Saturday, March 8, 2014

ፓትርያርኩ ‹‹ቤተ ክርስቲያን በዩኒቨርስቲ ምሩቃን አትመራም” ማለታቸው ቅሬታ ፈጠረ


  • ስለማኅበራት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት ተጠየቀ
  • ‹‹ማኅበራትበትኩረትሊመሩናጉዟቸውምእየተፈተሸሊስተካከልይገባል›› - መንግሥት
(አዲስ አድማስ የካቲት 29 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤እንዲህ ማለት አይችሉም›› በማለት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት በንግግራቸው ቅር የተሰኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት አገልጋዮች ጠየቁ፡፡

አገልጋዮቹ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፣ አቡነ ማትያስ ይሄን አስተያየት የሰነዘሩት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር የካቲት 21 እና 22 ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል የምክክር ጉባኤ በተካሔደበት ወቅት ነው፡፡


በምክክር ጉባኤው መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር ‹‹በባዮሎጂና ኬምስትሪ እንቀድስ እያሉ ነው፤›› ያሉት አቡነ ማትያስ፤ ‹‹ምን እያልኹ እንደኾን ይገባችኋል›› በማለት ማንን እንደሆነ የማሳየት ያህል የጠቆሙበት አስተያየት ያልተለመደና ጥቂት የማይባሉ የጉባኤውን ተሳታፊዎች ያሳዘነ እንደነበር የጉባኤው  ምንጮች አመልክተዋል፡፡

በምክክር ጉባኤው ላይ ለውይይት በቀረቡ ጽሑፎች፣ እስከ ሰማንያ ሺሕ የሚገመቱ መንፈሳውያን ማኅበራት በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እንደሚንቀሳቀሱ የተጠቀሰ ሲሆን  ቤተ ክርስቲያኒቱ ማህበራቱ በሕግና በሥርዐት የሚመሩበት ደንብ አውጥታ እስካልተቆጣጠረቻቸው ድረስ እየተከሠቱና ሊከሠቱ የሚችሉ ችግሮች በቀላሉ እንደማይታዩ ተመልክቷል፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በበኩላቸው፤በማኅበር ሽፋን ለግል ጥቅማቸውና ፍላጎታቸው የሚሯሯጡ፣ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ሕጸጽ የሚታይባቸው ማኅበራት የመኖራቸውን ያህል ጥሩ ሥነ ምግባር ያላቸው፣ ምእመናንን በማትጋት ለበለጠ ሀብተ ጸጋ የሚያበቁ ጠንካራ ማኅበራትም እንዳሉ ገልጸዋል፡፡  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምክክር መድረክና በቤተ ክህነቱ ጉባኤያት እየታየ ያለውማኅበራት አላሰራ አሉንበሚል በጅምላ የመፈረጅና የመኰነን ዝንባሌ፣ አብዛኞቹ ማኅበራት ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን እያበረከቱ ያለውንና  በቤተ ክህነቱ ቀጥተኛ አቅም ሊሸፈን የማይችለውን ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት ያላመዛዘነ ነው ብለዋል -የማህበራት አገልጋዮች፡፡

በአሁኑ ጊዜ ማኅበራት የአባሎቻቸውንና የበጎ አድራጊ ምእመናንን የገንዘብ፣ የዕውቀትና ሞያዊ አቅም በማስተባበር የገጠር አብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማት፣ አድባራትና የአብነት /ቤቶች በተቀናጀ መንገድ እንዲረዱ ያደርጋሉ፤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ዕድገት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሒዳሉ፤ በጠረፍ የሀገሪቱ ክፍል በሚያከናውኑት የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ምእመኑ በቋንቋው የሚገለገልበትን ኹኔታ ያመቻቻሉ፤ የቅዱሳት መካናት ተሳላሚዎችን ጉዞ በማስተባበር ሕዝቡ ቅርሱንና ባህሉን አውቆ እንዲጠብቀውና እንዲከባከበው ከማስቻላቸው ባሻገር ለሀገር ውስጥ ቱሪዝም መስፋፋትና መጠናከርም ያላቸው አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ሲሉ የማህበራትን ጥቅም አብራርተዋል፡፡
ማኅበራቱ አብዛኞቹን ተግባራት የሚያከናውኑት በየደረጃው ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች ፈቃድ እያገኙና መመሪያ እየተቀበሉ መኾኑን የሚገልጹት አገልጋዮቹ፣ በግንቦት 2004 .. የማኅበራትን ቁጥር ስለመቆጣጠር ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ በነበረው ጥናት መነሻነት ምልዓተ ጉባኤው ራሱን የቻለና ማኅበራቱን የሚያሠራ ሕግ እንዲዘጋጅ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች ያሉበት ደንብ አዘጋጅ ኮሚቴ ሠይሞ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ የማኅበራት አደረጃጀትና የፋይናንስ ቁጥጥር መርሕን ጠብቆ እንደሚወጣ ሲጠበቅ የቆየው ደንብ ከሚገባው በላይ መዘግየቱ ችግሩ ከቤተ ክህነቱ እንጂ ከማኅበራቱ አገልግሎትና ብዛት አለመኾኑን እንደሚያመለክት ይከራከራሉ፡፡

ፓትርያርኩ አድልዎ በሌለው መልኩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማስተዳደር በዕለተ ሢመታቸው ቃለ መሐላ መፈጸማቸውን የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ በምክክር ጉባኤው ላይ በተጠቀሰው አኳኋን የመናገራቸው ግፊት የተለያየ መነሻ ሊኖረው እንደሚችል አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

የመጀመሪያው መንሥኤ፣ የሙስናንና ብልሹ አሠራርን ችግር ለመቅረፍና ለማድረቅ በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ለአዲስ አበባ /ስብከት የተሠራው የመዋቅር፣የአደረጃጀትና የአሠራር ጥናት ተቃዋሚዎች የጥናቱ ባለቤት ነው በማለት በሚከሡት ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አመራር አማካይነት እንዲፈጠር የሚሹት ጫና ነው፡፡ ኹለተኛው ደግሞ በመንግሥት በኩል፣ ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ አክራሪነትና ጽንፈኝነት የሚታየው ህልውናቸውና ዓላማቸው ሃይማኖታዊና በሃይማኖቱ የበላይ ጠባቂዎች ይኹንታ በተቋቋሙ የወጣት ማኅበራት አደረጃጀቶች ውስጥ በመሸጉ አካላት ነው፤ ስለዚህም ማኅበራት በትኩረት ሊመሩና ጉዟቸውም እየተፈተሸ ሊስተካከሉ  ይገባል፤›› የሚለው ክሥ በመሪዎቹ ላይ ያሳደረው ማኅበራቱን የመቆጣጠር ጫና ነው፡፡
የአክራሪነትንና ጽንፈኝነትን ምንነትና መፍትሔዎችን በሚተነትኑት የመንግሥት ሰነዶች፣ የሃይማኖት ተቋማትን ለአክራሪነትና ጽንፈኝነት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል ከሚባሉት ኹኔታዎች ውስጥ÷ የሃይማኖት ተቋማቱ የሰው ኃይል አስተዳደርና የፋይናንስ ሥርዐት ለተከታዩ ሕዝብ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሌላቸው መኾናቸው፣ በሙስናና በአስተዳደር በደል ሳቢያ የሚፈጠር ግጭት፣ የሰው ኃይል አስተዳደር በዘመድ አዝማድና በጉቦ እየኾነ የሥራ ብቃት በሌላቸው ሰዎች የሚሠራበት፣ የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ የሚተችበትና አስተያየት የሚሰጥበት ሥርዐት አለመዳበሩ፣ ተከታዮችን አክራሪነትን የሚቋቋም በሃይማኖት ዕውቀት የማስታጠቅ ክፍተት ይገኙበታል፡፡

በመንግሥት ትንታኔ መሠረት፣አክራሪነትን የመዋጊያው ቁልፍ መሣሪያ ልማትንና ዕድገትን በማፋጠን የመልካም አስተዳደር ችግርን መቅረፍ፣ሕዝቡን በሃይማኖታዊ ዕውቀት ማስታጠቅ ነው፡፡ የሃይማኖት ተቋማትን ለአክራሪነትና ጽንፈኝነት ተጋላጭ ያደርጓቸዋል የተባሉት የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሠራር ችግሮች÷ ማኅበረ ቅዱሳን በተቃዋሚዎች አላግባብ በሚከሠሥበት የመዋቅር፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ትግበራ በማፋጠን እንዲኹም ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ በርካታ ማኅበራት በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ የገዳማትና የአብነት /ቤት ማኅበረሰብን በልማትና ተራድኦ ከመደገፍ ጀምሮ በሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ተልእኮ ንቃት ሊወገድ እንደሚችል ቅሬታ አቅራቢዎቹ ያምናሉ፡፡ ከዚኽም አንጻር ፓትርያርኩ ንግግራቸውን መልሰው በማጤን ማኅበራት አገልግሎታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል የሚያስችላቸው ኹኔታ እንዲያመቻቹ ጠይቀዋል፡፡

6 comments:

  1. እውነትም ቤተ ክርስቲያን በዩኒቨርስቲ ምሩቃን አትመራም

    ReplyDelete
  2. ቤተክርስቲያን በዩኒቨርስቲ ምሩቃን አትመራም የሚለው ቃል ለትርጉም እና ለትችት የተጋለጠ ነው። የቀድሞው ፓትሪያረክ እና አሁንም ያሉት በርካታ ሊቀ ጳጳሳት የዩኒቨርስቲ ምሩቆች ናቸው። የንግግሩ አንኳር መልዕክት ግን ሂሳብ እና ባይሎጂን እና ሌሎችንም አካዳሚክ ሳይንስ በማጥናት ቤተክርስቲያንን መምራት አይቻልም የሚለው አባባል ተገቢ እና ትክክል ነው። እንኳን ቤተክርስቲያንን የሚያክል ቀርቶ የአለማዊ ተቋማትን ለመምራትም እንኳን የማኔጅመንት ሳይንስ አስፈላጊ ነው። ማኔጅመንት ሳይንስ ስለተጠና ደግሞ ሁሉንም ተቋማት መምራት እንደማይቻል በተግባር የምናው ነው። ለዚህም ነው ፋይናንስ ማኔጅመንት፤ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት፤ ትራንስፓርት ማኔጅመንት፤ ትምህረት ማኔጅመንት፤ ቱሪዝም ማኔጅመንት ያስፈለገው። ቤተክርስቲያን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ከፍ ትላለች ስለዚህም የራሷ የሆኑ ትውፊት ስርዓት ያላት መሆኑ ለየት ያደርጋታል። እነዚህን ትውፊት እና ስርዓት በትምህርት ስርዓቱ ማካተት፤ ማለፍ የሚገባ የህይወት ተመክሮዎችንም ማለፍ እንደሚገባ ሊታወቅ ይገባል። ዩኒቨርስቲ ገብቶ አካዳሚክ ሳይነስ ማጥናት ለቤተክርስቲያን አመራር ሰጪነት ሚናን ለመረከብ ግባት ሊሆን እንደማይችል ሁሉንም የሚያስማማ ነው። ይህን ትምህርት መማር ደግሞ ሰውን ከቤተክርስቲያን የሃላፊነት ሚናን ከመጫወት የሚከለክል አይደለም። እንደዛማ ቢሆን የህክምና ባለሞያው የቅዱስ ሉቃስ ዕጣ ፈንታ ከወድየት ይሆን ነበር።

    ReplyDelete
  3. እውንትን መስካሪMarch 9, 2014 at 9:54 PM

    አብዮት ልጇን ትበላለች! እስክዛሬ ከወያኔና እርሱ ከሾማቸው ጋር ሽር ጉድ ስትሉ ክርማችሁ አሁን አብዮት ሊብላችሁ ሲሆን ተንጫጫችሁ። ዋልድባ ሲታረስ ገዳማቱ ሲቃጠሉ ካህናትና ምእመናን ሲታረዱ የት ነበራችሁ?

    ReplyDelete
  4. በእውነት ለእውነትMarch 10, 2014 at 12:37 PM

    ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤እንዲህ ማለት አይችሉም››

    በዚህ ቅር የሚሰኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልጅ ሳይሆን የማህበር ልጅ ነው! በየትኛው አይን ቢታይ ነው ይህ ንግግር ስህተት የሚሆነው ?

    "በእንተ ስማ ለማርያም" እያሉ ከውሾች ጋር ተላፍተው እድሜያቸውን በሙሉ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት እና በመማር ፣ እንደ መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሌት ተቀን እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ የኖሩ የቤተ ክርስቲያናችን እንቁዎች እያሉ ከረቫቱን ያሰረ የአስኳላ ተማሪ ምሩቃን ቤተ ክርስቲያንን እንዲመሩ ተፈልጎ ነው ????

    "አሁንስ ወጡን እረገጥሽው!" አለች አያቴ! ይህን ብትሰማ ኖሮ አያቴ "ወጡን እረገጥሽው" ሳይሆን "ተምቦራጨቅሽበት" ነበር የምትለው!!!

    ReplyDelete
  5. መቼ ይሆን ህይወታችን በተዋህዶ የጸና እና የቀና ክርስቲያኖች ነን ብለን እራሳችንን እያሳትን የብጹአን አባቶችን ስም ማጥፋት የምናቆመው? ይሄ እርስ በእርሱ ይጋጫል። የብጹዕ አባታችንን ንግግር በመንፈሳዊ እይታ እና በተዋህዶ መነጽር ብናየው የተናገሩት እኮ እራሱ ቅዱስ ወንጌል ነው።
    1ኛ ቆሮ 1፣27 "ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዚህን ዓለም ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤"። አሁንም የጳጳሳቱን ስም የምናጠፋው ከኛ ውጭ ጥበበኛ የለም ብለን ስለምናስብ ለደቂቃ እንኳን ቤተክርስቲያንን የሚመራት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አምኖ መቀበል ስላልቻልን ነው። በዚህ መንገድ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ከምናበረክታቸው ብዙ አገልግሎቶች ይልቅ የምናጠፋቸው ነገሮች በልጠዋል። የብጹአን አባቶች ሃዘንም የትም አያደርስም:: ቅዱስ ሲኖዶስን የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ነው ብለን የምናምን ከሆነ እና ለስድብ እንዲህ የምንቸኩል ከሆነ ቅዱስ ወንጌሉ እንዲህ ይለናል።
    ማቴ 12፣31 "..... ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ ኃጢአቱ አይሰረይለትም።"

    ReplyDelete
  6. ቤተክርሰትያን እኮ ባሕረ ጥበባት የተባለቸህው ለአለማዊ እውቀት በሩዋ ክፍት የሆነ ለአለማዊውም እውቀት መሰረት በመሆነዋ ነው፡፡ ! ቤተክርስትያን በተማረ ሰው አትመራም ብሎ መናግር እነኳን.. ክማንም አይጠበቅም መንግስትም ሌት ተቀን የሚያወተውተው ሁሉም ሰው ትምህርት እነዲያገኝና ሃገርን ገጽታ በሁሉ መልክ መቀየር የሚችል ትውልድ መፍተጠር ሆኖ ሳለ አንድ ትልቅ ያውመ በክርሰቶስ ደም የተመሰረተች ብዙ ቅዱሳን ዋጋ የከፈሉላት ቤተክርስትያን ሃላፊ መሪ አባት ከመንግስት ያነሰ አቋም እና አስተሳሰብ ይኖረዋል ? በጣም እርግጠኛ መሆን የምቸህለው ነግር በምግባር በሃይማኖት ሆኖ አለማዊእውቀትን የገበየ ሰው እንዴ 㙀ንዴጽ ቤተክርስትያን ይህንነ ትናፍቀዋለች እነጂ አትገፋውም!!!!

    ReplyDelete