Wednesday, March 28, 2012

የመጨረሻው ..‹‹የአዋጅ ምህላ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስያን››

(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2004.)- ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላትን መንፈሳዊ እሴትና የማይናወጽ ሐይማኖት ይዛ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስትሸጋገር የቆየችው (1) በእግዚአብሔር ቸርነት (2) በቅዱሳን ምልጃ እና (3) በአባቶቻችን ቆራጥ ሐይማተኝነትና ራሳቸውን ለቤተክርስቲያን አሳልፈው ለመስጠት በወሰዱት አርምጃ ነው:: ታዲያ በብዙ መከራና ፈተና ቤተክርስቲያናችን እዚህ ዘመን ደርሳ በአሁኑ ወቅት በውስጥም ሆነ በውጭ በመደራጀትም ሆነ በተናጥል በግልጽም ሆነ በድብቅ እየደረሰባት ያለው ፈተና የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰንብቷል:: ምንም እንኳን ቤተክርስቲያን በአለት ላይ የተመሰረተችና የሲኦል ደጆች እንደማያናውጧት ብናምንም አሁን በላይዋ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሟን እየመጠጡ ያሉት አካላት የሚያደርሱት ጥፋት ቀላል አይሆንም፡፡ በርግጥ አጠፋናት አደስናት እያሉ የሚደሰቱ ሁሉ ዘመናቸው ሲደርስ እንደሚያልፉና መታሰቢያቸው እንደሚረሳ እናምናለን:: በእኛ ዘመን በእኛ አቅም የሚጠበቅብንን ማድረግ ግን መዘንጋት የለብንም:: በቀደምት አባቶቻችን ዘመን እንኳን በቤተክርስቲያኗ ይቅርና በሃገሪቷ ለየት ያለ ክስተት ረሃብ፤ ቸነፈር፤ ጦርነት ሲነሳ ቤተክርስቲያናችን አዋጅ አውጃ ጸሎት ምህላ ታደርግና በረከትን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ታሰጠን እንደ ነበር በእኛ ዘመን እንኳ የምናውቀው ታሪክ ነው::

አሁን ባለንበት ዘመን እንኳን ለሃገር ችግር ቤተክርስቲያን መከራ ላይ ስትወድቅ ምህላ ሊታወጅ ቀርቶ ገዳማት በእሳት እየተቃጠሉ ምዕመናን ያላቸውን የሌላቸውን ሰብስበው ለማጥፋት ሲረባረቡ የቤተክህነቱ ሰዎች የተነሳውን እሳት ‹‹ምን ማጋነን ያስፈልገዋል›› በማለት ያፌዛሉ:: ገዳሟ ሲታረስ ፤በእሳት ሲቃጠል ፤ልጆቿ በጥይት ሲደበደቡ፤ የቤተክርስቲያኗ ጠባቂዎች አውቀው ከመተኛት አልፈው የነቃውን ለማስተኛት እየሞከሩ ነው ከዚህ በላይ ሌላ ሊመጣ አይችልም:: ለነገሩማ የእምነት ደካሞች ሆንን እንጂ አናብስትን ያስገዛላቸው አምላክ ገዳማቸውን ከእሳት መጠበቅ አይሳነውም:: ዓለም በቃን፤ የላመ የጣመ ይቅርብን፤ ብለው ሁሉን ነገር ታግሰው ከከተማ ርቀው የተቀመጡትን መነኮሳት መታደግም እንደማያቅተው እናውቃለን:: በእኛ አመለካከት እንደዚሁ ዝም ብለን ከቀጠልን ማህተባችሁን በጥሱ መባላችን አይቀርም:: መፍትሄው ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መጮህ ነው:: አብዝቶ መጮህ ፤ሳያቋርጡ መጮህ፤ መልስ እስኪገኝ መጮህ ፤ሳይፈሩ መጮህ ፤ሳይታክቱ መጮህ:: ከላይ ያለውን አርዕስ ስታዩ ምህላ በአዋጅ ተይዟል ብላችሁ እንዳታስቡ ፤ ይህን ማድረግ መንግስት ህዝብን ማነሳሳት ብሎ ስለሚመለከተው ይህ ይሆናል ብላችሁ አታስቡ ቤተክርስትያኗ ምህላ ብታውጅ ችግሩን እንደ ችግር አደጋውን እንደ አደጋ ተቀብላዋለች ማለት ይሆናል አሁን ግን ቤተክህነቱም ሆነ አባ ጳውሎስ ችግሩን ቢውቁትም እንደ አደጋ ለመቀበል የፈሩት ነገር እንዳለ በግልጽ ይታያል ፡፡በዋልድባ አካባቢ የሚገኙት አስራ ስምንቱ አብያተ ክርስትያናት ላይ የማፍረስ ስራ ሲጀመር የዛኔም ምህላ የሚይዙ አይመስለንም ከመንግስት ተስማምተው አብያተክርስያናቱን በዶዘር እንደሚያርሷቸው በእኛ በኩል አንዳች ጥርጥር የለንም 20 የአካባቢው ነዋሪ ከተነሳ 18 አብያተ ክርስትያናት ብቻቸውን ይቀራሉ ስለዚ ያፈርሷቸው እና ቦታ ይቀይሩላቸዋል ቤተክርስትያኖቹ ካልፈረሱ ግድብ መስራት አዳጋች ይሆንባቸዋል ሸንኮራም ማብቀል አይችሉም የመንግስት ባለስልጣናትም በአንደበታቸው እንዳመኑት ከሲኖዶስ ጋር መስማማት ላይ ተደርሶ ነው ይህ የሚሆነው ብለውናል አቡነ ሺኖዳ መንግስትን ተቃውመው 3 ዓመት በግዞት አሁን የተቀበሩበት ገዳም እንደወረዱ ታሪካቸው ይነግረናል ፡፡( እኛ ግን አልታደልንም) ባይሆን 20 ዓመት በፊት የነበረውን የመጨረሻ የምህላ ጊዜ ዞር ብዬ ላስታውሳችሁ ብዬ በማሰብ የመጨረሻው ‹‹የአዋጅ ምህላ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስያን›› ብዬ ለፅሁፌ አርእስቱን ተጠቅሜዋለሁ፡፡ 

በወታደራዊው መንግስት መጨረሻ የስልጣን ቀናት ህዝቡ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቆ ነበር እያንዳንዱ ቀን ሊያስከትል የሚችለው ነገር ማንም እርግጠኛ ካለመሆኑ ጋር አንዱ ካንዱ ይሻላል ብሎ ሊመርጣቸው ከማይችል ከሁለት ኀይሎች ጋርም የተፋጠጠበት ወቅት ነበር ፡፡ በአንድ በኩል አለሁ አልሞትኩም እያለ የሚፎክረው ወታደራዊ መንግስት በሌላ በኩል ደግሞ ወደ ፊት እየገፋ የነበረው ተቃዋሚ ኃይል አካሄድ ብዙ ግልጽ ስላልነበረ የህዝቡን ጭንቅ ይበልጥ አብሶት ነበር፡፡ 

በዚህ ሰዓት ሕዝቡ በሀይማኖቱ እየተሰበሰበ ምህላ ጸሎት ጀመረ ፡፡ በየአብያተ ክርስትያናት ህዝብ እየተሰበሰበ አለቀሰ ተከዘ እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠየቀ ፡፡ ያንዣበበው የእልቂት ደመና ዞር እንዲል ተማጸነ ፡፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን ታላቅ የምህላ ጸሎት በይፋ ተነገረና ብዙ ህዝብና የቤተክህነት ባለ ስልጣኖች ተገኙ፡፡ በዚህ እለት አለቃ አያሌው ታምሩ በቦታ ተገኝተው እንዲያስተምሩ ተጋበዙ ያስተማሩትም ትምህር በአጭሩ ይህን ይመስላል፡፡ 
‹‹ በህዝብና በአገር ላይ ያንዣበበው የጥፋት ደመና ይገፈፍ ዘንድ ህዝቡ ወደ እግዚአብሔር እያቀረበ ያለው እግዚኦታ አስፈላጊ እና ተገቢም ነው፡፡ ግን በተለይ የዛሬን የጸሎት መርሀ ግብር ያስያዙት ባለስልጣናት የት አሉ? ዛሬ እንደ ነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት መውደቅ ነው የሚገባን ምክንያቱም የመጣው ፍርድ አበሳ እና ውድቀት ማንንም ከማንም ሳይለይ የሚያንገላታ በመሆኑ ነው፡፡ በአገራችን በጎ ነገር ይኖር ዘንድ ከዋና መሪ እስከ ዝቅተኛ ኑሮ ድረስ ያለው ሕዝብ ከልባዊ ጾምና ጸሎት ጋር በእግዚአብሔር ፊት ሊወድቅ ይገባል ›› በማለት ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት በብዙዎች እንደ ትንቢት የሚቆጥሩት ትምህርት ሰጥተዋል ፡፡ 


አሁንስ ቤተክርስትያን እና ገዳማት ላይ የተጋረጠው አደጋ ምህላ የሚያስቆም አይደለምን ? መስመራቸውን አይተናል ጉዟቸውን ተመልክተናል ከሰው መልስ ብናጣ እንዴት ወደ አምላካችን መጮህ ያቅተናል? ፓትርያርኩ ዝም ብለዋል ቤተክህነቱም ነገ ላይ የሚስጠይቀውን መግለጫ ሰጥቷል የሲኖዶስ አባቶች ድምጻቸው ምን ይሁን አላወቅንም መንግስት በሚዲያዎች ማስተባበሉን ተያይዞት ስራውን በመከላለከያ ሰራዊት ደጀንነት እያከናወነ ይገኛል፤ የገዳሙ አባቶችን አቤቱታ ከማቅረብ ወደ ኋላ አላሉም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲም ሙስሊሞችን ባስተናገደበት ረገድ እኛን ሊያስተናግደን አልቻለም የጉዳዩ ግለት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እየሄደ ነው ምዕመኑም አብዝቶ በስራቸው እያዘነ ነው ፤በአሜሪካ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ አብዛኛው ምዕመኑ ስለ ገዳሙ እያለቀሰ ነበር ሰዎቹ እዚች ቤተክርስትያን ላያ ያላቸው አላማ ምንድነው ? ግብና መዳረሻቸውስ ? በዚህ በችግር ጊዜ ምዕመኑ ምህላ ካልያዘ ከዚህ የሚብስ ነገር ከየት ይመጣል ? 

የሰሜን ጎንደር /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳመ ዋልድባ ችግር ከተሰማበት ዕለት አንሥቶ ጸሎተ እንዲያዝ ዐውጀው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ይኹንና ‹‹እንዴት ጸሎት ያውጃሉ፤ ዐመፅ ለመቀስቀስ ነው ወይ?›› በሚል በአንድ የዞኑ ባለሥልጣን በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ጸሎት እንዳላውጅ ማን ይከለክለኛል?›› ብለው መልሰዋል፡፡ ለምን ምህላ አወጃችሁም ተባልን እኮ ? ይገርማል ምህላ እኮ ህዝብ  ፤ ሀገር ፤ ቤተክርስትያናት አደጋ ላይ ሲወድቁ ከአምላክ መልስ ለማምጣት ህዝበ ክርስትያኑ አንድ ላይ ሆኖ እንባውን እያፈሰሰ የችግሩን ጊዜ አምላክ እንዲያሳልፈው የሚያደርገው የህብረት ጸሎት ነው ፡፡ አሁን ግን ይህንም አታደርጉም ተባልን አሁን በቤተክርስትያናችን የውስጥ ቀኖና እና ዶግማ ላይ እጃቸውን ማሳረፍ ተያይዘውታል ፡፡ በመሰረቱ ምህላውን ቢፈሩ አይገርምም መፍራትም ይገባቸዋል የህብረት ጸሎት ሀገር ያቀናል መንግስት ይነቅላል ከአምላክ መልስ ያመጣል ምህረትን ያወርዳል መጥፎ ጊዜን ያሳልፋል ክፉዎችን ያሳልፋል እረ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ የምህላን ጥቅም የምናውቀው እኛ 40 80 የስላሴ ልጅነትን ያገኝን ክርስትያኖች እንጂ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተጠመቁት አይደሉም ፡፡ ቤተክህነቱ ትክክለኛ የቤተክርስትያኒቷ ችግር ያለችበት ሁኔታ ፍንትው ብሎ ሳይታየው ቀርቶ አይደለም ነገር ግን የፍራቻ አጥርን ከቦ ይዞት እንጂ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ደርግ ሊወድቅ ሲል በሀገሪቱ ላይ የተደቀነውን አደጋ ምዕመኑ ምህላ ይዞ በነበረበት ጊዜ ላይ ‹‹ በህዝብና በአገር ላይ ያንዣበበው የጥፋት ደመና ይገፈፍ ዘንድ ህዝቡ ወደ እግዚአብሔር እያቀረበ ያለው እግዚኦታ አስፈላጊ እና ተገቢም ነው፡፡›› ብለዋል ፡፡ አሁን ግን ቤተክርስተያን ላይ ያጋረጠው የመፈራረስ አደጋ ከፓትርያርኩ ጀምሮ ቤተክህነቱ እና መንግስት በአንድ መስመር ቆመው እያየናቸው ነው ፤ ምዕመኑ ምህላ እንኳን እንዳያደርግ እየከለከሉት ይገኛሉ ታዲያ የእምነት ነጻነት አለ ተብሎ በሚነገርባት ኢትዮጵያ ምህላ አባቶች ሲያሲዙ በሹማምንቱ መታገዱ ይህን ምን ይሉታል ? ቤተክርስትያን ሄደን በህብረት ጸሎት ማድረግ ከተከለከልን የትስ ሄደን አቤት እንበል ? በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ስለ ዋልድባ ገዳም ብለው ጉዳዩ አሳስቧቸው ጥያቄያቸውን በህጋዊ መንገድ ሊያቀርቡ የወጡትን ምዕመናን ኢምባሲው ጆሮ ሊሰጣቸው እና ችግራቸውን ሊሰማቸው እንኳን አለመቻሉ በርካታ የእምነቱ ተከታይ የሆኑትንና ያልሆኑትን ሰዎች አስገርሟል፡፡ በኦሪት መጽሀፍ ‹‹ፈርዖንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደነደነ፥ ›› ኦሪት ዘጸአት 8 32 ተብሎ ተፅፏል ፡፡ አሁንም መንግስት ልቡን እንደ ፈርኦን በጥያቄዎቻችን ላይ እያደነደነው ይገኛል የአባቶችንም ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎታል ይህ ግን ይበጀዋል ብለን አናስብም  

ከ1983  በኋላ በርካታ ፈተናዎችን ቤተክርስትያኒቷ አሳልፋለች በማሳለፍም ላይ ትገኛለች ፤ በአዋጅ ግን ምህላ ሲያዝ አይቼ አላውቅም ፤ ምህላውንም በፖለቲካ አይን ማየት ጀመሩ መሰል ፤ ምህላው ቢደረግ መንግስት ብቻ ሳይሆን ቤተክህነቱም ጭምር ለራሱ የፈራ ይመስላል ፤ ለዚህ ነው ሰው ምህላ እንያዝ ፤ ለምንስ ስለ ፈተናችን ምህላ አናደርግም ? ፤ ብሎ ሲጠይቅ አይሆንም አርፈህ ተቀመጥ የሚባለው ፤ ያውቁታል እግዚአብሔር የማንንም እንባ መና እንደማያስቀር ፤ አንድ ቀን ግን እንባችን ጎርፍ ሆኖ ይዟቻ ይሄዳል አልጠራጠርም ፡፡ ምህላ እኮ ማለት በህብረት ጸሎት እናድርግ ማለት ነው ፤ ስለ ሐጥያታችን እናልቅስ እናንባ ማለት ነው ፤ ችግራችንን በተሰበረ ልብ አምላካችን ጋር እናቅርብ ማለት ነው ፤ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም ፡፡ የእኛ መሳሪያችን ጎራዴ እና ሰይፍ ወይም ዘመናዊ መሳሪያ አይደለም ፤የኛ መሳሪያችን የህብረት ፀሎት(ምህላ)፤ ፆም  ፤ ስግደት ፤ እና የመሳሰሉት መልካም ነገሮች ብቻ ናቸው ፡፡ ታዲያ ምኑ ያስፈራቸው ይመስላችኋል?፡፡ 


ኦሪት ዘዳግም 10 16 ‹‹እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።›› ይህን መልዕክት ለቤተክህነት ሰዎች እና ለመንግስት ባለስልጣናት እናስተላልፋለን እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም መሆኑን እወቁ ፡፡ ነገር ግን ይህን ሳትሰሙ ብትቀሩ መጽሐፈ ምሳሌ 291 እንዲህ ይላል ‹‹ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።›› የምታደርጉት ነገር የመጨረሻ መጀመሪያ እንዳይሆንም መጠንቀቅ መቻል አለባችሁ፡፡ 

ደርግ ስልጣኑ አፈር ሊበላ ሲቃረብ  ቤተክርስትያን ምህላ እንድታደርግ በደብዳቤ ቤተክህነቱን ጠይቆ ነበር ቤተክርስትያኒቷም ተቀብላ ምህላ አውጃ በየአብያተክርስትያናት እና በገዳሞች የሰው ደም እንዳይፈስ ሀገር ሰላም እንድትሆን ሀገሪቱ ላይ የሚመጣውን አደጋ አምላክ እንደ ንፋስ አንዲያሳልፈው በምህላ ከምዕመን ጋር በአንድነት ጸለ㝕ች አዲስ አበባም ብዙ እልቂት ሳይከሰት በለሆሳሳ ሁሉን ነገር አለፈ መንግስት ወረደ መንግስት ተተካ ፡፡ ዛሬ ገዳሞቻችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ከመንግስት መልስ ብናጣ በምህላ ወደ አምላካችን እንዳንጮህ ጸሎታችን እንዳይሰማ እቅፋት ሆናችሁብን ነገ ግን ለራሳችሁ ህልውና ቤተክርስትያኒቷ ምህላ እንድታደርግላችሁ የምትጠይቁበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል ማን ያውቃል ? ስልጣን መጀመሪያ እንዳለው መጨረሻም እንዳለው እወቁ፡፡ በተጨማሪ ወደ ሮሜ ሰዎች 13 ‹‹ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ 


21 comments:

  1. melkame eyeta newe hulachenem mehela beneyeze egiziabehere yesemanale

    ReplyDelete
  2. kalhiwot yasemalen!

    ReplyDelete
  3. በምድራዊ ገዢ በከለባት ማህል
    ሰሚ ያጣዉ እንባ ወዳንተ ይጮሃል
    በል ፍረድ ዝም አትበል ሁሉ ይቻልሃል፡፡

    ReplyDelete
  4. Write,,,,write ,,,,write,,,,, it is preach to all EOTC members but warning to "leaders" of Betekhinet and Ethiopian Government too.

    TESFACHIN BESEMAY NEWUNA MELKAM LEMADREG ATIFIRU !!!

    ReplyDelete
  5. Andidargen,
    We should stop hoping a solution from the Government or related “fathers”. The solution is with us. Let us start the prayer and see what will come. We may not be able to pray in group but we can do it individually. I have an idea, let us discuss the issue with our true fathers and ask them a list of prayer that is appropriate for the current problem. Then we will make the prayer available online. Whoever wants to be a part of the solution will participate on the prayer. We are in the middle of "ABIY TSOME" and this is a good time to pray. The whole next week can be a good time. So what shalll we do?
    Task # 1) (Andadirgen)
    Please post a list of prayers and a convenient time (One week prayer) ( ask the fathers)
    Task # 2) for all individual who wants to be a part of the solution
    We tried our best, to request the government to respect our monastery. They don’t want to hear our voice. This is the time to cry and ask our Almighty to hear our voice. What we will do is. Let us confesses our sins to our priests and prepare for the prayer. then we will devote and pray for a week. Believe me, prayer is more than a thousand words, more than a million times protest. Let us back to our hear and pray for a week.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Good idea. Please let's do like this suggestion

      Delete
  6. Endet senebetachihu
    behagerim kehager wuchi yalem Ethiopiawi hulu yemimeraw yemiyastebabrew kahin yehaymanot meri biyatam weqtu talaku abiy tsom silehone hulum krstian bebetu wust (kebetersebu gar)yemiyawkewin tselot endiyaderg mele'ekt bitastelalifu ena qen tewesino bijemer min yimeslachihual?

    ReplyDelete
  7. እግዚአብሔር፡በቸርነቱ፡ይጎብኘን!!!
    ወላዲተ፡አምላክ፡በምልጃሽ፡አትርሺን!
    ወገኖቼ፡ቤተ፡ክህነት፡ውስጥ፡ሰው፡አለ፡ብለን፡አንጠብቅ፡፡ቅዱስ፡ሲኖዶስም፡በስም፡ብቻ፡ነው፡ያለው፡፡ምህላ፡ለማድረግ፡ፈቃድ፡የማይሰጡን፡ከሆነ፡ወይም፡የማያውጁ፡ከሆነ፡መቼም፡ሌላ፡አማራጭ፡የሚጠፋ፡አይመስለኝም፡፡ጊዜ፡ተወስኖ፡በየቤታችን፡ሆነንም፡ማመልከት፡እንችላለን፡ማለት፡በግል፡ከምናደርገው፡ተጨማሪ፡ማለቴ፡ነው፡፡ሚዲያ፡በተስፋፋበት፡ዓለም፡አገር፡ውስጥም፡ሆነ፡ ውጪ፡ያለነው፡ምዕመን፡ጊዜው፡ተነግሮን፡እንደተቻለን፡ማልቀስ፡ማመልከት፡እንችላለን፡፡ይህን፡ከቤተ፡ክርስትያን፡ስርዓት፡ጋራ፡በማስተባበር፡ሚዲያዎች፡ብትተባበሩን፡መልካም፡ነው፡፡በየጦማሮች፡በፌስ፡ቡክና፡በመሳሰሉት፡የሰሙት፡ላልሰሙት፡ቢያስተላለፉ፡ጊዜ፡ወስነን፡ወደ፡ፈጣሪያችን፡ማልቀስ፡እንችላለን፡፡ከነነዌ፡እንማር!!!

    ReplyDelete
  8. Ethiopia, by the Grace of God, is abundantly rich in religion, culture, and ethnicity as well as natural resources. But because of our denial and abandonment, as Ethiopians, of our inherent commitment to the True Ethiopianness, we are enduring the consequences. We face problems of spiritual and physical poverty, social, economic, health crisis, and political strife to the extent of waging fratricidal wars...

    To overcome these man-made hardships and help Ethiopia reach full potential, we need first and foremost, complete individual and national, mental and spiritual revival and renewal, by transforming ourselves from within through genuine REPENTANCE that invigorates our wholeness and restores the integrity in each one of us so that we really be changed for the better and become True Ethiopians.

    http://www.selamforethiopia.com

    ReplyDelete
  9. enante bet yetemekerchew egnya betem temekralech! Lemen self ateterum?Mahber kidusan( Mahbere Evil) now you cross the line, it will be easy for all of us if you guys register as a political party, please Leave our church alone.

    ReplyDelete
  10. Kalehiwot Yasemaln. May the Lord abundantly bless you for this message! Aleka Ayalew’s message was really prophetic. We Ethiopians are in desperate need of Mihla now. What other weapon do we have? Mihla got our forefathers immediate mercy from the Lord and blessings in seasons. Both European colonial visitations of Ethiopia were defeated by Mihla alone. Maybe we haven't noticed, as Ethiopians we have been in the mire for too long. Maybe we haven't heard, as Ethiopians we are a byword, and all the world whispers we are incapable, backward, unable to provide for ourselves. They call us the starved. Babes rule over us. Every passerby takes a piece of ours. We can't drink from our own well. We can't eat from our own yard. Foreigners take it while we watch. Everything we have is taken away. Today, they want to take away our monasteries. If it is not taken away it is burning. When else is mihla with heartfelt lekso needed if it is not now?

    ReplyDelete
  11. andadirgen tiruu tsihuf newu...gin betekrstianachin chigir enaa fetenaa yegetemat ke mejemeria jemiro newuu enji bev1983 jemiro mebalu bistekakel lela tirgum yasetewal.betekirstiyanachin eko be derg endihum kezam befit balu nigistat hulu chigirin tekuakuma yasalefech nat. minim enkuan yahunu bibisim amlak kidusan degmo yiredanal.

    ReplyDelete
  12. ኦሪት ዘዳግም 10፤ 16 ‹‹እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።››

    ReplyDelete
  13. የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ ይላሉ አበው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰርተቶ እንዳይበላ ከድህነት እንዳይወጣ ለምን መከፋፈልንና ስንፍናን በስማ በለው ታራግባላቸሁ? ለመሆኑ የየትኛው ሀሃይማኖትና ፖለቲካ ፓርቲ ተከታይ ናችሁ? ድህነት ራሱ ኢትዮጵያዊያንን ለወዋጋት የቀጠራችሁ ወታደሮች ትመስላላችሁ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Wedaje ante bzmnu poltika nfase twsedhe haymanotihine yekadeki meselgn. lemehonu manewu enqebu manewu metadu? bbetemenegesitachu eneqebina metade linore yechelale, bebetecrstine endehe yelem hulume yeande akale yeteleyayu beletoch new. Ebakihe ayenehen geltehe temeleket, yebetecrstine tselot lebetemenegestim yeterfal tefatwam enedihu.

      Delete
    2. What do you mean by "yemitadu" and Yeenkibu. Do you mean EPRDF is Yemitadu? I think you are a chirstian b/c you read this blog but you are realy one of those who think "poletics first" and then... you know what such kind of person mean, a person who simply needs to eat( hodamilaku), every thing is related to his immidiate need, he ethier is full of those wrong propogandas of EPRDF or with some critical problem with religious concept. It is purly religius issue not poletics but in EPRDF's role everybody who don't accept what they have said and with different ideas is an opposer or enemy, tserelimat, ashebari... I feel sorry instead of leasoning and correcting giving a targa for genune people will not be a solution rather it creats many enemies and finally colaps. So please don't relate everything with poletics.

      Delete
    3. የኢትዮጵያ ህዝብ ሠራተኛ ነበረ እኮ። እናንተ ፖለቲከኞች ከመጣችሁ በኋላ ሥራም የለም፣ የሚበላም የለም። ማርና ወተት እንደውሃ የሚንቆረቆርበት፣ የእርሻው ውጤት ሁሉንም ያጠግብ የነበረበት ጊዜ የክርስቲያኖች ዘመን እንደነበረ አታውቅም? እናነተ ጥበብ የሌላችሁ የፖለቲካ ሰዎች መጥታችሁ ስልጣን ላይ ስትቆናጠጡ አይደለም እንዴ ኢትዮጵያ በሰው ዘንድ የተናቀችው? እናንተ አይደላችሁም ወይ ድህነትን እና መከፋፈልን ያመጣችሁት? እናንተ አይደላችሁም ወይ ሥራውን ለቻይና የምትሰጡት? ጥበብ ስለሌላችሁ አይደለም ወይ መሬቱን ለህንድ የምትሰጡት? የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያርስ አድርጋችሁ መሬቱን ለውጭ አገር ሰው ትሰጣላችሁ። እናንተ አይደላችሁም ወይ ኢትዮጵያን ያለ አሳ ማጥመጃ ባህር ያስቀራችኋት? ድህነት ማለት እናንተ አይደላችሁም ወይ? ወደፊት እድሜ ከሰጠህ የክርስትናን ጥበብ እና ልማት በእግዚአብሔር ቸርነት እናሳይሃለን። እናንተ ልማት የምትሉት ጥፋቱን እንደሆነ ያን ጊዜ ታውቃለህ።

      Delete
    4. Egziabher lehizbe christianu mels siset yane echin yalkatin(yepolitica party nachihu) tidegmataleh. Atirsa!

      Delete
  14. dengle hoy menw ahuns tewshen?

    ReplyDelete
  15. Our holey fathers can not pass through such kind of blessed revolutions due to two reasons
    1. The government strongly influenced them even not to pray about the country Ethiopia during Kidasse
    2. The are best in spirituality but can not manipulate things through mail, internet, ets.
    So, this is z only way to reach in solution. I am sure that things will be changed with in a very short period if we do that immediately on the coming Monday, hemamatu.
    Please, those of you who did your best to organize things, try to list down all the tasks in detail, in a very systematic way and lets do that. If there is also very informative message, Bizuayehu Walle
    please, display them and let us send that to our friends through their Mobil number b/c majority of them may not have an access to search things through internet. Today is Friday, let as finish things on today up to Sunday, and let as start our pray starting from Monday.
    I am sure that we can see tremendous changes until Ester.
    God be with us, God bless Ethiopia and its people.

    ReplyDelete
  16. እግዚኦ አምላክ ሆይ
    ምንነው ዝም አልክ?
    አባት ሆይ አሁንስ ዝምታ ወርቅ አይደለም
    .............
    በምድራዊ ገዢ ማቀብ ተደርጎባት
    ኢትዮጵያ ካንተ ስኳሩ በልጦባት
    እንዴት ዝም ትላለህ የእኛ አባት?፡፡
    ሰሚ ያጣዉ እንባ ወዳንተ ይጮሃል
    በል ፍረድ ዝም አትበል ሁሉ ይቻልሃል
    በል ፍረድ ዝም አትበል ሰዓቱ ደርሷል።

    ReplyDelete