Tuesday, July 31, 2012

እረ ጉድ ነው


አንድ አድርገን በኢትዮጵያ ውስጥ መነበብ አልቻለችም
www.andadirgen1.wordpress.com  በዚህ ያግኙን 



(አንድ አድርገን ሐምሌ 24 2004 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ጊዜ የማይሰማ ነገር የለም ፤ በየቦታው የሚሰማው ነገር ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ነገሮች እየሆኑ ለመስማትም ሆነ ለመጻፍ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንገኛለን ፤ የዛሬ ዓመት ወር ገደማ “እኔ እየሱስ ክርስቶስን የምወልደው ሴት ነኝ” ብላ የተነሳች ሴት መከሰቷን በጊዜው በቦታው ተገኝተን በአይናችን ካየነው ፤ በጆሯችን ከሰማነው ፤ ከጋዜጦች ካነበብነው እና ከፖሊስ መረጃ ጋር በማመሳከር አንድ ጽሁፍ ማቅረባችን ይታወሳል ፤ በጊዜው የተከሰተችው ሴት ከዚህ በፊት ተሰምቶም ሆነ ታይቶ የማይታወቅ ተግባር ስለፈጸመች ብዙዎችን ጉድ አሰኝታ ነበር ፤ ከሰማይ የወረደ  መና ነው በማለት ብዙዎችን ምንነቱ ያልታወቀ ምግብ አብልታቸዋለች ፤ ይህ ሁሉ ሲደረግ ስለ እሷ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ ብዙ ነጫጭ የለበሱ ሴቶችን አስከትላ ገድሏን ሲመሰክሩላት ሲመለከቱ ይህ ነገር ህልም እንጂ እውን አይመስሎትም ፤ እኛ ከተደረጉት ነገሮች ሁሉ ለእናንተው ጆሮ ለዘብ ያለውን ጉዳይ ብቻ አቅርበናል ፤ ይች ሴት የተነሳችበት ዓላማ በጣም አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ ብዙዎችን “እኔ እግዚአብሔር የመረጠኝ ክርስቶስን የምወልደው ሴት ነኝ” በማለት በቤተክርስትያን ውስጥ በርካቶችን ያወዛገበች ፈት ሴት መሆኗን ለማወቅ ተችሏል ፤  በአዲስ አበባ አስኮ መንገድ የሚገኝው የአባታችን የአቡነ ሐብተማርያም ቤተክርስትያን በበአላቸው ቀን በመገኝት አውደ ምህረት ላይ በመውጣት ስትናገር የነበረው ነገር በርካታ ወጣቶችን በማስቆጣቱ ከፍተኛ ችግር መፈጠሩ የሚታወቅ ነው ፤ በጊዜው ያልተገባ ነገር ስትናገር የሰሙ ወጣት ምዕመናን ከአውደ ምህረት ላይ ውረጂ ሲሏት ባለመስማቷ አንጠልጥለው ሊያወርዷት ወደ አውደ ምህረቱ ሲያመሩ የሚመጣውን ጉዳት ከግምት በማስገባት ተሸቀንጥራ በግብር አበሮቿ አማካኝነት በመታጀብ  ቤተክርስቲያኑ ጎን  የሚገኝው መሰብሰቢያ አዳራሽ በመግባት ከተቆጡት ወጣቶች ማምለጥ ችላለች ፤  ይህ በእንዲህ እያለ በአዳራሽ ውስጥ አብረዋት የገቡት ግብር አበሮቿ ፖሊስ ዘንድ በመደወል ከሚደርስባት ጉዳት ሊያድኗት ችለዋል ፤ በጊዜው የነበሩ ወጣቶች ሁኔታውን ሲያስረዱ ስለ ቤተክርስቲያንና በድፍረት በአውደ ምህረት ላይ ስለተናገረችው ቃል እንባ እየተናነቃቸው ምግባሯንና ያደረገችውን ነገር መናገርና መግለጽ እስኪያቅታቸው ድረስ ደርሰው ነበር ፡፡

ይህ ከመሆኑ ከዓመት በፊት በ2002 ዓ.ም መጋቢት ወር አካባቢ ይችው ሴት ከግብር አበሮቿ ጋር በመሆን በደብረብርሃ ከተማ ተገኝታ ነበር ፤  ከተማውን በአግባቡ በማጥናት ማረፊያቸውን እያሰቡ ሳለ በሰዎች ጥቆማ አንድ የዋህ የእግዚአብሔር ሰው ጋር በመሄድ እንዲህ ይላሉ “ቤትህ እንድናድር እግዚአብሔር አመላክቶናል ፤ ሥላሴዎች ጠቁመውናል ፤ በጉራጌ ሀገር ከሚገኝው ገዳም ተልከን ነው የመጣነው ፤ በመላ ሃገሪቱ እንድንዞር ታዘናል ፤ ከበአታችን ከተነሳን አንድ ወር አልፎናል ፤ የእግዚአብሔር መልአክ እየጠቆመን እዚህ ደርሰናል ፤ አሁንም ምን ያህል ጊዜ እዚህ እንደምንቆይ አናውቀውም ፤ ተነሱ ስንባል ነው የምንነሳው” በማለት በጣም ትህትና በሞላበት ሁኔታ ይጠይቁታል፡፡ ያም ሰው እውነት መስሎት እግዚአብሔር የላካቸው ሰዎች ናቸው በማለት በመሰራት ላይ ያለውን ቤት ያልተጠናቀቀውን መኖሪያ እንካችሁ እስከፈለጋችሁ ጊዜ ድረስ ቆዩበት በማለት ይሰጣቸዋል ፤ ቢያንስ በቁጥር ከአስራ አንድ የሚበልጡት እነዚህ ሰዎች ካለማቅማማት በተከፈተላቸው ቤት በመግባት ለሁለት ሳምንት በላይ መቆየታቸውን ለማወቅ ችለናል ፤ የፈለጉትን ያህል ጊዜ በቤቱ ከቆዩ በኋላ “አሁን እግዚአብሔር በጸሎት ስንጠይቀው ወደ ሌላ ቦታ እንድንሄድ አመላክቶናልና መሄጃችን ደርሷል” በማለት ለ15 ቀን ያለ ክፍያ በማታለል የቆዩበትን ቤት አመስግነው ሊወጡ ሲሉ “ባዶ እጃችሁንማ አትሄዱም በረከታችሁ እኛ ላይ ይደርብን” የሚሉ ጥቂጥ ሰዎች  ብር በማዋጣት በሶና ስኳር ሰጥተው ሸኝተዋቸዋል ፤ አብሯው የሚሄደውን ህጻን “ይህ ልጅ በምን አቅሙ ነው ከእናተ ጋር በርሃ ለበርሃ የሚጓዘው?” በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልሱን በፈገግታ መመለሳቸው ሁኔታውን ካስረዱን ሰዎች ለማወቅ ችለናል ፤ በሚሄዱበት ቦታ ውሃ እንዳይጠማቸው የሚጠጣ ነገር በመቅዳት ፤ ምግብ እንዳይርባቸው  ስንቅ ቋጥረው እንደላኳቸው ጭምር በቦታው ከነበሩ ሁኔታውን ከመጀመሪያ እስከ ፍጻሜ የሚያውቁ በሶና ስኳር ከሰጧቸው ሰዎች መካከል በአካል በማነጋገር ለማወቅ ችለናል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል 10፤16 ላይ “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ” በማለት ተጽፏል ፤ እኛ ግን እንደ እባብ ልባም መሆኑ እንዳለብን ዘንግተን እንደ ርግብ የዋህ ብቻ በመሆን ራሳችን ተሰናክለን ሰዎችን እያሰናከልን እንገኛለን ፤

እነዚህ ሰዎች በአዲስ አበባ በተክለ ኃይማኖት ቤተክርስቲያን ያደረጉትን ነገር ህዝቡ እንዴት እንደተቃወማቸው ፤ ፖሊሶች በጊዜው ሁኔታውን በማረጋጋት ወደ እስር ቤት እንዳወረዷቸው የሚያሳየውን ቪዲዮ ይህ ነገር ለተፈጸመባቸው ሰዎች በሲዲ ሰጥተን አሳይተናቸዋል፡፡ ሰዎቹም ተመልክተው ካበቁ በኋላ “እግዚአብሔር የስራቸውን ይክፈላቸው” ብለው ለእግዚአብሔር አሳልፈው ሰጥተዋል ፤ እነዚህ ሰዎች ባደረጉት ተግባር በምዕመናን ጥቆማ ፖሊስ ሰዎቹን በተክለኃይማኖት በተክርስቲያን በመገኝት በቁጥጥር ስር አውሏቸው ነበር ፤ ፖሊስ በጊዜው በወንጀለኛ መቅጫ ህግ እንደሚጠይቃቸው ቢያሳውቅም ካለምንም ክስ ከቀናት በኋላ ሊለቃቸው ችሏል ፤

በአሁኑ ሰዓት ከሁለት ቀናት በፊት የአዲስ አበባው አልሳካ ያላቸው ሰዎች ቀን በመቁጠር ጊዜ በመውሰድ ወደ ደብረ-ሊባኖስ አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም በማምራት የሰላም አየር ሲተነፍስ የነበረው ገዳም “እኔ ቅድስት ማርያም ነኝ” በማለት ስትናገር ጸብ መነሳቱን ለማወቅ ተችሏል ፤ የአካባቢው ፖሊስ በቦታው በመገኝት ሁኔታውን በማረጋጋት ዳግም ወደ እስር ቤት አውርዷዋል ፤ ይችን ሴት ከግብ አበሮቿ ጋር በጉልበት ለማስወጣት በተደረገው ኃይል አንድ ፖሊስ በድንጋይ ጭንቅላቱ ላይ የመፈንከት አደጋ ደርሶበታል ፤ ሁኔታው ብዙ መነኮሳትን እጅጉን አስቆጥቷል ፤ ከአዲስ አበባም ጉዳዩን ለማጣራት ሰዎች ወደ ቦታው አምርተዋል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ፖሊስ ጣቢያ ሆነው የሰጡት ቃል ብዙዎችን አስገርሟል ፤

በዚህችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የዋሓንን አማኝ  በማታለል የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ እና ስርአት ለማጥፋት የሚጥሩ ብዙ ተኩላዎች እንዳሉ የማይካድ እውነታ ነው፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ከውጪ ያለችበት ከፍተኛ ፈተና ከፊት ተጋርጦ ሳለ እዚሁ በየገዳማቱ በየአድባራቱ ያሉትን የዋሀንን በፈለጉት ሀሳብ በመስበክ ሕዝቡን እያሳቱ እንዳለ ይህ እውነተኛ ምስክር ነው፡፡

አካሄዳቸው ቀላል የሚባል አይደለም አንድ ሰው ተነስቶ ስለ እሷ ሲመሰክር ሌላው ስለ እመቤታችን ፍቅር ብሎ ቁጭ ብሎ ያለቅሳል፡፡ ሰውን ለማሳመን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይወጡት ዳገት አለመኖሩ ደግሞ በጣም ይገርማል ፡፡ የማያቁት ገዳም የማይጠሩት በረሀ አለመኖሩን ሲያውቁት ደሞ ጉድ ይላሉ:: በጣም ብዙ ተከታዮችን ሲያዩ ደግሞ ይደነግጣሉ ፡፡ የደጋፊዎቹ ስብስብ ደሞ ህፃን ፤ ወጣት አሮጊቶች መሆኑን ሲያስተውሉ ‹‹ እረ ጊዜው ከፍቷል›› እግዚኦ…. ይላሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው በቤተክርስትያን ፤ በአውደ ምህረቷ ላይ መሆኑን ፤ በቅፅሯ ውስጥ መሆኑን ሲያውቁ የእግዚአብሔር ትዕግስቱ ይገርሞታል ፡

ጉዳዩ ምን ደረጃ እንደደረሰ ተከታትለን እናቀርብሎታለን..ይጠብቁን

ደብረ ብርሃን ላይ እነዚህ ሰዎች ያደረጉትን ነገር የቤቱን ባለቤት መልካም ፍቃደኝነት ጠይቀን ለሌላው መማሪያ ይሆነው ዘንድ ወደፊት እናቀርብሎታለን ፤

እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ

Monday, July 30, 2012

ፖሊስ በዋልድባ 49 መነኮሳትን ለማሰር እየፈለገ ይገኛል

አንድ አድርገን በኢትዮጵያ ውስጥ መነበብ አልቻለችም
www.andadirgen1.wordpress.com  በዚህ ያግኙን 


 (አንድ አድርገን ፤ ሀምኔ 24 2004 ዓ.ም)፡- መንግስት አሁንም የዋልድባን መነኮሳት ማወከብ ማሰርና መደብደቡን አላቆመም ፤ ከዚህ በፊት በርካታ መነኮሳትና ወጣቶች መታሰራቸው በጊዜው ገልጸናል ከተለያዩ ድረ-ገጾች እና የዜና ማሰራጫዎችም ሰምተናል ፤ ከዚህ በፊት የታሰሩት መነኮሳት ስብእናቸውን በሚያዋርድ ሁኔታ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ክብርን ዝቅ በሚያደርግ መልኩ እጅጉን አሸማቀው በክልሉ ፖሊስና በመከላከያ ሃይል አማካኝነት እያዳፉና በሰደፍ እየደለቁ ወስደዋቸው ፤ ከጥቂት ቀናት እስር በኋላም ደግመው ሊለቋው ችለዋል ፤ አሁን ግን መንግስት የያዘው አሰሳ በገዳሙ የሚገኙ ሁሉን አባቶችን የሚያሰጋ እየሆነ ይገኛል ፤ በገዳሙ የሚገኙትን መነኮሳት በጠቅላላ በሂደት ለመልቀም እንዲመቸው በመጀመሪያ ዙር 49 መነኮሳትን ማደን ተያይዞታል ፤ ከሚፈልጋቸው 49 መነኮሳት ውስጥ ሶስት ያህሉን ይዞ ወደ እስር ቤት አውርዷቸዋል ፤ ባሳለፍነው አርብ ከ3 እስከ 10 የሚደርሱ የመነኮሳትን ቤት ሲፈትሽ ውሏል ፤ ክፍት የሆኑት ቤቶች ላይ በቀጥታ በመግባት ፤ የተቆለፉትን ቤቶች ላይ ደግሞ ቁልፎቻቸውን ሰብሮ በመግባት ያለ ፍርድ ቤት ፍቃድ ቤቶቹን ሲበረብር ውሏል ፤ በጊዜውን “ከደጀ ሰላም” እና “ከአንድ አድርገን” ድረ-ገጾች ላይ ስለ ገዳሙ በተለያዩ ጊዜ የተጻፉ እና ፕሪንት የተደረጉ ጽሁፎች ፤ ስለዋልድባ ገዳም “ፍትህ” ጋዜጣ የዘገበችውን ዘገባ ጨምሮ ያስፈልጉኛል ያላቸውን ነገሮች ሁሉ አግበስብሶ ሊወስድ ችሏል ፤ በመሰረቱ የአንድ ሰው ቤት ወንጀለኛ ቢሆን እንኳን በህግ መሰረት መፈተሸ ያለበት ከፍርድ ቤት የወጣ ትእዛዝን መሰረት ተደርጎ ቢሆንም በማን አለብኝነት የተቀመጠው የሀገሪቱን ህግ የራሱ ጀሌዎችን በመላክ አፍርሶ ቤቶችን በጠራራ ጸሀይ ያለ ፍቃድ ሲያስበረብር ውሎ አምሽቷል ፤

Sunday, July 29, 2012

ለዋልድባ ቤተ ሚናስና ለቤተ ጣዕመ ክርስቶስ ማህበረ መነኮሳት የተጻፈ ደብዳቤ



(አንድ አድርገን ሐምሌ 23 ቀን 2004 ዓ.ም)፡- የዛሬ 102 ዓመት ወደ ኋላ ሄደን ታሪካችንን ስንቃኝ በጊዜው ዋልድባ ገዳም ቤተ ሚናስና ለቤተ ጣዕመ ክርስቶስ ማህበረ መነኮሳት መካከል በተነሳው የኃይማኖት ችግር በገዳሙ ውስጥ ያሉትን አባቶች ለብዙ ጊዜ ካከራከራቸው በኋላ ከማዕከላዊ መንግስት አፄ ምኒሊክ ዘንድ ጉዳዩ ደርሶ ምን ዓይነት መልስ እንደጻፉላቸው ለእናንተው አስተማሪ ሆኖ ስላገኝነው ለማቅረብ ወደድን፡፡

ቅድመ ታሪክ
አባ ጣዕመ ክርስቶስ ወደ ዋልድባ ገዳም ሲገቡ  ከውጭ መንኩሰው ነበር ፤ ስምረትን ግን የተቀበሉት ዋልድባ ገባም ውስጥ ማይፈዴ በተለይ አይጠየፍ ከተባለው ቦታ መሆኑን መዛግብት ያስረዳሉ ፤ ስምረትንም ያነሱአቸው አባት ናኩቶ ለአብ የመንፈስ ቅዱስ ልጃቸው የሆኑት አባ ገብረሚካኤል ናቸው ፤ እኒህ ሰው የሚታመሙትን መነኮሳት ሁሉ ሳይሰቀቁና ሳይጠየፉ ሁሉን አቅፈው ደግፈው ስለሚያስታምሙ አይጠየፍ የሚል ቅጽል ስም ተሰቷቸዋል ፤ ስለዚህ አብዛኛውን ጊዜ አባ ገብረሚካኤል በማለት ፋንታ አባ አይጠየፍ እየተባሉ ይጠሩ ነበር ፤ ይህን በጎ ተግባር ሲፈጽሙበት የነበረውም ቦታ በርሳቸው ስም አይጠየፍ እየተባለ እስከአሁን ይጠራል፡፡

Wednesday, July 25, 2012

Egyptian Coptic activists declare creation of Christian Brotherhood



The Christian Brotherhood has branches in 16 governorates in Egypt as well as three branches in Europe and one in Australia. (Reuters)

A group of Coptic activists in Egypt announced the establishment of the Christian Brotherhood to counter the growing influence of the Muslim Brotherhood especially after their candidate Mohammed Mursi won the presidential elections.

Tuesday, July 24, 2012

“ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ” ለመመስረት ጥያቄ መቅረቡ ተሰማ


  •   መንግስት በጥያቄው ደንግጧ
  •    “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡” የኢትዮጵያ ህገ መንገስት አንቀጽ 31

(አንድ አድርገን ሐምሌ 18 2004 ዓ.ም)፡- የሀገሬ ሰው “የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ” ይላል ፤  በአሁኑ ሰዓት  እንዲህማ አይታሰብብ የምንለው ጉዳይ እንደ ትልቅ ጉዳይ ብቅ ብሏል ፤ ይህ ጥያቄ ውስጠ ወይራ ነው ፤ መንግስት የሚደሰኩርለትን ዲሞክራሲን መሰረት አድርጎ የውስጥን አላማ ለማሳካት የተነሳ ጥያቄ ፤ ካለመጠይቅ ደጃዝማችነት ይቀራል በማለት የተነሳ ወቅታዊ ጥያቄ ፤ ሙስሊሙን ነጻ አወጣለው በማለት የሙስሊምን የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል የዘመናት ጥያቄዎቻውን ለመመለስ ያመቻቸው ዘንድ የጠየቁት ጥያቄ ፤ ……

Sunday, July 22, 2012

የተሃድሶያውያኑ ቀበሮ መነኩሴ

  • የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ  የማቴዎስ ወንጌል 715
(አንድ አድርገን ሐምሌ 16 2004 ዓ.ም)፡- ትምህርተ ሃይማኖቷ እምነቷና ሥርዐቷ ምሉዕ የሆነውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ርትዕት ሃይማኖት «እናድሳለን» በሚል ስልት ወደ ውስጧ ሠርጐ በመግባት ልጆቿን እስከ ሕንፃ ቤተክርስቲያኗ እንረከባለን ይላሉ፡፡ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎቻቸውን በማሰማራት በጎቿን በኑፋቄያቸው እያሳሳቱ ከመንጠቅ፣ በተለያዩ ርዳታዎች ስም እየደለሉ ከማስኰብለል ጀምሮ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዐቷን በማጣጣል፣ ቅዱሳት መጻሕፍቷን በማራከስ፣ መልካም ስምና ገጽታዋን በማጠልሸት የሚያደርጉት የጥፋት ጥረታቸው ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ በእናትነት እቅፏ ውስጥ ጡቷን ጠብተው ማዕዷን ተሳትፈው አድገው፤ ነገር ግን ንጹሕ እናትነቷን ክደው በውስጧ ሆነው በኑፋቄያቸው የሚቦረቡሯት ብዙዎች ናቸው፡፡ መዝሙራትን ለማስረሳት ፤ ትውፊትን ለማቃለል ፤ የእኛነታችንን መገለጫዎች ለመሸረሽር የማያካሂዱትን የውስጥ ለውስጥ ሴራዎች ቀጥለውበታል ፤ ነገር ግን  “የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።”  የማቴዎስ ወንጌል 16፤18  በማለት በወንጌል የተነገረላት ቅድስት ቤተክርስትያን አሁንም አለች ወደፊትም ሳትናወጽ ትኖራለች፡፡

Friday, July 20, 2012

“ማኔ ቴቄል ፋሬስ” ብሎ የሚጽፈው ጣት እንዳይቀርብባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ


(አንድ አድርገን ሰኔ 13 ፤ 2004 ዓ. ም)፡- በአሁን ወቅት ጆሯችን የሚሰማው ፤ ከጋዜጦች የምናነበው ፤ ከድህረ ገጾች የምንመለከተው ነገር የጠቅላይ ሚኒስትሩን መታመም የሚያመላክቱ ምንጫቸው ከተለያዩ ቦታዎች የሆኑ መረጃዎችን ነው ፤ በትላንትናው እለት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን ትንሽ የጤና እክል እንዳጋጠማቸው ከሀኪም እረፍት በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ስራ እንደሚመለሱ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ፤ ከአንድ ቀን በፊት አቶ ስብሀት ነጋ በፌዝ በቪኦኤ እንደተናገሩት “በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ” ብለዋል ፤ አይይ…ሰው ከተያዘ በኋላ ፌዝ ምን ይሰራል ? ነገረር ግን ደህና ሆነው ከ10 ወር በኋላም ቢመለሱ መልካም ይመስለናል ፤ ዋናው ጤና ነው ፤ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስራ መሆኑን እስከ አሁን አናውቅም ነበር ፤ ይገርማል ፤ ለካ የመንግስት ተቀጣሪ ናቸውን ? ሰው በህይወት ዘመኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሽታዎች ይጎበኙታል ፤ በቀላሉ ደረስ መለስ የሚሉ ህመሞች እንዳሉ ሆነው ከሰው እድሜ ጋር አብረው የሚዘልቁም አይጠፉም ፤ ባሳለፍናቸው 21 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታመሙ የሚባል ወሬ ሰምተን አለማወቃችን የአሁኑን ሁኔታ የተለየ አይን እንድንመለከተው አድርጎናል ፤ እንደ ፕሬዚዳንት ግርማ ባይታመሙም ለቼካፕ በየጊዜው ሳውዲአረቢያ ቢመላለሱ ኖሮ ህዝቡ ይለምደውና ተሽሏቸው ይመጣሉ ብሎ ለማሰብ መንገድ ይከፍትለት ነበር ፤ ነገርየው ቀልብ እንዲስብ ያደረገው ነገር የህመሙ ሚስጥራዊነት መሆኑን የተገነዘቡት አይመስሉም ፤ በዚህ ላይ የሀገሪቱ በጀት ማጽደቂያ ወቅት እና የህብረቱ መሰብሰቢያ ጊዜ በመሆኑ የነገሩን ምልከታ በሰዎች ዘንድ ቀየረው ፤ አሄሄ “ ሆድ ቁርጠትና ራስ ምታት ቢጤ ቢሆን በሽታቸው መቼ ከማያኑት ቴሌቪዥን ይጠፋሉ” ፤ መሪዎች የህዝቡን ሆድ ይቆርጣሉ የማህበረሰቡን ራስ ያሳምማሉ እንጂ እነርሱ ግን አያማቸውም ይባላል ፤ የጠላት ጆሮ አይስማውና “ለአቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የተቆፈረው ጉድጓድ ….” የሚልም አስተያየት ፌስ ቡክ ላይ አንብቤአለሁ ፡፡ ሌላኛው ደግሞ “ዳይት ጀምረው ነው እንዲህ የከሱት….” ብሏል ፤ የእስራኤል አምላክ ፈጽሞ ይማራቸው ፤ እጃቸውንም ከዋልድባ ገዳም ላይ እንዲያነሱ ያድርጋቸው፡፡

Tuesday, July 17, 2012

“የአቡነ ጳውሎስ ገድል” በ20ኛ በዓለ ሢመት መጽሀፍ



  • ባለፉት 20 ዓመታት በወር በአማካይ 28 ቤተክርስትያኖችን አቡነ ጳውሎስ እንዳሰሩ ይገልጻል (በ20 ዓመት 6800 ቤተክርስትያናት ተስርተዋል ይለናል)

(አንድ አድርገን ሐምሌ ሚካኤል ፤ 2004 ዓ.ም)፡- አንጸባራቂዎቹ 20 ዓመታትን በማስመልከት በጠቅላይ ቤተክህት አንድ መጽሀፍ ተዘጋጅቶ ነበር ፤ ይህን የአቡነ ጳውሎስን ገድል የሚተርክ መጽሀፍ ለማሳተም በርካታ ሺህ ብሮች እንደወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ የመጽሀፉ አዘጋጆች ምዕመኑ በብር ግዛ ቢባል እንደማይገዛ በማወቃቸው በሺህ የሚቆጠሩ መጻህፍትን በነጻ ሲያድሉ ተመልክተናል ፤ ሐምሌ 5/2004 ዓ.ም አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ከመንግስት የተጋበዙ ባለስልጣኖች ፤ የውጭ ጥቂት ዲፕሎማቶች ፤ ፈቅደው ሳይሆን ከየደብሩ የመጡ ካህናትና መዘምራን ፤ ብዛት ያላቸው ጳጳሳት የተገኙበት ስርዓት ነበር፡፡ ምዕመኑ ከ150 የማይበልጥ ሲሆን አብዛኛው ቦታውን የያዙት ተጋባዥ እንግዶች ነበሩ ፤ መሀል ላይ ያለው 10 ሜትር የሚያህል ቦታ ዳር ዳር የቆሙት ምዕመናን ለመታዘብ እንጂ በዓለ ሲመታቸውን ለማክበር የመጡ አይመስሉም ፤ የቅድስት ስላሴ የፊት ለፊቱ ደረጃ በቅጡ በምዕመኑ መሙላት አቅቶት አስተውለናል ፤ አቡነ ጳውሎስ በስተቀኝ እነ ተስፋዬ ውብሸትን ከበስተኋላ ዲፕሎማቶችን ፤ ከበስተቀኝ ደግሞ ሊቃነ ጳጳሳትን አስቀምጠው መሀል ቁጭ ብለዋል፤  በነጻ የሚታደለውን መጽሀፍ በግራ እና በቀኝ የሚያድሉ ሰዎች ተሰማርተው ሰው እጅ ላይ የማድረስ ስራቸውን ተያይዘውታል ፤ ፕሮግራም መሪው የአቡነ ጳውሎስን ፤ የተጋባዥ የመንግስት ባለስልጣናትን ፤ አምባሳደሮችን ስም ሲጠራ ለሰማ ምንድነው ይህ ሁሉ የመዓረግ ጋጋታ ማለቱ አይቀርም ፤የነሱ ስምና መዓረጋቸው ብቻ ከአንድ ገጽ ቢበልጥ እንጂ አያንስም ፤ የሚነበበውን ነገር ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጥ ሰው ማግኝት መታደል ይመስላል ፤ ማን እንደሚያነብ ስለምን እንደሚነበብ ፤ የጽሁፉ መልዕክትና ይዘት የነበረው እንግዳ ቢጠይቁ ከመቶ አምስቱ አይመልስሎትም ፤ በጣም አሰልቺ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ሰው እስከ 5 ገጽ ያነበበበትም ጊዜ ነበር ፤ አቡነ ጳውሎስ አስከ አሁን የሰሩት ወይም ወደፊት የሚሰሩት ስራ አሳስቧቸው ነው መሰል እርሳቸውም ንግግሩን በአጽንዎ እየተከታተሉ አይደሉም ፤ ታዲያ ይህ በዓለ ሲመት ለማነው የተዘጋጀው? የሚያስብል ሁኔታን ይመለከታሉ ፤ እኛ እንኳን የመጣነው 4 ኪሎ ስላሴ ቤተክርስትያን ግቢ ውስጥ እንደ ቦሌው ሌላ ሃውልት ካቆሙ ሃውልቱን ለማፍረስ እንጂ መርሀ ግብሩን ለመሳተፍ አልነበረም ፤ ማን ያውቃል ሀውልቱን እንደማይደግሙት ?

ሰዎች ምን አሉ ?



የመጀመሪያ አስተያየት ሰጪ
''አይቴ ለነውር ብሔረ ሙላዱ
በውስተ ኩሉ ብሔር እስመ ከመ ነግድ ይሄሉ
ጠይቆተ ዝኒ ነገር ከመ ይትገሀድ ለኩሉ
ኃጥእ ይሣለቅ ላዕለ ጻድቅ ከመ ዘንጹሕ ወሠናይ ባህሉ፥
እስመ እንዘ ሠርዌ በውስተ ዐይኑ  
እምነ ቢጹ ብሩህ አውጽኦተ ሐሠር ያስተዴሉ።
አይሁድኒ ሐዋርያተ በጽእሎቶሙ ጸዐሉ፥
ጊጉያነ ወአብዳነ ወሐሳውያነ እንዘ ይብሉ፥
ወብእሴ ጻድቀ ዘሀለዎሙ ይስቅሉ፥
እንዘ ውጹኣን እምነ ጽድቅ በጽድቀ ርእሶሙ ይትሌዐሉ። '' 
መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ንጉሤ።

መከራና ስደትን በቃችሁ ይበለን


ይህ ጉዳይ እንደ አንድ ዜጋ ሊያሳስበን ይገባል
ከጊዜ ለኩሉ

በታንዛኒያ የ43 ኢትዮጵያውያን ቀብር
(አንድ አድርገን ሐምሌ 11 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ከጥቂት የሰቆቃ ዜና እረፍት በኋላ ዳግም የወገኖቻችንን የስቃይ እና ሞት ባልተለመደ አኳኋን ካልተለመደ ስፍራ ሰማን። ከጊዜ ወደ ጊዜ ወገኖቻችንን እዚሁ እትብታቸው በተቀበረበት፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ዘመድ አዝማድ ከሚኖሩበት ፣የልጅነት ትውስታቸው አሻራ ካረፈበት፣ የአመት በዓል ግርግሩ ከሚደምቅበት፣ ቅዳሴው በተመሳሳይ ከሚሰማበት……አገር ይልቅ የባዕዳንን ምድር እየመረጡ በስደት ሕይወት መከራቸውን መጋት ቀጥለዋል። በቀድሞ ጊዜ፣ በዚያ ትውልድ፣ በደጉ ዘመን ኢትዮጵያዊ መባል ኩራትና ክብር እንዳልነበር ሁሉ አሁን የማንም መሳቂያና መሳለቂያ ለመሆን በቃን። በንጉሰ ነገስቱ ጊዜ አንድም ኢትዮጵያዊ እንኳን እንጀራ ፍለጋ ይቅርና ለትምህርትም ቢሆን ወደ ውጭ አገራት ተልኮ የቀረ አልያም በሌሎች አገራት ጥገኝነት የጠየቀ እንዳልነበር ታሪክ ምስክር ነው፡፡ በደርግ ዘመን በፖለቲካ አለመረጋጋትና በህይወት የመኖር ዋስትና ማጣት ምክንያት የተጀመረው የሕዝብ ስደት ማዕበል አሁን ይበልጥ ተባብሶ ቀጥሏል።

Saturday, July 14, 2012

የአልፎንዙ እሾሆች


ከተስፋዬ አዳነ 
(አንድ አድርገን ሐምሌ 7 ፤ 2004ዓ.ም)፡-መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአርባ በላይ ስሟ የተጠቀሰ፣ ለብዙዎች የነጻነት ተምሳሌት የሆነች ፣አውሮፓውያን የካህኑ ንጉሥ ሀገር እያሉ የሚጠሯት፣ አፍሪካውያን የጥንካሬያቸው ምስክር የሚያደርጉት የደጋግ ህዝቦች መኖሪያ የቅዱሳን ምድር ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ!!!

ኢትዮጵያችን በተለያዩ ምክንያቶች ቅድስት ሀገር ተብላ ተጠርታለች፣ ምድራችን ክርስትናን ቀድመው ከተቀበሉ ሀገራት መካከል በቀዳሚው ረድፍ ትገኛለች፤... ያኔ ገና መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት እነ ጴጥሮስ በተለያየ ልሳን ህዝቡን ስለ ክርስቶሰ በሚሰብኩበት ወቅት ኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትሯን ልካ ስለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰብካለች፣ በራሷ አፍሪካዊና ጥቁር ኢትዮጵያዊ ከክርስትና ጋር ተዋውቃለች፤ እኛ ኢትዮጵውያን እንደሌሎቹ ከጣኦት አምልኮ አይደለም ወደ ክርስትና የተሸጋገር ነው፤ ክርስትናን የተቀበልነው እግዚአብሔርን ስናመልክ ቆይተን ነው ፤ ለዚች ሀገርም መጤዎች አይደለንም፡፡ኢትዮጵያ ያለ አምልኮተ እግዚአብሔር የኖረችበት የለም፣ ያለ ደም ክርስትና የተሰበከባት ይህች ቅድስት ምድር ለቅደስትነቷ ምንጭ ለጥንካሬዋ መሰረት፣ ለስልጣኔዋ መነሻ የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስትያንን መነሻ በማድረግ የተለያዩ ወረራዎች ተካሂደውባታል፡፡ ወረራዎቹም አስከፊ የሆነ የሰው ልጅ እልቂትንና ከባድ የሆነ የቅርስ ውድመትን አስከትለዋል፤ እነዚህ ወቅቶች በዋናነት አምስት ሲሆኑ ዘመነ ሰማዕታት ወይም የስደት ዘመን ተብለው በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ይጠራሉ፡፡