Thursday, March 22, 2012

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ኑዛዜ


እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፡፡
የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እለምናችሁዋለሁ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አድርጉ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እለምናችኋለሁ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እለምናችሁዋለሁ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን  እለምናችኋለሁ!
የተወደዳችሁ ልጆቼ ልጆቼ እኔ እስከ መቼም አልተኛምበማንኛችሁም ላይ ቅሬታ የለኝምከእግዚአብሔር ትእዛዛት መካከል ለእናንተ አንዲቱንም ከመናገር እንዳልሸሸግሁ እግዚአብሔር ምስክር ነው፡፡ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የዕባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፡፡ እናም ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፡፡  ያልኳችሁን ካደረጋችሁ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡ ያልኳችሁን ካደረጋችሁ ሰማያዊ ጸጋ አይጎድልባችሁም፡፡
የተወደዳችሁ ልጆቼ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ስለ ነፍሴ ጸልዩልኝ  ሳልፈቅዳቸውም ሆነ ካለማወቅ የሠራኋቸውን መተላለፎቼን እንዳይቆጥርብኝ እና  በፊቱ ዕረፍትን ይሰጠኝ ዘንድ ጸልዩልኝ፡፡


ለጳጳሳት ለማህበረ ካህናት

  • ፍቅራችሁንና እየለመንሁ ትፈቱኝ ዘንድ በአክብሮት እማጸናለሁ፡፡ እነሆ አሁን ከእናንተ ርቄ ትቼያችሁ ሔጃለሁ ፊታችሁንም ለማየት አልችልም፡፡ ሁላችሁም ስለ እኔ በመጸለይ እንድትደክሙ መምህሬ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀበለኝና ይቅር እንዲለኝ በቅዳሴያት ሁሉ እንድታስቡኝ እለምናችኋለሁ፡፡
  • የእረኞች ሁሉ እረኛ ክርስቶስ እንደ እርሱ ፈቃድ እና እንደልቡ አሳብ እናንተንና ነገሮቻችሁን ሁሉ የሚመራ ስለ ነፍሳችሁ መዳን  ጻድቅ እረኛን ይመርጥላችሁ ዘንድ እለምነዋለሁ!!
 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዲህ ነበር ያሉት፤ "ግብፅ ውስጥ የማይታወቅ (የተሰወረመነኩሴ በአሁኑ ጊዜ የለም፤ ኢትዮጵያ ብትሄዱ ግን ብዙ የተሰወሩ መናንያንን ታገኛላችሁ" ነበር ያሉት፡፡ ይህ ገዳም ደግሞ ዋልድባ ነው ፤ እባካችሁ እንታደገው                                                                                        
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

(ይህ የኑዛዜ ቃል በቅዱስነታቸው ቃለ ኑዛዜ ተብሎ በቀብራቸው ዕለት የተነበበ ሲሆን አንዳንዶች ለሁሉም ፓትርያርክ (The Patriarchal Commentary!) የሚነበብ  ነው /Once again as much confusion has arisen this is NOT HH personal will rather it is the Commentary to be read at the funeral of every Patriarch!/  ብለዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ከላይ እንዳያችሁት ተርጉሜዋለሁ!  ትልቅ ምስጋና ቃለ ኑዛዜውን ለላከልኝ ለንፍቀ ዲያቆን ቢሾይ ማርቆስ  (especial gratitude for Sub deacon Bishoy, St Barbara & St Noufer’s Coptic Orthodox Church in Sydney Australia) 

አስባችሁታል ይህ ኑዛዜ ለአቡነ ጳውሎስም ይነበባል………. . .. ይገርማል

13 comments:

  1. Kidanemariam Ze Did LibanMarch 22, 2012 at 5:49 AM

    Due you think the same will be read when Aba Paulos passes away? If it is it will be one of the most an fair thing in the world!

    ReplyDelete
  2. ድንቅ ኑዛዜ!እውነተኛ እረኛ ስለ ልጆቹ ግድ ይለዋል! በረከትዎ ይደርብን ቅዱስነትዎ !በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ይጸልዩልን!መልካም እረኛ ይሾምልን ዘንድ ያሳስቡልን?

    ReplyDelete
  3. nefs yemarelin. realy diacon kale hiwot yasemalin. it will be the will of God to have got good kepper.

    ReplyDelete
  4. yehe leabune pawlos aynebebem.abune pawlos sinazezu yemilut neger binor "adera EPRDF tebeku " new yemilut

    ReplyDelete
    Replies
    1. "EGZIABHER YAKEBEREWEN SEWE AYAWAREDEWEM!"tenesh sele metenagerut neger eferu,haymanotena temkehetegna ye zere telachan atekelakelut!Egziabher lebuna yestachehu!

      Delete
    2. "EGZIABHER YAKEBEREWEN SEWE AYNEKEWEM"tenesh selemetenagerut neger eferu,poletica haimanot atekelakelu,Egziabher kezih tera ye zeregna astesaseb yawtachu!lebona yestachu!Abatun ye mayakeber......!

      Delete
    3. aha seytanenem bebetekiristian sineges zem malet tegebi aydelem.leban leba ,zemawiwen zema malet yigebal.nebeyu Natan Dawiten zem endalalew ewneten menager yitebekibenal.ene bebekule abune pawlos bimotu dese yelegnal bayhon yebase endaymeta eferalehu

      Delete
  5. ይህ ኑዛዜ ለአቡነ ጳውሎስም ይነበባል...............Hahahahahaha

    ReplyDelete
  6. ስምከ ሕያው ዘኢይመውት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚሰጥ ቅጽል ነው
    ግን አቡነ ሽኖዳነ አደንቃለሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. እንኳን የአቡነ ሺኖዳ ስም አይደለም የዘመናችንን ዘፋኞች እንኳ ስማቸው ከመቃብር በላይ እንዲኖር ዓለም ትደክማለች፡፡
      ልመናቸው ፀሎታቸው ይሰማልን አሜን
      እንኳን የአቡነ ሺኖዳ ስም አይደለም የዘመናችንን ዘፋኞች እንኳ ስማቸው ከመቃብር በላይ እንዲኖር ዓለም ትደክማለች፡፡
      ልመናቸው ፀሎታቸው ይሰማልን አሜን

      Delete
  7. "Wuha biank bemin yaworardutal, Milachis biabit bemin yibetutal ..." Bitsuan abatochachin Abune Gorgorios ze'ziway & Abune Shinoda ze'gibts endalmotu Bitsue abatochin Abune Gorgorios ze'zequala besemonu sirachew ayitenal, -libonayisten-. 'wub'

    ReplyDelete
    Replies
    1. i a saying you are the true father of all christian not only for orthodox tewahdo

      Delete
  8. ooooooooooooo i am too feel bad, really i don't know what i say to the death of the pop.pop shenodaiii is a man who is i extremly appriciate and admire.so God take him to heaven.

    ReplyDelete