* በግለሰብ ቤት አምልኮን መፈጸም አይፈቀድም፡
(አንድ አድርገን የካቲት
30 2007 ዓ.ም)፡- ባሰላፍናቸው ሃያ አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ በርካታ የእምነት ተቋማት የተቋቋሙበት ዓመታት መሆናቸው
ይታወቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ወደ መንግስት ተጠሪ ቢሮ ያቀረበው(በጊዜው አቶ ጌታቸው እና ወ/ሮ
ሮማን ገሥላሴ በተጠሪነት ሲያገለግሉት የነበረው )ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከአንድ ሺህ በላይ አዲስ እምነት ለማቋቋም ጥያቄዎች
ለፌደራል ጉዳዮች እንደቀረቡ እና ከነዚህ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት
የእምት ተቋም ለማቋቋም የጠየቁ ቡድኖች ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሊያሟሉ ይገባሉ ያላቸውን መስፈርቶች ማሟላት በመቻላቸው ፍቃድ እንደተሰጣቸው
ያትታል፡፡