Saturday, November 14, 2015

በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለማየት የታሰበ የመጀመሪያ ጉዞ(አንድ አድርገን ህዳር 4 2008 ዓ.ም)፡- ከድርቅ እና ከርሀብ ጋር የተቆራኝ ታሪካችን አሁንም በእኛው ዘመን ተከስቶ ማየት እጅግ ያሳዝናል ፤ ቀድሞ የነበሩት ሁለት ክፉ ጊዜያት በእኛ ዘመን ራሳቸውን ሊደግሙ በመንገድ ላይ ይገኛሉ ፤ የ66 እና የ77 ርሃብ ተብሎ በታሪክ የምናውቀው ጊዜ ራሱን ሊደግም እያኮበኮበ ይገኛል ፤ ከ15 ሚሊየን በላይ ወገን የርሃብ ደመና አደምኖበታል ፤ መንግሥት 8.2 ሚሊየን ሕዝብ አደጋ እንደተጋረጠበት እማኝነቱን ሰጥቷል ፤  አሁን እጅግ አስቸጋሪውን ነገር መንግሥት ‹‹ርሃቡን ከአቅሜ በላይ አይደለም›› በማለት በሚያስተላልፈው ዜና ብዙዎች ብዙ ረድኤት ሰጭዎችን እና በሀገር ውስጥ ያሉትን ሰዎች እያዘናጋ ይገኛል ፤ መርዳት የምንችልበት እውቀት ፤ ጉልበት እና ገንዘብ እያለን መንግሥት በርሃብ የተጎዱ ዜጎችን ራሴ እደርስላችኋለሁ ብሎ መነሳቱ ተጎጂዎቹ ዘንድ እርዳታ በሌላ እሳቤ እና መንገድ እንዳይደርስ አንቅፋት የሆነ ይመስለናል ፡፡ ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ አልጀዚራ እና ቢቢሲ ከመንግሥት ፍቃድ አግኝተው በተለያዩ ቦታዎች ላይ ደርሰው ያቀረቡት ዘገባ ዝናብ እጥረቱ ወደ ድርቅ ፤ ድርቁም ወደ ርሃብ መሸጋገሩን  ፤ እንስሳት በየቦታው በርሃብ ምክንያት እያለቁ መሆኑን ፤ ሰዎችም እየተጎዱ የሚበሉትና የሚጠጡት እስከማጣት እንደደረሱ አመላክተውናል፡፡ 


አሁን ትልቁ ጥያቄ በምን መንገድ የተጎዱ ዜጎች ጋር እንድረስ? የሚለው ነው  ፤ ከቀናት በፊት ከዚህ በፊት በግል ጋዜጦች ላይ የምናውቃቸው ሰዎች ተሰባስበው ለተጎዱ ወገኖች ዘንድ ለመድረስ የባንክ አካውንት ከፍተው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፤ ይህ አይነት አካሄድ ይበል የሚያስብል ነው ፤ ለሌሎችም በየአካባቢው ለሚገኙ ሰዎች መነሳሳት የሚፈጥር ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ 


‹‹አንድ አድርገን›› blog በቅርብ የምናውቃቸውን ሰዎች በማሰባሰብ አሁን የተከሰተውን ችግር ጥልቀት ለመረዳት እና ሕዝቡም እንዲውቀው ለማድረግ ያስችለን ዘንድ አምስት ሰዎችን ያካተተ ቡድን ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ለመሄድና ጉዳቱን ለመመልከት እቅድ የያዝን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ፤ የመጀመሪያው ጉዞ ከሳምንት በኋላ ከህዳር 11 - ሕዳር 19 ለስምንት ቀን ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጉዞ የምናደርግ  መሆኑን በየቦታው ያየነውን የታዘብነውን ፤ በድምጽና በምስል ይዘን የምንቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡  


ራሳችን ራሳችን እንድረስ ….      

Monday, November 9, 2015

ዛሬም በመተት ወይም ከጋኔን በመዛመድ ተአምራት የሚያደርግ ስለተገኘ ብቻ የእግዚአብሔር ነው ከማለት ልንታቀብ ይገባናል

ዲ/ን አባይነህ ካሴ
(አንድ አድርገን ጥቅምት 30 2008 ዓ.ም)፡-ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ጋኔንን በመዛመድ የማሳሳት እና የማምታት ድርጊት የሚፈጽሙ እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ሌላ ምስክር አያሻንምና እንደዚህ ያሉ ሰዎች ዛሬም በመኖራቸው ልንጠራጠር አይገባንም፡፡ ስልታቸውም ያው ተመሳሳይ እና ያልተለወጠ በመኾኑ እንግድነት አይሰማንም፡፡ ተመሳስሎ ማጭበርበር!

Sunday, November 8, 2015

ቅዱስ ሲኖዶስ ያለፈቃድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም በሚዲያ የሚያስተምሩትን በሕግ እጠይቃለሁ አለ

(አዲስ አድማስ ጥቅምት 27 2008ዓ.ም)፡- ቤተ ክርስቲያኒቱ በማታውቀው ሁኔታ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈቃድ ሳያገኙ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ትምህርታዊ ስብከት የሚያስተላልፉ፤ ዝማሬ የሚያሰሙ፤ ጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ ጋዜጦችና ልዩ ልዩ በራሪ  ወረቀቶችን የሚያሳትሙ በአገሪቱ ሕግ እንዲጠየቁ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፤ የሚመለከታቸው የሚዲያ አካላትም ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፤ ብሏል፡፡ 

Thursday, November 5, 2015

“ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል”

በጥበቡ በለጠ
(አንድ አድርገን ጥቅምት 20 2006 ዓ.ም) ከሰሞኑ የሐገራችን አጀንዳ ሆነው የከረሙት መምህር ግርማ ወንድሙ ናቸው። በተለያዩ ድረ-ገፆች እና የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ ስለ መታሠራቸውና ስለ መከሠሣቸው ጉዳይ የተለያዩ ፅሁፎች አስተያየቶች አቋሞች ሁሉ ሲንፀባረቁ ቆይተዋል። በርግጥ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ ስለሆነ ምንም ማለት ባይቻልም ስለ ኢትዮጵያ ሀገራችን የሀይማኖት እና የአማኝነት ጉዳይ እስኪ እንጨዋወት።

መንፈሣዊነት እና ሰይጣንን ማባረር ፡ መምህር ግርማ Vs ዳንኪረኛው ጥበቡ ወርቅዬ

በጥበቡ በለጠ 
  •  ጠያቂና አሳቢ አእምሮ ከሌለን ሰው የመባላችን ምስጢርም አጠራጣሪ ይሆናል።
  • የሰይጣን ማስወጫው ምንድን ነው? መስቀል? መቁጠሪያ? መዳፍ? ፀሎት? እምነት?
  • መምህር ግርማ ወንድሙ እና ጥበቡ ወርቅዬ ሰይጣን ሲያያቸው እንዲህ የሚርበተበትላቸው ከሆነ ለምንስ በጋራ ተቀናጅተው ይህን ሁሉ ህዝብ የሚያሰቃዩትን ሰይጣኖች አያስወጡልንም?
  •  የቅስና ማዕረግ ሲፈለግ የሚነሳ ፤ ሳይፈለግ የሚደበቅ ማዕረግ ነውን?(  መምህር ግርማ በአንድ ወቅት ስልጣነ ክህnት ሳይኖርዎት እንዴት ያጠምቃሉ? ተብለው ሲጠየቁ ‹‹አይ ደብቄው ነው እንጂ የቅስና ማዕረግ አለኝ ›› ብለው ቆባቸው አድርገው መምጣታቸው የምናስታውሰው ጉዳይ ነው፡፡)

‹‹መምህር›› ግርማ ተጨማሪ የተጠረጠሩበት ወንጀል ይፋ ሆነ

  •  ቤታቸው ላይ በተደረገው ብርበራ ስምንት ሲም ካርዶች ተገኙ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ከሲምካርዶቹ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች እየተጠበቁ ይገኛሉ
  •  ቤተክህነት አቶ ግርማ ሕገ ወጥ አጥማቂ መሆናቸውን የሚያስረዳ ማስረጃዎቿን ለአዲስ አበባ ፖሊስ አቅርባለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 2008 (ኤፍ..)

‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙ አዲስ የተጠረጠሩበት ወንጀል ይፋ ሆነ። ይህ የተጠረጠሩበት ወንጀል ሀሰተኛ ሰነድ መገልገል የሚል ነው ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

Wednesday, November 4, 2015

መምህር ግርማ ማናቸው? በቀድሞው ዳኛ ዘውዱ ታደሰ "

  •  መምህር ግርማ እውነት አጥማቂ ነውን ?
  • የመጀመርያ ሚስቱ በአሁን ሰአት ተለያይተው ሰው ቤት እንጀራ በመጋገር ነው የምትተዳደረው

(አንድ አድርገን ጥቅምት 23 2008 ዓ.ም)፡- እኔ መምህር የሚባለውን ሰው አቶ ነው የምለው ግርማን የማውቀው የቀድሞ ጦር ሰራዊት መቶ አለቃ ሆኖ በጡረተኝነት በመቂ ከተማ ነዋሪ እያለ ትዳርም የነበረውና 2 ልጆች እንዳሉትም አውቃለው።  አቶ ግርማን የት እና እንዴት አወኩት? እኔ የምስራቅ ሸዋ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኜ 1996 መቂ እኖር ነበር ፤ ከዛም ጋር ተያይዞ በቤተክርስቲያና ቅርብ ስለነበርኩ ከምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አብነ ጎርጎሪዬስ ጋር የቀረበ ግንኘነት ስለ ነበረኝ ፡፡ የዝዋይን ሀመረ ኖህ መንፈሳዊ ኮሎጅ ሰበካ ጉባኤ ሆኜ 3 አመት መርቻለው በዚህ ጊዜ አቶ ግርማ የዘበኝነት (የጥበቃ ስራ ) ማስታወቂያ ስናወጣ ወታደር ስለሆነ ተፈትኖ አልፎ በእኔ ፊርማና ማህተም ቀጥሬዋለው፡፡

Monday, November 2, 2015

ሲኖዶሱ በዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ከመንግስት ጎን በመሆን ለመደገፍ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 2008 (ኤፍ..) የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ከመንግስት ጎን በመሆን ለመደገፍ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ። የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ 11 ቀናት ተካሂዶ ዛሬ የተጠናቀቀውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አጠቃላይ መግለጫ ሰጥተዋል።