Monday, March 19, 2012

እኛስ ሞተናል


(አንድ አድርገን መጋቢት 11 ፤ 2004ዓ.ም )፡- በዋልድባ ገዳም መንግስት ሊሰራ ያሰበውን የስኳር ፋብሪካ እንደማያቋርጥ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ስብሰባ ላይ አሳውቋል ፤ በጊዜው በስብሰባ ላይ የተገኙ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አንዱ የስኳር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አባይ ጸሀዬ ተገኝተው ነበር ፤ የአካባቢው የኢህአዴግ ደጋፊዎች እና ለካሜራ ያህል ጥቂት እኛን የማይወክሉ አባቶች ለታይታ ባሉበት ስብሰባውን አካሂዷል ፤ ከስብሰባውም በኋላ የዋድባ ገዳምን ይነካል የሚባለው አሉባልታ ጥቂት ሰዎች የሚያወሩት ወሬ ነው በማለት አጣጥሎታል ፤ በስብሰባው መጨረሻ ላይ ስድስት ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የዋልድባ አባቶች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም አልቀየሩም ‹‹እኛን ሰውታችሁ ስራችሁን ትሰራላችሁ ›› ብለዋቸዋል ፤ የገዳሙ አበምኔት በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት ቤታቸው ተመዝብሯ ፤ እሳቸውም በፖሊስ ተወስደዋል እስከ አሁን ድረስም ያሉበት አልታወቀም ፡፡

እኛም ዝምታው ተመችቶን መረጃዎችን ከኢንተርኔት ፤ ከፌስ ቡክ ፤ ከተለያዩ ብሎጎች እና ዌብ ሳይቶች ላይ እየለቀምን ከማንበብ እና ከመናደድ ውጪ ምንም ማድረግ አለመቻላችንን ሳስበው ይገርመኛል ፤ ፍርሀታችን መስመሩን ስቷል ፤ የማንጠቅም ሰዎች  በስመ ክርስትያ መሆናችንን ሰዎች በደንብ እያወቁልን ነው ፤ ነገሮችን ሁሉ አሳልፈን ለእግዚአብሔር እንሰጣለን ፤ ይህ መልካም ነገር ነው ነገር ግን እኛ አንዳች ነገር ሳናደርግ እግዚአብሔር ያውቃል ብሎ መቀመጥ ተገቢ አይደለም ፤ ክርስትያናዊ አካሄድ ነው የሚል እምነት የለንም ፤ በግብጽ ያሉ ክርስትያኖች ከአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ሲደርስባቸው ማንም ወደ ቤቱ የሚገባ ክርስትያን የለም ፤ ይባስ ቤቱ ያለው ወጥቶ ድርጊቱን ይቃወማል ፤ ተጨማሪ ጉዳት ቤተክርስትያናቸው ላይ እንዳይደርስ ይከላከላሉ የቻሉትን ያህል ይጠብቃሉ ፤ ባለፈው ዓመት የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት አክብረው ሲያበቁ በመኪና ውስጥ በተቀመጠ ቦንብ 32 ሰዎችን በነፍስ ማጣታቸውን እናስታውሳለን ፤ የዛን ጊዜም መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር ችለው ነበር፡፡ ተቃውሟቸውም የዓለም ህዝብ አድምጧቸዋል ፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም በጊዜው የግብጽ መሪ ለነበሩት ለሁስኒ ሙባረክ በጉዳዩ ዙሪያ መልእክት ልከውላቸዋል ፤ ይህ የተቃውሟቸው ድምጽ በመንግስት ላይ ያመጣው ተፅህኖ ነው ፤ መንግስትም ይህ አይነት ነገር እንዳይፈጠር ከቤተክርስትያን በሮች አንስቶ ክርስትያኖች በሚሰበሰቡበት ቦታ ላይ በርከት ያሉ ፖሊሶችን መመደብ ስራውም ግዴታውም ጭምር ነው፡፡  እነዚህ ክርስትያኖች ከ80 ሚሊየን የግብጽ ህዝብ ውስጥ 10 በመቶውን ብቻ የሚይዙ ናቸው ፡፡  በሀገራችን ትልቁን ቁጥር የምንይዘው ኦርቶዶክሳውያን ነን ፤ የግብጽን ክርስትያኖች ያህል እንኳን በሀገራችን አቤቱታችንን ያሰማንበት ጊዜ አለመኖሩ ሳስበው  ማህበረሰባችን መብትና ግዴታውን አያውቅም ያስብላል፡

ለምን እናንተን ለማስረዳት ሩቅ ሀገር እሄዳው  ፤ በቅርቡ በአዲስ አበባ ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ የተፈጠረውን ነገር የማያውቅ በጋዜጣ ያላነበበ ፤ በሬዲዮ ያልሰማ ፤ ተባራሪ ወሬዎች በጆሮው ያልደረሰው ሰው አለ ብዬ አልገምትም ፤ እስኪ የማውቀውን የተፈጠረውን የገባኝን ያህል ላስረዳዎት፤ በእስልምና እምነት የላይኛው ክፍል ‹‹መጅሊስ›› ይባላል ፤ ይህ አካል በየሶስት ዓመቱ ሙስሊም ማህበረሰብ እየመረጠው ህዝብ ወክሎት የሚቀመጥ አካል ነው   ፡፡ ነገር ግን  እንደ ኢህአዴግ ፖለቲካ ሰዎቹ በቦታው ላይ የመተካካት ሂደትን ተከትለው ለረዥም ዓመታት ተደላድለው ተቀምጠዋል ፤ መጅሊስን በህዝበ ሙስሊሙ  አልተመረጠም ፤ የመተካካቱ ሂደት ፖለቲካዊ እና በደም መሆኑ በህዝቡ ዘንድ ተሰማ፤ ህዝቡም ውስጥ ውስጡን ጉርምርምታ መፍጠር ጀመረ ፤ አወሊያ ብለው የሚጠሩት በ1956 ዓ.ም የተመሰረተው የሙስሊም ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ፤ ሆስታል እና የተለያየ ተቋማት የሚገኙበትን ቦታ ሰዎቹ ‹‹አህባሽ›› በሚባል አስተምህሮ ከህገ-መንግስቱ ጋር የማይሄድ አይዲዎሎጂ  አስማሪዎችን ከአረብ ሀገር አሰልጥኖ በማምጠት ውስጥ ውስጡን የራሳቸውን ስራ መስራት ተያያዙት ፤ ይህ ነገር ሰዎች ዘንድ ደረስ ፤ መንግስትም ጉዳዩን በጊዜው ደርሶበት ማስቆም ቻለ ፤ ይህ በእንዲህ እያለ ህዝበ ሙስሊሙ አንድ ጥያቄ አነሰ ‹‹ መጅሊስ ይውረድ ›› ፤ ‹‹ ህዝቡ የመረጠው መጅሊስ ተመርጦ ቦታውን ይያዝ›› ‹‹አሁን ያለው መጅሊ እኛን አይወክልም›› ‹‹የአህባሽ አስተምህሮ በአወሊያ ውስጥ ይቁም›› የሚል ፡፡  ይህን ጥያቄ በምን መልክ መንግስት ዘንድ እናቅርብ ብለው ጉባኤ ሰርተው ተወያዩ ፤ በጊዜው እኔ ከአንዳንዱ ሙስሊም የተሻለ መረጃ ነበር ፤ የአቅሜን ያህል ጠጋ ብዬ አደምጥ ነበር ፤ መረጃዎችንም አነብ ነበር ፤ ፓልቶክ ሩሞቻቸውንም እከታተል ነበር ፤(ይህን የማደርገው አላማቸውን ለማወቅ ፤ ስትራቴጂያቸውን ለማጥናት እንጂ ለሌለ ነገር አይደለም ፤ የመረጃ ትንሽ የለውም የሚል አቋም ስላለኝም ጭምር ነው)፡፡  ከዚህ በኋላ  አስተማሪዎቻቸውን ከሀረር ፤ ከደሴ ፤ ከጅማና ከአርሲ አሉ የሚባሉትን በክልል በሚገኙ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አማካኝነት ሰበሰቡ ፤ ህዝቡ የራሱን ጥቆማ ማካሄድ ጀመረ ፤ መንግስት ፊት ቀርቦ ጥያቄዎቻችንን ማን ያስተላልፍልናል ፤ መልስም ያመጡልናል ያሏቸውን ሰዎች ጠቆሙ ፤ የተጠቆሙትም ሰዎች በህዝብ ድምጽ ተመርጠሀል ተብለው ህዝቡ የጣለባቸውን ሀላፊነት አሸከሟቸው፡፡

የተመረጡት ተመራጮች ለብቻቸው ስብሰባ አካሄዱ በምን አይነት መንገድ መሄድ እንዳለባቸው ፤ የህዝቡን ጥያቄ በምን መንገድ ጫፍ ድረስ ይዘው እንደሚሄዱ መልስም እንደሚያመጡ ጊዜ ወስደው ተወያዩ፡፡ከዚህ በኋላ እነዚህ በህዝብ የተመረጡት ሰዎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ፤ እኔ እስከማውቀው ድረስ ‹‹መጅሊስ ይውረድ›› በሚል አላማ አዲስ አበባ እና ክፍለ ሀገር  የሚገኙትን የሙስሊም ማህበረሰብ ከ 100 ሺህ ሙስሊም በላይ በየመስኪዳቸው ማስፈረም ችለዋል ፤ ይህንም እንደ ማስረጃ በማያያዘዝ የህዝቡ ጥያቄ ነው ፤ ሊመለስ ይገባዋል በማለት ፤ የፌደራል ጉዳዮች ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፤ የፌደሬሽ ምክር ቤት ፤ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ፤ እስልምና ጉዳዮች ፤እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ፊርማውን አባሪ በማድረግ ጉዳያቸውን በደብዳቤ መልክ ለተጠቀሱት ቦታዎች አስገብተዋል፡፡  

ይህን ካደረጉ በኋላ ግን አርብ አርብ ለስግደት ሲገናኙ ጉዳዩ በአፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው ሲወተውቱ ለ8 ሳምንታት ቆይተዋል ፤ መንግስትም ይህ ጥያቄ ወደ ሌላ ነገር እንዳያመራ በመፍራት አርብ በመጣ ቁጥር አወሊያ አካባቢ ብዛት ያላቸው ፌደራ ፖሊሶች ፤ አድማ በታኝ ውሀ የጫኑ የፖሊስ መኪኖች ፤ ራሳቸውን አመሳስለው ለመስገድ የገቡ ፖሊሶች አብረዋቸው ማየት የተለመደ ነገር ነበር፡፡ እኔም ጉዳየን በቅርብ ስለምከታተል የሆነው የተደረገው ነገር ሁላ ይደርሰኝ ነበር ፤ በወቅቱም ማህበረሰቡ በሞባይል ፤ በበበራሪ ወረቀት ፤ በኢሜል እና በተለያዩ መንገዶች ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ማንም አርብ ቀን እንዳይቀር መረጃ ሲለዋወጡ ህዝቡንም ሲያነሳሱ ሰንብተዋል ፤  ከ3 ሳምንት በፊት በፋና 98.1 ሬዲዮ ላይ ህዝቡ የወከላቸው  ተወካዮች እና መጅሊሱን ፊት ለፊት አገናኝቷቸው የህዝብን ጥያቄ ሁለቱንም ሲጠይቋቸው ለ1፡30 ያህል ጊዜ አርፍደዋል ፤ ጋዜጠኞቹ የመንግስትን ፍራቻን (ይህ ድርጊት ከቁጥጥራችሁ ውጪ ቢወጣስ? ፤ የእናንተ ሀላፊነት አስከ ምን ድረስ ነው? ከህዝቡ ጋር እንዴት ነው የምትገናኙትት? አክራሪ ሙስሊሞች መሀላችሁ አሉ ይባላል? እና በርካታ ጥያቄዎች ተጠይቀው መልስ ተሰቶባቸዋል)  ፤ የህዝቡን ጥያቄ በመጭመቅ ፤ የተወካዮችን ማንነት በሚመለከት በጣም ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎችን ሲጠይቋቸው ለመስማት ችያለሁ ፡፡ ተወካዮቹ አካሄዳቸውን ስለማውቅ ያልሆነ ነገር ብመለከት መጀመሪያ ለፖሊስ ጠቋሚ ሰው ራሴን አድርጌ አዘጋጅቼ ነበር ፤  እነሱም ስማርት ነበሩ ፤ የመንግስት አካሄድ የገባቸው ሰዎች ናቸው ፤ አላማቸውንም ያልሳቱ ፤ ጥያቄያቸውም መሰረታዊ እና ተገቢም ጭምር ነው ብዬ እኔ በራሴ አምናለሁ፡፡

መንግስት ጉዳዩ አስፈርቶት መጀመሪያ የካቲት 5 ቀን መልስ እሰጣችኋለሁ ብሏቸው ቀጠሮ ቢይዝም ቀጠሮውን የውሀ ሽታ አድርጎባቸው ነበር ፤ ህዝቡም ነገሩ ገብቶት መልስ እስከምናገኝ ድረስ ተቃውሟችንን እንቀጥላለን በማለታቸው ጉዳዩን የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር መስሪያ ቤት በዶ/ር ሽፈራው አማካኝነት  ለየካቲት 26 ቀን ቀጠሮ ሰጣቸው ፤ በዚህ ጊዜ ግን የመንግስት የሚመለከታቸው ባለስልጣናት ፤ ከመጅሊስ የተወከሉ ሰዎች ፤ ከእስልምና ምክር ቤት ፤ ከትላልቅ አባቶች እና ጥያቄውን ባቀረቡት ተወካዮቻቸውን ሰብስቦ መፍትሄ ሰጥቷቸዋል ፡፡ መፍትሄውም  ‹‹በጣም በአጭር ጊዜ መጅሊስን የሚወክሉ አባቶችን በህዝቡ አማካኝነት የመምረጥ ስራ እንደሚከናወን ቃል ገብቶቸዋል›› ፤ ተፈጻሚነቱ ላይ ጥያቄ ቢኖርም ፤ ይህንም ለማድረግ ሀገራዊ ምርጫ ስለሚሆን ትንሽ ጊዜ እንዲሰጡትም አሳስቧቸዋል ፡፡›› ይህንም መረጃ ለመላው ህዝብ ለማስተላለፍ ባለፈው አርብ ቀን 07/07/04 ዓ.ም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ከማታው የ2፡00 ሰዓት የዜና ሰዓት በኋላ ሰፊ ጊዜ በመስጠት የመንግስትን መልስ ለማህበረሰቡ ሊያደርስ ችሏል፡፡  

(ይህ ሁሉ ሂደት እንደምታነቡት ቀላል አይደለም፡፡) የእነሱ ጉዳይ በእንደዚህ አይነት መልኩ ሲስተናገድ የእኛ ጉዳይ ደግሞ በትግረኛ ፕሮግራም ላይ ዋልድባንና አካባቢውን ባልታረሰው በኩል በካሜራ ቀርጸው እየተወራ ያለው ነገር ውሸት ነው ፤ የፈጠራ ወሬ ነው፤ ይህን የሚያወሩት የመንግስት ተቃዋሚዎች ናቸው ፤ ጸረ ልማት የሆኑ ቡድኖች ናቸው ፤ ሀገሪቷ እንዳታድግ የሚፈልጉ የውጭ ተላላኪዎች ናቸው በማለት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የማይወክሉ ለሆዳቸው ያደሩ አባቶችን አነጋግሮ እማኝ በማቅረብ  አሪፍ ውሸት ልብሱ የሆነ ዶክመንተሪ ፊልም ሰርተው ለህዝቡ አስተላልፈዋል ፤  ህዝቡንም ይባስ ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል ፤ እውነታው ግን የዚህ ተገላቢጦሽ        መሆኑን ከዚህ በፊት በጽሁፍም ሆነ በቪዲዮ ያቀረብናቸው ማስረጃዎችን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

እኔ ይህን ሁሉ ያልኩት የሙስሊሙ ነገር ለእኔ ገዶኝ አይደለም ፤ ነገር ግን ይህን ለእኛ መማሪያ መሆን ይችላል በሚል መልኩ ማንሳት ፈልጌ ነው ፤ እኛስ ለምን ህብረት ፈጥረን ጥየቄዎቻችንን ለመንግስት አናቀርብም ? እኛ እኮ ብዙ ነን ፤ ይህ ሰውን ለአመፃ ጥሪ ማነሳሳት አይደለም ፤ ቤታችን ሲፈርስ እያየን ለምን ዝም እንላለን ? ፍርሀታችን ገደቡ የቱ ጋር ነው ? መቼ ነው ጥያቄዎቻችንን በህብረት የምናቀርበው ?  ሰው ለእንዲህ አይነት አላማ ሲጠራ መጀመሪያ የሚታየው እስር ቤት ነው፤ በመታሰርም ጥያቄ ማቅረብ እና መፍትሄ ማግኝት አንድ ነገር ነው ፤ ከ2 ወር በፊት ግብረሰዶማውያንን በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ሁሉም በፌስ ቡክ ሆኖ ሲቃወም ማንም ቀዳሚ አልነበረውም ፤ ግብረሰዶማውያን ስብሰባ በሚያደርጉበት ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ የወጡት ወጣቶች ግን ከ10 አይበልጥም ፤ ለነገሩ አይደለም ልጆች የሐይማኖት  አባቶችም ይህን ጉባኤ ጋዜጠኛ ጠርተው መቃወም አልቻሉም ነበር ፤ ይህ የሚያሳየው ማህበረሰባችን በምን አይነት የፍርሀት እስር ቤት ውስጥ እንዳለ ነው ፤ እነዚያ ወጣቶች ግን ታስረው ተፈቱ እንጂ ምንም የሆኑት ነገር የለም ፤ አሁን እያልኩ ያለሁት አብረውን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና ፤ በከተማው  ከ20 በመቶ የማይበልጠው ማህበረሰባቸው ጥያቄያቸውን በህብረት ሆነው ማቅረብ ሲችሉ እኛ ግን ዋልድባን የመሰለ ገዳም በዶዘር ሲንዱት እያየን አሁን ከኮምፒዩተር ኋላ ሆነን ጉዳዩን መከታተል እንፈልጋልን ፤ አባቶቻችን ፤ የገዳሙ መነኮሳት አቋማቸውን ለዓለም በአሜሪካ ድምጽ በኩል አሳውቀዋል ፤ በአሜሪካ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእምነቱ ተከታዮች በዋሸንግተን በሚገኝው የአሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት ጥያቄ ለማቅረብ ተነሳስተዋል ፤ እኛ ግን በኢትዮጵያ የምንገኝ አማኞች ጨጓራችንን በነገሩ እየላጥን ዝምታችንን ውጠን ቤታችን ቁጭ ብለናል ፤ እረ ትንሽ እናስብ አቡነ ሺኖዳ የሞቱት ሞት እኛም እኮ አይቀርልንም ፤ እሳቸው መክሊታቸውን ተጠቅመውበት ከቀናት በፊት በሞት ተለይተውናል ፤ ‹‹ኖሮ ኖሮ ሞተ››  ከሚባልልን ‹‹ስለ እምነቱ ኖሮ ሞተ›› ቢባል የተሻለ ነው ፤ ዋጋችንም ስለ እምነታችን ስንኖር አምላክ አያስቀርብንም፡፡ እና ጠርንፎ የያዘን የፍርሀት ድልድይ የቱ ጋር ይፍረስ ? ፤ ህገ መንግስቱ ሰዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ጥያቄያቸውን ለመንግስት በሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ማቅረብ እንደሚችሉ ይደነግጋል ፤ የምንሰበሰበው መንግስት ግልበጣ አይደለም ፤ የፖለቲካ ጥያቄም ለማንሳት አይደለም ፤ የኑሮ ውድነቱ በቤት ኪራዩ መማረራችንን ለመግለፅ አይደለም ፤ እነዚህማ ከደምና ከስጋችን ጋራ ተዋህደው ለምደናቸዋል ፤ ጥያቄያችን የሚሆነው ‹‹ማንነታችንን አትናዱብን›› የሚል ነው ፡፡እያልኩ ያለሁት አሁን ቤተክርስትያናችን ስላለችበት ሁኔታ በህብረት ሆነን መንግስትን የሚመለከታቸውን አካላት እንጠይቅ ፤ እምነታችን ለተጋረጠባት ከባድ ፈተና የመፍትሄ ሰው እንሁናት ፤ ይህችን እምነት ከአባቶቻችን እንደተረከብናት እኛም አላፊ ነንና ለልጆቻችን እንደተረከብናት እናስረክብ ፤ ጆሯችን ችግር ሰሚ ብቻ ሳይሆን አእምሯችን ደግሞ ችግር ፈቺ ይሁን ፤ ለቤተክርስትያን እንኑርላት ፤ ለመጪው ትውልድ ፍርሀትን አናውርስ ፤ የግብጾች የእምነት አንድነት ፤ ስለ እምነታቸው የሚከፍሉትን ዋጋ ለእኛም ትምህርት ይሁነን ፤ ይህን ነው እያልን ያለነው፡፡

የሙስሊሞቹን ጉዳይ ከመንግስት ባልተናነሰ መልኩ መረጃው እኔ ጋር አለ ፤ መረጃ ስላለ ብቻ ሰዎች ዘንድ ማቅረብ ተገቢ አይደለም ፤ ነገር ግን ከላይ የጠቀስኩት የእነሱ አካሄድ ለእኛም ትምህርት ይሁነን እንበርታ እንተባበር ፤ በአንድ እንቁም ፤ የምንለያይባቸው ጉዳዮች ቢበዙም አንድ የሚያደርጉን ነገሮች ይልቃሉና በእነሱ ላይ አንድ ሆነን ድምጻችን እናሰማ ፡፡ የተግባር ሰዎች ካልሆንን ለቤተክርስትን አንረባትም ፤ ምንም አንጠቅማትም ፤ የሰማነውን ነገር ፤ ጆሯችን የገባውን ወሬ ከማመላለስ ውጪ ምንም አናደርግላትም ፤ በርካታ በውስጣችን መፍታት የሚገቡን ጉዳዮች አሉን ይህን አውቃለው ፤ ነገር ግን እነዚህ ችግሮች ፋታ የሚሰጡ ናቸው ፤ አሁን ያለንበት ጊዜ ላይ የተፈጠረው ችግር ግን ፋታ የሚሰጥ አይደለም ስለዚህ በአንድነት እንቁም ፤ አንድ መሆናችን ለጥያቄያችን ጉልበት የመንግስትንም ጆሮ ለማግኘት ያስችለናል ፤ እባካችሁ ገነገሩን ይዞ በውስጥ መብላላት አይጠቅመንም ፤ በህይወት ዘመናችን የሚጠበቅብንን ስራ መስራት ካልቻልን ከመቃብር በታች ካሉት ሰዎች በምን ተሻልን ? ስለ ቤተክርስትያን ኑረናል እንላለን ፤ ነገር ግን ሙተናል ፤ የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ  …‹‹ለእናንተም ለወዳጆቼ እላችኋለሁ፥ ሥጋን የሚገድሉትን በኋላም አንድ ስንኳ የሚበልጥ ሊያደርጉ የማይችሉትን አትፍሩ።››የሉቃስ ወንጌል 12 ፤ 4 ይላል 

አቡነ ጴጥሮስ ስለ ሀገራቸው እና ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ብለው በጨው በረንዳ በ8 ጥይት የተገደሉት ለእኔ እና ላንተ(ቺ) ሲሉ ነው  ፤ እነርሱ ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ከውስጥና ከውጭ ጠላት ይህችን ሀገር ይችን ቅድስት ቤተክርስትያን  ባያቆዩልን ኖሮ ዛሬ እኔና አንተ(ቺ) ካቶሊክ ፤ ፕሮቴስታንት ወይም ሙስሊም ሆነን ከእግዚአብሔር ልጅነት በራቅንና በተገለልን ነበር ፤ ክብር ይግባቸው ስለ እኛ ብለው በዱር በገደል ስለወደቁ አባቶቻን ፤ አሁን ይች ቤተክርስትያን ላይ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ ጠላት ተነስቶባታል ፤ የመፍትሄ አካል ደግሞ አሁን ያለነው እኔና አንተ(ቺ) እንጂ ያለፉት አባቶቻችን ዳግም ተነስተው መስዋዕትነት አይከፍሉልንም ፤ እነሱ ሩጫቸውን ጨርሰው እዚህ ጋር አድርሰውናል፤ እኔና እናንተ ግን ሩጫውን ጀምረናል …............ 


እኛ ይህን ብሎግ ስንከፍት ዋናው አላማችን የቤተክርስትያንን መረጃ ሳናዛባ በጊዜው ምዕመኑ ዘንድ አድርሰን ምዕመኑ የመፍትሄ አካል እንዲሆን በማሰብ ብቻ ነው ፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም የተደበቀና የተሰወረ ነገር የለንም ፤ መረጃ ለተጠቀመበት አቅም አለው ፤ ለችግሮች መፍትሄ ከማስቀመጥ አኳያ መረጃ የማይተካ ሚና ይጫወታል ፤ ያለንን መረጃ ታቅፈነው እሳት ከምንሞቀው ይልቅ ሰዎች ዘንድ ብናደርስ የተሻለ እይታ ፤ የተሻለ ሀሳብ ይመጣል ለችግሮችም የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንችላለን ብለን እናምናለን ፡፡ ለቤተክርስትያናችን የምናስተላልፈው መረጃ ለችግሯ መፍትሄ ካልሆናት ፤ የአንባቢን ቁጥር ከመጨመር የዘለል ስራ ካልሰራን ፤  የተላለፈው መረጃ እና የተገኝው ውጤት መመዘን ካልተቻለ ትርፉ ድካም ስለሆነ ማቆምን የመሰለ መፍትሄ አይታየንም ፤ ይህን መረጃ የምንሰበስብበት ፤ የምንጽፍበት ፤ አስረጅ መጽሀፍቶችን የምናገላብጥበትን ጊዜ ፤ ለኢንተርኔት የምናወጣው ወጪ ሌላ ስራ ብንሰራበት በገቢው ለአንድ ቤተክርስትያንን የሚያስፈልገውን ጧፍ እጣን ማሟላት ያቅተናል ብለን አናስብም ፤ ጸበል ሄደን በሽታ ያደከማቸውን ሰዎች ጸበል ብናመላልስ የተሻለ ነው ብለን እናስባለን ፤ አስታማሚ የሌላቸውንም ማስታመምም ትልቅ ስራ ነው ፤ ለማንኛውም የራሳችንን ስራ ወደፊት ራሳችን ዳኛ ሆነን ቀጣይነቱ ላይ እንፈርድበታለን ፤ ምን ዋጋ አለው መፍትሄ የማይሄን ነገርን ማመላለስ ? በስተመጨረሻ ሁላችሁ ለዋድባ ገዳም ለተጋረጠበት አደጋ እንዴት የመፍትሄ አካል እንሁን ብላችሁ አስቡ………እስቲ ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን


                                                                                                                              

                

20 comments:

  1. Why not you mention who you are so that we can follow you!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. WHY U NEED TO KNOW WHOM WROTH THE FACT ? THIS IS YOUR MOTHER EOTC CALLING YOU SO PLAN AND DO YOUR PART.

      Delete
    2. yes it is true. tell us who you r. lead us. we will follow.

      Delete
    3. eotc call me to pray. not to fight. the answer is in lords hand not in our power. it is not eotc voice.

      Delete
    4. EOTC calls you to pray not to eat. So why you EAT??

      Delete
  2. ክርስትያኖች ከ80 ሚሊየን የግብጽ ህዝብ ውስጥ 10 በመቶውን ብቻ የሚይዙ ናቸው ፡፡ በሀገራችን ትልቁን ቁጥር የምንይዘው ኦርቶዶክሳውያን ነን ፤ የግብጽን ክርስትያኖች ያህል እንኳን በሀገራችን አቤቱታችንን ያሰማንበት ጊዜ አለመኖሩ ሳስበው ማህበረሰባችን መብትና ግዴታውን አያውቅም ያስብላል .eza yalu eko kirestyanochi and honew new egan endekutrachin mebzat hasabachinim yetelayayena endekutrachin yebeza silehone new ers bersachin tekefaflen minim lewit anametam manim gebto betachinin yibezebzewal enji ahunim bihon erasachinin memermer kirs=tyanun yekefafelutim erasachewin ende YONAS agaltew niseha kalgebu tifatu aykomim.

    ReplyDelete
  3. Yegbagne lekerstos becha enlalen

    ReplyDelete
  4. አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያስፈልግን መረጃው እንጂ የመረጃው አቅራቢ ማንነት አይደለም ! !
    መረጃውን በራሳችን ማረጋገጥ እንችላለን ፤ስለዚህ ምላሹን ለመስጠት የራሳችንን አስተዋጾ እናድርግ !

    ReplyDelete
    Replies
    1. It is true the Holy Bible says "kefreyachew tawkuachewalachu" so every body it is not that much necessary who are they. what is useful is what are they doing and is their information true??

      Delete
  5. "እኛም ዝምታው ተመችቶን መረጃዎችን ከኢንተርኔት ፤ ከፌስ ቡክ ፤ ከተለያዩ ብሎጎች እና ዌብ ሳይቶች ላይ እየለቀምን ከማንበብ እና ከመናደድ ውጪ ምንም ማድረግ አለመቻላችንን ሳስበው ይገርመኛል ፤ ፍርሀታችን መስመሩን ስቷል ፤ የማንጠቅም ሰዎች በስመ ክርስትያ መሆናችንን ሰዎች በደንብ እያወቁልን ነው" አዎ ትክክለኛ አባባል ነው እራሴንም ከዚህ አባባል አኳያ ፈትሼዋለሁ መረጃዎችን ከኢነተርኔት በመሰብሰብ ከመናደድ ከማልቀስ ውጪ አንድም ያደረኩት አስተዋጽኦ የለም በዚህም በእጅጉ እራሴን ወቅሻለሁ ግን እኮ ወንድሞቺ ለሁሉም ነገር እኮ አስተባባሪ ይፈልጋል አኔ በዚህ በኩል ደካማ ነኝ ነገር ግን ከጎናችሁ ለመሰለፍ እና ድምጼን ለማሰማት ግን ከንግዲህ በኋላ ዝግጁ ነኝ! የእዚህ በሎግ አዘጋጆች በምታቀርቡልን መረጃ ሁሉ እጅግ በጣም ደስተኛ ነን ለተዋህዶ እምነት እያደረጋችሁ ያላችሁት አስተዋጽኦ ቀላል እንዳይመስላችሁ ብዙ የተዋህዶ ልጆችን ከአጽራረ ቤተክርስቲያኖች የጥፋት ተልዕኮ እንዲጠነቀቁ/እንዲጠበቁ አድርጋችኋል ስለቤተክርስቲያናችንም ወቅታዊ መረጃዎችንም ከናንተ አግኝተናል የስራችሁ ውጤት ለእናነተ በግልጽ ባይታያችሁም ለእኔ ግን እጅግ ብዙ እንደሆነ እገነዘባለሁ አሁንም በእኛ ተስፋ አትቁረጡ በርቱልን! እሲቲ አሁነም የዋልድባንም ሆነ የሌሎች አብያተ ክርስቲያኖች ጉዳዮችን በጋራ ድምጻችንን የምናሰማበት መንገድ አመቻቹልን በኢነተርኔት/በፌስቦክ ብዙ ነገር ተሰርቷል እኮ! በግብጽ እና በሌሎች አረብ ሃገራት ሲደረጉ የነበሩትን ሁላችንም የምናስታውሰው ነው! ከዚ ሁሉ በላይ ግን ሁላችንመ በጸሎት እንትጋ!! አምላክ የምህረት እጁነ ይዘርጋልን የእመቤታችን አማላጅነት የመላዕክት ጠባቂነት የጻድቃን የሰማእታት ተራዳዒነት አይለየን አሜን!!

    ReplyDelete
  6. ጥሩ ቀን ዛሬ ነዉ ሁሉንም አልሰማንም አናዉቅም ማለት አንችል ሰምተናልም እናዉቀዋለንም የሚጠበቅብንን ግን በተግባር አልገለፅነዉም! ስለዝህ ሁሉም ሰዉ የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል! መረጃን ከዬትም እናግኝ እዉነትነቱን ካረጋገጥን ምንጩን ማወቅ ብዙም አስፈላጊ አይደለም ለማሰርና ለማሳሰር ካልሆነ በቀር! ስለዝህ ለቤ/ክ ዘብ እንቁምላት ብዙ ቤ/ክ ሲቃጠል ብዙ መስኪዶች ደግሞ ተሰርተዋል ብዙ ክርስቲያኖች ሲገደሉ ብዙ ሙስሊሞች ተወልደዋል ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል አስበን እንትጋ!
    አምላከ ቅዱሳን ይርዳን!

    ReplyDelete
  7. wede wendemoche ena ehetoche be semet sayehon be menfesawinet kehone del enadergalen GIN NIBOCH YETESAKA SERA LEMESRAT AWURA(NIGIST) YASFELGACHEWAL enam kedmiya yerasachinen amerar benastekaken meknyatum benamtsi,selamawi self benaderg...... lemnden new teblew yemiteyekut mehemnu sayhon kelay yalut nachew yane enesu yemisetun melse ewenet le EOTC new? enam kidmiya amerarochachinen enastekakel malete yeh teyake kebad behonm esty enmokrew .Beterefe bezi blog mereja yemtsetun betam eyamesegenku gin kretaye lemn new mereja becha yemtsetut lemn yemefthe akals athonum lemn yezih ken ezi beta endezih enadreg atlum? eremjjaw yejemerrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrr!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  8. You raised good point! I guess, this has been the query's of so many christians too, for several years. We have individual determination and are concious enough about things in relation to our church. Now, in my view there is a big confusion as to who is the responsible person to adress and handle issues like the case in point, based on reliable evidences. This is the big gap that makes evidences valueless without any consumption for the purpose. We need an association who can manage things based on the laws of the Country. This association need to be meant to talk with different medias, government officials in order to realise those safeguards provided in the Constitution and other laws. Accordingly, I see a sort of confusion that every body seems to look for the actions to be made by mK for every problem related with the church. But, this is wrong for one thing it is very problematic for MK to handle every issues( managerial problem at least) for the other every issue will not fit the very purpose of MK, legal jurisdiction issues. Therefore, in order to tackle the problem we have to establish an association Country wide that should be registered and licensed which can act on behalf of the churh. But, till it gets official license it may act as organiser for different church related emergency services, for instance the Ziquala and Asebot fire burn issues.
    For the establishment of this association, the current problems of Waldiba, Ziquala and Asebot can serve as a steping stone.
    Therefore, lets organise christians who are voluntary to handle the case of waldiba, to negotiate it with teklay betekinet first and the concerned government officials subsequently and so on....
    After a while, the association should be structured comprising different departments in it that would adress different themes of the church.
    Regards,

    ReplyDelete
  9. One way could be to submit our questions through the coalition of Sunday Schools in Addis and the neighboring areas that could be scaled up to country wide.

    ReplyDelete
  10. በእውነት ትክክል ናችሁ ለቤተክርስቲያናችን ዛሬ እኛ አለንልሽ ካላልናት ማን ይበላት መቼም የሌላ እምነት ተከታዮች መጥተው ስለ እኛ ቤተክርስቲያን አይጮሁልንም እኛ አለሁሽ እንበላት እንጂ? አምናለሁ ክርስቲያን ይሞታል እንጂ አይገልም እኛም መጋደል አለብን የሚል ሀሳብ የለኝም ግን በስላማዊና ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ እናቅርብ ማለት ትክክለኛ ሀሳብ ነው፡፡ ለ አንድ አድርገን ብሎጎች ችግሩ ምን መስላችሁ ስብሳቢ እንፈልጋለን እኔ ብቻዬን ብወጣ ምንም አልጠቅምም ግን ስብስበ ብለን ብንወጣ መፍትሔ እናገኛለን ይህን የሚያደርግ ደግሞ ያስፈልገናል ሀሳባቹ የእውንተ ከሆነ እባካቹ ስብስቡን እንወጣለን፡፡ በ11/7/2004 ቤተ ክህንት አካባቢ በዝቋላ ጉዳይ እንደወጣን ሳታወቁ አትቀሩም አሁንም ቢሆነ እርግጠኛ ነኝ ጥሪ ቢደረግልን እንወጣለን የኦርቶዶክስ ትዋህዶ ወጣት ለቤተ ክርስቲያኑ ነብሱን ይሰጣል ለዝቋላ አቦ የወጣው ህዝብ አይታችሁት የለ??? እውነት ወጣቱ ስራ የለውም??? አለው ግን የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ ብሎ ነው የወጣው አሁንም ቢሆን ስብሳቢ ያስገልገናል እናንተም አካሄዱን ካወቃችሁ ምሩን እንፍጠን አንዘግይ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፡፡

    ReplyDelete
  11. ውድ የአንድ አድርገን ብሎግ አዘጋጆች እውነት እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ!!!የሁል ጊዜ ጩኸቴ ነበር እባካችሁ ህዝቡን ማስተባበር የሚችል አንድ አካል አቁሙልን መረጃዎችን የምንለዋወጥበትን ዘዴ ፍጠሩልን እኛ የፖለቲካ ጥማት የለብንም፣ እያልን ያለነው የራሳችንን አንትኩብን ነው ።የማንረባ እንቅልፋሞች መሆናችንን ስላወቁ በሃገሪቱ ከሞላው ባዶ መሬት መርጠው የአባቶቻችንን ርስት ናዱብን ከዚህ በላይ ምን ሊያመጡብን ይችላሉ? ሁላችንም ቆስለናል! ከመነኮሳቱ ጋር እንሰዋ፣ መልስ ካጡ ይግደሉን እኛ ግን የድርሻችንን እንወጣ። እባካችሁ ነህምያን ሁኑን??

    ReplyDelete
  12. ebakachehu werewen teten የድርሻችንን እንወጣ eneweta. 1 adirgenoch enamesegenalen

    ReplyDelete
  13. ye "nehmiya yale................." egna end Nabute "Yeabatochen erst alesetem..." enbel ebakachhun nehmiyan felgulen ebakachhun ahun bemenged sebeb eyaresut new nege wedewst zelkew sayigebu yemitebekebenen enadereg................ebakachu nehmiyan felgulen

    ReplyDelete
  14. eree please tadia yehenen yemesele issue eyale men entebekalen yehon and yemiyadergenen akal aququmuna baza lay enguaz (sebsabi or selamawi self yemideregibet ken, bota ,alamaw,eskemen deres(gibu),merejaw lemen yahel gize yesetew , ena yemesaseluten negeroch setteled addergu ena fetan lewet enamet.
    ene yezequala abo mekatel sijemer be kedaminet botaw lay kederesut sewoch andu nebereku kezan ken behuala gin yewetatun moral ayeche betam geremognal becha sayehon belelochim yebetekerestiyanua chigeroch lay selamawi self binaderege ena yebekulachinen serten enelef beye sewochin anagree neber degafachewen kestugn behula gen mechee ena yet bota man lahulum and ayenet mereja yyesetal yemil neber gin ye semen AMERICA wen self mesale aderegewalehu silezi endesuu or ke muslimochu yategegnewen lemed meseret bemadereg ke were wede sera engeba nege ayedelem zarewenuuuu .please please weree anaderegew .....melesun ke andaderegen befetenet etebekalehu enem andu kefit kedami endehonku menager ewedalehuuuuuuu.....its a right time ....GOD WITH us!!!!!
    thank you. andaderegen.....

    ReplyDelete
  15. Good day! I know this is kinda off topic but I was wondering which blog platform are you using for
    this site? I'm getting sick and tired of Wordpress because I've had problems
    with hackers and I'm looking at options for another platform. I would be fantastic if you could point me in the direction of a good platform.
    Look at my website - cool articles for teenagers

    ReplyDelete