Thursday, June 29, 2017

በእንተ ፍልሰተ አጽሙ ለመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ

የሊቅነቱን ማዕርግ ከፍ አድርገው ከሰቀሉት የቅርብ ጊዜ ሊቃውንት እንደ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ያለ ስመ ጥር አላውቅም፡፡ ሊቅነትን ከምግባረ ሃይማኖት አስተጻምረው፣ አዋሕደው እና አስማምተው የያዙ ዐይናማ ሊቅ ናቸው፡፡ እኒህ ኹለቱን አንድ ላይ ለማስኬድ ብዙ ጊዜ መቸገር አለና! በአካለ ሥጋ በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. ከእኛ ቢርቁም ደማቆቹ የብርዕ ትሩፋቶቻቸው ዛሬም ያበራሉ፡፡ ኵኲሐ ሃይማኖትን እና መድሎተ አሚንን እንደ መጻሕፍተ ሊቃውንት ያልተመለከተ ሊቅ ይኖራል ብሎ መድፈር አይቻልም፡፡ በጽሑፋቸው ውስጥ የሊቁን የትሕትና ቁመና ስንመለከት እጅ እንነሳዋለን፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ወደር የማይገኝለት የሚንቀለቀል ቅናትም ያሳዩናል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በነገረ መለኮት ትምህርታቸው እንዴት የረቀቁ ሊቅ እንደነበሩ ቁልጭ ብለው ይነበባሉ፡፡ ዘመን ተሻጋሪ የኾነው ሥራቸው ዛሬም እንደመብራት ያበራል፡፡ የክህደትን ጨለማ ይገላልጣል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ትጋት የሚባለውን ሽልማት አበርክተውላቸዋል፡፡ በሽልማታቸውም መልሰው ሸልመውናል፡፡ በደረቡልን ካባ ሲበርደን እንሞቅበታለን፤ ሲሞቀን እንበርድበታለን፡፡

የሐዋሳ ተርቦች እየተናደፉ ነው!By :- D/n Abayneh Kasse
"አምላክህ እግዚአብሔር የቀሩት ከፊትህም የተሸሸጉት እስኪጠፉ ድረስ ተርብ ይሰድድባቸዋል" ዘዳ ፯፥፳።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሐዋሳ ለመላዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አርአያ የሚኾን ተግባር በማከናወን ሥራ ተጠምዳለች፡፡ ለአቅመ መናፍቅ ያልደረሱ ነገር ግን እንደ ዲያቆን ታደሰ ወርቁ አጠራር ለሐራጥቃ "አድራሽ ፈረሶች" የኾኑ ሳይሠሩ የሚጎርፍላቸው ገንዘብ እንቡር እንቡር እንዲሉ ዕድል የሰጣቸው ስለኾነ ለጊዜውም ቢኾን የቤት ሥራችን ኾነዋል፡፡ አድራሽ ፈረስ ማለት ተሸካሚ እንደማለት ነው፡፡ ልክ የወባ በሽታን እንደምትሸከመው ቢንቢ ወይም ትንኝ መኾናቸው ነው፡፡ በአፍርንጅ ቃል "vector" የሚለው ሳይገልጠው አይቀርም፡፡ ዛፍን ለመቁረጥ ቅርንጫፎቹን መመልመል እንደሚቀድመው ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ቅርንጫፎቹን በመመልመል ወደ ጉንዱ ትሔዳለች፡፡ የወባን በሽታ ለመከላከል ወባ ማራቢያዎችን ማጽዳት እንደሚገባው ማለት ነው፡፡ ሐዋሳዎች በዚህ ጉዳይ ላይ በልዩ ትኩረት እየሠሩ ሲኾን በሚያኮራ ውጤትም ወደ ከፍታው ማማ እየተረማመዱ ነው፡፡

Tuesday, June 20, 2017

ጠባቂ የሚሹ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች
17 Jun, 2017
By ምሕረተሥላሴ መኰንን  

  • << በቅርሶች ጥበቃ ሁሉም አካል መረባረብ ያለበት ሲሆን፣ ትውልዱም ለታሪኩና ለባህሉ ተቆርቋሪ መሆን ይገባዋል፡፡ ከየቤተ ክርስቲያኑና  የሚሰበሰቡ ቅርሶች በአግባቡ ካልተጠበቁ ዋጋ የለውም፡፡ አሳልፈን እየሰጠናቸው ያለነው እኛው ነን፤›› አባ ብስራተአብ

ኢትዮጵያ በዓለም የሥነ ጽሑፍ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ጥንታውያን መጻሕፍትና የነገሥታት ደብዳቤዎች መካከል 14ኛው ክፍለ ዘመን አርባዕቱ ወንጌል፣ 15ኛው ክፍለ ዘመን የጳውሎስ መልዕክቶች፣ 15ኛው ክፍለ ዘመን ግብረ ህማማትና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኅትመት መጽሐፍ መዝሙረ ዳዊት ይጠቀሳሉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በተዘዋዋሪ ከመዘገበው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ያደረጉት ንግግር በተጨማሪ ሦስት የነገሥታት ደብዳቤዎችም (አፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ የላኩት ደብዳቤ፣ አፄ ምኒልክ ለሞስኮው ቄሳር ዳግማዊ ኒኮላስ የላኩት ደብዳቤና ከሸዋው ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ለእንግሊዟ ንግሥት የተላከው ደብዳቤ) ተመዝግበዋል፡፡ አምስቱ በማይክሮ ፊልም የተቀረፁ ጥንታውያን መጻሕፍት ደግሞ ታሪክ ምኒልክ፣ መጽሐፈ ሔኖክ፣ ታሪክ ነገሥት፣ ቅዳሴና ፍትሐ ነገሥት ናቸው፡፡

Monday, June 12, 2017

በሰዓሊተ ምሕረት ጉዳይ ያልተመለሱልን ጥያቄዎች!

·        ፓስተር ኦላቭ (Rev.Dr Olav Fyske የኖርዌይ ሉተራን እምነት ፓስተር፣ የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ) ጸሎት አድርጌያለሁ ብሎ ሲፈጽም እየተጠራሩ መቀባባት ተጀመረ።
·        የእኛዋ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ / አባ /ማርያምም ቀርበው ተቀቡ:: እርሳቸው ደግሞ ፓስተር ዮናስ ይገዙን (በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የመካነ ኢየሱስ ፕሬዘዳንት) በአደባባይ ቀቡ።
በሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተፈፀመው ድርጊት ይፋ ከሆነ ጀምሮ ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል። ጉዳዮቹን አድበስብሶ ለማለፍ የሚደረገው ጥረት ደግሞ የበለ ለምን እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን በመላው ዓለም በሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ፈጥሯል።
ይህ ጉዳይ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እኔንም ይመለከተኛልና እስኪ የተፈጠሩትን ጥያቄዎችን መልስ ለማግኘት አንድ ሰው ላነጋግር ብዬ ተነሳሁ። እናም በቀጥታ ጄኔቫ ደውዬ / ንጉሡ ለገሠ (በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ) ጋር በስልክ ተነጋገርኩ። / ንጉሡን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲህ ያለ ጫና ለምን አሳደረ? ይህ አካሄድ ሕዝቡ በምክር ቤቱ ላይ ያለውን አስተሳሰብ አያበላሽውም ወይ? አልኳቸው። እርሳቸውም ላቀረብኩላቸው ጥያቄ በአክብሮት መልስ ሰጡኝ። የሰጡኝን መልስ በራሴ መንገድ ለንባብ እንዲሆን ፅፌ አቅርቤዋለሁ። ጽሁፉ ያልተመለሰላችሁን ጥያቄ ከመለሰ መልካም ነው። ከዚያ በተረፈ ግን በሌሎቹ መምህራን የተሰጠውን ጠንካራ አስተያየት በማጠናከር እንደፃፍኩት ይታወቅልኝ።