Friday, March 23, 2012

የባቦጋያ መድሐኒአለም የቦታ ጉዳይ

(አንድ አድርገን መጋቢት 14 2004ዓ.ም)፡- ብዙ ሰው ቤተክርስትያን ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ በመገናኛ ብዙሀን አማካኝነት ካልሰማ በስተቀር የሚደረገውን ነገር ሁላ ምንም የማያውቅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ፤ ሁሌ ነገሮች ተሸርበውና ተከናውነው ሲያበቁ ነው ምዕመኑ መረጃ የሚደርሰው ፤ ይህ ደግሞ አሁን ቤተክርስትያ ያለችበትን የፈተና ወቅት ህዝቡ መረጃ እንዳይኖረው ፤ መብቱን በጊዜው እንዳይጠይቅ ፤ ለቤተክርስንም መፍትሄ እንዳያመጣ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ እናገኝዋለን፡፡

ከወራት በፊት ባቦጋያ አካባቢ የሚገኝውን የቤተክርስትያን ቦታ ፤ ከ10ሺህ ካሬ በላይ መሬት  ለተጨማሪ ሪዞርት ማስፋፊያ መሸጡን ፅፈን ነበር ፤ ይህን በተመለከተ ቤተክርስትያኗ እና የሪዞርቱ ባለቤት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ፍርድ ቤት ማምራታቸውን በጊዜው ጠቁመን ነበር ፤ ህዝብ ወክሏቸዉ ስለ ባቦጋያ መዲሀኒአለም ቤተክርስትያን መሬት ሲከታተሉ የነበሩት ግለሰቦች ሕዝብን ለአመፅ ቀስቅሳችኋል በሚል የአደአ ወረዳ አቃቤ ህግ በመሰረተባቸዉ ክስ ፍርድ ቤቱ 06/07/2004.

1. በአቶ ሰለሞንና / ደሱ ረቢ-እያንዳዳቸዉን 200ብር ቅጣት ሲጥልባቸዉ
3. መቶ አለቃ አበጀ እንዳፍቱና / ሲሳይ -በነፃ አሰናብቷል


13/07/2004. ስለ መሬቱ በነበራቸዉ የፍርድቤት ቀጠሮ ደግሞ የተከሳሾቹ አቶ ታዲዎስ ጌታቸዉና መኮንን ጉርሙ ጠበቃ ከሳሾቹ በሕዝብ በፍርድ ቤት ተወክለዉ ሳለ ከየትም የተሰባሰቡ ናቸዉ እንጅ ሕዝብ የወከላቸዉ ስላልሆነ መክሰስ አይችሉም በማለት ባቀረበዉ የተቃዉሞ ሐሳብ 20/07/2004 ከሳሾች የዉክልና መረጃቸዉን እንዲያቀርቡ ተቀጥረዋል፡፡

እኛም የመተኛት አዝማሚያ ይታይብናል ፤ ሁሉም ምእመን የቤተክርስትያን ጠበቃ መሆን አለበት ፤ ነገር ግን ሁሉንም ነገር መፍትሄ ለመስጠት ስንነሳ ብልሀት እና በእውቀት ካልሆነ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ፤   ስለቤተክርስትያን መቆምም ህዝብን መቀስቀስ ሆነ እንዴ ? ስለ ቤታችን መከራከራችን መብታችን ይመስለናል ፤ የቤተክርስትያኗ መሬት ስለሆነ መመለስ አለበት የሚል ነው ጥያቄያችን ፤ የአባቶቻችን ርስት አንሸጥም ባልን ህዝቡን አነሳሳችሁ ተባልን ፤ እንደ ዝቋላ አይነት እሳት ቢነሳ ህዝቡ ሆ ብሎ ማጥፋት ይችላል ፤ አይተናል ፤ እኛ እየከበደን ያለው የውስጥ ውስጥ ሴራውን ነው ፤ ይህ ቦታ ሲሸጥ የመንግስት እጅ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ሰዎችም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አላቸው ፤ እነዚህን እንዴት አውቀን ስራቸውን እናጋልጥ? ይህ ነገር ከባድ ነው ፤ የቦታው ባለቤት መድሐኒአለም ካልረዳን  የሚከብድ ይመስለናል፡፡ 

4 comments:

  1. please we must design the strategy to protect our church from internal and external enemies and please please don't fall easily hopeless :: those of you have knowledge (idea) regarding to the strategy please design with public as well as secretly to protect the church:: these strategy must be free from political ideology and ethnic agenda:: the people is ready if there is appropriate and true hero designer:: if we try some the God is with us

    ReplyDelete
  2. money has bought the mentality of our patriarich. the problem and the solution is he himself

    ReplyDelete
  3. I am so confused for so many issues of our church conflict resolutions. ባቦጋያ መድሐኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ጥምቀት ታቦት ሳይወጣ ነው ያለፈው። ምዕመኑ በሩላይ እያለቀሱ ያሳለፉት። This is true and it happen in 47 Km far from the capital. I am thinking one solution not only to this particular but also the coming ..... The Holy Synodose assign a council which may have a power for conflict resolution to protect our church and the properties all parts of the country. I know this is very silly and thrash idea but I believe that instead of being silent trying is better or someone will come more better idea than this. ይሄ ቀውስ ፓፓስ ከነካካው ግን ያው ‹‹ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ ›› የሚሆነው። እንደው ቢጨንቀኝ ነው ነገራች፤ ዝም ብሎ ማፈግፈግ ብቻ ሆነብኝ እና ነው። I have a strong believe God show us all these people grazing grass like King Nabokedenetsore. God has his own time for all unless they confence! እግዚአብሔር በዝች አገር ላይ የሆነ ነገር ማምጣቱ አይቀርም።መግሥትም እንዳበደ ውሻ ሁሉንም መነካካቱ በዝቶበታል። መንግሥት ሊወርዲ ሲል ከታቦት ይጣላል እንደሚሉ።
    Andadirgen God bless you! You will get your wage from our heaven father!
    ኢታይረነ ሙስናሀ ለሐገርትነ ኢትዮጵያ!
    አሜን!

    ReplyDelete
  4. Appreciate this post. Let me try it out.
    Feel free to surf my blog post - kasa

    ReplyDelete