Thursday, March 5, 2015

የክተት ጥሪ ወደ ዝቋላ ገዳም ‹3›

የካቲት 26 2007


በዝቋላ ገዳም የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም ድረስ ያልጠፋ ስለሆነ እሳቱን ለማጥፋት እና ኦርቶዶክሳዊ ግዴታችንን ለመወጣት እኛ ኦርቶዶክሳዊያን እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በነገው ዕለት ማለትም 27/06/07 . ከጠዋቱ አንድ ሰዓት በመስቀል አደባባይ ተገናኝተን ለመሄድ ተዘጋጅተናል ስለሆነም ወደ ቦታው ለመሄድ የምትሹ በቦታው እና በሰዓቱ እንድንገናኝ ይሁን!!!

          *የመጓጓዣ መኪና በነፃ ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል*

 የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ መገጣጠሚያ ድርጅት ቀደም ሲል በገባው ቃል መሠረት አሁን ከደብረዘይት ከተማ ሁለት ቦቴዎችን በማንቀሳቀስ ወደስፍራው እንዲያመሩ እያደረገ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንደኛው ቦቴ ሺህ ሊትር ውኃ ጭኖ ድሬ እየተባለ የሚጠራውን አካባቢ አልፎ ወደ ዝቋላ እያቆራረጠ ሲሆን ሁለተኛው ቦቴ ደግሞ ውኃ እየሞላ መኾኑ ታውቋል፡፡ ከመሣሪያው በተጨማሪ የበኩሉን የሰው ኃይል ድጋፍ እንደአስፈላጊነቱ ለማድረግም ቃል መግባቱን ሰምተናል፡፡ ይኽንን የፈቀዱት ኃላፊዎች እንዳስረዱት ከኾነ ይኽ ሀገራዊ ጉዳይ በመኾኑ እና የዜግነት ግዴታም ነው፡፡ ጉዳያችን ስለኾነ ወስነናል ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment