Monday, December 29, 2014

በመንበረ ፓትርያርኩ ቅ/ማርያም ገዳም በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ መመዝበሩ ተገለጸ



አንድ አድርገን ታኅሳስ 20 2007 ዓ.ም
(Addis Admass:- )በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ የፓትርያርኮች መንበር (መንበረ ፕትርክና) በኾነችው ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብና ንብረት በአስተዳደር ሓላፊዎችና ሠራተኞች መመዝበሩን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ጥቆማው የቀረበው፣ የገዳሟ ማኅበረ ካህናትና የልማት ኮሚቴ የቤተ ክርስቲያኒቱን የገንዘብና የንብረት አሰባሰብ በተመለከተ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር እንዲዘረጋ የገዳሟ ልማት ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ ለኾኑት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ባቀረቡት ማመልከቻና ሪፖርት ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ መተዳደርያ ቃለ ዐዋዲና ደንቡን መሠረት አድርጎ በሀገረ ስብከቱ የተዘጋጀው የገንዘብ ቆጠራ፣ የንብረት አመዘጋገብና አጠባበቅ መመሪያ የካህናቱን፣ የምእመናኑንና የእያንዳንዱን ሠራተኛ የሥራ ድርሻና ተጠያቂነት በግልጽ ማስቀመጡን የጠቀሱት ማኅበረ ካህናቱ÷ የገዳሟን ገንዘብና ንብረት የመቆጣጠርና የመከታተል መብታቸው በአስተዳደሩ ሓላፊዎች ተነፍጓቸው የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራና የንብረት ቁጥጥር ለማድረግ ሳይችሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

Tuesday, December 23, 2014

እነሆ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ደስ አላት





አንድ አድርገን ታኅሳስ 15 2007 ዓ.ም


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ክፍል የተቋቋመው የዛሬ 50 ዓመት በ1957 ዓ.ም በስድስት ተማሪዎች ብቻ ነበር፡፡ ዛሬ ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ በታሪኩ ከፍተኛ የሆኑት 287 ሐኪሞችን ባሳለፍነው ሳምንት ታኅሳስ 12 2007 ዓ.ም 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ልዩ ጊዜ ማስመረቅ ችሏል፡፡ ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል ከ140 ተማሪዎች በላይ የማእረግ ተመራቂዎች ነበሩ፡፡ እነሆ በዚህ ዓመት ከተመረቁት ከ100 በላይ ሐኪሞች በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን በግቢ ጉባኤ ታቅፈው ትምህርታቸውን ከእምነታቸው አንድ በማድረግ ቀን በትምህርት ለሊት በአገልግሎትና በስራ ላለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታትን በርካታ ውጣውረዶች ካሳለፉ በኋላ የዘመናት ህልማቸውን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሊያዩ ችለዋል፡፡

Sunday, December 21, 2014

ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

  • / ሲኖዶሱ በአድባራት ሓላፊዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ  ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነውፓትርያርኩ

(አዲስ አድማስ ታህሳስ 11 2007 ዓ.ም):-  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ማኅበር ላይ ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ባላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አፈጻጸም ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል ፓትርያርኩ ማገዳቸው ተገለጸ፡፡ ፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር 30 ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ቤት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› በማለት ያገዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተካሔዱ ጉባኤዎች÷ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል፤ ይህም አነጋገር ጉባኤውን ቅር አሰኝቷል፤›› ያላቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

Friday, December 19, 2014

በባህርዳር የሚገኝው መስቀል አደባባይ ታቦት ማደሪያ ‹‹ለልማት ይፈለጋል›› መባሉን ተከትሎ በተካሄደ ተቃውሞ ሰልፍ የንጹሀን ደም ፈሰሰ


አንድ አድርገን ታኅሳስ 11 2007 ዓ.ም


ትላንት እለተ አርብ ታኅሳስ 10 2007 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚገኝው መስቀል አደባባይ ታቦት ማደሪያ ‹‹ለልማት ይፈለጋል›› መባሉን ተከትሎ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ሃይሎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ቁጥራቸው ያልታወቀ  ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ትላንትና ዕለት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት የተቀሰቀሰው ድንገተኛ ተቃውሞ ተባሶ መቀጠሉን የገለጹት ምንጮች ሕዝቡ ከባህርዳር ወደ ጎንደር የሚወስደውን ድልድይ በመቆጣጠር ተቃውሞውን መግለጹ ታውቋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ መልስ ካላገኙ ድልድዩን እንደማይለቁ አስታውቀው እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡  የተቃውሞ ትዕይንቱን በሃይል ለመበተን ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ከፍተኛ አደጋ የደረሰ ሲሆን በተለይ ቀበሌ 10 የሚባለው ቦታ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል፡፡ ተቃውሞውን ተከትሎ ከጎንደር ወደ ባህር ዳር የሚወስደው መንገድ መዘጋቱ ተገልጿል፡፡

Saturday, December 13, 2014

በዋልድባ የሥኳር ልማት አካባቢ የአንበጣ መንጋ ተከሰተ

  • እኛ አፈር ጠባቂዎች ነን፥ ቦታው የመድኃኒዓለም ነው፡፡ ስለዚህ እርሱ ይጠብቀዋል ከእኛ የሚጠበቀው የዘውትር መወድስ፣ ፀሎት እና ልመና ብቻ ነው የገዳሙ አባቶች
  • ሁለት ታላላቅ ሊቀ አበው ሳምንት በፊት ወደ ማይጸብሪ ፖሊስ ተወስደው ታስረው ተፈትተዋል፡፡
  • ወታደሮች ዛሬም ድረስ ከገዳሙ አለቀቁም፡፡
  • በመስከረም ወር ላይ በችግኝ ማፍያ አካባቢ የተነሳውን የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት በሚል መንግሥት የረጨው መድኒት በርካታ የወልቃይት አውራጃ ነዋሪዎችን ከብቶች ጅቶባቸዋል፡፡
  • መንግሥት አሁንም 3900 የሚሆኑ አባወሮችን ከመዘጋ ወልቃይት እንደሚያስነሳ እየተነገረ ነው፡፡

 አንድ አድርገን ታኅሳስ 4 2007 ዓ.ም

በወልቃይት ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ይህን ይመስል ነበር

(‹‹ዋልድባን እንታደግ ፤ Save Waldda ››)፡- በዋልድባ ከሳምንት በፊት ከማይጸብሪ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ታጣቂዎች  ወደ ገዳሙ ዘልቀው በመግባት ሁለት ሊቃነ አበውን አስረው ወደ ማይጸብሪ አውራጃ ፖሊስ ጣባያ በመውሰድ በእስር ቤት አሳድረው መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ በሁኔታው ያዘኑ በርካታ መነኮሳት ምን በድለው ነው? ምን ጥፋት ተገኝቶባቸው ነው? በማለት ጥያቄ ቢያነሱም መልስ ሊያገኙ አልቻሉምዓመት ከመንፈቅ በፊት በአቶ ሲሳይ መሬሳ የሚመራው የአውራጃው አስተዳደር በአበንታንት ዋልድባ ገዳም ያለውን የነበረውን የአበውን ትውፊት ወደጎን ብለው፥ በጉልበታቸው እና በሥልጣናቸው በመጠቀም የእግዚአብሔርን ቦታ እና ቤተመቅደስ የሚያስተዳድሩትን አባቶች በማን አለብኝነት በመምረጥ 1ኛ/ አባ ገብረዋሕድ መምሕር የአበረንታንት መድኃኒዓለም ገዳም አበመኔት እና  2ኛ/ አባ ገብረሕይወት መስፍን (የቀድሞ ታጋይ) እቃ ቤት አድርጎ ከሾሟቸው በኃላ ችግሮች እየበዙ እና እየጠነከሩ መምጣት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል። በተለይ የቀድሞው ታጋይ እያንዳንዷን በገዳሙ ውስጥ የሚደረጉትን እና የሚታሰቡትን በሙሉ በመቅረጸ ድምጽ በተደገፈ ማስረጃ ለመንግሥት በማቀበል፥ “ጸረ ልማት” ወይም “ጸረ ሰላም” ናቸው ብለው የሚሏቸውን መናንያን፣ መነኮሳት እንዲሁም ባሕታውያን  በፈለጉ ጊዜ ወደ እስር እንዲጋዙ፣ ድብደባ፣ እና ለስደት እንዲዳረጉ እያደረጉ ይገኛሉ

Friday, December 5, 2014

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር

አንድ አድርገን ኅዳር 27 2007 ዓ.ም

  • ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል  በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል፡፡” ምሳሌ 1917
ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር ከስምንት ዓመታት በፊት በአቶ መለሰ አማካኝነት የአእምሮ ህሙማንን ለመርዳት የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ ከተቋቋበት ጊዜ አንስቶ በተለያየ ችግር ጎዳና ወድቀው የነበሩ ሰዎችን በማንሳት ሲረዳ ቆይቷል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ውስጥ ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበርን ከሦስት ጊዜ በላይ ሄደን መጎብኝት ችለን ነበር ፡፡ እኛ ቦታው ላይ ደርሰን የተመለከትናቸው ራሳቸውን የማያውቁ ፤ እናት ፤ አባት ፤ እህት ፤ ወንድም ፤ ዘመድና የእኔ የሚሉት ሰው የሌላቸው በአእምሮ ህመም እጅግ የተጎዱ ከ35 በላይ ህመምተኞች በወቅቱ ለመመልከት ችለናል፡፡  እነዚህን  ወገኖች  ዘር ፤  ቀለም ፤  ሃይማኖትና ፤  ጾታ   ሳይለይ   ጌርጌሴኖን    የአዕምሮ  ህሙማን  መርጃ  ማኅበር  የተቻለውን ያህል  እያደረገ ይገኛል፡፡

Tuesday, December 2, 2014

የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ከ54 ዓመት ቆይታ በኋላ ዳግም ለህትመት በቃች


አንድ አድርገን ኅዳር 24 2007 ዓ.ም
ታላቁ አባትና የተዋሕዶ አይን የነበሩት አለቃ አያሌው ታምሩ  አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት የተባለው ካቶሊካዊ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ባሕርያት አካላዊ ተዋሕዶ የምታምነው ትምህርት በሚል ስም በ1951 ዓ.ም ላሳተመው መጽሐፍ ሙሉ መልስ ሆኖ የተዘጋጀው ‹‹መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና›› የሚለው በአባታችን የተጻፈው መጽሐፍ ከ54 ዓመት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በአለቃ አያሌው ቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የአባታችንን ዕረፍት 7ተኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ መጽሐፏ ለህትመት አብቅተዋታል፡፡

Monday, December 1, 2014

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ የተናገሩት

  • ይህችም የሕዝብና የአሕዛብ ተስፋ የተመሠረተባት ፤ የእግዚአብሔር ሕጉ የተጻፈባት፤  አምልኮቱ የታወቀባት ፤ ኪዳኑ የጸናባት ጽሌ የሥግው ቃል  እናት የእመቤታችን ማርያም ምሳሌ ስለ ኾነች መታሰቢያነቷ ሳይለወጥ ጽዮን በጽዮንነቷ ጸንታ ትኖራለች፡፡
  • አክሱም ጽዮን ማርያምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ በወቅቱ አንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ወጪ 
    ተደርጓል፡፡

አንድ አድርገን ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም
ለአክሱም ጽዮን ይህን የአዲሱን ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ስንመሠርትላት ከዚህ ሰዓት ላደረሰን አምላካችን ውለታውን ለመመለስ የሚያበቃ ዐቅም የለንም፡፡ በ1928 ዓ.ም ስለ ሀገራችን ነጻነት እየተዋጋን በትግሬ ላይ በነበርንበት ጊዜያት ከሰላማዊ ሰዓት ይህን ሥራ እንድንሠራ ያበቃን ፈጣሪያችንን በሃይማኖት ለምነነው ነበር፡፡ ሀገራችን በጠላት ከተወረረች በኋላ በስደት አገር በነበርንበት ዘመን ኹሉ ስለዚሁ ነገር ሃይማኖትና ተስፋ ከሕሊናችን አልተለዩም፡፡

Friday, November 21, 2014

ሃና ላይ የተፈጸመው ተግባር የምንኖርበትን ማኅበረሰብ ዝቅጠት የሚያሳይ ነጸብራቅ ነው



ሃና ማለት ይች ናት ፤ በማኅበረሳባችን መካካል በወጡ እኛን በመሰሉ ሰዎች ለ5 ቀናት የአስገድዶ መድፈር ተካሂዶባት ህይወቷን ያጣችው ሃና ፤ እግዚአብሔር ነፍሷን ያሳርፍ ፤ ይህን ከመሰለ  ከእምነታችንና ከባህላችን ያፈነገጠ የረከሰን ተግባር  ወደፊት ላለመስማትም ሆነ ላለማየት ሁላችን ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡ ለቤተሰቦቿና ለጓኞቿ መድኃኒዓለም መጽናናትን ያድልልን፡፡

Thursday, November 20, 2014

ርዕሰ አድባራትና ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም በከፍተኛ ጥበቃ ላይ ትገኛለች

ከሳምንት በፊት በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ሲስተጋባ የነበረው ‹‹ቃል ኪዳኑ ታቦት ተሰርቋል›› የሚለውን አሉባልታ ጋር በተያያዘ በአካባቢው ማኅበረሰብ በአካባቢው ፖሊስና በፌደራል መንግሥት በተላኩ የደህንነት ሰዎች አማካኝነት በአሁኑ ሰዓት  ርዕሰ አድባራትና ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም በከፍተኛ ጥበቃ ላይ እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

Friday, November 14, 2014

‹‹ፈጣሪ አምላክ አገራችንንና ህዝቧን ከጥፋት ይታደግ ዘንድ በጸሎት እንትጋ!!›› የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኃይማኖት ተቋማት ያቀረቡት ጥሪ

አንድ አድርገን ህዳር 6 2007 ዓ.ም
አገራችን የክርስትናና እስልምና ኃይማኖቶችን በመቀበል ቀደምት በመሆኗ ብቻ ሳይሆን የኃይማኖቶቹ ተቋማት፣አባቶችና ምዕመናን በመከባበርና መቻቻል አብረው በሠላም በመኖር ለዓለም ህዝብ ተምሳሌት መሆናችን የምንኮራበት ነው፡፡ ለዚህም የቤተ እምነቶቹ አባቶች ለምዕመናኑ ያስተማሩት የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶችና በአብሮነት ላይ የቆመ የአገር ፍቅር ስሜት፣ እነዚህንም እንዲጠብቋቸውና እንዲያከብሯቸው አርዓያ በመሆን ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡
አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትም ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ ሁሉ የእነዚህ ኃይማኖቶች ተቋማትና ምዕመናን መዓቱ እንዲርቅና ምህረቱ እንዲወርድ ፈጣሪያቸውን በጾምና በጸሎት በመለመን/ በመማጸን፣ በሃይማኖታዊ የሞራልና ሥነ ምግባር እሴቶቻቸው መሠረት በመተዛዘን በመረዳዳትና በመተጋገዝ የተገኘውን በመካፈል በአብሮነት ስሜት በርካታ ክፉ ጊዜያትን መሻገራቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡