Friday, November 2, 2012

የሃሪኬን ዐውሎ ነፋሳት መነሻቸው ከኢትዮጵያ መሆኑን የናሳ ሳይንቲስት አረጋግጠዋል


በፍቅር ለይኩን
(አንድ አድርገን ጥቅምት 23 2004 ዓ.ም ) ፡- የአሜሪካን በተለያዩ ጊዜያት የመቱ አውሎ ንፋሳትና ወጀቦች መነሻቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራራማ ቦታዎች መሆናቸውን የናሳ ሳይንቲስቶች ጥናቶች በተለያዩ ጊዜያት ሲያመለክቱ ነበር፡፡ ኦውን ኬሊ የተባሉ የናሳ ተመራማሪ 2006 . ጥናታቸው፡- A lot of hurricanes start out over the Ethiopian Mountains. Air steadily flowing over those mountains and they cause waves in the air. በማለት የሄሪኬን አውሎዎችና ወጀቦች መነ ሻ ኢትዮጵያ መሆኗን በጥናታቸው አመልክተዋል፡፡

ሌላኛው የናሳ ሳይንቲስትና ተመራማሪ የሆኑት ስኮት ብራውን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሄሪኬን መነሻዎች ከባሕሮችና ከውቅያኖሶች ዳርቻዎች ነው ከሚለው በተጨማሪ ለሄሪኬን መከሰት ከምዕራብና ምስራቅ አፍሪካ የሚነሱ ንፋሳትና አውሎዎችም የብዙዎች ሳይንቲስቶችና አጥኚዎች ትኩረትን እየሳቡ መምጣታቸውን በጥናታቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

Wall Street Journal የናሳ ሳይንቲስቶችን ጥናት ዋቢ በማድረግ እንዳስነበበው ደግሞ አሜሪካንን የመታው ‹‹ሄሪኬን አርል›› የተባለው አውሎና ወጀብ መነሻው ከኢትዮጵያ እንደነበር በወቅቱ አስነብቦ ነበር፡፡ እንዲሁም እ.. 2003 . የተከሰተው ‹‹ሄሪኬን ኢሳቤላ›› የሚል መጠሪያን ያገኘችው አውሎና ወጀብም መነሻዋ ከኢትዮጵያ እንደነበር ተገልጾ ነበር፡፡

2008, ABC News, “The Real Home of Hurricanes: Ethiopia?” በሚል የሀሪኬን አውሎና ወጀብ ከኢትዮጵያ ከየትኛው ቦታ እንደሚነሳ በአኒሜሽን በተደገፈ ምስል ጭምር ዘግቦ ነበር፡፡ የዘንድሮው አሜሪካን ምስራቃዊ ግዛት በመምታት ወደ ሰሜናዊ አሜሪካ ግዛትና ካናዳ እየገሰገሰ ያለው ሄሪኬን ሳንዲ መነሻው በትክክል ከየት እንደሆነ ባይገለጽም ከምስራቃዊ አፍሪካ ግዛት ሊሆን እንደሚችል ግን ያለፉትን የሄሪኬን መነሻዎች ጥናቶች ዋቢ በማድረግ አንዳንድ ሳይንቲስቶች እየተናገሩ ነው፡፡

ስለ ሄሪኬን ሳይንሳዊ ጥናቱና መረጃው እንዳለ ሆኖ ነፋሳትን፣ አውሎዎችንና ወጀቦችን በተመለከተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት አስራ ሁለት የንፋስ መስኮቶች እንዳሉና ከእነዚህ የነፋሳት መስኮቶች መካከል አራቱ ብቻ የምሕረት ሲሆኑ የተቀሩት ስምንቱ የመዓት ወይም የቁጣ የነፋሳት መስኮቶች/ መዛግብቶች መሆናቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንቶች ይናገራሉ፡፡ የክርስትና ሃይማኖት መመሪያ የሆነው ቅዱስ መጽሐፍም በዮሐንስ ራእይ፡- ‹‹በምድር ላይ ምንም ዓይነት ንፋስ በባሕርም ሆነ በምድር ላይ እንዳይነፍስ መላእክት አራቱን የምድር ንፋሳት ያዙ፡፡› (ራእይ ፯፣፩) በማለት አራት የነፋሳት መስኮቶች እንዳሉ ቅዱስ ዮሐንስ በራእይ ፍንጭ መስጠቱን የራእይ መጽሐፍ ይናገራል፡፡


እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ገለጻ ከሆነ በምስራቅ ወይም በአዜብ በኩል የሚነሱ ንፋሳትና አውሎዎች የመዓትና የቁጣ መገለጫዎች እንደሆኑ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይናገራሉ፡፡ በዚህ እውነት መሠረትም በተደጋጋሚ አሜሪካን ግዛቶችና በዙሪያዋ ያሉትን ሀገራት የመቱ አውሎዎችና ነፋሳት መነሻቸው ከምስራቅ/ከአዜብ ነው የሚለው ጥናት ትክክለኛነትን የሚያረጋግጥ ይመስላል፡፡

ስለ ምስራቅ ነፋሳት ጽኑነትና አደገኛነት ለአብነትም ያህል ከክርስቶስ ልደት በፊት መላውን ዓለም የመታውን ጽኑ ራብ አስቀድሞ በራእይ የተገለጸለት ዮሴፍ ስለ ድርቁና ክፉ ስለሆነው የራቡ ዘመን በግብፅ ሳለ የተመለከተውን ራእዩን ሲገልጽ፡- ‹‹በምስራቅ ንፋስ የተመቱ ሰባት እሸቶች ወጡ፡፡›› በማለት በምድር ላይ ለሰባት ዓመት ጸንቶ የቆየውን ራብ አስቀድሞ እንደተነበየ ሙሴ በዘፍጥረት መጽሐፍ ገልጾታል፡፡

የክርስትና ሃይማኖት መሠረት የሆነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም በመዋእለ ስብከቱ ለአይሁዳውያን ‹‹… በምስራቅ ንፋስ ሲሆን ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፣ ይሆንማል፡፡›› (ሉቃ ፲፪፣፶፭) በማለት በምስራቅ የሚመጣው ንፋስ ለምድሪቱ ክፉ አደጋ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ሰማያትን በማንበብ ትተነብያላችሁ፣ ግና የዘመኑን ምልክት በቅጡ ለማንበብ አለመቻላቸውን/መስነፋቸውን በመገሰጽ በቁጣ እንደተናገራቸው ወንጌላዊው ሉቃስ ጽፎልናል፡፡

አይሁዳዊው ሊቀ ነቢያት ሙሴም ሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ያወጣባቸውን ተዓምራቶችና የኤርትራ ባሕርን ያሕዌ እንዴት እንደከፈለው በዘጸአት መጽሐፍ ሲገልጽ፡- ‹‹ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምስራቅ ነፋሳት አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፣ ባሕሩንም አደረቀው፣ ውኃውም ተከፈለ፡፡›› በማለት ስለ ምስራቅ ነፋሳት ኃያልነትና እግዚአብሔር በድንቅ ተዓምራት ሕዝቡን እንዳሻገራቸው በማስታወስና እንዲሁም ጠላቶቻቸው የሆኑትን ግብፃውያንንም እንዴት በእግዚአብሔር መዓት ቁጣ በባሕር እንደተከደኑ ሲገልጽ ደግሞ፡-‹‹ነፋስ አነፈስህ ባሕርም ከደናቸው፣ በኃይለኞች ውኆችም እንደ አረረ ሰጠሙ፡፡ ይለናል፡፡ (ዘጸ ፲፭፣፲፤ ፲፬፣፳፩)

ንፋሳት የእግዚአብሔር የቁጣ መዓት መገለጫዎች እንደሆኑ የሚናገሩ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ፡፡ ‹‹ወጥመድን በኃጥአን ላይ ያዘንባል፣ እሳትና ዲን አውሎ ንፋስም የጽዋቸው ዕድል ፋንታ ነው፡፡ በሌላ ስፍራም፡- ‹‹እሳትና በረዶ አመዳይም ውርጭ ቃሉን የሚያደርግ አውሎ ንፋስ፤ ተናገረ አውሎ ንፋስም ተነሣ ሞገድም ከፍ ከፍ አለ፡፡››
በማለት መዝሙረኛው ዳዊት እነዚህ የተፈጥሮ ኃይላት የእግዚአብሔር ቃል/ትዕዛዝ ተገዢዎች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ (መዝ ፶፣፫፣ ፸፯፣፲፰፣ ፻፯፣፳፭፣ ፻፵፰፣፰)፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስም፡- ‹‹እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል የክንዱም መውረድ በሚነድድ ቁጣ ነውና በምትበላ እሳት ነበልባል በአውሎ ነፋስም፣ በወጨፎ፣ በበረዶ ጠጠርም ይገለጻል፡፡›› ይለናል፡፡ (ኢሳ፴፣፴) ‹‹እነሆ የእግዚአብሔር አውሎ ንፋስ እርሱም ቁጣው የሚያገለባብጥ አውሎ ንፋስ ወጥቶአል የዓመፀኞችን ራስ ይገለብጣል፡፡›› (ኤር ፳፫፣፲፱)
ንፋሳት ከመዓት ውጭም የእግዚአብሔር ክብር፣ ኃይል፣ ክንድና ጽናት መገለጫዎች እንደሆኑ መዝሙረኛው ዳዊት ሲናገር ‹‹እግዚአብሔር በኪሩብ ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በነፋስ ክንፍም ሆነ እግዚአብሔር ታየ››፣  ‹‹የነጎድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነበር፣ መብረቆችህ ለዓለም አበሩ፣ ምድር ተናወጠች፣ ተንቀጠቀጠችም፡፡›› ይለናል፡፡ (፪ሳሙ ፳፪፣፲፩፤ መዝ ፸፮፣፲፰)፡፡

በዘንድሮ ምስራቃዊው የአሜሪካን ግዛት በመምታት ወደ ሰሜንና ወደ ካናዳ እየገሰገሰ ያለውን ‹‹ሀሪኬን ሳንዲ›› የሚል ስያሜ
ያገኘቸውን አውሎና ወጀብ ያስከተለችውን ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ውድመት የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
በሰዓት 80 ማይልስ በላይ የሚጓዘው ይኸው አውሎ ንፋስ ኃይለኛ ወጀብና ዝናብ ጭምር የቀላቀለ መሆኑንና እስካአሁን ድረስ 50 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን እንዲሁም በዚሁ አደጋ 700 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ብርሃን አጥቶ በጨለማ ውስጥ መዋጣቸው እየተነገረ ነው፡፡
በዚሁ “super storm” በአሜሪካ ታሪክ አቻ ያልተገኘለት፣ እጅግ አስከፊና ታይቶ የማይታወቅ በተበላው በሀሪኬን ሳንዲ አውሎና ወጀብ የተነሳ ስልክ፣ መብራትና የትራንስፖርት አገልግሎት በከተማዋ መቋረጡ የመገናኛ ብዙኃን ይፋ አድርገዋል፡፡
በተለምዶ The October Surprisings/ የጥቅምት ወር አስገራሚ ክስተቶች/ ድንገቴዎች በሚል .. 1970ዎቹ ጀምሮ በአሜሪካውያን ጋዜጠኞች ዘንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅትን ተከትሎ የሚከሰቱትን አስገራሚና አስደንጋጭ ተፈጥሮአዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ክስተቶችን ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ያልተጠበቁ ክስተቶችን ይዘግባል፡፡ ከሁለት ወር በፊት በሀሬኬን አውሎ ንፋስ አደጋ ቅድም ትንበያ የተነሣ የባራክ ኦባማ ተቀናቃኝ የሆኑት ሩሚኒ በፍሎሪዳ ሊያደርት የነበረውን ኮንቬንሽን በመሰረዛቸው በምርጫ ዘመቻቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አድርሶባቸው
እንደነበር ተገልጾአል፡፡

ከዚሁ ከሃሪኬን ሳንዲ አውሎ ንፋስ ጋር በተያያዘ በዘንድሮ የአሜሪካ ምርጫ የሀሪኬን ሳንዲ አውሎ ንፋስ ያስከተለው ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ the October Surprising/ አስገራሚ የጥቅምት ክስተት/ድንገቴ በሚል ሊጠቀስ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ በዚሁ ተፈጥሮአዊ አደጋ የተነሳ ባራክ ኦባማም ሆኑ ተቀናቃኛቸው ሩሚኒ የምርጫ ዘመቻቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል፡፡ ይህ አደጋ በተለይ ለባራክ ኦባማ የምረጡኝ ዘመቻ ፈታኝ የሆነ ክስተት ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ከወዲሁ እየገለጹ ነው፡፡

5 comments:

  1. በዚሁ አደጋ ከ700 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ብርሃን አጥቶ በጨለማ ውስጥ መዋጣቸው እየተነገረ ነው፡፡ Please correct the number. US population is less than 300 million.

    ReplyDelete
    Replies
    1. hi man i think you donot counting number u.s has 350 million people

      Delete
  2. - መብራት የተቋረጠባቸው የተባለው ወደ ሰባት ሚሊዮን ቢባል ይመሰላል ፡፡ ችግር ላይ የወደቀውን ህዝብ ቁጥር እንዲህ ከገመቱት ፣ ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር ቻይናን ሊያስመስላት ነው ፡፡
    - ሌላው በዚህ አደጋ የሚደንቀው በአካባቢ ያለው ህንጻ ሁሉ ሲወድምና ሲጋይ የድንግል ማርያም ሐውልት ብቻዋን ቆሞ መገኘቱ ነው ፡፡ ነፋስ መከላከያ ኃይል ይኖረው ይሆን ወይስ የአምላክ እናት መታሰቢያ ስለሆነ ግንባታው ላይ ለየት ያለ ጥንቃቄ ተደርጎለት
    - አዲስ በሽታ ሲመጣ ምንጩ አፍሪካ ፣ አሁን ደግሞ የማዕበልና የሞገድ መነሻው ሲባል አፍሪካ ከተባለልን ፤ ነገሩን በንቃት መከታተል ደግ ነው ፡፡ እንደተባለው እውነት መነሻው ከወደዚያ ከሆነ ፣ እነርሱ በኑክሊየራቸው ሲያስፈራሩን እኛም በንፋሳችን ማለት እንዲያስችለን የመስኮቶቹን ቁልፍ ለመቀበል እስቲ በጸሎትና በእምነት አግዙ
    - ምድራዊ ቁጣዎች ተበራክተዋል ፤ የሰው ልጅም በገፍ የሚሞትበት ተፈጥሮአዊና ሰው ሰሯሽ መንገድ ጨምሯል ፡- የመሬት መንቀጥቀጥና የህንጻ መደርመስ ፣ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ፣ የባህር ሞገድ ፣ የነውጠኞች ቦንብ ፣ ሰደድ እሳት ... ታድያ መጽሐፍ የሚገልጸው ዋዜማ ወይስ አጋጣሚ ይባል ይሆን

    ReplyDelete
  3. even if it is what relevancy does it have? what benefit does this has for Ethiopia or the world?
    weapon of mass destruction belew yemetuben ende?? egna yemenatefaw anso endih yale yeteleat wore bananafes tiru new, kehonem lenetsely yasfelegal Geta mihretun endiyaword.
    agerachenen ye kuta sayhon yemeheret meleketegna yaderegelen!!!!

    ReplyDelete
  4. ውድ አንባቢያን፥ የምሥራቅን ነፋስ በማስነሳት የምድርን አማጽያንን በተለያየ ጊዜ እንደሚቀጣ እግዚአብሐር ደግሞ ደጋግሞ በቅዱስ መጽሐፍ ገልጿል። የቅኔው ወርቅ ቅጣት ስለ ጽዮን ይፈጸማል ነው። ጽዮን አይሁድ አይምሰላችሁ። ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ጽዮን አሥራቷ ኢትዮጵያ ናት። ፍርድም ከጽዮን ነው። እግዚአብሒር ቃል ገብቷልና። አሁን ደግሞ የኛ የኢትዮጵያውያን አመጽ በዝቶ ወደሰማይ ደርሷልና፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ሲባል የሚሰማም ጠፍቷልና ባለፈው ከሰማይ የወረደው አይነት እሳት በኢትዮጵያ በከባድ ሁኔታ እንዳይወርድ አጥብቃችሁ ጸልዩ።

    ዘፍጥረት ም ፵፩ ፣ ፮ - እነሆም ከእነርሱ በኋላ የሰለቱና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት እሸቶች ወጡ፤
    ዘጸአት ፲፣ ፲፫ - ሙሴም በግብፅ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ እግዚአብሔርም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ ማለዳም በሆነ ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።
    ዘጸአት ፲፬፣ ፳፩ - ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም አደረቀው፥ ውኃውም ተከፈለ።
    መዝሙር ፵፰፣ ፯ - በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ።
    ትንቢተ ኤርምያስ ፲፰፣ ፲፯ - በጠላት ፊት እንደ ምሥራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።
    ትንቢተ ህዝቅኤል ፲፯፣ ፲ - ተተክሎስ፥ እነሆ፥ ይከናወንለት ይሆንን? የምሥራቅ ነፋስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።
    ትንቢተ ህዝቅኤል ፲፱፣ ፲፪ - ነገር ግን በመዓት ተነቀለች ወደ መሬትም ተጣለች የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱዎች በትሮችዋም ተሰበሩና ደረቁ፥ እሳትም በላቻቸው።
    ትንቢተ ሆሴዕ ፲፫፣ ፲፭ - በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆን የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የእግዚአብሔር ነፋስ ከምድረ በዳ ይመጣል፤ ምንጩንም ያደርቃል፥ ፈሳሹንም ያጠፋል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።
    ትንቢተ ዮናስ ፬፣ ፰ - ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና። ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ።

    ወስብሃት ለእግዚአብሔር።

    ReplyDelete