Thursday, March 29, 2012

አመድ ሆኗል ብለን የተውነው ነገር ውስጡ ፍም አለመያዙን እርግጠኛ እንሁን

(አንድ አድርገን መጋቢት 20 2004 ዓ.ም)፡- ይህ የተሀድሶዎች ጉዳይ አንዳንዴ ትልቅ የመወያያ አርዕስ ይሆናል አንዳንዴ ደግሞ የሌለ እስኪመስል ድረስ ዝም ይላል፡፡ አሁን እያየን ያለነው ነገር ይህ ነው ፤ ቤተክርስትያንን ከእነዚህ ሰዎች አስተምህሮ ለመጠበቅ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል በመፅሄት ፤ በጋዜጣ በድምጽ እና በምስል ያስደገፉ በርካታ መረጃዎች ተለቀው ሰዎች ዘንድ ደርሰዋል ፤ አሁን ግን አልፎ አልፎ ይህን ችግር የተለያዩ ቦታዎች እንዳለ ፈፅሞም እንዳልጠፋ የሚያሳዩ ነገሮች እየተከሰቱ ነው ፤ ዋናዎቹ እና ፊት አውራሪዎቹ ከሳምንታት በፊት በቤተክሀነት አዳራሽ ጉባኤ ለማድረግ አስበው መከልከላቸውን ለመግለጽ ሞክረን ነበር ፤ ይህን ሲከለከሉ ሌላ አዳራሽ ከቤተክርስትያኒቷ ፍቃድ ውጪ ቤተክህነቱ ጉባኤውን ሳይፈቅድ ምዕመኑን አዳራሽ ሰብስበው ማካሄድ ችለው ነበር ፤


በጉባኤው ላይ አቶ በጋሻው ደሳለኝ ‹‹ለሱባኤ ገዳም ሄዷል› ተብሎ ጉባኤውን እንዳልተካፈለ መረጃ ደርሶናል  እኛ ግን ጥያቄ አለን ገዳም ያሉትን መነኮሳት ከገዳም ለማውጣት ካልሆነ በቀር ሌላ አላማ ይዞ ሱባኤ  ይገባል የሚል ግምት የለንም  ነገሩ እውነት ከሆነ እሱም ገዳም ከሄደ  የገቡትን ለማውጣት እንጂ ለሌላ ነገር እንደማይገባ እናውቃለን  ከወራት በፊት የደረሰን መረጃ እኛም አይተን ያረጋገጥነው ነገር አባቶችን ከገዳም የማውጣት ስራ ሲሰሩ ነበር  አንድ ሙስሊም ከወሎ አካባቢ የተነሳ ሰው ትምህርታችንን ተምሮ ገዳም ልግባ ካለ በኋላ ራቅ ያለ ገዳም ገባ ፤ በኋላ ብዙ ዓመት በጾም በጸሎት ሲተጉ የነበሩትን አባት የተሻለ ነገር እንዳለ በመምከር ከገዳም አውጥቶ ወደ ምስራቅ የሀገራችን ክፍል አዋሽን ተሸግሮ ይዟቸው ሊሄድ ችሏል  ቦታው ላይ ሲደርሱም ቤተክርስትያን እንዲቀጥሯቸው  የቤተክርስተያኒቷን ትምህርት እንደተማሩ አገልግሎቱን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ካስረዳ በኋላ እሱን አሰበ ተፈሪ ተሻግሮ ሂርና አካባቢ የሚገኝ አንድ ደብር ውስጥ ሊቀጥሩት ችለዋል፡፡  እሳቸውን ደግሞ ቦርደዴ ከሚገኝበት 20-30 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝው አዲስ የኪዳነምህረት ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ አድርገው መድበዋቸው ነበር  ሲጀመርም ሂርና የተመደበው ሰው ሙስሊም የሆነ ለጥፋት የተሰማራ ሰው በመሆኑ ጊዜው ሲደርስ ስራው ተደርሶበት  በሰበካ ጉባኤው ተባሮ ካበቃ በኋላ ጀለቢያውን ለብሶ አሰበ ተፈሪ አንዱ ሆቴል በፖሊስ መያዙን እናስታውሳለን  እኛን ከገዳም ወጡት አባት ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቦታው እንደሚያገለግሉ እንደነበር የሆነውን ሁላ ሰውየው ከተያዘ በኋላ ማስረዳት ችለው ነበር ፡፡ ታዲያ አሁን እየተደረገ ያለው ነገር እየገባን ይመስለኛል  ከተማ ሰው ቢያጡ የላመ የጣፈጠውን ይቅርብኝ ብሎ ገዳም የገባውን ሰው የማውጣት ስትራቴጂ ይዘው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ይህም ሰው ከዚህ የተለየ ነገር ይሰራል ብለን አናምንም፡፡


ሌላው ይህን ችግር ፈተናው ፈተና ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርገው ቤተክርስትያኒቷ በአዳራሽ መስበክ የከለከለች ቢሆንም ይህን የሚቆጣጠር ክፍል አለመኖሩ ጭምር ነው ፡፡ አመድ ሆኗል ብለን የተውነው ነገር ውስጡ እሳት አለመኖሩን እርግጠኛ መሆን መቻል አለብን ፤ ይህ በእንዲህ እያለ በቅርቡ ከወደ ደብረዘይት የተሰማው እየተደረገ ያለው ነገር ደግሞ አሁንም ፈተና መሆናቸውን ያሳየናል፡፡  

ደብረዘይት ከተማ ውስጥ ያሉ ስብከተ ወንጌል ሃላፊዎች ተሃድሶያውያኑን ሲጋብዙ ለምን ትጋብዛላችሁ? ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን መመሪያ ለምን አታከብሩም ? ሲባሉ  እከሌ እከሌ ተብሎ የደረሰን ደብዳቤ የለም፡፡ በደፈናው ተቆጣጠሩ ተባልን እንጂ እየሉ ይገኛሉ ፡፡  ለነገሩ ልባቸው እያወቀ ቢጋብዙም ለምዕመኑ ካላቸው አክብሮት ብቻ መልስ ሊሰጡ ይሞክራሉ፡፡ እናም  ቅዱስ ሲኖዶሱ አጉራ ዘለል ሰባኪያንና ዘማሪያን ብሎ ያገዳቸውን አካላት በስም ዝርዝር ለየሃገረ ስብከቱ ካተበተነ ተለይቶም ካልታወቀ ችግሩ የሚያቆም አይደለም ፡፡ እኛ የታየንን ችግር በየጊዜው ከመጻፍ ወደ ኋላ አንልም ፡፡ ለሁሉም የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የጻድቃን ሰማዕታት ተራዳዒነት አይለየን አሜን!!!

13 comments:

  1. tiru eyeta newe negem kene wediyame ayetegnum...seyetan yaneqelafale endea egna manqelafate yelebenem

    ReplyDelete
  2. ask higewot sebaki to bring letter from betekhnet

    ReplyDelete
  3. እውነት ነው….ውድ አንድ አድርገኖች…እንዚህ ቀሳጣውያን ውስጥ ለውስጥ እየተሾሎከለኩ ዓላማቸውን ለማስፈፀም ደፋ ቀና እያሉ ነው……አንድ ነገር ላካፍላችሁ…..ህገወጦቹ ለምሳሌ እንደ እነ ሀዋዝ፣ ዕዝራ፣ ዳግማዊ እና ወ.ዘተ በደብረ ሰላም ቅ/እስጢፋኖስ ቤ/ያን በተከታታይ ወቅት በዚሁ በያዝነው መጋቢት እንዲሁም ባለፉት ጥርና የካቲት ወራት ላይ በስብከተ ወንጌል እየተጋበዙ እየመጡ ሲዘምሩ ተመልክቼአለሁ፣፣ እናም ከባድ የሆነ ስጋት ፈጥረውብኛል…..እናም እባካችሁ ከአስፈላጊው አካላት/ከቤተክርስትያኑ አስተዳዳሪ፣ ከሰ/ትቤቱ እና ከደብሩ ቀናኢ አገልጋዮች / ጋር ተነጋግራችሁ ለመፍታት እንዲሁም የተጣራ መረጃ በመካነ ድራችሁ በመልቀቅ ህዝቡ እንዲዋጋ እንድታረጉ አሳስባለሁ…..

    ReplyDelete
  4. Can somebody say he/she love God while hating his/her brother ? it is not good to make religion politics.

    ReplyDelete
  5. Thanks for your information. I miss the Preaching service of Megabe Hadis Begashaw. Would you kindly tell me which church in Debrezeit he is going to preach and if possible the dates? i will definitely attend that....

    ReplyDelete
    Replies
    1. geta ande gize mene letayu metachu yeneguse slebse yelebese sewen woyis........ sewwn yemetay kehone anten lemesbek ene ebekalehu fetarin fleg kirostos hule gize Yetenakewen yanesal kirestena behiwot menor enji tiru tiru wengel bemesemat aydelem .begashawem bihone seleyikereta siyastemer neber .yikertan gene endemewared yemikoter hone min litimar tihedaleh egziabhere lebuna yisten amen

      Delete
    2. wondime/ehite ene eko yemihedew yegzabherin qal lemsimat newe. Atisatu wongel eko yegzabher kal newe...yegzabher kale demo hulu negerachin newe. Hulem linsema yigebal. Wongelin lemastemar demo tesga yasfelgal. Megabe Hadis Begashaw yemesbek tsegaw kalachew sewoch andu newe. Silezih yesun sibeket badamit ende hatiatgena atkutergn. Hatiyat yemibalut tilacha, budnetgnaet, adma, qinat,...yemsesaelut nachew enjii wongel mesmat aydelem. Zim bilen besew were animera...egziabher hilinan yeseten lemastewal newe...

      Delete
  6. በቅርቡ በባሕርዳር ከተማ የጠቅላይ ቤተ ክህንት የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ ሆኖ ተሸመውአዕመረ በጋሻው ችግር እንደሌለበት ስለተረጋገጠ ለወደፊቱ ተነጋግረን ልትጠሩት ትችላላችሁ እያለ ውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደነበረ እናውቃለን፡፡ አዕመረ በደብረ ማርቆስ ከተማ በመናፍቅነቱ የሚታወቅና ከስራት ጋር ብዙዎችን ወደ ኑፋቄው መስመር ያስገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡
    አባ ጳውሎስም መናፍቅነቱን ባረጋገጡ ማግስት ለሥራቸው አመቺ መሆኑን አረጋግጠው በሕገወጥ መንገድ ሾመውታል፡፡ ከገባ በኋላ በየሄደበት ሁሉ የተሰጠውን ስልጣን ካለ አግባብ በመጠቀም የሚያደርገውን ደባ ለወደፊቱ በመረጃ አስደግፎ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡
    አሁንም ቢሆን ምዕመናን ማወቅ ያለባቸው የሚሠጠው ትምህርት ምን ይዘት እንዳለውና ኦርቶዶክሳዊ ላሕይ የተላበሰ መሆን አለመሆኑን ነው፡፡ እርግጥ ከእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ ይታወቃል፡፡ ከሥራቸው ታውቋዋላችሁ ስለተባልን መጠንቀቅ ይጠበቅብናል፡፡
    የስብከተ ወንጌል መምሪያው ሰው አንደሌለው አውቀው ክፋታቸውን ሁሉ ለመትፋት ከፍተኛ ዝግት ላይ መሆናቸውን ግን ማወቅ የሁላችንም ድርሻ መሆን አለበት፡፡

    ReplyDelete
  7. The central issue should be the contents. It should be focused on what he teaches/preaches. You have to ask first whether he preaches Gospel or not and avail the power of salvation by Christ or not. This should be the center for your arguement about. Otherwise don't bother about who preaches for whome and how.

    ReplyDelete
  8. Man can only see the face(outward) but only God can see what is in the heart. I wonder how an orthodox christian can write some thing like the above. The writer seems to know what is inside Begashaw's heat, what if the writer is wrong. What if Begashaw went to the gedam to fast and pray and nothing else. Don't you think the writer should repent for writing this. My simple advise for my fellow orthodox christians is please let us not say any thing that we are not 100% sure. As Lord Jesus says on the bible" let your words be yes if yes and no if no, nothing else.

    ReplyDelete
  9. ewenet new.....eskahun demo yaletenekbachew tehadeso aweyanem alu for example megabit16 debre ziet kidane meheret bete kerstiyan werawi beal lay endetagelegel yeteterachiwa zemarit tebeye ZEBENAY alebabesua yebetekerestianen enbe yaletebek netela satelebes wede bete kerstian keter gibi west bekidasee seat gebeta lek le agelegelot seat sideres bicha be deberu sebekete wengel kefel tal bemadereg lemagelegel mokeralechi bezemarewam ye anditen netsu tehadesoawit mezemur bemanegoragor manenetuan "egna endi nen"bemil akuhan yemeselal angoragura weredalechi .yemigeremew demo mata betuaf seatem yehenenu alebabes bebetekerestiyanu keter gebi west medegemua new "lemen netelashin atelebeshim sitebal" tebela be and wetat beteteyekechibet weket "lehed ayedel ende" bemalet ZEBENAY tezebanalechii .benetelawem fanta ende "chiris browen"zefagnu kofeyawan aderega neber....yayuatem ande neger teze yalachewem altefum "EZAM YAGELEGELALU EZIM YAGELEGELALU" YALEW PROTESTANTU PASTER astawesewal. echin teneshiye yetehadeso kurachi yeteruatem besebeket wengelu taleka gebenet yemitawekut yedeberu asetedadari nachew.

    ReplyDelete
  10. SILE AYIMERENA BEGASHAWI ENDIHUM YAREDI YOHANS ,ASEGIDI SAHILE BEZIRZIRI NEGIORASCHIHULAHU YIHI SEWI MENAFIKI MHONUNI ATITERATERU,

    ReplyDelete
  11. የሆነው ሁሉ ሆኖ እንዳለ ግን የእግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ ነውና ስለ ክፋት ድርጊታቸው ሁሉ ልብ ይስጣቸው ማለት ተገቢ ነው ... የነርሱ ጠፍቶ መቅረትም ያሳዝናል አስተዋይ ልቡናን ለነርሱም ለኛም ያድለን

    ReplyDelete