- “ኢጣልያኖች የምኒሊክን ሐውልት ሲያወርዱ የተመለከተ አንድ ትንሽ ልጅ ጮሆ አለቀሰ፡፡ ኢጣልያኖችም ለምን እንደጮህና እንዳለቀሰ ልጁን ጠየቁት፡፡ልጁም የንጉሴን ምስል ስላወረዳችሁ ነው አላቸው፡፡ ኢጣልያኖችም ከሙሶሎኒ ሌላ ንጉስ እንደሌለ ነግረውና ገርፈው አባረሩት…” ኒውዮርክ ታይምስ የካቲት 13 ቀን 1937 ዓ.ም እትም
(አንድ አድርገን ህዳር 20 ቀን
2004 ዓ.ም)፡- ለዚች ሀገር እጅጉን ብዙ ውለታ ከዋሉት የሀገር
መሪዎች ግንባር ቀደም መሪ ዳግማዊ አጼ
ምኒሊክ ናቸው
ቢባሉ ማጋነን አይሆንም፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ሚኒሊክ ከጂቡቱ አዲስ አበባ ድረስ ተዘርግቶ ማየት የፈለጉት ከ10 ዓመት በላይ
በርካታ ዋጋ የከፈሉበትና የደከሙበት የባቡር ዝርጋታው በርካታ መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የአዲስ አበባ ምስራቅ
መውጫ አቃቂ ከተማ እንደደረሰ ህይወታቸው እንዳለፈ ታሪክ ይናገራል
፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርም የዛሬ 100 ዓመት ሚኒሊክ ሊያዩት ያሰቡትን ባቡር እሳቸውም ማየት ቢመኙትም ስራው በእሳቸው ዘመን
ተጀምሮ ስራው ሳይጠናቀቅ ለህዝቡ ሚስጥር በሆነ ህመም ህይወታቸው
ሊያልፍ ችሏል፡፡ የሚኒሊክ ሞት ህዝቡን ክፉኛ ይረብሸዋል ሀገሪቱ ላይም አለመረጋጋት ያመጣል ተብሎ ስለታሰበ ከሞቱ በኋላ ከ1902 -1906 ዓ.ም ድረስ ሞታቸው ለህዝብ
ሚስጥር ነበር በማለት ታሪክ ይነግረናል ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊም ህዝቡ ነሐሴ 15 2004 ዓ.ም አረፉ ተብሎ ቢነገረውም ፤ ሌሎች ጉዳዩን በቅርብ እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ከሞቱ
40 ቀን አልፏቸው ሞታቸው ይፋ እንደወጣ ይናገራሉ፡፡