም እግዚአብሔርን የሚሳደብ አስተሳሰብ ወይም ፍልስፍና ያለው ነው። ይህም በዘመናችን ተከናውኗል። ገና ሐሳዊ መሢሕ አልተወለደም ማለት ትክክለኛ ትምህርት አይመስለኝም።

  የዘመናችን ሳይንስ የፈለቀው “ኢየሱስ ጌታ ነው “ ከሚሉ ምእራባውያን ነው። በአሁኑ ዘመን ሳይንስ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ፒ ኤች ዲ ትምህርት ድረስ የሚያስተምረው ነገር በሙሉ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ከኢቮሉሽን እስከ ቢግ ባንግ፣ ከፍልስፍና እስከ ሳይኮሎጂ ድረስ የሳይንስ ሥራው እግዚአብሔርን መንቀፍ ከሆነ ቆየ። የብዙዎቹ ጸረ ክርስቶስ የሆኑ የሳይንስ አስተሳሰቦች ምንጭም አይሁድ ነን የሚሉት ናቸው። ተመራቂዎቹም የሳይንስን ቆብ በግንባራቸው ላይ ይደፋሉ፣ ቀለበቱንም በቀኝ እጃቸው ያደርጋሉ። በግንባር የሚደፋውን እና በቀኝ እጅ የሚደረገውን ቅኔ ወርቁ ምን እንደሆነ ቅዱሳን እንደሚነግሩን ተስፋ አደርጋለሁ። ሌላው ደግሞ እሥራኤል ማለት ክርስቲያን ሆኖ ሳለ ፀረ ክርስቶስ አይሁድ ነን ባዮችን ሰብስበው (እንዲያውም ብዙዎቹ ክርስቲያን ከሆኑ በኋላ ክርስቶስን እንዲክዱ አድርገው) ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው “እነሆ እሥራኤል” ብለው ያቆሙም እነሱው ናቸው። ሦስት አመት ተኩል ማለት ደግሞ እንዲሁ የቤተክርስቲያን የሆነ ትርጉም ያስፈልገዋል።

  ፫ኛ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ሆኖ ልክ እንደ ፕሮቴስታንት አይሁድ ነን የሚሉትን “እሥራኢእል” ብሎ መጥራት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር አይደለም። ክርስቶስን መሳደብ ስለሚሆን መምህር ምህረተአብ አይሁድን አይሁድ ብሎ ቢጠራ የተሻለ ይመስለኛል።

  ምስጋና ለመድኃኔዓለም።
  ኃይለሚካኤል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. I always impressed by your comments. Why not give us a full sermon on this topic by yourself. You do not have to show us your face if you do not need to, just an audio is enough. I adore your comments more than the articles themselves. I grew up listening Megabi Hadis Haile Michael (ZeDebre Haymanot Mekane Eyesus) and I feel his voice in your comments. God bless!

   Delete
 4. ሰላም፥

  ተጨማሪ ለማድረግ በዳንኤል ፰፥፳፩ አውሬው የሚነሳው ክግሪክ ከሚጀምረው የምእራባውያን መንግሥት ነው እያለ የእግዚአብሔር መልአክ እየተረጎመው እንደገና ተመልሶ የሚነሳው ከመካከለኛው ምስራቅ ነው ማለት ተገቢ አይደለም። የእግዚአብሔርን መልአክ ትርጓሜ ወደ ጎን ማድረግ ይቻላልን? ግልጽ እኮ ነው ፥ የምእራባውያን የሆነ በክርስቶስ ስም የሚመጣ፣ ቅዱሳንን ሳይቀር የሚያስት የትኛው ነው? መልአኩም ዳንኤልን እንዲህ አለው፥ ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል። አለው። አሁን የፍጻሜው ዘመን ስለሆነ አውሬው ማን እንደሆነ እንኳን ለሌላ ለአውሬው ተከታዮች ለራሳቸው እንኳን ግልጽ እየሆነ መጥቷል።

  ምስጋና ለመድኃኔዓለም።
  ኃይለሚካኤል።

  ReplyDelete
 5. ቀጣይ ትምህርቱን ለማድመጥ ፣ የሚገኝበትን አድራሻ ካገኛችሁ ብትለጥፉልን መልካም ነው ፡፡
  አመሰግናለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 6. tiru bilewal Hayle Michael....melkam mikir.

  ReplyDelete