Thursday, March 29, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ

  • ስብሰባው የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ፤
  • ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” (አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 .)የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትበዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተየሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማትየሚል ስብሰባ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2004 . በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

አመድ ሆኗል ብለን የተውነው ነገር ውስጡ ፍም አለመያዙን እርግጠኛ እንሁን

(አንድ አድርገን መጋቢት 20 2004 ዓ.ም)፡- ይህ የተሀድሶዎች ጉዳይ አንዳንዴ ትልቅ የመወያያ አርዕስ ይሆናል አንዳንዴ ደግሞ የሌለ እስኪመስል ድረስ ዝም ይላል፡፡ አሁን እያየን ያለነው ነገር ይህ ነው ፤ ቤተክርስትያንን ከእነዚህ ሰዎች አስተምህሮ ለመጠበቅ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል በመፅሄት ፤ በጋዜጣ በድምጽ እና በምስል ያስደገፉ በርካታ መረጃዎች ተለቀው ሰዎች ዘንድ ደርሰዋል ፤ አሁን ግን አልፎ አልፎ ይህን ችግር የተለያዩ ቦታዎች እንዳለ ፈፅሞም እንዳልጠፋ የሚያሳዩ ነገሮች እየተከሰቱ ነው ፤ ዋናዎቹ እና ፊት አውራሪዎቹ ከሳምንታት በፊት በቤተክሀነት አዳራሽ ጉባኤ ለማድረግ አስበው መከልከላቸውን ለመግለጽ ሞክረን ነበር ፤ ይህን ሲከለከሉ ሌላ አዳራሽ ከቤተክርስትያኒቷ ፍቃድ ውጪ ቤተክህነቱ ጉባኤውን ሳይፈቅድ ምዕመኑን አዳራሽ ሰብስበው ማካሄድ ችለው ነበር ፤

Wednesday, March 28, 2012

ሌላ ቀውስ

(አንድ አድርገን መጋቢት 20 2004ዓ.ም)፡- በተለያዩ ጊዜያት በመንግስት አማካኝነት በሰፈራ ፕሮግራም በተለያዩ ቦታዎች ተነስተው ወደ ተለያዩ ክልሎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በ1993 ፤ 1995 እና በ1997 ዓ.ም መስፈራቸው ይታወቃል ፤ ዛሬ ጠዋት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ከ3 መኪና ያላነሱ ሰዎች ከነ ሙሉ ቤተሰቦቻቸው የሚዛን ተፈሪ ፤ቤንች ማጂ እና ሸካ ዞኖች አካባቢ የሚገኙ ባለስልጣናት ተባረው ለመንግስት አቤት ለማለት መሬት ላይ ወድቀው ይገኛሉ ፤ በጣም ህጻናት ፤ ወጣቶች ፤ አሮጊቶች ሽማግሌዎች ይገኙበታል ፤ አካባቢው ላይ የሰፈሩት  ዜጎች አብዛኞቹ ከአማራ ክልል የመጡ እና ቦታው ላይ መሬት ተሰቷቸው ኑሯቸውን በግብርና ላይ የሚመሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፤ አቤቱታቸውን ለመንግስት ለማሰማት መንገድ ያደሩ 4 መኪና አውቶቡሶች እዳሉም ለማወቅ ችለናል ፤ እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ማደሪያም ሆነ መጠለያ ሳይኖራቸው በሜዳ ላይ 4 ኪሎ ስላሴ በር ላይ ተበትነው ይገኛሉ ፤ ጥያቄያቸውንም በተወካዮቻቸው አማካኝነት  ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡   ሰው በሀገሩ እንደ ዜጋ ተከብሮ መኖር ካቃተው ሌላ ምን ተስፋ ሊኖረው ይችላል? እኛ እንደ ክርስትያን እንደ ወገን እነዚህን ሰዎች ምግብ ብናቀርብላቸው ምን ይመስላችኋል? ከመንግስት መልስ ካላገኙ እነዚህ ዜጎች አቅራቢያ የሚገኝው ስላስ ቤተክርስትያን ነው የምንገባው ብለዋል ፤ ከቤተክርስትያን ውጪ መሸሻ የት ሊገኝ ?(4፡00 ሰዓት )በአሁኑ ሰዓት ከቦታው እንደደረሰን የአይን እማኞች መረጃ መሰረት መንግስት መኪና አቅርቦ ሁሉንም የመጡትን ሰዎች ከቦታው ላይ አንስቷቸዋል ፤ ወደ የት ይሂዱ አላወቅንም ፤ የመገናኛ ብዙሀን በዚህ ዙሪያ ምን እንደሚሉ ወደፊት የምንሰማው ይሆናል ፤ ስላሴ ቤተክርስትያን ደጃፍ አሁን ቢመጡ ምንም ያልተፈጠረ ያህል ረጭ ብሏል፤ 

በቀኑ ቤተክርስትያኒቱን ለማረፊያነት ጠይቀው ቢሆንም አስተዳደሩ ግን ሊፈቅድላቸው አልወደደም

የመጨረሻው ..‹‹የአዋጅ ምህላ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስያን››

(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2004.)- ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላትን መንፈሳዊ እሴትና የማይናወጽ ሐይማኖት ይዛ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስትሸጋገር የቆየችው (1) በእግዚአብሔር ቸርነት (2) በቅዱሳን ምልጃ እና (3) በአባቶቻችን ቆራጥ ሐይማተኝነትና ራሳቸውን ለቤተክርስቲያን አሳልፈው ለመስጠት በወሰዱት አርምጃ ነው:: ታዲያ በብዙ መከራና ፈተና ቤተክርስቲያናችን እዚህ ዘመን ደርሳ በአሁኑ ወቅት በውስጥም ሆነ በውጭ በመደራጀትም ሆነ በተናጥል በግልጽም ሆነ በድብቅ እየደረሰባት ያለው ፈተና የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰንብቷል:: ምንም እንኳን ቤተክርስቲያን በአለት ላይ የተመሰረተችና የሲኦል ደጆች እንደማያናውጧት ብናምንም አሁን በላይዋ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሟን እየመጠጡ ያሉት አካላት የሚያደርሱት ጥፋት ቀላል አይሆንም፡፡ በርግጥ አጠፋናት አደስናት እያሉ የሚደሰቱ ሁሉ ዘመናቸው ሲደርስ እንደሚያልፉና መታሰቢያቸው እንደሚረሳ እናምናለን:: በእኛ ዘመን በእኛ አቅም የሚጠበቅብንን ማድረግ ግን መዘንጋት የለብንም:: በቀደምት አባቶቻችን ዘመን እንኳን በቤተክርስቲያኗ ይቅርና በሃገሪቷ ለየት ያለ ክስተት ረሃብ፤ ቸነፈር፤ ጦርነት ሲነሳ ቤተክርስቲያናችን አዋጅ አውጃ ጸሎት ምህላ ታደርግና በረከትን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ታሰጠን እንደ ነበር በእኛ ዘመን እንኳ የምናውቀው ታሪክ ነው::

Tuesday, March 27, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ ስብሰባ ጠራ

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 19/2004 .ም፤)· ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት /ቤት፣ ከዋልድባ ገዳም ተወክለዋል የተባሉ መነኰሳት፣ ከጎንደር ከተማ የተመረጡ ምእመናንና በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት ነገ፣ መጋቢት 19 ቀን 2004 .ም፣ የመንግሥት ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ስለ ደቀነው ስጋት፣ በተጨባጭም ስለታየው መጋፋት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ስብሰባውን የጠራውን ብአዴን/ኢሕአዴግ ሲሆን የሚካሄደውም በጎንደር ከተማ መሆኑ ተመልክቷል፡፡


Monday, March 26, 2012

የዋልድባ ገዳም መብት ለማስከበረ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2004ዓ.ም)፡-26/03/2012 ዓ.ም  በአሜሪካን ሀገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አማኞች  ዋልድባ ገዳም ላይ መንግስት ሊሰራው  ያሰበውን የስኳር ልማት በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል ፡ ሰላማዊ ሰልፉን እንዲሳተፉ ለብዙ ሰንበት ተማሪዎች ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ለአባቶች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት በአባቶች ጸሎት ተጀምሯል ፣ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ 450 ሰዎች የፈረሙበትን የህዝብ ድምጽ አያይዘው አቤቱታቸውን አቅርበዋል ፡ የኢምባሲው ሰራተኛ ነኝ የሚሉ አንድ ሰው ነገ ተመልሰው እንዲመጡ አሳስበዋቸዋል ፣ በፊት በተለያዩ ሲኖዶሶች ሲተዳደሩ የነበሩት ክርስትያኖች ይህ ጉዳይ አንድ ያደርገናል እንጂ ሊለየንም አይችልም በሚል ሀሳብ ተስማምተው በአንድነት ሰላማዊ ሰልፉን በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት አድርገዋል ።  በጊዜውም
ሀይል የእግዚአብሔር ነው
ማዳን የእግዚአብሔር
ጥበብ የእግዚአብሔር
አንመካም በጉልበታችን
እግዚአብሔር ነው የኛ ሀይላችን
እያሉ ሲዘምሩ ተደምጠዋል። እውነት ነው «ሀይል የእግዚአብሔር ነው» እኛ ጉልበት ኖሮን ለውጥ ላናመጣ እንችላለን ፣ ጉልበት ግን የእግዚአብሔር ነው ፡ ኃይል ግን የእግዚአብሔር ነው  ። የእግዚአብሔርን እጅ እንጠብቃለን ፣ ከ420 ዓመት በኋላ እስራኤልን ከባርነት ያወጣ አምላክ እኛንም አይተወንም ፡ አይረሳንም ። እኛን የሚጎነኝበት ለጥያቄያችን መልስ የሚሰጥበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በተስፋ እንጠብቃል ።