Thursday, March 6, 2014

አደናጋሪው የ‹‹መጋቢ ሐዲስ››ነት ጉዳይ

  • መጋቢ ሐዲስ ለመባል ምን ያስፈልጋልመጋቢ ሐዲስ የሚል መአረግ ለተሰጠው አገልጋይ ከእሱ ምን ይጠበቃል?
  • ቤተ ክርስትያን ለምን አይነት መምህራን መጋቢ ሐዲስ የሚል የመአረግ ስም ትሰጣለች ?


(አንድ አድርገን የካቲት 28 2006 ዓ.ም)፡- ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ የቅዱሳን መጻሕፍት ሃሳብን መነሻ አድርጎ የሚወጣው ሥርዓት ምን አይነት የሥጋ ወይም የነፍስ ትሩፋት እንደሚያሠራን ከየትኛው ፈተና እንደሚጠብቀን ወይም ለየትኛው የሰይጣን ወጥመድ በር እንደማይከፍት በማጥናት ይዘጋጃል፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት የነበሩ የእግዚአብሔር ቅዱሳን የሠሯቸውን ሥርዓቶችን ያጸናል፡፡ ያሉና የነበሩ ሥርዓቶችንም ሸክም የሚሆንባቸውና ወደ ተሻለ መልአካዊ ሥርዓት እስኪደርሱ ድረስ ሊጨነቁ የሚችሉ አዲስ አማኞችን በክርስትና አምልኮ ውስጥ ተሳታፊ ለማድረግ የነበረውን ሥርዓት ተሻሽሎ እና ዘመኑን ዋጅቶ ለእነርሱ ሊሰራላቸው ይችላል፡፡ እነዚህ ሁሉ መንገዶች ግን እግዚአብሔር ወደሚወደው የቅዱሳን ኑሮ የምዕመናንን ሕይወት ማሳደግና ለመልካም ሕይወት ማዘጋጀት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለ3ሺህ ዘመን ከቆየችበት የአምልኮ ሥርዓት አንፃር የተመሰከረላት እና የምዕመናንን ሕይወት በመጠበቅና በማሳደግ በመንከባከብ ጠብቃ እንድትኖርና ከብዙ የፈተና እሳቶች እንደ ወርቅ ነጥራ እንድትወጣ ሊቃውንቶቿ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ባስቀመጠችው የእውቀት ልኬት መሰረት ለመምህራኖቿ ለዘመናት ምዕመኑን እንዲያንጹ እና እንዲያገለግሉ የምትሰጣቸው የአገልግሎት ማዕረጎች ያሏት ሲሆን አሁን አሁን እነዚህ በአበው የቆዩት ሥርዓቶች ስልጣንና ፍቅረ ንዋይ ባወራቸው ሰዎችና የተሸከሙት የኃላፊነት ክብደት ምን ያህል መሆኑን ባልተገነዘቡ አንዳንድ አባቶች አማካኝነት በአንድም በሌላ መንገድ ማዕረጋቱ ሲመዘበሩ እየታዩ ይገኛሉ፡፡

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8
‹‹ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፥ ገንዘብ አመጣላቸውና። እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ። ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም። እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።›› የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 18-23
                                                                                                 

አሁንም ባለንበት ዘመን እግዚአብሔር የሚገለገልበትን ነገር በገንዘብ ለማግኝት የሚጥሩ በገንዘብ ኃይል ቅስናውን፤ ድቁናውን፤ መጋቢ ብሉይ ፤ መጋቢ ሐዲስነትንና የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱን የማዕረግ ስሞች በአቋራጭ ሩጠው ጠቅልለለው የራሳቸው ያደረጉ ፤ የተሳካላቸውና በመሮጥ ላይ የሚገኙ ሰዎች አሉ፡፡ እኝህን የመሰሉ ሰዎች ከሁለት ዓመት በፊት ጵጵስናን ለመሾም ከ300,000 እስከ 500,000 የኢትዮጵያ ብር በጉቦ መልክ ፤ በእጅ መንሻ መልክ ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡ ለእነዚህ አይነት ሰዎች ምግባሩ እና ትምህርቱ ሳይኖራቸው የማይገባቸውን የአገልግሎት መጠሪያ ለማግኝት ለሚባዝኑ ሰዎችና ካለ አግባብ ላገኙት ሰዎች የእኛ መልእክት ከላይ የሐዋርያት ሥራ ላይ ‹‹የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ››  ካለው የጴጥሮስ መልዕክት የሚለይ አይደለም፡፡ 

ቤተ ክርስቲያን ካላት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ውስጥ መምህራን ብላ ከምትጠራቸውና ስሙንና ማዕረጉን ከምትሰጣቸው የማዕረግ አይነቶች ውስጥ ጥቂቱን ለማየት እንሞክር፡፡
  1. ሊቀ ማእምራን ፡- ይህ ማለት የአዋቂዎች አዋቂ ማለት ሲሆን በተለምዶ አራት አይና ይባላል፡፡ መጽሐፍተ ብሉያትን ፤ መጽፍተ ሐዲሳትን ፤ መጽሐፍተ ሊቃውንትን ፤ ሐይማኖተ አበውን ቄርሎስን ፤ 14ቱን ቅዳሴያትን የዮሐንስ አፈወርቅንና የፍትሐ ነገስትን አንድምታ ትርጓሜ ጠንቅቆ ያወቀና ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምር መምህር ሊቀ ማእምራን የሚለውን የማእረግ ስም በቤተክርስቲያኒቱ በጳጳሳቷ አማካኝነት ትሰጠዋለች፡፡ 
  2.  መጋቢ ብሉይ፡- መጋቢ ብሉይ ማለት የብሉያት መጻሕፍት መምህር ሲሆን በትርጓሜ ቤት ለዓመታት ቆይቶ ትርጓሜውን ያካሄደ ምስጢር ያደላደለ ፤ መጽሐፍተ ብሉያትን ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምር ምሁር ለሆነው ለዚህ ሰው መጋቢ ብሉይ የሚለውን ስም ቤተክርስቲያን አክብራ ትሰጠዋለች፡፡ 
  3.  መጋቢ ምክር ፡- ይህ ማለት ማከሪ ፤ መሪ ፤ አስተማሪ ማለት ሲሆን የመጽሐፈ መነኮሳትን ፍሊክሲዩስን አረጋዊ መንፈሳዊና ፤ ማርይስሐቅን አንድምታ ትርጓሜ ያወቀ ምስጢር ያደላደለ ፤ ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምር ምሁር ለሆነው ለዚህ ሰው ይህ የቤተክርስቲያናችን የማእረግ ስም ይሰጠዋል፡፡ 
  4. መጋቢ ስብሐት(መጋቢ ሐዋዝ)፡- ይህ ማለት የድጓ ፤ የአቋቋም እና የዝማሬ አስተማሪ ማለት ሲሆን የያሬድን ጸዋትወ ዜማ ማለትም ድጓ ፤ ፆመ ድጓ ፤ ዝማሬ መዋሲት ከነይትባህሉ ጠንቅቆ የሚያውቅና ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምር ምሁር ለሆነው ለዚህ መምሕር መጋቢ ስብሐት ወይም መጋቢ ሐዋዝ የሚለው ስም በክብር ይሰጠዋል፡፡ 
  5. መጋቢ እሩያን ፡- መጋቢ እሩያን ማለት ቅዳሴያቱን ከነምልክቶቻቸው ጠንቅቆ ያወቀና ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምረውን ሰው መጋቢ እሩያን የሚል የአገልግሎት ስም ይሰጠዋል፡፡ 
  6. መጋቢ ምስጢር ፡- ይህ ማለት ጥበብን ፤ ምስጢርን ተንታኝ ፤ አስተማሪ ፤ ለተመረጡ ልዑካን የበላይ ፤ የበላይ መምህር የምስጢር ባለቤት ማለት ነው፡፡ ምስጢርን ገልፆ መንገዱን መርቶ ቅኔውን ከነ አገባቡ ልቅም አድርጎ ማስተማርና ብዙዎችን ማፍራት ለሚችለው መምህር የመጋቢ ምስጢር የአገልግሎት ስም ቤተክርስቲያን ትሰጠዋለች፡፡ 
  7.  መጋቢ ሐዲስ ፡- የመጨረሻውና በአብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚሰጡ ማዕረጋት ውስጥ መጋቢ ሐዲስ የሚለው የማዕረግ ስም አንዱ ነው፡፡ መጋቢ ሐዲስ ማለት የሐዲሳት መጻሕፍት መምህር ማለት ሲሆን መጋቢ ሐዲስ ለመባል ደግሞ በአባቶች እግር ስር ሆኖ ዓመታትን ያሳለፈ የግዕዝን ቋንቋን ጠንቅቆ የሚያውቅና ማንኛውንም ለማስተማር የሚጠቀምባቸውን ምዕራፋትን ከግዕዝ ወደ አማርኛ ከአማርኛ ወደ ግዕዝ በማንኛውም ጊዜ መጽሐፍ ማገላበጥ ሳያስፈልገው ማስተማር የሚችል ፤ በስነ ምግባሩ የተመሰከረለት የእግዚአብሔርን ኃይል አጋዥ በማድረግ በጎችን በእግዚአብሔር ቃል ከተኩላዎች የሚጠብቅ ፤  ከዚህ ማዕረግ ቀድሞ ያሉትን አገልግሎት አይነቶች በስርአቱ ያለፈ እና በመምህራን የተመሰከረለት መሆን ይጠበቅበታል፡፡ 

 አንድ ሰው መጋቢ ሐዲስ ወይም የሐዲስ ኪዳን መምህር በትርጓሜ ቤት ቆይቶ  ትርጓሜውን ያካሔደ ምስጢር ያደላደለ መጽሐፍተ ሐዲሳትን ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምር ምሁር ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ማለት 35ቱን መጽሐፍተ ሐዲሳትን ንባቡን ከነትርጓሜው ምስጢሩን ከነአንድምታው ማወቅና ለሐዲስ ኪዳን መጽሐፍቶችም ተጠያቂና ኃላፊነትን መውሰድ የሚችል ሊሆን ይገባዋል፡፡ በሐዲስ ኪዳን ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ ብሉይን ከሐዲስ ሐዲስን ከብሉይ እያጣቀሰና እያመሰጠረ ሙሉ መልስ ሊሰጥ ይገባዋል፡፡  ይህ ማለት ግን 35ቱን የሐዲሳት መጻሕፍት ብቻ ይማራል ማለት ሳይሆን በተማሪ ቤት ሳለ ተመርቆም ከወጣ በኋላ በተያያዥ ለሐዲስ ኪዳን የሚጠቅሙ ብዙ መጻሕፍቶችን ማገላበጥ እና  ማንበብ የሚገባው አገልጋይ መሆን ይኖርበታል፡፡ በተለይ ሐዲስ ኪዳንን ከማቴዎስ ወንጌል እስከ ራዕይ ዮሐንስ ድረስ በደንብ አድርጎ መተርጎምና ማስተማር የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡

ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን ጎን ለጎን ሳይሆን ፊትና ኋላ ሆነው የተደነገጉ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሐዲስ ኪዳንን ለማተት ለመተንተንና ለማወቅ ለምዕመኑም ለማሳወቅ የብሉይ ኪዳንን ማንነት በክለሳ መልክ ማየት ማወቅና መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ በዘመነ ብሉይ የነበረው ዘመን ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔ እየተባለ ይጠራ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜ ድኅነተ ዓለም እንዲደረግ እውነትና ምህረት የሰፈነበት የይቅርታ ዘመን እንደመጣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፍቶ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ ፤ ድህነተ ሥጋ ድህነተ ነፍስ እንዲሰጥ ትንቢት በገላትያን መልእክቱ ምዕ 4፤4 “ጊዜው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ” ብሎ በገለፀው መሰረት የምህረት ቃል ኪዳን የተገባበት ነው፡፡ የኋላውን ጥሎ የፊቱን አንጠልጥሎ ስለማይሆን የሐዲስ ኪዳን መምህር የጠለቀ የሐዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን እውቀት ያስፈልገዋል፡፡ ይሁንና ይህን የማዕረግ ስም ለመቀበል በርካታ ዓመታት በአባቶች እግር ስር ቁጭ ብሉ መማርን ቢጠይቅም አሁን አሁን ግን መጠሪያው ኃላፊነት በማይሰማቸው አባቶች እንደ ሸቀጥ ከመደርደሪያ አንስቶ እንደመስጠት ቀላል ሆኖ እየተመለከትነው እንገኛለን፡፡




በዚህ ስም የሚጠራው አንዱ አቶ በጋሻው ደሳለኝ አይደለም ወንበር ዘርግቶ ሊያስተምር ይቅርና በአባቶች የተዘረጋን ወንበር ረግጦ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የግዕዝ ቋንቋ Nuclear Physics የሆነበት በግዕዝ መናገርም ይሁን ጆሮ ቢቆረጥ ግዕዝን መስማት የማይችል ፤ የግዕዝን ቋንቋ በአግባቡ የማያውቅ ሰው እንደ ቤተክርስቲያን ሥርዓት እንደ እነ አለቃ አያሌው ታምሩን የመሰሉ ሊቃውንቶች የቆሙበት የቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ቆሞ አንድነትና ሦስትነት በአግባቡ ያልገባው ሰው ‹‹መጋቢ ሐዲስ›› ተብሎ ማስተማር አይችል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርት በአግባቡ ያልተማረ እና በምንፍቅና አካሄዳቸው ከ9 ዓመት በፊት በሲኖዶስ ከነ ፅጌ ስጦታው በኋላ ከኮሌጁ በተሀድሶያዊ እና ምንፍቅና አካሄዳቸው ደብዳቤ ተጽላቸው ከተባረሩት ሰዎች አንዱ በመሆኑ ይህ የክብር የእውቀት ማእረግ ለእርሱ አይገባውም፡፡ ጓደኛው ትዝታውም ሳሙኤልም ቢሆን በሕገ ወጥ መንገድ የተቀበለውን ቅስና መስቀል አውጥቶ ለማሳለም ፤ ለምዕመናን የንስሀ አባት ለማሆን ፤ ቀድሶ ለማቁረብ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አብያተክርስቲያናት ውስጥ እንደማይሳካለት አውቆ በብዥታና በድብቅ ከዓመት በፊት ከምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ከሊቀ ጳጳሱ በችሮታ የተቀበለውን ቅስና ይዞ ወደ አሜሪካ ማቅናቱ ይታወቃል፡፡
ሌሎቹ ቀድሞ በእጃቸው ያስገቡትን የማዕረግ ስም ይዘው የሌሎችን ጉባኤ በማደናቀፍ ሥራ ተወጥረው ፤ የማይገባቸውን ቦታ ይዘው ቀን እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየናዱ ለሚገኙት ማስተዋልን ያድልልን

20 comments:

  1. ፍራቻው እስከ መቼ ነው አንዱ ግዕዝ ሳይችል ቤተ_ክርስቲያንን ሲያቃልል አንዱ የማይገባውን ቅስና ይዞ እዚህ ተአድሶን ለማስፋፋት መጥቶ ያገለግላል ለምን አሜሪካን ላይ ያሉትን የተሃድሶ ቤተ ክርስትያኖች ለምእመኑ በግልጽ እንዲያውቃቸውና እንዲጠነቀቅ አይድረግም እስቲ ስለነሱ መርጃ ይኑረን ብዙ ሰው ሳያጠፉ እባካችው እመቤታችን ተዋሃዶ ሃይማኖታችንን ከመናፍቃን ተሃድሶ ትጠብቅልን በርቱ.

    ReplyDelete
  2. ትናንት ደህና ነገር አስነበባችሁን ብለን አመስግነን ሳንጨርስ ይኽው ክሳችሁን ጀመራችሁ ስለሰው ካላወራችሁ ጽድቅ ያለ አይመስላችሁም አይደል ይቅር ይበላችሁ ፡፡ አሁን ይህ ያንጻል አረ እባካችሁ አስተውሉ የሚጠቅመውን ከማይጠቅመው ለዩ እንኳን የሰው ድካም መልካም ጎኑም ቢሆን ሰው ህይወት ላይ ምንም አያመጣም፡፡ ምንም ይሻላችሁ አይ ማቅ ፡፡ ይሁን ደግሞ እኮ መጋቢ አዲስ ይባል ሌላውም ማዕረግ አይጠቅምም ሰው በክርስቶስ መሆን ብቻ ነው የሚጠቅመው የሚያድነው በክርስቶስ ማመን ብቻ ነው በቃ፡፡ አሁን በእናንተ ቤት ጥሩ ነገር ማስነበባችሁ ነው በግል ማማቱ ሲያንሳችሁ በፆም የሰውን ሀጥያት እያጎሉ ማውራት ምን ይሉታል፡፡ አታፍሩም በዚህ ሰአት ሰውን ስለክርስቶስ እየነገርንው ወደ መዳን እንመሚመጣ በማድረግ ፋንታ በየቤቱ ስለሰው እንዲያወራ ሀሚተኛ እያደረጋችሁት እንደሆነ አስባችሁታል፡፡ እኔ አላማዬ እገሌ ትክክል አገሌ እንዲህ የምትሉትን ብታቆሙ ጌታ ሲመጣ ይጠይቃችኋል ህዝቤን አጣማችኋል ሀማተኛ አድርጋችሁትል ይላችኋ አስተውሉ፡፡ ጌታ ማስተዋልን ይስጠን፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. So, if you don't know about this things how are you gonna fix it. The problem we have is, we don't have information; as a result we don't defend our church. When people like begashaw come to the stage we need to say fix your problem before you come to the stage of the church. That is why you and I need to know the problems of the church. This is not "hamet" this is fact, if they don't write it we wouldn't have full information. It is up to you, how to use the information.

      Delete
    2. ሃሜት የምትለዉ ሰዉዬ እቅጩን ልንገርህ ጴንጤ ስለሆንክ ላንተ ላይጎረብጥህ ይችላል በማዕረግ ስም በሙያዉ ሰዉ ሲጠራ ለኛ ግን ለተዋህዶ ልጆች አይመቸንም።ክርስቶስን አዉቃለሁ ላልከዉ ጌታ ክርስቶስን አታዉቀዉም አንተ የምታዉቀዉ ሓሰተኛዉን የመናፍቃንን ክርስቶስ ነዉ።

      Delete
  3. You are expected ti be constructive. We know that Deacon Begashaw has problem in respecting cannon of ETOC. But he is not heretic. The holy synod freed him from tsi while advising him to each according the cannon of EOTC. You as christian are supposed to approach this person politely and straighten him by giving him love! Otherwise you are serving satan by spreading hate. You are stronggly begged in the Name of God to stop name mongering and revelation of sin of Indivduals sothat EOTC will be in peace whileyYou are encouraged to raise issue that can bring institutional change and making us informed about EOTC.

    ReplyDelete
  4. የአምላካቸን መስፈርት ግእዝ አይደለም

    ReplyDelete
  5. እንደተባለው ከሆነማ በደርዘን ሙሉ ያለ ችሎታና ያለ ሙያ ቅስና የተቀበሉ የማህበሩ ኣባላት ምን ሊባሉ ነው የጠላነውን ብቻ የምናወግዝ ከሆነ ምቀኝነት ካልሆነ በቀር እናንተም ቤት ያለውን እስቲ ንገሩን አቡነ ዘበሰማያትን በግዕዝ መድገም የማይችል ተንሥኡ ብሎ በዲቁና መቀደስ የማይችል ቅስና ሲቀበሉ የት ነበራችሁ እስቲ ንገሩን የእኛ ሕግ አክባሪዎች

    ReplyDelete
    Replies
    1. እንደተባለው ከሆነማ በደርዘን ሙሉ ያለ ችሎታና ያለ ሙያ ቅስና የተቀበሉ የማህበሩ ኣባላት ምን ሊባሉ ነው የጠላነውን ብቻ የምናወግዝ ከሆነ ምቀኝነት ካልሆነ በቀር እናንተም ቤት ያለውን እስቲ ንገሩን አቡነ ዘበሰማያትን በግዕዝ መድገም የማይችል ተንሥኡ ብሎ በዲቁና መቀደስ የማይችል ቅስና ሲቀበሉ የት ነበራችሁ እስቲ ንገሩን የእኛ ሕግ አክባሪዎች--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------wondime minewu enidezih tera honik? lenegeru tehadiso limadu newu.

      Delete
  6. what about መለዕከ ሰላም

    ReplyDelete
  7. Geez is not measurement of our faith. Geez was a just language . that is it. in our generation this language nobody use it . it nothing...............not related to any kind of faith..............

    ReplyDelete
    Replies
    1. " it nothing......" ተሳስተሀል አብዛኞቹ የዕምነታችን መሰረት የሆኑት መፃህፍት የተፃፉት በግዕዝ ነው። ጀርመን ጣሊያን ፈረንሳይ እነዚህ አገሮች ግዕዝን በድግሪ ደረጃ ያስተምራሉ። ለምን ይመስልሀል ብዙ በግዕዝ የተፃፉ ብዙ ሚስጢራት ስላሉ ነው የጀርመኑ ባየር ሙኒክ መድሀኒት ማምረቻ ሲከፈት መሰረት ያደረገው ምንን ይመስላች.......

      Delete
    2. ehe denikoro yeasun eyetale ferenige yitekemibetal esu yeawere haianot yizo yikerakeral menafik 666

      Delete
  8. don't mix mahibere kidusan in your own view .Also,don.t pjut mk web site in your blog.Mahibru ktemesretbet alama wuchi sigawi eyaderegachu fetena tabezalchu. sidb yasferdal.matw 6...who saya his brother deaf..read .

    ReplyDelete
  9. አየ ቤተ ክርስቲያኔ ሠው አይውጣብሽ የተባልሽ ይመስል እኛው ልጆችሽ እኔ እበልጥ እኔ እየተባባልልሽ ለጠላት ተጋለጥንልሽ ምነው ማ.ቅ በሥልጣንማ አናንተ ትበልጡ የለ ሰላም ለኪ የማታውቁት ሁሉ ቄስ ዲያቆን ሁናችኄል

    ReplyDelete
  10. Am tired of hearing individuals' complains. Please, let's use the website to feed christians in the world with the words of GOD & save their lives.

    ReplyDelete
  11. amilake esirael yidiresilin lela minim ayibalim menafikan wererun lenegeru tinibit yifesem zenid gid new haimanot timeneminalech gin atitefam menafikan betechristianin lematifat bitaserum eyesus christos bedemu wagituatal enidewim zare ekul tom getachin silemechereshaw zemen yasitemarebet gin ya ken yimeta zenid gid new

    ReplyDelete
  12. please instead of complaining and brushing black ink to someone let us learn our followers bible and our church originality. you are making the followers to be confuse through mentioning individuals. tell us tell us and learn us about our religion

    ReplyDelete
  13. betam yegeremal sewen metefo eyalu beyadebabau menager geta aywodwem ande semon yemeskelu sere kumartegnch belo tseafe belachew talak semaete adergachehute neber ahun degmo aweredacheut gen hulum aytekemem getan esebut

    ReplyDelete
  14. ግዕዝን ማክበር ጥሩ ነዉ ነገር ግን ግዕዝን እንደ ነባር ቁዋነቁዋ ወስደን ብናጠናዉም መልካመ ነዉ ግነ የመዳነ መሣሪያ አድርገን ባናየዉ ይሻላል እንዲያዉም ቤተክርሰቲያናችንን እያጋለጠ ያለ ማሣሪያ ነዉ ምነዉ ቢሉ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ገድላት የሚነበቡት በግዕዝ ስለሆነ ምዕመናን በእምነት ብቻ እየተቀበሉት እዚህ ደርሰዋል አሁን ግን ወንጌልን በአማርኛ የተማሩ ሰበኪያን በግዕዝ ተጀቡኖ በየቀኑ የሚለፈፈዉን የጥፋትና የምንፍቅና ትምህርት ሲገልጡልን ለስደት ተዳርገዋል እነ መጋቤ ሐዲስ በጋሻዉ ጉዳይ ግን የሐይማኖተ ሳይሆን የማቅ አባል ሁን አልሆንም ስለሆነ የሱን ጉዳይ ከሃይማኖት ጋር ባታያይዙት ይሸላል ያላለዉን አለ እያላችሁ ለንሰሐ ያማይመች ታርጋ አትለጥፋበት።

    ReplyDelete