
በአውደ ምህረት ላይ የእግዚአብሔርን ቃል እንደማስተማር ራሳቸውን ነጻ ለማድረግና በመጣር “ ኢንተርኔት ላይ አንድ
አድርገን የሚባል ድረ-ገጽ ስሜን እያጠፋ ነው ፤ ባልሰራሁት ስራ እየወነጀለኝ ነው” በማለት ተናረዋል ፤ “አንድ አድርገን” ከዚህ
በፊት ያደረጉትን ነገር ከመዘገብ ውጪ ስማቸውን አላጠፋችም ፤ አባ ናትናኤል ከተሃድሶያውያን ጋር በማበር ለአውደ ምህረት በማይመጥኑ
ሰዎች አማካኝነት ሲያስፈነጩበት ነበር ፡፡
ምዕመኑ እኝህን በመሰሉ ሰዎች መታወክ መቻል የለበትም የሚል አቋም አለን ፤ “አንድ አድርገን” ፍርድ ቤት በሰሩት
ስራ በወንጀል ተከሰውና በፖሊስ ተይዘው ወደ ሀዋሳ ሲሄዱ የሆነውን ነገር ተናግራለች ፤ ፤ ምግባራቸውን እና ስራቸውን አደባባይ
ላይ አስቀምጣለች ፤ ወደፊትም በሄዱበት ሁላ ከእኩይ ስራቸው ካልተመለሱ የሰሩትን ፤ ለመስራት ያሰቡትን በመከታተል ሰዎች ዘንድ
መረጃ ታደርሳለች ፤ ቤተክርስትያኒቱን እንደ ምስጥ ሆነው ከውስጥ የሚቦረቡሯን ሰዎች አይታ ዝም ማለት አይቻላትም ፤ እኛን
መስለው ነገር ግን ከእኛ ያልሆኑትንም ሰዎች በመከታተል ሚስጥር ስራቸውን በአደባባይ ታሰጣለች፡፡
የዛሬ አመት እኝህን አባት አንቀበልም ያለው ምዕመናን በግድ እንዲቀበል ተደርጎ ነበር ፤ መላከ ገነት አባ ናትናኤል መላኩ አሁን ደግሞ የትኛው ቤተክርስቲያን ይመድቧቸው ይሆን ? እኛ እንደ ቀድሞ ወደ ቦታቸው እንዳይመልሷው እንሰጋለን፡፡
ቸር ሰንብቱ
yih zegeba ewnet silemohunu min mereja ale? please if there is any?
ReplyDelete