Thursday, July 5, 2012

“ማህበረ ቅዱሳን አክራሪና ጽንፈኛ ማህበር ነው” በማለት በጦላይ ጦር አካዳሚ ለአመራሮች ስልጠና ተሰጠ(አንድ አድርገን ሰኔ 27 2004 ዓ.ም)፡- የመንግስት አካሄድ ከቀን ቀን እየከፋ እየመጣ ነው ፤ ነገሩ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የምንሰማው እና የምናየው ነገር ጥሩ አይደለም ፤ በየዓመቱ ከሰኔ እስከ መስከረም አጋማሽ በቀበሌ ፤ በክፍለ ከተማ ፤ በክልል በወረዳ ደረጃ ያሉ የኢህአዴግ አባላት ጦላይ ጦር ማሰልጠኛ ካምፕ  በመላክ ፖለቲካዊ ትምህርት እንደሚማሩ ይታወቃል ፤ ሀገሪቱ በተለያዩ ሀገራት ሰላም ማስከበር ብላ የምትልካቸው ከወታደር አንስቶ እስከ ጀኔራል ድረስ ያሉ ሰዎች ጦላይ ሳይደርሱ የፖለቲካ መርፌ ሳይወጉ ደቡብ ሱዳንም ሆነ ቡሩንዲ መሄድ አይቻልም ፤ ለተራ ወታደር ከሶስት እስከ ስድስት ወር የሚደርስ በተለያዩ ነገሮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሲሰጥ በአመራር ደረጃ ያሉት ደግሞ እስከ ሁለት ወር የሚያቆይ ስልጠና እንደሚወስዱ ይታወቃል ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ከ800 በላይ የኦህዴድ አባላትን ወደ አዲስ አበባ በማምጣት የተለያዩ ፖለቲካዊ የስልጣን ተዋረድ ላይ ያስቀመጣቸው ኢህአዴግ ለሁለት ወር ያህል ጦላይ ማሰልጠኛ ሄደው በቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ ሲስተም  አማካኝነት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የተለያዩ ሚንስትር ዴታዎች አማካኝነት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ለሁሉም አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በኪራይ ቤቶች የሚገኙ ቤቶችን  ያለምንም ክፍያ እንደተሰጣቸው  ይታወቃል ፤ ኪራይ ቤት ለታጣላቸው ከተማዋ ውስጥ ያሉትን  ኮንዶሚኒየም ቤቶች መርጠው አባል እስከሆኑ ድረስ እንዲኖሩበት ተሰቷቸው ፤ በአሁኑም ሰዓት ድርጅቱን በማገልገል በገጸበረከት በተበረከተላቸው ቤቶች ውስጥ ኑሯቸውን እየኖሩ ይገኛሉ ፤ አሁን እኛን ይህ ጉዳይ ለመጻፍ ሳይሆን አነሳሳችን ጦላይ የጦር አካዳሚ ምን አይነት ስልጠና እንደሚሰጥ ? ፤ ምን አይነት አመራሮች ወደ ቦታ ሄደው እንደሚሰለጥኑ ?  ለምን አላማ እንደሚታጩ ? ቦታው ያለውን ገጽታ ለናንተው ለማስገንዘብ ያህል  ነው፡፡


በአሁኑ ሰዓት ጦላይ ጦር አካዳሚ ከቀበሌ አንስቶ እስከ ከተማ መስተዳድር ኃላፊዎች  ፤በክልላዊ መንግስት ደግሞ ከታችኛው ከወረዳ የስልጣን እርከን አንስቶ እስከ ክልላዊ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት የሚገኙ የኢህአዴግ አባላትን  በመመልመል ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ ፤ የትግራይ ፤ የአማራ ፤ የደቡብ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስቶች የኢህአዴግ አባላት ገብተው የተማሩት ነገርና የተሰጣቸው መመሪያ ከዚህ በፊት በየዓመቱ ከሚሰለጥኑት ስልጠና የተለየ መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያስረዳሉ ፤ በስልጠናው ላይ ሰፊውን ጊዜ የወሰደው እና ራሳቸው ቋጥረውት አልፈታ ያላቸው ጉዳይ ቢኖር እነሱ እንደሚሉት የ”አክራሪነትና የጽንፈኝነት” አጀንዳ ነው ፤ በስልጠናው ላይ  ማህበረ ቅዱሳን የኦርቶዶክስ አክራሪ ማህበር እንደሆነ ፤ አመራሮቹ በያሉበት ቦታ ላይ ወደ ስራ ሲመለሱ አካሄዱን እንዲከታተሉትና እንዲዋጉት ፤ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ በየደረጃ ያሉ አመራሮች እርምጃ እንዲወስዱበት ፤ ማህበሩ ጽንፈኛ አቋም እንዳለው ህገመንግስታዊ የእመነት ነጻነቶችን እንደሚጋፋ  ፤ ለሀገር አስጊ የሆነ ማህበር እንደሆነ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ አጀንዳዎችን በማንሳት  አስረግጠው  ለኢህአዴግ አመራር ስልጠና ሰጥተዋል ፤ ይህ መረጃ የደረሰን በስልጠናው ላይ ከተካፈሉ በአካል ከምናውቃቸው አመራሮች  አማካኝነት ነው ፤  ይህ በስልጠና ደረጃ የተደረገ ተግባር መሆኑ ለየት ያደርገዋል ፤ ሌላ ሌላውን ትተነዋል፡፡

ከሳምንት በፊት “አዲስ ራእይ” ላይ ያለውን ሀሳብ ማስረዳት እንደሞከርነው መንግስት ግቡን ለመምታት ያመቸው ዘንድ በህዝቡ መሃል ይህን ጉዳይ ለማስረጽ እና ጊዜው ሲደርስ እርምጃ ሲወስድ ጠያቂ አካል እንዳይኖር ለማድረግ በኢቲቪ አማካኝነት የተሰራውን ፊልም አስመልክቶናል ፤ የ10 ሰዓት ቃለ መጠይቅ የ1፡30 ፊልም ወጥቶታል ፤ አዲስ ራእይ መጽሄትን መሰረት አድርጎ ቀጭን መመሪያ በመስጠት በኢቲቪ ጋዜጠኞች የተሰራው ፊልም  ከአዲስ ራእይ መጽሄት ቃል በቃል ከአንድ አንቀጽ በላይ በማንበብ ለፊልሙ እንደ ግብአት ተጠቅመውበታል ፤ (የተሰራውን ፊልም ጋዜጠኛው ያነበበውን የአዲስ ራእይ አንቀጽ ከቀናት በኋላ አነጻጽረን እናቀርብሎታለን)፡፡  

ስለዚህ ይህን ስራ እየተሰራ ያለው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስቶ እስከ ታችኛው አመራር ድረስ የእዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ መሆኑን እነዚህ ነጥቦች አስረጅ ናቸው ፤ የሚቀጥለው እርምጃው ህዝቡን እስከ ታች ድረስ ወርዶ ማወያየት ይሆናል ፤ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኝት ያስችለው ዘንድ በስትራቴጂያዊ አካሄድ ስብሰባዎች ያካሄዳሉ ፤ እስከ አሁን ድረስ ህዝቡን ያሳተፈ ሳይሆን የኢህአዴግ አባላት የጠራ አቋም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲይዙ ስብሰባዎችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ አድርገዋል ፤ ቀጥሎም በእስልምናም ይሁን መልስ ተደርገው በኦርቶዶክሳዊያን የተዘጋጁ መጽሃፍቶችና ሲዲዎች ላይ ያተኩራል የሚል ወሬም ደርሶናል ፤ እያለ እያለ ግቡን እስኪመታ ድረስ የጀመረውን መንገድ ይቀጥላል ፡፡

የመንግስትን አካሄድ በመመልከት ከዚህ በፊት በንዝህላልነት ከቆምንባቸው ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ የወደፊት የሚመጣውን ነገር ግምት ውስጥ በማስገባት ሁኔታዎችን ልንከታተላቸው ይገባናል ፤ አሁንም የተሰራውን ፊልም በደንብ ማህበረሰቡ እንዲመለከተው “በተመልካች ጥያቄ” በማለት ለቀጣይ ቅዳሜ ፊልሙን ደግመው ለማቅረብ ኢቲቪ ፕሮግራም ይዞልናል ፤ ህዝቡ የሰጠው አስተያየት አሁንም እየሰጠ ያለው ይቅርታ የሚያስጠይቅ ሆኖ ሳለ በህዝብ አስተያየት ብለው ፕሮግራሙን ለመድገም ማስታወቂያ እያስነገሩ ይገኛሉ ፤ የትኛው ህዝብ ነው ይደገም ያለው ?
የአሁኑን የጦላይ ስልጠናን ውጤት አሁን ላይ ላንመለከተው እንችላለን ከወራት በኋላ ግን ስለቤተክርስትያን ማንኛውም ምዕመን ጥያቄ ሲያነሳ የዛኔ ጦላይ የተረገዘው የሚወለድበት ጊዜ ይሆናል ፤  እንዴት ይህ ጉዳይ ከምን ተነስቶ እዚህ ደረጃ ደረሰ ብለው ሃሳብ አይግባዎት ፤ ነገ የሚደረግን ህገ-ወጥ ተግባርና የእጅ አዙር ተጽህኖን በማሰብ ራስዎን ለዚያ ጊዜ ያዘጋጁ ፤ ያለፍንበትን ያለንበትንና የምንሄድበትን መንገድ እናስተውል ፤ በግለሰብ ደረጃ አቋም ይኑረን ፡፡ ‹‹ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 ፤17 ይላል ፡፡ቸር ሰንብቱ…..

35 comments:

 1. Ayzoachihu. Egziabherin yizo mefirat yelem. Amilak yabertan. Yabertachihu.

  ReplyDelete
 2. It seems good decision. sorry to miss you! God only knows about the coming time!

  ReplyDelete
 3. letelayune endayehone betam enaznalen

  ReplyDelete
 4. ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 ፤17....እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 5. MK Gudih Fela!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. MK men gud alebet? mastewalen ersu getachen medhanitachen yesteh

   Delete
  2. endefelek tehadiso menzat kelekelh aydel, minm gud yelem yesraeln ginb yemiyaferes amlak enji yemiyasdengit amlak alyaznim,

   Delete
  3. no, ክርስትና በፈተና የተሞላች ናት ነገር ግን በእ/ር ሀይል ሁሉም ይከሽፋል!!!1

   Delete
  4. Tew Yihin yahil des ayblih. Egziabher sayfekid minim yemihon neger yelem.

   Delete
 6. አልገባኘም ይሄ ነገር ስለ ሃይማኖት ነው ፖለቲካ ነው ተስልፈን መንግስትን አንጣል ከሆነ ለምን መሳርያ አታስታትቁንም ም

  ReplyDelete
  Replies
  1. mengistachin menekosatu yepoletica alama alachew ale ante/anchi demo metshaf kidusum politica new eyalk/eyalsh new??.

   Delete
 7. ወያኔዎች የአውሬው (666) ተከታዮች መሆናቸውን እወቁ :: ስለዚህ የሚያከናውኑት ሁሉ ከሚከተሉት የአጽራረ -ኃይማኖት ዕምነታቸው የመነጨ ነው ::

  ReplyDelete
 8. EGZIABHERE Yabertachu Andadrgen

  "" INFORMATION IS POWERFUL THAN A WEAPON""

  ነገ የሚደረግን ህገ-ወጥ ተግባርና የእጅ አዙር ተጽህኖን በማሰብ ራስዎን ለዚያ ጊዜ ያዘጋጁ ፤ ያለፍንበትን ያለንበትንና የምንሄድበትን መንገድ እናስተውል ፤ በግለሰብ ደረጃ አቋም ይኑረን ፡፡ ‹‹ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 ፤17 ይላል ፡፡

  ReplyDelete
 9. ወንድሜ MK ጉድህ ፈላ ያልከው በታም ተመቸህኝ ለካንስ እነሱ ብቻ ናቸው ለቤተክርስቲያን የምያስቡት የኮነንካቸው መስሎህ ተጋድሎዋቸውን መሰከርክላቸው። አንዳንደም እውነት ማውራት ትሩ ነው ይልመድብህ የምትመሰገን ነህ።

  ReplyDelete
 10. “ዱባ ምረር ምረር እንደቅል ምረር
  በየዋህነትህ ስትቀቀል እንዳትኖር፡፡”

  ReplyDelete
 11. ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 ፤17....እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 12. ባናጣችሁ ጥሩ ነው:: ካቅም በላይ ከሆነ ደግሞ እግዚኣብሄር የሚያደርገውን እንጠብቃለን:: እኛ የሚጠበቅብንን ካደረግን እግዚአብሄር ቤተክርስቲያናችን "የሲኦል ደጆች ኣይችሏትም" ብሏልና እስከ እለተ ምጽኣት መኖሯ ግድ ነው::

  ለኣንባብያን
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.proxfree.com ወይም www.sslbrowser.com የሚሉትን ሳይቶች በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ወስብሀት ለእግዚኣብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር::

  ReplyDelete
 13. it is not new things. they discuss in different time at different place. but mk still .... this may give 4 mk strengh more. God bless them!!!!!!!

  ReplyDelete
 14. Woy kedimo Melse Yimotina negru hulu yabekal(Aba Paulosm Kejerbachin yiwordu yihonal)

  ReplyDelete
 15. Kezih Yebelete Gud Yelem!Letekit gizie Abren Ensekayalen.Atifiru!Enisebaseb.

  ReplyDelete
 16. ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.proxfree.com ወይም www.sslbrowser.com የሚሉትን ሳይቶች በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ወስብሀት ለእግዚኣብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር::
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.proxfree.com ወይም www.sslbrowser.com የሚሉትን ሳይቶች በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ወስብሀት ለእግዚኣብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር::
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.proxfree.com ወይም www.sslbrowser.com የሚሉትን ሳይቶች በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ወስብሀት ለእግዚኣብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yes we believe the power of GOD.He will stand at side of innocent.But we should do our part. They are not simple enemy.They are working without rest to fulfill their agenda [to kill the cantory and disintegrity peoples]
   GOD bless us

   Delete
 17. መረጃ ማለት እንዲህ ነው፤ ነገር ከመሆኑ በፊት ቀድሞ ማሳወቅ እኛም ነቅተን አንከታተላቸዋለን፡፡ ማኅበሩን ለሕዝብ አስጊ አሉት እራሳቸው ለራሳቸዉ የሚያሰጋቸው መስሎ ስለታያቸው፡፡

  ReplyDelete
 18. ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.openbanana.com በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.openbanana.com በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.openbanana.com በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.openbanana.com በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ
  ደጀ ሰላምን ለማንበብ www.openbanana.com በመጠቀም የተዘጉ(የታገዱ )ገጾችን በመክፈት ማንበብ ይችላሉ

  ReplyDelete
 19. MK gudih fela sayhon tehadiso gudih fela new yefrd ken derese.Amlakachin yewnet amlak new aytalelm.

  ReplyDelete
 20. kirstina yale fetena alede?

  ReplyDelete
 21. Meles is sick. Waldiba Saints should forgive and pray for him . Ofcourse he has to repent for he has touched what must not be touched. He is a guy who tochued what the communist Derg did not do. If he is wisdomful, he has to repent and automatically stop the encroachment of the monastry. This may help save him self from the everending hell fire.

  ReplyDelete
 22. Egziabher yasiben.

  ReplyDelete
 23. http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2012/07/tplf-anti-Muslim-campaign-analysis.pdf
  endate new yeha neger " የክርስትና (በተሇይም ፕሮቴስታንት) የበሊይነት የነገሰባት ኢትዮጵያን
  መፍጠር ይፈሌጋሌ " yemibalew neger men yahele ewnate new?

  ReplyDelete
 24. Please andadirgen, try sending us your reports/articles through an email. it is very important.

  ReplyDelete
 25. Egizeabeher Ethiopianena hizebochowan yetebekee

  ReplyDelete
 26. Ebakachhu yetehadisowechn sera kmagalet atboznu. Betkrstiyan wust enddamotra ttabqew new na yalut.

  ReplyDelete
 27. If you wish for to increase your experience only keep visiting this web page and be updated with the latest information posted here.
  Feel free to surf my weblog ; GFI Norte

  ReplyDelete