Wednesday, July 11, 2012

ኢቲቪ ሁለተኛውን አናዳጅ ፊልም ሊሰራ ነው(አንድ አድርገን ሐምሌ 4 ፤ 2004 ዓ.ም) ፡- የዛሬ ሳምንት ግድም “ብዙ ሃይማኖት አንዲት ሃገር” በሚል ርእስ ዶክመንተሪ ፊልም በኢቲቪ ባለሙያዎች ተሰርቶ ለህዝብ መቅረቡ ይታወቃል ፤ ሆኖም እስከ አሁን ድረስ ተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች እና በሃገሪቱ ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦችን እንደተመለከትነው አንድም ኢቲቪን ደግፎ “ጎሽ” ያለው አለመኖሩ የስራውን ዝቅጠት እንድንመለከት አድርጎናል ፤ ይህ ፊልም ለማን እንደተዘጋጀ ግራ የገባቸው በርካታ ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች አጋጥመውናል ፤ ባለፈው ሳምንት የወጣው የሙስሊም ጋዜጣ ላይ እንደተመለከትነው ሙስሊም ማህበረሰብ በዚህ ፊልም ክፉኛ ማዘኑን አስነብቦናል ፤ ባሳለፍነው አርብም ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ መመልከት ችለናል ፤ በኦርቶዶክስ አማኙ ዘንድም ሁኔታው በጣም ግራ እንዳጋባቸው ብዙዎች ሲናገሩ አስተውለናል ፤ ከ33 ሚሊየን በላይ የኦርቶዶክስ አማኞች ከ25 ሚሊየን በላይ ሙስሊም ማህበረሰቦች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ በኢቲቪ የቀረበው ፊልም ላይ ሁለቱም ወገኖች ቅሬታ ካላቸው እውን ይህ ፊልም ምንን ታሳቢ አድርጎ እና ለማን እንደተዘጋጀ እስከ አሁን ግልጽ አይደለም ፡፡


በጣም ትልቅ የታሪክ ስህተት የተሰራበት ይህ ፊልም በኢቲቪ ጓዳ ከቀናት በፊት መገምገም ችሎ ነበር ፤ በግምገማ ላይ ከውስጥ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የታሰበው እና የተሰራው ስራ አራምባ እና ቆቦ እንደሆኑ ከህዝቡ የደረሳቸው የቁጣ መልእክቶች አመላክቷቸዋል ፤ ለዚህም ስህተት ይህን ፕሮግራም ያዘጋጁት ሰዎች እንደተቀየሩ እና በሌሎች ባለሙያዎች የተሻለ ይዘት ያለው የባለፈውን ስህተት ሊያርም የሚችል ዶክመንተሪ እንዲያዘጋጂ ቀጣይ የቤት ስራ ተሰቷቸዋል ፤ የፕሮግራሙን ይዘትን ሲደርስ የምትመለከቱት ይሆናል ፤ በስብሰባው ላይ ከተነሱት ሃሳቦች ውስጥ የተሰራው ስራ ምን ያህል የታሰበለትን አላማ አሳክቷል ? ምን ያህልስ መልዕክት ማስተላለፍ ችሏል?  የማንም እምነት መጤ ቢሆን ለኛ ትርፉ ምንድነው  ? ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ብትባል ወይንም ባትባል ምን የሚያመጣው ችግር አለ ?  ይህ ፊልም የሃሳብ ልዩነቱን ለምን ሊያሰፋው ቻለ ? የተሰራው ስራ ያለውን ችግር ከማረጋጋት እና ከማባባስ ረገድ ያለውን ከህዝብ ግብረ መልስ ተነስቶ መገምገም የሚሉት ይገኙበታል ፤

እውነቱን ለመናገር ይህን ዘጋቢ ፊልም ተመልክቶ ውስጡ የረካ ሰው አለ ብሎ ለመናገር አያስደፍርም ፤ ሁሉም ያዘነበት ስራ መሆኑን ለማወቅ የኢቲቪ 982 ስልክ ተቀባይ ሆኖ በቦታ ላይ መቀመጥ ብቻ በቂ ነበር ፤ መንግስት የራሱን ጥቅም ለማስጠቅ እና የእጅ አዙር አላማውን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ለማሳካት የሄደው መንገድ ለራሱ ትምህርት ሆኖት አልፏል ፤ ለዘመናት በአንጻራዊ ሰላም ሲኖር የነበረውን ማህበረሰብ አንዱ በአንዱ ላይ ሌላ እይታ እንዲኖረው ማድረግ ለማንም የሚበጅ አካሄድ አይደለም ፤ እኛ ለዘመናት እንተዋወቃለን ፤ የሰውን ታሪክ በቃለ-መጠይቅ ለመናድ የታሰበውን የአላዋቂ አካሄድን እንቃወማለን ፤ “ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” እንዳይሆን ለስራችሁ ተጠንቀቁ ፤ ታሪካችን ታሪካቸው ነው ፤ ታሪካቸው ታሪካችን ነው ፤ ሁለቱ አንድ ሲሆን ታሪካችን  የኢትዮጵያ ታሪክ ይሆናል ፤ በበርካታ ቦታዎች ላይ መልካም ተሞክሮዎችን አስመልክታችሁናል ፤ ይህን የመሰለ ተግባር በማጎልበት የተሻለ አገልግሎት ለማህበረሰቡ የሚፈጠርበትን መንገድ ማመቻቸቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ እነዚህን አካላት ለእናንተ የፊልም ግብአት ስትሉ ብቻ መጠቀማችሁ ተገቢ ነው አንልም፡፡

አሁንም ያለውን ሁኔታ እንዲያረጋጋ ሌላ ተጨማሪ ፊልም እንዲያዘጋጅ የተሰጠው ቡድን የክርስትያኑን እና የሙስሊሙን ስረ መሰረት ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል ፤ የኦርቶዶክሳውያን መምህራን መጤ ናችሁን? የሚል ታሪክን እና የቤተክርስትያኒቱን መሰረት ያላገናዘበ ጋዜጠኛ እንዲኖር አንፈልግም ፤ በባለፈው ፊልም ላይ በጣም አሳፋሪ ታሪክ አዋቂ መሳይ ወጣት(ተመስገን ዮሀንስ) ያደረጋችሁትን ቃለ-መጠይቅ ለምን እንደቆረጣችሁት ፤ ለምንስ ለህዝቡ እንዳላደረሳችሁ መጠየቅ እንፈልጋለን ፤ ማህበራትን የአክራሪነት መነሻ መሆናቸውን የተናገረውን ንግግር ለምን ቆረጣችሁት? የዚህን ሰው ጀርባውን መጀመሪያ እወቁት ፤ አክራሪነትን በምን አንግል በመመልከት እንደመለሰ ያደረገው ቃለ-መጠይቅ ኢቲቪ ያላቀረበውን እኛ መመልከት ችለናል ፤ የተመስገን ዮሀንስን መልስ ከራሱ ማንነት ጋር በማያያዝ ወደፊት ቃለመጠይቁን ከእውነታው ጋር በማመሳጠር ለአንባቢያን እናደርሳለን ፤ በተጨማሪ ፓስተር ዳዊት ከዓመታት በፊት በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሰራውን ስራ በቪሲዲ ተመልክታችሁ ስታበቁ ተጋባዥ አድርጋችሁ በማቅረባችሁ የሱን ዝቅጠት ብቻ ሳይሆን የናንተንም የወረደ አመለካከት ለመመልከት ችለናል ፤ ፊልሙን ስትሰሩ “አዲስ ራዕይ” መጽሄትን እንደ ትልቅ ግብአት ተጠቅማችሁ ስታበቁ ነገሩ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳይኖረው በመስጋት ምንጫችሁን ሳትናገሩ በማለፋችሁ አስገርማችሁናል ፤ ዶክመንተሪ ፊልም ሲሰራ ሰሪው አካል ፊልሙ ላይ የተጠቀመበትን ጽሁፎች ከየት እንዳገኛቸው የማን አመለካከት መሆናቸውን እንዲያስቀምጥ የሙያው ስነ ምግባር ያስገድዳል ፤ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ  “አዲስ ራእይን” መጽሄትን ለምን አንቀጽ በአንቀጽ አነበባችሁልን? “አዲስ ራእይ”ን ቀድሞ ላነበባት የኢቲቪ ፊልም ትረካ እንጂ ፊልም አለመሆኑን ይረዳ ነበር ፡፡

በአሁኑ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የቀረበው ዘጋቢ ፊልም ተመልካቹ እርሱን  የሚመጥነው ሆኖ አላገኝውም ፤በመካከለኛው የኢትዮጵያ ታሪክ የተደረጉ ጦርነቶች ፤ በጊዜው የወደሙ ንብረቶችና ሃብቶች ፤ሃይማታዊ እንደሆነ ብቻ አድርጎ ማቅረቡ ስህተት ነው፤ አንድ ዘጋቢ ፊልም ከመሰራቱ በፊት ሰሪዎች ከተመልካቹ የተሻለ በቂ እውቀት ይኑራቸው ፤ እድሜ ዘመናችሁን በታሪክ ትምህርት ላይ ያሳለፋችሁ ሰዎች ነገ ታሪክ የሚሆነው መንግስት ስለ ታሪክ ቢጠይቃችሁ ስላበቀላችሁት ነጭ ጸጉር ብላችሁ ብቻ እውነቱን ተናገሩ ፤ ያልተጠየቃችሁትን አትመልሱ ፤ እናንተ ነገም ታሪክ ሆናችሁ ታሪክ ጠያቂ እንደሚነሳባችሁ እወቁት ፤ መልከ ጼዲቅ የነበረበትን ጊዜ የማያውቅ ጋዜጠኛ ስለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መጤ መሆን አለመሆን ጥያቄ ማንሳት አይገባውም ፤ እባካችሁ ፖለቲካዊ ዶግማ ደግማችሁ ያልተጻፈ አታንቡልን ፤ ያልተከሰተን ድርጊት አትንገሩን ፤ ያልሆነው እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ይበልጥ አጀንዳውን  ከማራገብ ውጪ ፋይዳው ሀገራዊ ጥፋት መሆኑን እወቁ ፤  ሊፈቱ የማይችሁ የሚመስሉ ችግሮች በመነጋገር ሰፊ ውይይት በማድረግ እልህ አስጨራሽ ትእግስት ታክሎበት በርካቶች በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ላይ ለችግሮቻቸው መፍትሄ ሲያመጡ ተመልክተናል ፤ አሁን ግን መንግስት እየሄደ ያለው መንገድ እንደ ሃገር ጫፍ ያድርሰው አያድርሰው መጀመሪያ መመልከት ያለበት ይመስለናል ፤ የማያዘልቅ መንገድ መጀመር አንድም ድካም ነው አንድም መንገዱን ሲጀምሩ አለማስተዋል ነው ፤ በሌላ በኩል 100 ዓመት ወደ ኋላ በመሄድ “እናንተ እኮ ተበድላችኋል” ማለት ሰውን ላልተፈለገ አመጽ ስለሚያነሳሳው ሀሳቡን የሚያነሱ ሰዎች ከሀሳቡ ጀርባ ሊመጣ የሚችለው ነገር ቢያስተውሉት መልካም ነው ፤ አሁን እኛ እንደ ሃሳብ የምናቀርበው ነገር ቢኖር ከእምነት ተቋማት ላይ መንግስት ረዥሙን ክንዱን ያንሳ ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ አቅም ያለው መንግስት ሳይሆን ህዝቡ ራሱ መሆኑን መጀመሪያ  ይወቅ ፤ የመንግስት ሚና መሆን መቻል ያለበት የእምነት ተቋማት በራሳቸው መፍታት የማይችሉትን ጉዳይ የመንግስትን እርዳታ ሲጠይቁ ብቻ ለሀገር ሰላም ፤ ለምዕመናን ደህንነት ሲባል ብቻ መንግስት ጣልቃ የመግባቱን ስራ ቢሰራ መልካም ነው፡፡

በሌላ በኩል ከእምነቶች መካከል አንዱ የአንዱን እምነትና ስርኣት ጥላሸት የመቀባት ስራ የሚሰሩ ሰዎችን የሚሰሩት ስራ አግባብ አለመሆኑን የራሳቸውን እምነት በራሳቸው ዛቢያ ዙሪያ በመዞር የእምነት ነጻነቶቻቸውን ተጠቅመው በዛቢያቸው እንዲሽከረከሩ ትምህርት ቢሰጣቸው ፤ የሌላውን ስም ካልጠሩ ያላስተማሩ የሚመስላቸው የእምነት መምህራኖች የያዙትን የተሳሳተ አቋም እንዲያስተካክሉ ቢደረጉ ፤ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያነሳሱ የጋዜጣና የመጽሄት ጽሁፎች ፤ የመጽሀፍ ህትመቶች ፤ የቪሲዲ እና የካሴት የተቀረጹ ድምጽና ምስሎችን መቆጣጠር የሚያስችል መንገድ ቢቀየስ መልካም ነው የሚል እምነት አለን ፤

ቸር ሰንብቱ

13 comments:

 1. egziabher Ethiopian Yitebik!!!

  ReplyDelete
 2. ከመቼ፡ጀምሮ፡ነው፡ደግሞ፡የእስላሙ፡ቁጥር፡ከ25ሚሊዮን፡በላይ፡የሆነው፡፡ተቃውሞ፡ለማቅረብ፡ብቻ፡ብለን፡በውሸት፡ብዙ፡ነን፡ለሚሉት፡የውሸት፡ምስክር፡ባንሆን፡ጥሩ፡ነው፡፡አሁን፡ያለው፡ችግር፡ካለፈ፡በሁዋላ፡ያስጠይቀናል፡፡

  ReplyDelete
 3. yewesha sebesebe bichohe wedehezebu mene melekete masetelalefe ayechelem

  kenetu yekentu kenetu mafera television

  yehe temesegen yohannes yetebale gelesebe manewe esu?

  ReplyDelete
 4. write observation and comment

  ReplyDelete
 5. ውድ አንድ አድርገን
  በጣም ሚዛናዊ ለሆነው ዘገባችሁ በኢትዮጵያ ሙስሊም ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
  ሙስሊሙ ህብረተሰብ ድሮ የተፈጸመበት በደል የመንግስታት ችግር እንጅ የህዝበ ክርስቲያኑ ችግር አለመሆኑን ጠንቅቆ
  ይርረዳል።መንግስት ግን ይህን ነገር በፊልም ቀርጾ ያመጣበት ምክንያት ሁለት ሲሆን
  1ኛ/የሙስሊሙን ብሶት በመቀስቀስ ከሌሎች እምነት ጋር ለማባላት እና ስልጣኑን ለማራዘም
  2ኛ/ጥንት ያልነበረ የሃይማኖት ነጻነት ለሙስሊሞች ኢሃዲግ አስገኝቷል ለማለት
  ነገሮችን ለማሳጠር መንግስት አሁንም ታዋቂ ግለሰቦችን እና ሽማግሌዎችን ኢንተርቪው እያደረገ እንደ መጀመሪያው
  ፊልም ውሸቶችን ቆርጦ እየቀጠለ ይገኛል፡፤ሰዎችን ከማይፈልጉበት ቦታ አስገድዶ ፎቶ እና ቪዲዮ እያነሳ
  በማይፈልጉት ቦታ እና ከማይፈልጓቸው ሰዎች ጋር በማስገደድ ቪዲዮ እየቀረጸ አሁንም ለማታለል ስለሚሞክር
  በጽናት መቃወም እንዳለብን አትዘንጉ፡፤
  ሙስሊሞች ያቀረቧቸው ተራ ጥያቄዎች ከመመልስ ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ እና የተወከሉ ኮሚቴዎችን በማዋከብ እና
  በየጊዜው በማሰር የሙስሊሙን ት እግስት እየተፈታተነ ይገኛል።ህዝበ ክርስቲያኑ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ እስካላመነ ድረስ እኛ
  መንግስትን ቅንጣት ታክል እንደማንፈራ እና መብታችን እስኪከበር ድረስ በየደረጃው እና እንደመንግስ እርምጃ ትግላችንን እና ጥያቄያችንን በማሳደግል እምነታችን ለመሞት ቆርጠን ተነሰናል።
  ልብ በሉ!!! የሙስሊሙ ጥያቄ እጅግ መሰረታዊ መሆኑን አትዘንጉ።ያልመረጥነው መጅሊስ አይመራንም እና ነጻበሆነ ምርጫ
  የሚወክሉንን እንምረጥ/ያወሊያኮሌጅ መሰረታዊ ትምህርቱን ይቀጥል እንጅ ለመጅሊስ አይሰጥብን/አህባሽ የሚባል መሰሪ ቡድን በመንግስት ታግዞ በ እኛ ላይ እምነቱ በግድ መጫኑ ይቅር
  እንደ እምነት ግን ሰብኮ ማሳመን ከቻለ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት የሚል አላማ ብንይዝም መንግስት ግን እኔ ሙስሊሞችንን በማስገደድ የአህባሽን መንገድ ብቸኛ አማራጭ አደርጋለሁ ብሎ መነሳቱን በአንክሮ ስለተረዳን ነው ትግላችንን መቀጠል ያስፈለገው
  ከውስጥ አዋቂ ምንጮች በደረሰን ኢንፎርሜሽን መሰረት ከኢሃዲግ ማእከላዊ ከፍተኛ ባልስልጣናት ከ 20ዎች 16ቱ
  መንግስት ከሙስሊሙም ይሁን ከ ክርስቲያኑ እምነት ላይ እጁን ካላነሳ ሃገራችን ወደ ከፋ እና የተወሳሰበ ችግር ውስጥ
  ትወድቃለች የሚለውን ያንጸባረቁ ቢሆንም አቶ ሪድዋን እና አቶ መለስ ሌሎች ሁለት ሰዎች በድምሩ 4 ሰዎች ብቻ ወደኋላ አንመለስም በማለት ከጊዜ፡ወደ ጊዜ፡ከአንድ መንግስት ሳይሆን ከአንድ ሽፍታ የማይጠበቅ ነገር እየሰሩ ይስተዋላል።
  ልብ ይበሉ!!የአሸባሪነት ህግ በኢትዮጵያ ፓርላማውን በመጠምዘዝ እንዲጸድቅ የተደረገበት ምክንያት ነጻ ፕሬስን ለማፈን እና
  ነጻነት ናፋቂ የሆኑ ኮከብ አርቲስቶችን በአሸባሪነት ስም ዘብጥያ ለመወርወር ቅድመ ዝግጅት መሆኑ ነው!!
  ኢትዮጵያ ሃገራችን እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት የአሸባርዎች ጥቃት ያልደረሰባት መሆኑ ቢታወቅም ባለፈው ጊዜ
  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መንግስት አስቦ የነበረው ሴራ ከፍተኛ የአየር ሃይል ማናጀሮች በመቃወማቸው እና ሚስጥሩ
  በመውጣቱ እስከአሁን ተፈጻሚ አልሆነም።ፕሮግራሙ የነበረው መንግስት የመንገደኛ አቅሮፕላን በሌላ ሰው የተጠለፈ አስመስሎ
  ሃገር ውስጥ አደጋ ማድረስ እና የህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የሚባሉትን ከሁለቱም እምነት ያሉትን ሰዎች ሰብስቦ ማሰር ነበር።
  ይህንን ነገር ወደፊት መልኩን ቅይሮ ላለመደገሙ(ላለመታሰቡ) ጋራንት የለንም።
  በቅርቡ ባገኘነው መረጃ መሰረት መንግስት የተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎችን ወደ ሚጠረጠሩ ግለሰቦች ቤት በመውሰድ እና ፎቶ በማንሳት ቪዲዮ በመቅረጽ እጅ ከፍንጅ ተያዙ በማለት በሃሰት ወንጅሎ እስር ቤት እንደሚወርውር መረጃዎች ደርሰውናል።
  ስለዚህ የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ ካወቅን ሙስሊሙ እና ክርስቲያኑ የሚጋጭበት ምክንያት አይኖርም!ያኔ የመንግስት ሴራ ይከሽፋል።
  ስለዚህ እኛው በራሳችን የመቻቻል እና የመመካከር መንፈስ ፈጥረን ኢትዮጵያን እንታደግ እንላለን፡፤

  ReplyDelete
 6. kale hiwot yasemalen

  ReplyDelete
 7. 5.6. የክርስትና (በተሇይም ፕሮቴስታንት) የበሊይነት የነገሰባት
  ኢትዮጵያን መፍጠር ይፈሌጋሌ
  ላሊው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ክርስትናን የበሊይ ከማዴረግ አንጻር የሁሇት
  አካሊትን ሚናና ፍሊጎትን ማየት ይገባሌ። የመጀመሪያው ከዒሇም የፕሮቴስታንት
  ፖሇቲከኞች በኩሌ ኢትዮጵያንና ናይጄሪያን የፕሮቴስታንት ማዕከሌ አዴርጎ
  የመቅረጽ ከፍተኛ ፍሊጎት አሇ። ሇዚህም ሲባሌ በፖሇቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
  ሃይማኖታዊ መስክ እጅግ አስገራሚ ዘመቻ እየተካሄዯ ነው። በየዒመቱ
  በፕሮቴስታንት ዴርጅቶች (ሃይማታዊና ሌማታዊ) በኩሌ ወዯሀገር የሚገባው ገንዘብ
  ወዯ አንዴ ቢሉዮን ድሊር ዯርሷሌ። የአማኛቸውን ቁጥርና ጥራት ከማሳዯግ
  64

  አንጻርም ፈጣን እንቅስቃሴዎች እየተዯረጉ ነው። ሙለ ሇሙለ ከምዕራቡ ዒሇም
  ፍሊጎትና አካሊት ጋር በመሥራታቸው የተነሳ የነርሱ ማንኛውም እንቅስቃሴ
  በጥርጣሬ ከመታየት የጸዲ ሆኗሌ። የመንግሥት ሰነዴ በሚባለት እንኳን የጸረ-
  እስሌምና ዘመቻውን አባሪ አዴርገው ጥቂት ነጥቦች ስሇ ማህበረ ቅደሳን ሲያነሱ
  አስገራሚ በሆነ ፍጥነት በገንዘብ እና በባሇስሌጣናት የሚመራውን የፕሮቴስታንት
  አክራሪነትን ሇመንካት አሌዯፈሩም። በፖሇቲካው መስክም ከ2002 ምርጫ በኋሊ
  ያሊቸው ተሰሚነት እጅግ በሚገርም ሁኔታ አዴጓሌ። ከምክትሌ ጠቅሊይ ሚኒስተርና
  የዉጭ ጉዲይ ሚኒስትሩ፣ የፌዲራሌ ጉዲዮች ሚኒስተር፣ የኦሮሚያ ክሌሌ
  ፕሬዝዲንት፣ የዯበቡ ክሌሌ ፕሬዝዲንት፣ የኦሮሚያ ጸጥታ ኃሊፊ፣ የአዱስ አበባ
  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዲንትና በርካታ ባሇስሌጣናት ወዘተ በፕሮቴስታንት አብያተ
  ክርስቲያናት ቀጥተኛ ተሳትፎ ያሊቸው ግሇሰቦች እንዯሆኑ ይነገራሌ። እንዱያውም
  አንዲንድቹ የሲኖድሱ የቦርዴ አባሊት ናቸው። በዚሁ የሙስሉሙ የመበት ጥያቃ
  ሂዯት እንኳን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ባሇስሌጣናት በአውሮፓና አሜሪካ
  የሚገኙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን በማስተባበር የተሇያዩ ሚዱያዎች
  በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዲዮች ሊይ የሚያቀርቡትን ዘገባ ሚዛን ሇማሳት ያዯረጉት
  ጥረት አንደ ማሳያ ነው። የሙስሉሙን ፖሇቲከኞች በተቃራኒው ስናይ ዯግሞ
  ዯህና ሥፍራ የተቀመጡት ጥቂት ከመሆናቸው ጋር ከሃይማቱ ጋር ያሊቸው
  ቅርርብና ከአማኙ ጋር ያሊቸው ትስስር እጅግ የሊሊ ነው። በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ
  ሚና ሉኖራቸው ቀርቶ ‹‹ሇሙስሉሙ አዯሊህ እንዲሌባሌ›› በሚሌ ስጋት ሙስሉሙን
  የሚጫኑም አለ። መንግሥት የምዕራቡን ፍሌጎት ከመጠበቅ አንጻር ረጅም እርቀት
  ከመጓዝ ባህሪው አንጻር እስከ ጥግ በዚህ ጉዲይ አብሯቸው ሉሰራ ይችሊሌ።

  የምዕራቡ ዒሇም በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ክርስትና ሊይ ‹‹ከኢስሊም ይሻለናሌ›› የሚሌ
  ምርጫ እንጂ ያሊቸው ተፈሊጊነት ከፕሮቴስታንቱ ጋር ፈጽሞ ሇንጽጽር የሚቀርብ
  አይዯሇም። ምክንያቱም ኦርቶድክሱ የራሱ ታሪክና ሃይማኖታዊ ቀኖና ያሇው
  በመሆኑ ከምዕራቡ ፍሊጎት አንጻር እምብዛም የሚስብ አይዯሇም። ታዛዥነቱና
  የነርሱን ፍሌጎት ከመተግበር አንጻር ፕሮቴስታንቱ እጅግ ተመራጭ ነው።
  ኦርቶድክሱ ‹‹ኢትዮጵያዊ/የኢትዮጵያ›› ከመሆኑ አንጻር በተመሳሳይ አጀንዲ ሊይ
  65

  አብሮት የሚሰራ (የሚያብር) ዒሇም አቀፍ አማኝ እምብዛም የሇም። በዚህ በመሰሌ
  ምክንያቶች ከኦርቶድክሱ ይሌቅ ፕሮቴስታንቱ ቅዴሚያ ይሰጠዋሌ።

  ይህም ሆኖ ግን በርካታ ወሳኝ የኢህኣዳግ ባሇስሌጣናት የኦርቶድክስ አማኝ ስሇሆኑ
  ከምዕራቡ ፍሌጎት ቀጥል አሌያም በተቀራረበ ሁኔታ እንኳን ‹‹የኦርቶድክስ
  ክርስትናን ሔሌዉና የማስጠበቅ የሞራሌና የታሪካዊ ኃሊፊነት አሇብን›› በሚሌ
  (ሇማስመሰሌ ይሁን እውነተኛ ፍሊጎት) ከቆይታ በኋሊ መሌሰው ያነሱት አጀንዲ
  እንዯሆነ ይገመታሌ። ይህም ቢሆን በአስተዲዯራቸው የተከፋው ሔዝብን ዴጋፍ
  ማግኛ ዘዳ እንጂ ሰዎቹ ያን ያህሌ የሃይማኖት ሰው ሆነው አይዯሇም። ጸረ ሁለም
  ሃይማኖት ነኝ ይሌ የነበረው ዯርግም በስሌጣኑ ብቂያ ግዚያት ይህን መሰሌ
  መዘንበሌ አሳይቶ እንዯነበር ይነገራሌ። ይህ ግን ሇእምነቱ ከማበር ሳይሆነ
  በማስመሰሌ የሚገኘውን የፖሇቲካ ካርዴ ሇመጠቀም ነው። ባሌተሇመዯ መሌኩ
  የጠቅሊይ ሚኒስትሩ በተዯጋጋሚ መስቀሌ ሲሳሇሙ መታየት መጀመራቸውም ሇዚህ
  ማሳያ ሉሆን ይችሊሌ።
  Source:-
  በኢትዮጵያ እስሌምና ሊይ የተቃጣው
  የኢህአዳግ ዘመቻ፡ መንስኤዎቹ፣
  ተጽእኖዎቹና ቀጣይ ሁኔታዎች

  አብዯሊህ አዯም ተኪ
  (ከህዲር 7/1989-ታህሳስ 28/2004 የኢህአዳግ አባሌ)
  Pages 63-65

  ReplyDelete
 8. ጥሩ ና አስተማሪ ጽሁፍ ነው በርቱ እውነታን ለመናገር የማንደፍርበት መንግስት ጋር እየኖረ ያለ ህዝብ እውነትን ከሌላ መስማት ተፈርዶበታልና፡፡ የእኛ መንግስት የህዝብ ሰላም እና አብሮነት (አብሮ መኖር) አሳስቦት አያውቅምና፡፡ ከሰሞኑ ዶክመንተሪ ያየነውም መንግስታችን የራሱ ፖለቲካዊ ጥቅም ስላለው ብቻ ነው ፕሮግራሙን ያዘጋጀው፡፡ ምናልባትም እናንተ አንዳላችሁት አላማው ያልተሳካ ከመሰለው ሌላም ፊልም ሰርቶ ያሳየናል ለኢህአድግ እና ጀሌዎቹ የፈጠራ ፊልም መስራት እና ውሸት መፈብረክ ምን ገዶት፡፡

  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

  ReplyDelete
 9. ከመቼ፡ጀምሮ፡ነው፡ደግሞ፡የእስላሙ፡ቁጥር፡ከ25ሚሊዮን፡በላይ፡የሆነው፡፡ተቃውሞ፡ለማቅረብ፡ብቻ፡ብለን፡በውሸት፡ብዙ፡ነን፡ለሚሉት፡የውሸት፡ምስክር፡ባንሆን፡ጥሩ፡ነው፡፡አሁን፡ያለው፡ችግር፡ካለፈ፡በሁዋላ፡ያስጠይቀናል፡፡

  ReplyDelete
 10. አምስት ኪሎ ቅ/ማርያም መንበረ ፓትርያርክ ላይ ከፓትርያርኩ ፎቶ ቀጥሎ የተጻፈው ግርም ብሎኛል፡፡
  ‹20 ውጤታማ አመታት›
  ምን ለማለት ነው! ይህ ነገር ምድራዊ ዋጋ እየተመዘነለት ነው

  ReplyDelete
 11. እኔ የምለው ማህበረ ቅዱሳን ከፓትርዬርኩ አፍንጫ ስር ተቀምጦ የወያኔን መንግስት ተገን አድርጎ በቤተክርስቲያኗ ሲጫወትባት አንድ ቀን እኳ ምእመናኖችን አሰባስባችሁ አቤት የማትሉት የሚሰራው በደል ጥሞአችሁ አለ ማለትነው? ልቦና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete