Thursday, March 22, 2012

የወ/ሮ የእጅጋየሁ መፅሀፍ በሚዛን ላይ


(አንድ አድርገን መጋቢት 14 ፤ 2004ዓ.ም)፡-  በባለፈው ሳምንት በአንዱ ቀን በአራት ኪሎ ስላሴ ቤተክርስትያን አካባቢ የሆነ ወረቀት የሚለጥፉ ሰዎችን ተመልክቼ ምን ይሆን ብዬ ጠጋ አልኩኝ ፤ የሚለጥፉት ነገር ወ/ሮ እጅጋየሁ አዘጋጀሁ ያለችውን የመፅሀፍ ማስታወቂያ መሆኑን ተመለከትኩኝ ፤ የወረቀቱ ጀርባ በቢጫ ቀለም ያለው ሲሆን ፅሁፉ ደግሞ ጥቁር ነው ፤ ከላይ በትልቁ ‹‹ አነጋጋሪው መፅሀፍ በገበያ ላይ ዋለ ›› የሚል በቀይ ቀለም የተፃፈ ከርቀት ማንም ሰው በሚያነበው መልኩ ተፅፎ ተመለከትኩ ፤ ዝቅ ብዬ ስመለከት መፅሀፉ ‹‹ በሃይማኖት ሽፋን ………… እስከ መቼ›› የሚል ርዕስ አለው ፤ መሀሉ ላይ የሶስት አባቶች ሀውልት ሰፍሮበታል የመጀመሪያው የአቡነ ጳውሎስ ፤ ሁለተኛው  ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ፤ ሶስተኛው ደግሞ በግብፅ በርሀ የሚገኝው ባለፈው ቅዳሜ በሞት የተለዩን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ መሆናቸውን ተመለከትኩኝ ፤ ግን ለምን የእነዚህን አባቶች ሀውልት ልትጠቀም ቻለች ? ብዬ ራሴን ጠየኩኝ ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ አቡነ ጳውሎስ የራሳቸውን ሀውልት በ400 ሺህ ብር አሰርተው ሲያስመርቁ የአሰሪ ኮሚቴው የበላይ ሆና ስታንቀሳቅስ የነበረችው ይህችው ሴት ናት ፤ አሁን ደግሞ ሀውልቱ ይገባቸዋል ሌሎች አባቶች አሰርተዋል ለእሳቸው እኛም ብናሰራ ምን ችግር አለው?  ለአቡነ ጳውሎስ ሐውልት ሲያንስባቸው እንጂ አይበዛባቸውም  የሚል መልዕክት እንዳለው ለማወቅ ብዙም አያዳግትም ፤ ይህ ሀውልት አንድ ሺህ መጽሀፍ በእርሱ ዙሪያ ለመፃፍ ቢነሱ ቀኑ ሲደርስ እንደሚፈርስ እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ፤ ይህ ከስርዓተ ቤተክርስያን ውጪ ነው ፤ ይህ ሀውልት ቆሞ ቤተክርስትያንን ለሚቀጥለው ትውልድ አናስተላፍም ፤ ከአባቶቻችን እንዲህ አይነት ስርዓት አልተቀበልንም ፤ እኛ በዘመናት መሀል የመጣን የቤተክርስትያንን ትውፊቷን ፤ ቀኖናዋንና ዶግማዋን ለቀጣዩ ትውልድ ጠብቀን እንድናስተላልፍ  በዚህ ዘመን የተገኝን ምዕመን ነን ፤ ጠባቂዋ የማያንቀላፋው የሰማይና የምድር ፈጣሪ መድሐኒዓለም ነው ፡፡ ትላንት ሲኖዶስ ይፍረስ ብሎ በወይዛዝርቶች እና እኛን በማይወክሉን ሰዎች ተጽህኖ አማካኝነት እስካሁን ቢቆም ወደፊት ይቆያል ለትውልድም ይተላለፋል ማለት አይደለም ፤ አትሳሳቱ ፤ 

ደርግ ህዝቡ ያልተቀበለውን የሌሊንን ሀውልት ሲያቆም ጠያቂም አልነበረውም ፤ ስርዓቱ ሲገረሰስ ግን ይህን ሀውልት ያፈረሰው ማን እንደሆነ የምናስታውሰው ነው፡፡ ኢህአዴግ የሌሊን ሐውልት ላይ እጁን ሳያነሳ ህዝቡ እንዴት እንዳፈረሰው ለማወቅ ታሪክ ጠራቂ ሰዎችን ማፈላለግ የሚያሻ አይመስለንም ፤ ማህበረሰቡ የማይቀበለው ነገር ለመፍረስ ጊዜ ብቻ ነው የሚጠብቀው ፤ የምንይልክ ሀውልት መሀል አራዳ ላይ ፈረሱ ደረቱን ገልብጦ የምታዩት በአድዋ ላይ ለሀገራችን ያደረጉትን አስተዋፅኦ መሰረት በማድረግ ነው ፤ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ደግሞ ለጣሊያን አልገዛ በማለታቸው አሁን ጨው በረንዳ ብለን በምንጠራው አካባቢ ላይ በ1928 ሀምሌ 28 ቀን በ8 ጥይት ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት ይህችን ሀገር እና ቤተክርስትያናችንን  ለአሁን ስላቆዩልን ጭምር ነው ፤ አሁን ቆሞ የምታዩት ሀውልት እንደ አቡነ ጳውሎስ ሀውልት በድብቅ የተሰራ ስራ አይደለም ፤ ማንንም ሰርፕራዝ ለማድረግም አይደለም ፤ የሌሊን ሀውልት  ያገኝውን እጣ ፈንታ የአቡነ ጳውሎም ሐውልትም ይደርስበታል ፤  ጊዜ እውነት ለያዘ ሰው ፈራጅ ነው ፤ ጊዜንና ዘመንን የሚያቀዳጅ ደግሞ አንድ አምላክ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡

ሰው በሚመነኩስበት ጊዜ ፤ ለቤተክርስትያንና ለሀገር በሚጸልይበት ወቅት ላይ እንዴት የቤተክርስትያን እሾህ ሆኖ ይነሳል ?  እኛ እስከሚገባን ድረስ እግዚአብሔር እስከዚች ሰዓት ጠብቆ ዛሬን የጨመረልን ንስሀ እንድንገባባት ስጋው ደሙ እድንቀበልበት ይመስለናል ፤ እንደ መልካም ስራችን ነው ብለን አናምንም ፤ ሰው እድሜው 80 ሊሞላ 2 ዓመት እየጎደለው እንዴት ልብ አይገዛም ? እንዴት ለመልካም ነገር ተባባሪ አይሆንም? እንዴትስ ያሳለፈው ነገር አያስተምረውም ? እድሜ ትምህርት የሚሆነው ለተጠቀመበት ብቻ ነው ለሌላው ደግሞ ሸክም ነው ፡፡ እኔ በበኩሌ ይህን ጉዳይ ከቤተክርስትያን ጋር ብቻ አያይዤ አልመለከተውም ፤ ለምን?  ብትሉኝ ፤ ማህበረሰቡ አንድን በእድሜ የገፋ ሰው የሚሰጠው ክብር ሳይ እኔም እዚህ በደረስኩኝ ያሰኝኛል ፤ ትልልቅ ሰዎች ለቤተክርስትያንም ሆነ ለሀገር ዋርካ ሆነው መመልከት ደስ ያሰኝኛል ፤ ትልልቅ ሰዎች ትውልድ እንዲቀጥል ትልቁን ሚና ይጫወታሉ ፤ በዘመናት ያዩትን የሰሙትን ለቀጣይ ትውልድ ከማስተላለፍ አኳያ የማይተካ ሚና አላቸው፤ ታዲያ ሰው ይህን ስራ በሚሰራበት ወቅት እንዴት ቤተክርስትያኗን ለማፍረስ ሰይፍ ይዞ ይነሳል ?

የወ/ሮ እጅጋየሁን መፅሀፍ የተቀነባበረ ድርሰት እውነታ ላይ ያልተመሰረተ  መጽሀፍ መሆኑን ለሰዎች ለመፃፍ አስቤ ስነሳ የዋልድባ የዝቋላ እና የአቡነ ሺኖዳ ሞት መፅሀፉ ላይ ብዕሬን እንዳላነሳ ያዝ አድርገውኛል ፤ለምን ቢባል አሁን ከጠቀስኳው ስራዎች በላይ ስላልሆነ ነው ፤ አሁን ግን ነገሮች ረጋ ስላሉ መፅሀፉን በጊዜው  መተቸት ተገቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፤ ሁሉንም ነገር በጊዜው መልስ መስጠት ተገቢ ነው ብዬም አምናለሁ ፤ የዛሬ ወር አካባቢ አባ ሰላማ ድረ ገፅ ላይ ለወጣው ፅሁፍ የዘመኑ ቀሳጥያንና ስራዎቻቸው በሚል መልስ መስጠታችን ይታወቃል፤ 4ሺ ጊዜም ተጎብኝቷል ፤ ነገር ግን ከሰዎች እንደተረዳነው ዘገየ እንጂ መልካም ነው የሚል አስተያየት ተሰቶናል ፤ የሴትየዋን ዋና ዋና ሀሳቦች ብቻ አንስቼ የተረዳሁትን ያህል ለእናተው ለማሳየት ሙከራ አድርጌአለሁ

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አቡነ ጳውሎስን ሰርፕራይዝ”አድርጌበታለሁ የሚሉትንና ከብር አራት መቶ ሺህ በላይ ገንዘብ እንደወጣበት የተናገሩለትን “ሐውልተ ስምዕ” በተመለከተ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የተሰኘ መጽሐፍ ማሳተማቸው ይታወቃል ፤ አዲሱ የመጀመሪያውን መፅሀፍ የሰውን ቀልብ ለመሳብ በሌላ ማስታወቂያ ተመልሰው ያመጡት ነገር ነው (የሞኝ ዘፈን ይመስል) ፤ የመጀመሪያው ‹‹ሀውልቱ እስከመቼ›› ይላል ይህኛው ደግሞ ‹‹በሀይማኖት ሽፋን ……..እስከመቼ›› ይላል፡፡የተለጠፈው ማስታወቂያ ላይ ከበታች የሰውን አእምሮ በሚስብ መልኩ የሚቀጥለሉት ፅሁፎች ቀርበውበታል ፤ እኛ ለምናውቀው ብቻ መልስ እንሰጣለን፡፡
  1.   ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለሰባት ዓመታት በእስር ቤት ለምን ተንገላቱ ?
ደርግ በዘመኑ  ከህግ ውጪ ሰዎችን ያሰቃይ ፤ ያንገላታ ነበር ፤ አቡነ ጳውሎ ስለ አንዲት ሀይማኖታቸው ብለው ይሆን የተንገላቱት ? እኛ ይህ ነው የሚል ሀሳብ የለንም ፤ በአሁኑ ሰዓት ግን ምዕመኑ አበሳውን የበላው  ቤተክርስትያናችን  የተንገላታችው ባለፉት 20 ዓመታት በእርሳቸው ፍትሀዊ ያልሆነ አመራር መሆኑን መናገር እንችላለን ፤  አፋችንን ሞልተን መናገር የምንችለው ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ብለው አለመሆኑን ነው ፤ መፅሀፍ ተፅፎ የሰው ስራው አይቀየርም ፤ ስራው አይቀልም ወይም አይከብድም ፤ ስው ምግባሩ እና ስራው መሰረት ሆኖለት ነው ለተሻለ ስብእና የሚያበቃው ፤ በተፈበረከ የወይዛዝርት ወሬ አይደለም ፤
2.    አቡነ ጳውሎስ ጎላ ሚካኤል ማረፊያ መቃብር ቤት ጠይቀው ለምን ተከለከሉ?
አሁን ይህ ነገር ምኑ አስማሪ ሊሆን ይችላል ፤  ባይሆን ባለፈው በሲኖዶስ የአባቶች ስብሰባ ጊዜ ማነው በራቸውን የደበደበው ? ማነው ከዚህ በፊት ያልተደረገን ነገር በአባቶቻችን ላይ ለማድረግ የደፈረው ? ፤ ለምንስ መንግስት ጉዳዩን ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍ ፈለገ?  ብለው ለምን አልጠየቁም?  በምድር ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነው የሚለው መጽሀፉ ፤  በህይወት በምትኖሩበት ዘመናት ክርስትያን ከሆናችሁ አልጋ በአልጋ ነው የሚል ነገር አልተማርንም ፤ የቤተክርስትያን አስምህሮ እንዲህ አይደለም ፤ አባቶች መከራ ቢደርስባቸው ሁሉን የሚያስችል አምላክ ፈተናውን እንዲያቀልላቸው ፤ ወይም እንዲያሳልፍላቸው ይጸልያሉ እንጂ በዚህ ጊዜ ይህ ፈተና ደረሰብኝ ፤ እንዲህ ሆኜ እንዲህ ተደርጌ ብለው አያወሩም ፤ ይህን መሰል ነገር ለመንፈሳዊ ሰው ተስማሚ ምግባር አይደለም ፤
3.    ቅዱስ ፓትርያርኩ በአሜሪካ 7 አብያተ ክርስትያናት እንዴት መሰረቱ ?


  • ተገነቡ ስለተባሉት 7 አብያተክርስትያናት ያለው እውነታ
ወ/ሮዋ ይህን የፃፉላቸው ከአቡነ ጳውሎስ ህይወትን የሚያትተው መፅሀፍ ተነስተው ነው ፤ መዋዕለ ዜናቸው እንዲህ የሚል ዜና ጽፎላቸዋል።‹‹በስምንት ዓመት ውስጥ ይሆናል ተብሎ በማይታሰብ አስገራሚ ሁኔታ በሐገረ ባእድ የሚከተሉትን ሰባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ቤተክርስትያናትን አቋቁመዋል›› ይላል። ፤ ለነገሩ ሰው እንዲያውቀው የምፈልገው ከእሳቸው ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች ጠቀም ያለ ብር ከተሰጣቸው አይደለም የአባ ጳውሎስን ዜና መዋዕል ይቅርና የሰይጣንን ገድል ለመጻፍ ወደ ኋላ የማይሉ ሰዎች ናቸው፡፡ እኝህ ሴት ደግሞ ሌላ ውሸት ሊዋሹን በርካታ ልብ ወለድ መሳይ ነገሮችን ፤ ከዚህ በፊት ያልተደረጉ ፤ መረጃ የሌላቸውን የፈጠራ ወሬዎች በመፅሀፍ መልክ አዘጋጁልን ፤ ከተጠቀሱት ሰባት ቦታውች ውስጥ
  1. በአሪዞና ኪዳነምህርት አስርተዋል ተብሎ ዜና ቢነገርላቸውም በአሪዞና ኪዳነምህርት የምትባል ቤተክርስትያን የለችም።
  2. የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን በታምፖ ፍሎሪዳ ተሰርቶ አገልግሎቱ ሳይቋርጥ የምእመናን ቁጥር በዝቶ የእግዚአብሄር መንግስት በሰፊው እየተሰበከ ይገኛል ይላል ፤ የአባ ጳውሎስ ዜና መዋእል።ሆኖም ግን እንዲህ የሚባል ቤተክርስትያን በታምፖ ፍሎሪዳ የለም ተብሏል።
  3. የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በላስቬጋስ ኒቫዳ አቋቁመዋል ቢባልም በኒቫዳ በዚህ ስም የሚታወቅ ቤተክርስትያን የለም።


ሌሎቹ አራቱ ደግሞ ቀድሞ የነበሩ ሲሆኑ አባ ጳውሎስ የእኔ ናቸው ብለው በራሳቸው ስም በማድረግ የማይገባቸውን ዝና አግኝተውበታል ።በኒዮርክ፤በሎስ አንጀለስ፤በሳንዲያጎ፤በዳላስ ያሉትን እኔ ነኝ ያሰራዋቸው ይላሉ ፡፡ ወይዘሮዋም ይህን ደግመው የገደል ማሚቱ በመሆን አስተጋብተውልናል ፡፡ አንድ አባት እንኳን እውነት ሆኖ ይህን ሁሉ ቤተክርስትያን ቢሰሩ ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅ ሰርተው እንዳልሰሩ ይሆናሉ እንጂ በመጽሀፍ መልክ በህይወት እያሉ ስራቸው ታትሞ ፈተና እንዲሆንባቸው ቤተክርስትያን አትፈቅድም ፤ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት እንደ ፀሀይ የሚያበራ ስራቸው ከሞቱ ከ50 ዓመት በኋላ ነው በእግዚአብሔር ፍቃድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በአባቶች ብርታት ተፅፎ ለትውልድ የተላለፈው፡፡ ቤተክርስትያን ልጆቿን ዘወትር የምታስተምረው ከውዳሴ ከንቱ እንድንርቅ ነው ፤
ይህን ስፅፍ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሲበርድ በእጃቸው ሲሞቅ በማንኪያ የሚበሉት አቡነ ፋኑኤል ሲኖዶስ ፊት ቀርበው የጵጵስና ማዕረግ በተሾሙበት ዕለት የዋሹት ውሸት ትዝ አለኝ ፤ አባቶችም ዋሹ ፤ ልጆች ዋሹ፤ ውሽት ውሸት ነው የተሻለ ትርጓሜ ልንሰጠው አንችልም፡፡በአሜሪካ ሀገር የዋሽንግተን ዲሲ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ሰርቼ አስረክቤአለሁ ብለው ፤ ምልዓተ ጉባኤው በደስታ ተቀብሎት ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተጨብጭቦላቸው ነበር ፡፡“ሰርቼ አስረክቤያለሁ” የሚሉት ቤተ ክርስቲያን ግን፤ በባለቤትነት የተመዘገቡት ከሶስቱ ግለሰቦች አንደኛው  አቡነ ፋኑኤል ናቸው፡፡  ይህችን የመሰለች አካሄድ አቡነ ፋኑኤል ከአባታቸው ከአቡነ ጳውሎስ ይሆን የተማሯት? ፡፡ በጊዜው የነበሩ አባቶች ላያውቁ ይችላሉ፡፡ መረጃ ላይኖራቸው ይችላል ፡፡  በምስራቅ ሐረርጌ ላይ የተመደቡ አንድ አባት ዋሽንግተን ስለተሰራው ስራ በአገልግሎት ድካም ሙሉ መረጃ ላይኖራቸውና ላያውቁ ይችሉ ይሆናል፡፡  እውነት መስሏቸው ደስ ተሰኝተው ቢያጨበጭቡላቸው አይገርምም  መረጃው ስለሌላቸው ነው ፡፡ ይች መረጃ ደግሞ ከእኛ አታመልጥም፡፡
4.    ቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ የግድያ ሙከራ ለምን ተደረገ ?
እኛ እንኳን የዚህን አይነት የተቀነባበረ ወሬ እስካሁን አልደረሰንም ፤ አቡነ ጳውሎስ መቼ ነበር የመግደል ሙከታ የተካሄደባቸው ? እኛ የምናውቃት ነገር ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ተከናወነ የሚለውን የዚህን የተገላቢጦሽ የሆነ መረጃ ነው ያለን ፤ የእሳቸው የስጋ ዘመድ የተባለ ሰው ስላደረገው ነገር(እዚህ ጋር ስለ ጉዳዩ ማውራት ተገቢ አይደለም) ፡፡ ወ/ሮ እጅጋየሁ ብር ሊኖራቸው ይችላል ፤ መፅሀፍም ፅፈው የተሳሳተ መረጃንና የተፈበረከን ወሬን በመጠቀም ሊያሳትሙ ይችሉ ይሆናል ፤ ነገር ግን እውነታን መቀየር በጣም አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል የተገነዘቡ አይመስለኝም ፤ ሰዎች በአይናቸው ያዩትንና የተመለከቱትን በአሉባልታ ወሬዎች ከጭንቅላታቸው ማጥፋት አይቻልም፡፡ በጣም እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ይህን የመግደል ሙከራ ሰዎች እስከዛሬ ሰምተውት አያውቁም ፤ ወ/ሮዋ ግን ተደርጓል ብለው ያለ ተጨባጭ መረጃ ይሞግታሉ፡፡
5.    ፓትርያርኩ ለ7 ዓመታት በእስር ቤት ያንገላቷቸውን የደርግ ባለስልጣናት መንግስት ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ከፍተኛ ትግል ማድረጋቸውን አንብበዋል ?
ከ1967 እስከ 1983 ዓ.ም. ሥልጣን ላይ በነበረው ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ (በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ)፣ በንጹኀን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ብዙ የሚያስብል ነው ፤ ደርግ በዘመኑ ከ400ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል ፤ አንድ ትውልድ አጥፍቷል ፤ ኢህአዴግ ስልጣነ መንበሩን ሲረከብ የደርግ ባለስልጣናትን ወደ ቃሊቲ አውርዷቸዋል ፤ በዚያም የ19 ዓመት የእስር ጊዜ አሳልፈዋል ፡፡ እነዚህን ሰዎች ያስፈታቸው የሀይማኖት አባቶች ጥያቄ አለመሆኑን አስረግጠን መናገር እንችላለን ፤ በአባቶች አማላጅነት እነዚህ ሰዎች አልተፈቱም ፤ ምህረትም አልተደረገላቸውም ፤ መንግስት በምን አይነት መንገድ ምህረት ለማድረግ ሲያስብ ህጉን በማይጋፋ መልኩ ፤ የተጎጂ ቤተሰቦች ጥያቄ በማያነሱበት መልክ መሆን ስለሚፈልግ እርቀ ሰላሙ ላይ አባቶች እንዲሳተፉ ተደረገ እንጂ በአባቶች ውትወታ  አይደለም የተፈቱት ፤ በዚህ ይቅርታ ላይ የአባቶች ሚና ምን ያህል እንሆነ ለማወቅ የሚያስችል አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ ማግኝት ከባድ ነው፡፡ እንዲያው ይህን መልካም አጋጣሚ አስታኮ ዝናን ወደ ራስ ለመሳብ ካልተደረገ በቀር የመንግስታችንን ባህሪ እናውቀዋለን፡፡ የሐይማኖት አባቶች ምን ያህል ተሰሚነት እንዳጡ ብዙ ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅብኝም ፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው የICASA ጉባኤ ላይ የተደረገውን ነገር ማስታወስ ብቻ በቂ ነው ፤ አዳራሹ በጋዜጠኞች ተሞልቷል ፤ የሐይማኖት አባቶች ስለ ግብረሰዶማውያን መግለጫ የሚሰጡበት ጊዜ ተቃርቧል ፤ ሁሉም የፕሮግራሙን መጀመር እየተጠባበቀ ይገኛል ፤ በመሀል ግን የጤና ጥበቃው ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ በፍጥነት በጉባኤው ላይ ተገኝተው አባቶችን ወደ ውስጠኛው ክፍል ይዘዋቸው ገቡ ፤ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ያህል ከተነጋገሩ በኋላ ፕሮግራሙ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ለጋዜጠኞች ተናገሩ ፤ ለምን ? ተብሎ ሲጠየቅ ለጋዜጠኞች የማያመረቃ መልስ ሰጥተው ጉባኤውን በተኑት ፤ ግብረሰዶማውያንም በአዲስ አበባ ተሰብስበው ፤ ግብረሰዶማውያንን እንዴት በአፍሪካ ማስፋፋት እንደሚቻል መክረው ተለያዩ ፤ ታዲያ የቱ ጋር ነው የአባቶች ተሰሚነት ያለው ?፤ ምኑ ጋር ነው መንግስት ላይ ተፅህኖ ፈጣሪዎች የሆኑት ? ከሀይማኖት አባቶች ተሰሚነት አኳያ የአንድ ሚኒስትር ተሰሚነት በሚያጋድልበት ሀገር ላይ እየኖርን እንዳለን እናውቃን ፤ ለአቡነ ጳውሎስ ዝና  ያልተደረገውን ተደርጓል ብንል ትዝብት ላይ ይጥለናል ፤ የሀይማኖት አባቶች መንግስት ላይ ተፅህኖ ፈጥረው እነዚህን ታሳሪዎች አስፈቷቸው ካልን ተለይተው ጥቂቶች ብቻ ለምን ተፈቱ ? ያልተፈቱትንም ስም ዝርዝር ማቅረብ ይቻላል፡፡ እንደ እኛ እምነት እርቅ ጥሩ ነው ፤ ይቅርታ ማድረግ መልካም ነው ፤ ይህ ግን የተደረገው በአባቶች ጫና አይደለም፡፡ ሴትየዋ ‹‹የባለቤትን ፀባይ የማውቀው እኔ ነኝ›› አለች አሉ፡፡

መጀመሪያ ከአንድ ሲኖዶስ ወደ ሶስት ሲኖዶስ የተከፋፈሉት አባቶች ሳይታረቁ ሌላውን ለማታረቅ መጣር በሰዎች ዘንድ ራስን ትዝብት ላይ መጣል ነው ፤ ሰው መጀመሪያ የበደሉትን ሰዎች ይቅርታ ካላደረገ ፤ አሱም ለበደላቸው ላኮረፋቸው ሰዎች ይቅር ይቅር በሉኝ ሳይል ሌላ ቦታ ሄዶ ሌሎችን እርቀ ሰላም ያወርዳል ማለት አይታሰብም ፤  በሚቀጥለው ሰኔ ወሬ እኝህ በሀገር ውስጥ እና በምድረ አሜሪካ ያሉ አባቶች ከተኳረፉ ድፍን 20 ዓመት ይሞላቸዋል ፤
6.    ቅዱስ ፓትርያርኩ ሀብትና ንብረታቸውን ለቤተክርስትያን ማውረሳቸውን  ሰምተዋል?
ይህ ደግሞ ይገርማል ፤ የትኛውን ንብረታቸውን ነው ያወረሱን ? ለቤተክርስትያን ውርሱ ቀርቶባት ያለውን ሀብቷን ራሱ በአግባቡ እንድትጠቀምበት ማድረግ ቢችሉ ትልቅ ነገር ነው ፤ ከ17,000 ብር በላይ ለአንድ የእሳቸው የስጋ ዘመድ የሂሳብ ሰራተኛ ይከፍሉ እንደነበር ለምን አልፃፉልንም ? ፤ እንደ መዥገር የተጣበቋትን ሰዎች የስጋ ዘመዶች እና ስለሚያገኙት  ጥቅማቸውንስ ለምን አልጻፉልንም ?  ፤ ዘለው ስለ ውርስ ከምን ያወሩናል?  ፤ መጽሀፍ ቅዱስ መጀመሪያም መነኩሴ ምንም ሀብት አይኑረው ይላል ፤ እሳቸው ቢያወርሱም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ፤ ግን አላወረሱም ፤ ከቤተክርስትያን የወሰዱትን ለቤተክርስትያኗ ሰጡ ተብሎ ቢስተካከል ጥሩ ነው፡፡ ቤተክርስትያን የብር ችግረ ኖሮባት አያውቅም ፤ ያለባት ችግር የመልካም አስተዳደር ፤ የጎጠኝነት ፤ ዘርን ፈልጎ መጠቃቀም ፤ አድልዎ ፤ በደል ፤ እንጂ ሌላ አይደለም ፡፡  አንድ ዲያቆን አዲስ አበባ አድባራት ላይ ለመቀጠር እስከ 4000 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ለቤተክህነት አስተዳዳሪዎች የሚከፍልበት ጊዜ ነበር ፡፡
7.    የ‹‹ሀውልቱ ይነሳ›› ሀሳብ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ወይንስ የሌሎች ድብቅ አላማ እና ተንኮል?
ይህ ደግሞ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ሆኖ ሳለ የ‹‹ሀውልቱ ይነሳ›› ሀሳብ የሌሎች ድብቅ አላማ ነው አሉን ፤ ይህን እኮ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች ሁሉም ናቸው የተቃወሙት ፤ ባለፈው ዓመት የሲኖዶስ ስብሰባም በአንድ ድምጽ ከስርአተ ቤተክርስትያን ውጪ ነው በሚቀትሉት 20 ቀናት ይፍረስ ብለው ውሳኔ ያሳለፉት ፤ ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ አለ ፡፡ እርስዎ አቡነ ጳውሎስን ሰርፕራይዝ ለማድረግ ከእነ አቶ  በጋሻው ጋር በመሆን ትልቅ ስህተት ሰርተው ካበቁ በኋላ አሁን ደግሞ የ‹‹ሀውልቱ ይነሳ›› ሀሳብ የሌሎች ነው ሊሉን ተነሱ ፤ ይገርማል ፤ እኛ ሰው በህይወቱ እያለ ለምን ሀውልት እንደሚያሰራ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የጻፈውን ጽሁፍ ሄዶ ማንበብ ብቻ በቂ ነው ፤ ምዕመኑ በልቡ አፍርሶታል ፤ ህዝበ ክርስትያኑ በአቡነ ጳውሎስ አይነ ያወጣ ስራ በጣም አዝኗል ፤ ይህ አዘኔታ ደግሞ ለእሳቸውም ጥሩ አይደለም ፤ አምላክ አሁንም ማስተዋን ይሰጣቸው ዘንድ ለንስሀ ሞትም ያበቃቸው ዘንድ ክርስትያናዊ ጸሎታችን ነው ፤ ትልቁ አባት የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ በህይወት ዘመናቸው ከ200-300 መጻህፍት ለምእመኑ አበርክተዋል ፤ ከዓመታ በፊት በየሳምንቱም አንድ መፅሀፍ ይፅፉ ነበር ፤ እንዲህ አይነት ስራ ሰርተው አባትነታቸውን ፤ እረኝነታቸውን በአግባቡ ተወጥተው ከ40 ዓመት በላይ በመንበረ ማርቆስ ወንበር ላይ ተቀምጠው ባለፈው መጋቢት 08/2004ዓ.ም ወደማይቀረው የማይሞት ስራ ሰርተው  ሄደዋል ፤ አቡነ ሺኖዳ ሀውልት ሲያሰሩላቸው እሱን ተመልክቶ ለራስ ጣኦትን ከማስገንባት ፤ ለምን አቡነ ሺኖዳ ብዙ በርካታ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ መፅሀፍት ጽፈዋል ፤ እኔም ለልጆቼ ይህን ላድርግ ብለው መንፈሳዊ ቅናት አድሮባቸው መፅኀፍ አይፅፉም?  ፤  ከእኛ ሀጥያት ብዛት ፤ ከበደላችን ብዛት የተነሳ መልካም አባት ለበጎች እረኛ የሚሆን አባት ሊሰጠን አልቻለም ፤ እኔ አቡነ ጳውሎስ ላይ እጄን አልጠቁምም ፤(የራሴን ሀጥያት ነው ዘወትር የማየው ፤ እኛ እንዲህ ሆነን አምላክስ እንዴት መልካም አባት ይስጠን ፤ ይህ የማይታሰብ ነው፡፡)
8.    እግዚአብሔር በሾማቸው አባቶችና አገልጋዮች ላይ አድማና ስድብ የሚፈፅሙት እነማን ናቸው ከጀርባቸውስ ማን ተገኝ ?
(ጥሩ ስራ በሰራ ከአፋችሁ ያልጠፋው ማህበረ ቅዱሳን ነውን …?)
9.    በመጨረሻም ‹‹ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ ድንቅና ወቅታዊ መጽሀፍ›› የሚል ፅሁፍ አለው፡፡

(እንደ እኛ መልዕክት መፅሀፉ ላይ ምንም ቁም ነገር አያገኙበትም ይህን መፅፍ ካነበቡ በኋላ ያቃጠሉት ጊዜ ስለሚያበሳጭዎ እንዲያነቡት አንመክርም ፤ ገለባ ብቻ ነው ፤ ፍሬውን አያገኙትም ፤ መጽሀፉ ውሸትን ለትውልድ ለማስተላለፍ ታስቦ የተሰራ ስራ ነው ፤ እኛ ደግሞ ለአንባቢያን እኛ አንብበን ያጠፋነው ጊዜ ይበቃል ፤ እርስዎ ጊዜዎን አያጥፉ እያልን እንመክራለን ፤ እነሱ ለስራቸው አምላክ ይጠይቃቸዋል ፤ እኛ ግን ባለን በምናውቀው ነገር እንጽና፡፡)

 ‹‹የምንፈራው እውነት የለም››
                                                                                       

13 comments:

  1. ማህበረሰቡ የማይቀበለው ነገር ለመፍረስ ጊዜ ብቻ ነው የሚጠብቀው። ሰው በሚመነኩስበት ጊዜ ፤ ለቤተክርስትያንና ለሀገር በሚጸልይበት ወቅት ላይ እንዴት የቤተክርስትያን እሾህ ሆኖ ይነሳል? በአሁኑ ሰዓት ግን ምዕመኑ አበሳውን የበላው ቤተክርስትያናችን የተንገላታችው ባለፉት 20 ዓመታት በአቡነ ጳውሎስ ፍትሀዊ ያልሆነ አመራር መሆኑን መናገር እንችላለን። መጽሀፍ ቅዱስ መጀመሪያም መነኩሴ ምንም ሀብት አይኑረው ይላል ፤ እሳቸው ቢያወርሱም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ፤ ግን አላወረሱም ፤ ከቤተክርስትያን የወሰዱትን ለቤተክርስትያኗ ሰጡ ተብሎ ቢስተካከል ጥሩ ነው፡፡ መጽሀፉ ውሸትን ለትውልድ ለማስተላለፍ ታስቦ የተሰራ ስራ ነው።
    እግዚአብሔር ይስጥህ። ሰለእውነት የሚመሰክሩ ብጹአን ናቸው። ሀሰት በእወነት ቦታ ሊነገር የሚችለው ሀሰት ተናጋሪ አንደበት እስኪዘጋ ድረስ ነው። እውነት ግን በሀሰት ውስጥም ሆኖ ሀሰት እስኪወገድ ድረስ ይኖራል። እና ስናውቀው ፣ እንደተማርነው እውነተኛ ታሪክ የሚጻፈው ታሪኩ የሚጻፍለት አካል በህይወት ሳይኖር እና ታሪኩን የሚጽፈው አካል ምንም አይነት ተጽእኖ በማይደረግበት ወቅት ነው። ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት አውነተኛ ታሪክ ሊጻፍላቸው የሚችሉ ሰዎች በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ወቅትና በፊት ለነበሩ ሰዎች ብቻ ነው። እኒህም ሰዎች በወቅቱ የነበሩና አሁን ግን በህይወት የሌሉ መሆን አለባቸው። ከደርግና ከኢሀዲግ መንግስት ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው መሆን አለባቸው። ከዚህ ውጭ የተጻፈ ታሪክ ሁሉ ተአማኒነት የለውም። ሰለ አቡነ ጳውሎስ የሚጻፈው ምንም አይነት ታሪክ አሁን ሀሰትና ሀሰት ብቻ ነው። የአቡነ ጳውሎስ እውነተኛ የህይወት ታሪክ የሚጻፍበት ወቅት አሁን አይደለም። እውነትን አሁን ለማሳተም ስለማይቻል ማለት ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. thank you you are really right poeple do not cost your time and money to buy the book

      Delete
  2. Amlake kidusan beka bilo yihichin setiyo ena meselochuan kesihitetachew yemimarubetin kalhonem qitaun yasayachew lela min yibalal. minew yezihch betekrstian genzeb, habt, kirsua teziko teziko alalik ale? atirua denua, botawa be'esat sitefa yanin lematifat genzebuan metekem alchalechim endih yale likimkami neger lay gin begef yiwetal. Elzabel hoy chiferaw yibkash. ejishin ena egrishin sebsibi!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  3. ሴትየዋ ለምን አርፋ አትቀመጥም ንስሀ ገብታ በመቁረቢያዋ ሰዓት ምን ነክቶዋታል!!! ትገርማለች!!!

    ReplyDelete
  4. "ቤተክርስትያን ውርሱ ቀርቶባት ያለውን ሀብቷን ራሱ በአግባቡ እንድትጠቀምበት ማድረግ ቢችሉ ትልቅ ነገር ነው " አዎ ተወቃሽ ትውልድ እንዳንሆን ቤተክርስቲያኖቻችንን ቅርሶቻችንን ተጠብቀው ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፍ ትውልድ ያድርገን!! ይህንን ተግባር የምያስፈጽም ቅዱስ አባት ይስጠን! ገዳማቶቻችን እየተደፈሩ ቅርሶቻችን እየተመነዘሩ በቤተክርስቲያችነ ላይ ጥፋት እየደረሰ ነው በምነሰማው ሁሉ ውስጣችን ነደደ!! እንደ ወ/ሮ እጅጋየሁ ያሉ የቤተክርስቲያናችን ነቀዞችን አምላክ መቼይሆን የሚነቅልልን?!! እሷ ምነው የአንድ ሰው ነገር እነዲህ ቆሮቆራት!! በዚህ እድሜዋ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ገብታ ከምትበጠብጠን በሶስት መንግስታት የሰራቻቸውን ሃጠያቶች ይቅር እንዲላት ምነው ወደአንዱ ገዳም ሄዳ /የምታምንበት ከሆነ ማለቴ ነው ግን እጠራጠራለሁ/ ወደአምላኳ ብትጸልይ!! እሳቸውስ እውነተኛ መነኩሴ ቢሆኑ ተይ ሊሏት የገባ ነበር!! እረ ወገኖቼ ምነው እንዲህ ሃጠያታችነ በዛ!! በእኛ ትውልድ እነዲህ አይነት ነገር በመከሰቱ ውሰጤ እጅጉን ቆሰለ! አምላክ በምህረቱ ይጎብኘን!

    ReplyDelete
  5. ስብሐት ለአብ ስንቱን ያሳየን (ያሰማን) ይሆን ልብ ይስጥልን ሌላ ምን ይባላል

    ReplyDelete
  6. I am really sorry to write this, but what can I do except to write it
    Elza min nekat? Keken wede ken ewuket sayihon dinikurina eyeseferebat new oko. Lib yistish belulign enaniteye. genzeb aemirowan silasaworew guzowa wede mot mehonun lemayet balemechaluwa enazinalen.
    Lemehonu Andit set Kepatriarik sir min tiseralech? esachewus Esuan Lemin Akerebuwat? Ere betekihinet hizibun benefisim besiga eyegedelew silehone tinish bitarem tiru new.
    "Beten Yewenbedewoch Washa Aderegachihuwat" Yale Geta jirafun Yizo Sayimeta rasachihun bitateru melikam new.

    ReplyDelete
  7. Fitsame Zemen new Ewunetin yizen enigadel. Amlakachin yatsenanal.

    Lesatut libonan yistilin.

    ReplyDelete
  8. Interesting but you could include many things like the 4millio birr car, the money lost to his recration, the amount of money corapted each year from the church, his handness to the government and attaching the church, his religious attitud etc. I know it is enormeous to enumerate his bad acts but if you tuch the issue of for example I gave all my properties to the church you could elaborate it highly and make it how the saying is realy funny.

    Please write as much as possible his evel dids though it is clear to the public, people may even missleaded by such kind of nonsense book.

    ReplyDelete
  9. BESMEAM ER Gud Ewnetena negat Eyader yeteral Aydel Ayyy GETA AMELAK Kedusan ETHIOPIAN aytewatem Egezyabeher betun Matedat yawekal

    ReplyDelete
  10. አሁን ይሄ ሁሉ ሩጫ "አባ" ጳውሎስን እውነተኛ ለማስባል ነው? እንዴ የሚናገሩበትንም ጊዜ አይለዩም ግን? እኛ እኮ በዚህ ትውልድ ውስጥ ያለን ነን ከአይናችን በላይ የእሷን ፈጠራ እንድናምን ነው? ወይ አለማፈር! እሳቸው እንደው ከልባችን ከወጡ ቆዩ!ምንም ማስተባበያ አያስፈልግም አምላክ ጊዜውን አቅርቦ ይገላግለን እንጂ እኔ በእራሴ እንደ ልጅ የሚያዝን ልብም የለኝ። ከዚያ በፊት እንደ ቅዱስነታቸው አቡነ ሽኖዳ ሁሉ አልቅሶ ይቀብራቸው ዘንድ ያሳዘኑትን ምእመን ይቅርታ ቢጠይቁ መልካም ነው እላለሁ። አምላክ ልብ ሰጥቶ ለንስሃ ያብቃዎ፣ ተገላገልን ከመባል ይሰውርዎ!አልቅሶ ቀባሪም ይቸግራል እኮ እናንተ

    ReplyDelete
  11. who cares about the dead fish, may be her suporter bege,yared and others..

    ReplyDelete
  12. Who cares abaut the dead fish except elzabel ?

    ReplyDelete