Thursday, March 15, 2012

የዘመኑ ቀሳጥያንና ስራዎቻቸው


   በዲ/ን ያሬድ ጥዑመልሳን

‹አባ ሰላማ›› ድረ-ገፅ ላይ ለወጣው የተሰጠ መልስ
(ዝምታችን ነገሮችን ሳናውቅ ቀርተን አይደለም)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
‘ስምዑ ወአጽምኡ ዘንተ ኩልክሙ እለ ትነብሩ ወስተ ዓለም”


(በአለም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህን ስሙ አድምጡም፡፡) መዝ(፵፰፥፩)

(አንድ አድርገን ፤ መጋቢት 06 ፤ 2004 ዓ.ም) በመጀመሪያ ደረጃ የተወደዳችሁ ይህን ጽሁፍ ወይም መልዕክት የምታነቡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች፣ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፣የቅድሰት ድንግል ማርያም የአስራት የቃል ኪዳን ልጆች ፣ የጻድቃን የሰማዕታት ወዳጆች በእግዚአብሔር ስም እንደምን አላችሁ፡፡ አሜን እስከ መቃብር ድረስ የወደደን የድንድል ማርያም ልጅ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጥረታት አንደበት ሁሉ የተመሰገነ ይሁን፡፡

በልጅነት አእምሮዬ በዚች መልዕክቴ ማስተላለፍ የፈለግኩት አንዲት ትንሽ ቁም ነገር አለችኝ፡፡ መርጌታ” ሙሴ የሚባል ሰው በአባ ሰላማ የመናፍቃን ድህረ ገጽ ላይ የህያው ተስፋ ድምጽ ከተባለ ምንፍቅናን ከሚዘራ ሬዲዬ ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ በተግባር ስላልኖረባት ቤተ ክርስቲያናችን የሰጠው አስተያየት የራሴን ሀሳብ ለመስጠትና ለአባ ሰላማውያን ድህረ ገጽ አዘጋጆች እና ለግብረ አበሮቻቸው ማለት የምፈልገው ነገር ስላለኝ ነው፡፡ እንደ ልቤ የተባለው መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር( ፶፯፥፫) ‘ኃጥአን ከማኅጽን ጀምረው ተለዩ፣ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፣ ሀሰትንም ተናገሩ” ይላል፡፡ ዛሬ እውነት እንደ ጭራ የቀጠነበት ኃጥአን ሀሰትን በአደባባይ በእውነት አውደ ምህረት ከልባቸው አንቅተውና አመንጭተው እነዲሁም የሀሰት አባት ዲያብሎስ አጀንዳ የሚያራምዱበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ስለ ኦርቶዶክስ ታዋህዶ ሀይማኖታችን ዛሬ በተለያዩ የዕምነት ድርጅቶች፣ በበራሪ ወረቀቶች፣ በጋዜጦች፣ በመጽሔቶች ፣ በተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ብዙ ይባላል፡፡ በርካታ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎች በዲያብሎስ አቀናባሪነት በሰዎች አስፈጻሚነት በምድራችን ይዘራሉ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ከሌሎች ፍጥረታት አልቆና አክብሮ ነው የፈጠረው፡፡ ይህም አንዱ ግዕዛን አእምሮ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ በተሰጠው አእምሮ እግዚአብሔር አምላክ በመጀመሪያው ትምህርት ቤት በኤደን ገነት የሰውን ልጅ አስተምሮታል፡፡ ይህን ብታደርግ በህይወት ትኖራለህ፤ ይህን ባታደርግ ግን ትሞታለህ ብሎ ነግሮታል፡፡ የሰው ልጅ የተሰጠውን ነጻ ፍቃድ ተጠቅሞ ይህን ብታደርግ ትሞታለህ የተባለውን ትምህርት በመተላለፍ በራሱ ላይ ሞትን አምጥቷል፡፡ ከዚያም ወዲህ በተለያየ ዘመናት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመረጣቸው ቅዱሳን እያደረ፣ ብህልም በራዕይ እየተገለጠ፣ በቃል እየተነጋገረ የሰውን ልጆች አስተምሯል፡፡ በመጨረሻም እራሱ በኣካል በሰወች መካከል ተገኝቶ በቃልም በተግባርም አስተምሯል፡፡ 


ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተግባር ካስተማራቸው ነገሮች አንዱ እናትና አባትህን አክብር የሚለውን ህግ ነው፡፡ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ ክብር ነበረው፡፡ እንዲሁም በተለይ በዘመኑ በሰዎች አስተሳሰብ ኃጢያተኞች፣ ድሆች፣ በሽተኞች፣ በአጠቃላይ በአለም ዘንድ በወቅቱ የተናቁ ለሚባሉ ሰዎች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይኸ ነው ሊባል በማይችል መልኩ ትልቅ ቦታ ሰጥቷቸዋል፡፡እንዲያውም በወንጌሉ እንደምናነበው ማቴ(፫፥፲)’’እኔ ኃጥአንን እንጂ ጻድቃንን ወደ ንስሃ ልጠራ አልመጣሁም’’ ብሎ ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ክብር መስጠትን የአስተማረን እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እግኢአብሔር ያከበራቸውን ማን ያዋርዳቸዋል እንዲል፤ እኛ ማን ነንና የት ላይ የተጻፈውን ፣ ማን የተናገረውን ሰምተን ነው ሰዎችን የምናቃልለው፡፡ ሰዎች ለሰዎች ከብር እንዳይሰጡ የሚፈልግ ዲያብሎስና ሰራዊቶቹ ብቻ ናቸው፡፡

እኛ የምንመራው በመጽሀፍ ቅዱስ ነው እንላለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የት ቦታ ነው ለቅዱሳን አባቶች፣ ለቅዱሳን ሰማእታት ፣ ለቅዱሳን ሀዋርያት ፣ ለቅድስት ድንግል ማርያም፣ ለሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ክብር አትስጧቸው የሚለው፡፡ እውነት የሚያስብ አእምሮ ካለን ሰዎች ለምን ቅዱሳንን አከበራችኋቸው ብሎ እግኢአብሔር የሚቀጣን ይመስላችኋል፡፡ ከተረዳነውና ካስተዋልነው እንዲያውም ቅጣቱ በተቃራኒው ነው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ በዓለም ስራ እንኳን የስጋን የኑሮ ዘይቤ ለማሻሻል እራሳቸው ፈጥረው ሳይሆን ስላሴ የሰው ልጅ እንዲጠቀምበት የፈጠሩትን በማቀላቀል ፣ በማደባለቅ፣ ፈልጎ በማግኘት ሳይፈጥሩ ፈጠርን ብለው የሚያገኙትን ፈጠራ ምክንያት በማድረግ አንቱ ብላ በስማቸው ሀውልት አቁማ፣ መንግድ ሰይማ ክብር ከሰጠች ለነፍስ ስራ ብለው ለተጋደሉና ታላቅ ስራ ለሰሩ ቅዱሳን ሰዎችማ እንዴት ክብር ይነፈጋቸዋል፡፡ በእውነት ይኸ ሰይጣን ያደረበት ሰው ካልሆነ በስተቀር እንኳን ከሰዎች የበለጠ ስራ ሰርተው ቀርቶ የሰው ልጅ በመሆናቸው እንኳን ክብር ይገባቸዋል፡፡

ዛሬ በዓለማችን እንደ አሸን የፈሉ ለቁጥር የሚያዳግቱ በግለሰብና በተለያዩ ድርጅቶች ስም የሚጠሩ በርካታ የሀይማኖት ድርጅቶች ነን፣  ኢየሱስን እንከተላለን የሚሉ ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች እንደአስፈላጊነቱ ይከፈታሉ አልሳካ ሲልም ተመልሰው ይዘጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጠቀም ያለ ትርፍ በማግኘታቸው እስካሁን የዘለቁም አይጠፉም፡፡ የሚከፍታቸውም ሰው ነው፤ የሚዘጋቸውም ሰው ነው፡፡ የተቋቋሙትም በግለሰቦች ፊርማ ከመንግስት ጋር በተፈራረሙት ውል መሰረት ነው፡፡ ሰለዚህ ህገ ደንባቸውን ያረቀቁት እራሳቸው በተስማሙበት መንግድ ነው፡፡

በስላሴ አምሳል የተፈጠራችሁ ክቡራንና ክቡራት አንድ ነገር ልበል ፡፡ ሀይማኖት የሚመሰረተው በማን ነው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ሰዎች ተሰባስበው ህግና መመሪያ አውጥተው ፣ ድምጸ ውሳኔ ተካሂዶ የእነ እከሌ ሀሳብ ይሻላል ተብሎ፣ የሀይማኖቱ ስም ይኸ ይሁን ተብሎ የተመሰረት ሀያማኖት ነው እንዴ? በእርግጠኝነት አይደልም፡፡ እኛ ሀይማኖትን በቀጥታ የተቀበልነው ከእራሱ ከጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ነው፡፡ የምንመራበት የሀይማኖት ስርዓትም እራሱ በተግባር ያሳየንና በቃልም ያስተማረን ስርዓት ነው፡፡ ስለዚህ የኛን ሀይማኖት የመሰረቱት ግለሰቦች አይደሉም፡፡ ሀይማኖት እኛን መሰረተን እንጂ ሀይማኖቱን እኛ አልመሰረትነውም፡ ከመንግስታትም ጋር ሀይማኖት ልንመሰርት ነው ብለን አልተፈራረምንም፡፡ እንዲውም መጀመሪያ መንግስታት እንዲመሰረቱ ህግና ደንብ አውጥታ የሾመቸው ይህችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ናት፡፡ የእኛ ሀይማኖት ሌሎች ነገሮች እንዲመሰረቱ ሁኔታዎችን አመቻችታለች እንጂ በማንም ግለሰብ አቋም አልተመሰረተችም፡፡ በመሆኑም እንዴት በግለሰቦች አስተሳሰብና አቋም  የተመሰረተ የሀይማኖት ድርጅት በጌታችን በመድሀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተን ሀይማኖት ሊተችና ይኸ  ትክክል ነው ፤ ይኸ ትክክል አይደለም ሊል ይችላል፡፡ በጣም ትልቁ ስህተት እዚህ ጋር ነው፡፡ መጨረሻ የመጣ አይን አወጣ እንደሚባለው ማለት መሆኑ ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ሀይማኖት ሀይማኖት የሚባለው ለሰው ልጆች ክብር ሲሰጥ ነው፡፡ ሰዎችን የሚሳደብና የሚያንቋሽሽ ሀይማኖት እንዴት ሀይማኖት ሊሆን ይችላል ? የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ለማወቅ በመጀመሪያ ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ይማራል፣ ይረዳል፡፡ የተማረ ሁሉ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡ ይሁዳ ከ11ዱ  ሀዋርያት ጋር 12ኛ ሆኖ ቁጭ ብሎ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  እግር ስር ተምሯል፡፡ ስለተማረ ግን አላወቀም፡፡ ዛሬ በአለማችን በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አንድ የትምህርት መስክ ተማሪዎች ይማሩታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የተማሩና የሸመደዱ ሰዎች ሁሉ ግን ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አያውቁትም፡፡ በሀይማኖት ውስጥ ማወቅ ለሽልማት አያበቃም፡፡ ቤተክርስቲያናችን አንድም ቀን እኒህ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቀው አውቀዋልና መሸለም ይገባቸዋል ብላ ምንም ሽልማት አልሰጠችም፡፡ ይህ አስተሳሰብ የሚሰራው ለዓለሙ ብቻ ነው፡፡ በእምነት አይን ይህ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ዮሀንስ ራዕይ ብናነብ የትኛውም ቦታ ላይ እከሌ ወይም እከሊት የሚባል ሰው እውቀት ስላለው ጸደቀ የሚል ታሪክ የለም፡፡ ይህን ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ቅዱስ ጰውሎስ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ፣ ጳጳሳት፣፣ ካህናት፣ ዲያቆናት ምን አይነት ሰው መሆን እንዳለባቸው በግልጽና በማያሻማ መልኩ አስቀምጦታል፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ሐዋርያትን ሲመርጥ ሀብታችሁን ንብረታችሁን ቤተሰባችሁን ጥላችሁ ተከተሉኝ ነው ያላቸው፡፡ ሀዋርያትም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲከተሉ፣ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር ስር ቁጭ ብለው ሲማሩ እንዲሁም ሁሩ ወመሀሩ ተብለው ወደ ዓለም ሲላኩ በደመወዝ ተቀጥረው፣ ሀብት ንብረት ተሰጥቷቸው፣ የስራ ቅጥር ፎርም ሞልተው አይደለም፡፡ እነርሱም በሀሳባቸው ውስጥ ከትምህርት በኋላ ይህን ያህል ስጋዊ ደመዎዝ ይከፈለን ይሆናል የሚል አመለካከት በአእምሮአቸው ውስጥ አልነበረም፡፡ በየትኛውም የሀገራችን አድባራትና ገዳማት በሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶች በመማርና በማስተማር ላይ የሚገኙት የቤተክርስቲኒቱ ልጆች ሀሳባቸው እግዚአብሄርን ማገልገል እንጂ ተምሮ ተቀጥሮ ደመዎዝ መብላት አይደለም፡፡ ዛሬ  በአንዳንድ የይሁዳ ወንድሞች አየተደረገ ያለው ነገር ግን ሌላ ነው፡፡ እኔ ይኸን ያህል ዓመት በአብነት ትምህርት ቤት ተምሬያለሁ፣ የተማርኩትም ይኸን ያህል ደመዎዝ ይከፈለኛል ብዬ አስቤ ነበር፣ ቅኔ ተቀኝቻለሁ፣ ዜማ ተምሬአለሁ፣ አቋቋም አስመስክሬአለሁ፣ቅዳሴ ቀጽያለሁ እየተባለ ይነገራል፡፡ ጥሩ ነበር መማሩ ግን ምን ዋጋ አለው፡፡ ስህተቱ የተፈጠረው መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ አንድ ሰው መንፈሳዊ ትምህርት የሚማረው ዳቦ ሊገዛበት፣ በደመዎዝ ሊቀጠርበት፣ ስልጣን ሊይዝበት፣ ኑሮውን ሊያደላድልበት፣ ስጋውን ሊያደልብበት፣ ተምሬ ነበር ብሎ ጉራውን ሊነፋበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርስበት እና የእግዚአብሔርን መንግስት በመመስከር ዓልጫውን ዓለም ወደ ጨውነት ሊለውጥበት ነው እንጂ፡፡

ቅድም እንዳልኩት ይህ አስተሳሰብ የሚሰራው ለዓለሙ ነው፡፡ ሀይማኖት ውስጥ እንደዚህ ሚባል ነገር የለም፡፡ ሀይማኖት ማመን ነው፡፡ ያመነ ሰው ደግሞ ይበልጥ እግዚአብሔርን እንዲያውቀውና እንደ እግዚአብሄርነቱ እንዲያመልከው ስለ እግዚአብሔር አምላክነት፣ ዘላለማዊነት ፣ ንጉሰነት ፣ ፈጣሪነት ፣ ቸርነት ይማራል፡፡ ስለ እግዚአብሔር አምላክነት አወቀ፣ ተማረ ማለት ደግሞ አሁን እግዚአብሔርን አውቄዋለሁና ደመወዝ ክፈሉኝ፣ እዚህ ቦታ ቅጠሩኝ የሚባልበት ነገር አይደለም፡፡ ደመወዝ ከፋዩ ራሱ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሀዋርያት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አንድ ጥያቄ ጠይቀውት ነበር፡፡ ሉቃ(፲፰፥፳፰)‘ሁሉን ትተን ተከትለንሀል፤ እንግዲህ ምን እናገኝ ይሆን?’’ ብለው ጠይቀውት ነበር፡፡ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመልስላቸውም ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ የተከተላችሁኝ እናንተ በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ እናንተም በ12ቱ ዙፋን ትቀመጣላችሁ። በአስራ ሁለቱም ነገደ እሥራኤል ትፈርዳላችሁ’’ ነበር ያላቸው፡፡ እዚህ ላይ የምንረዳው ነገር ሁላችንም የምናምነውና የቤተክርስቲን ትምህርትን የምንማረው ተቀጥሮ ደመወዝ ለመብላት አለመሆኑን ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለማገልገል ነው፡፡

በቅርቡ አንድ መምህር ነበርኩ የሚል ሀይማኖቱን የለወጠ ወይም የካደ ሰው የተናገረው ነገር የሆነ ነገር እንድል ህሊናዬን ስላስገደደው ነው፡፡ ግለሰቡ ‘መርጌታ” ሙሴ ይባላል፡፡ እንግዲህ መሪጌታ የሚለውን ቃል እንዳለ እንውሰደው እና፡፡ መሪ-ጌታ የሚባል ቅጽል ወይም ማዕረግ የሚሰጠው ሰው የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በማመን እና እናንተን የተቀበለ የላከኝን ይቀበላል እንደሚለው የእርሱ ተከታዮች የሆኑ ቅዱሳን ሀዋርያት፣ ጻድቃን ሰማዕታት አማላጅነትና ተራዳኢነት በመቀበል፣ ሊቃውንት ያስተማሩትን ትምህርት እና ምግባር በመማር የእነርሱን ፈለግ ምዕመናን እንዲከተሉ ቃለ እግዚአብሔርን የሚያስተምር፣ ሌት በማህሌት፣ ቀን በጸሎት ፍትሀት እግዚአብሔርንና ሰዎችን ለማገልገል ለተማረ ሰው የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ ሰውየው የህያው ተስፋ ድምጽ ለሚባል የመናፍቃን የሬድዬ አገልግሎት በሰጠው ቃለ ምልልስ እንደገለጸው የቤተክርስቲንን ትምህርት እንደ ይሁዳ ተምሯል፡፡ ሲማር ግን፡-
1.     የተማረው ተምሮ እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን ረዳት ቤተሰብ ስለሌለውና ከቤተክርስቲያን የሚገኘውን ፍርፋሪ እየበላ ከትምህረት በኋላ በደመዎዝ ተቀጥሮ የተደላደለ ኑሮን ለመኖር ነበር፡፡
2.  የተማረው የቤተክርስቲንን ትምህርት ቃል በቃል በሽምደዳ እንደ ዓለማዊ ትምህርት እንጂ ሀይማኖታዊ ምግባርን ከአባቶች አልተማረም፡፡
3.     የቤተክርስቲንን ትምህርት ሲማር ጎን ለጎን የሰይጣንን ትምህርት በመማርና ከሰይጣን መናፍስት ጋር በመዋረስ ነበር፡፡
አንድ ምሳሌ እዚህ ጋ ላንሳ፡፡ ብዙዎቻችን የመረጃ መስቀመጫ ዲስክ ወይም ሚሞሪ እናውቃለን፡፡ እዚህ ሚሞሪ ውስጥ ብዙ የእውቀት መጽሀፍት፣ የፍልስፍና መጽሐፍት፣ ሰይጣናዊ መጽሀፍ ይቀመጥበታል፡፡ መጽሐፍቱ የተቀመጠበት ሚሞሪ ይህን ያህል መጸሐፍ ስቶር (store) አድርጓልና ይኸ ዲስክ ምሁር ነው አይባልም፡፡ ይህ ግለሰብም ከመረጃ ማስቀመጫ ዲስኩ በምንም አይነት መልኩ ልዩነት የለውም፡፡ የቤተክርስቲንንም ትምህርት፣ የሰይጣንንም ትምህርት ሴቭ ሲያደርግ ብቻ ነበር የኖረው፡፡ አጋንንትም እራሳቸው እኮ የእግዚአብሔርን ቃለ በመሸምደድ፣ የቅዱሳንን ስም በማጥናት እኔ መላኩ----ነኝ እያሉ ሰዎችን ያስታሉ፡፡ ምን አልባት ሴቭ ያደረገው የሰይጣን ትምህርት አይሎበት ሰይጣንን ለብዙ ጊዜ በታማኝነት አገልግሎታል፤ አሁንም እያገለገለው ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰውየው ሲኖር  እውቀት እንጂ እምነት አልነበረውም፡፡  ሲኖርም ይኖር የነበረው ከሰይጣን ጋር እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር አልነበረም፡፡ የተማረውም፣ እቅዱም እግዚአብሔርን ለማገልገል አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ነገሩን ሁሉ ሲያየው እንደጠበቀው አላገኘውም፡፡ ሀይማኖት ውስጥ ብር ሳይሆን መከራ መኖሩን ከፊትም አልተረዳም ነበር፡፡   በቀጥታ የጠበቀውን ስላላገኘ ከሰይጣን ጋር ወዳጅነት በመመስረት ገንዘብ ሊገኝ የሚችልበትን መላ መፈለግ ጀመረ፡፡ ከሰይጣን ጋር ተዋረሰ ማለትም የሰይጣን ማህበርተኛ ሆነ፡፡ ከሰይጣን ጋር የሰዎችን ደም ለመጠጣት፣ ገንዘባቸውን በምትሀት ለመዝረፍ፣ ሀይማኖታቸውን ለማስካድ ውል ተፈራረመ፡፡ በዚህም ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ሰዎችን በአደረበት የአጋንንት መንፈስ በመጠቀም ሲዘርፍ፣ ሲያሳድድ ከቆዬ በኋላ የሰይጣን ስራ እየከሰረ፣ ደምበኛ እያጣ፣ ምዕመኑ ለአታላዮች፣ ለመናፍስት ጠሪዎች፣ቦታ አልሰጠ እያለ፣ በማህበረሰብ እየተገለለ፣ መተዳደሪያ እያጣ ሲመጣ ሌላ ዘዴ ደግሞ ማሰብ ጀመረ፡፡ሰውዬው ከመሰረቱም ቢሆን ፍላጎቱ ገንዘብና ገንዘብ ብቻ ነው፡፡ አሁንም ይህን ስጋዊ ፍላጎቱን ላያሳካለትና ሊያሟላለት የሚችል የኑፋቄ ትምህርት የሚያስተምሩ፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት በሚላክላቸው ገንዘብ የተመሰረቱ የሀይማኖት ድርጅቶች ላይ ተጠግቶ መኖርን እንደ አማራጭ በመጠቀም እንደገና ድሮ ከተዋረሰው ሰይጣን በተጨማሪ ሌላ አዲስ አጋንንት ተዋረሰ፡፡ ሰውየው አሁን ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የተቀበለው ሌላ አዲስ ሰይጣን ነው የተዋረሰው፡፡

ግለሰቡ ከተናገራቸው ነገሮች አንዱ እስከ ዛሬ ለመላዕክት፣ ለቅዱሳን፣ለሰማዕታት፣ለድንግል ማርያም ቅኔ ስቀኝ ቆይቻለሁ፡፡ ይህ ግን ስህተት ነበር ብሏል፡፡ መቼም አንተ ለቅዱሳን አልተቀኘህም፡፡ አንት ስትቀኝ የነበርከው ለዲብሎስ ነው፡፡  አሁንም እንደዚሁ፡፡ ከአንድ የሳር ቤት ላይ አንዲት ሳር ተመዝዛ ብትወድቅ ቤቱ በተመዘዘችው ሳር ምክንት ውሃ አያፈስም፣ ዝናብ አያስገባም፡፡ ቤቱም አይፈርስም፡፡ የተመዘዘችዋ ሳር የምታገኘው ትርፍ ቢኖር ከገለባ ጋር ተደባልቃ እሳት ላይ መቃጠል ብቻ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም አንተ እኮ ከሳሯም እንደ አንዱ አልነበርክም፡፡ አሁንም እግዚአብሔር አስተዋይ ልቦና ከሰጠህ ልነግርህ የምፈልገው ነገር በአንተ ከቤተክርስቲያን መውጣት ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አትፈርስም፤  አትበተንም፡፡ ምን አልባት እንደ አንተ እውቀት እነጂ ዕምነት የሌላቸው ሰዎች የአንተንና የግብረ አበሮችህን ፈለግ በመከተል ስራቸው በራሱ ከቤተክርስቲያን አንድነት ሊለያቸው ይችላል፡፡ ቤተክርስቲያን ግን አንድ ነገር ትሆናለች ብለህ አትስጋ፡፡ እንኳን በአንተ በቤተክርስቲያን ቦታ ውስጥ ምንም አይነት የአገልግሎት ድርሻ ባልነበረህ፣ የአንተን አርአያነት አንድም ሰው ይከተል ባልነበረበት ሁኔታ ቀርቶ፤ መድረክ ይዘው፣ የቤተክርስቲን አስተዳዳሪ ሆነው፣ ብዙ ህዝብ ዕምነት ጥሎባቸው በነበሩት ግለሰቦችም በክህደትና በኑፋቄ ምክንያት ከቤተክርስቲን ሲለዩ በምንም መልኩ ልቦናው የማይሸረሸር አማኝ ህዝብ ያላት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ቤተክርስቲያናችን በግለሰቦች ስላልተመሰረተች ግለሰቦች ቢክዱ ሀይማኖቷ ግን እንደተጠበቀች ርትዕት ሆና ለዘለአለም ትኖራለች፡  ስለነበርክበት የሰይጣን ስራ ብትናገር ፣ ብታወራ ቤተክርስቲያን ያስተማረችህ ሳይሆን እራስህ ከሰይጣን የተማርከው ትምህርት ነው፡፡ ቀድሞውንም የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላት ነበርክ እንጂ የእግዚአብሔርን መንግስት የምትሰብክ  የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር አልነበርክም፡፡ ለማንኛውም ቤተክርስቲን ማቴ(፲፮፥፲፫)”አናቅጸ ሲኦል ኢይሔይልዋ’’ የሲኦል ደጆች አይችሏትም ነው የሚለውና ቤተክርስቲያን ሁልጊዜም ትገፋለች፤ በአንተ አልተጀመረም፡፡ ይሁዳ ይሁዳን እየተካ ዛሬ አንተና ግብረ አበሮችህ ላይ ደረሰ እንጂ፡፡ ለእውነተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንም የሚያስደንቅ ነገር የለውም፡፡ ያወቅንህም አሁን አንተ በአዋጅ በሚዲያ አስነግረህ የስምኦን መሰሪ ወንድም መሆንህን ስትነግረን ነው፡፡

ፓስተር ሙሴ በእርግጠኝነት ልነግርህ የምፈልገው ነገር በትምህርት ብትበልጠኝም በሀይማኖት ግን አትደርስብኝም፡፡ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው እበልጥሀለሁ፡፡ አንተ ከምታውቀው በላይ እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በሃይማኖት ነው እንጂ በእውቀት ብዛት አይታወቅም፡፡ እንደ አንተ መሪጌታ የሚለው ማዕረግ ላይ ባልደርስም ፤ የምስክርነት ወረቀት ባልቀበልም እኔም እንደ አንተ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ተምሬያለሁ፡፡ እኔ ባወኩት እውቀት በእግዚአብሄር ላይ ትልቅ እምነት አለኝ፡፡ ብዙ ተምሮ እንደ አንተ ሀይማኖት ከሌለው ሰው ምንም ሳይማር ሀይማኖት ያለው ሰው ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም ሰው የሚማረው እንዲያምን እንጂ እንደ አንተ ለዳቦ አይደለም፡፡ ደግሞ ትንሽ አታፍርም ስትናገር፡፡ እኔ ዓላማዬ ከተማ መቀጠርና መቀመጥ ነበር፡፡ አይ ክርስትና !!! እኔ ሳውቀው የእኛ እውነተኞቹ መምህራን እንደ አንተ ከተማ መግባት አይደለም አላማቸው፡፡ መንግስተ ሰማያት መግባት እንጂ፡፡ ድሮም አንተ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን አባቶች ስር ምንም እምነት ሳይኖርህ ፤ የሚረዳህ ሰለሌለ ብቻ ፍርፋሪዋን ለምደህ ተማርክ እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲንን መርጌቶች አትወክልም፡፡ እዚህ ቦታ አገልግል ተብዬ ተለምኜ ነበር፡፡ ይህ ዲስኩር ነው፡፡

ግን አንድ ጥያቄ  እስቲ ለአንተና ለግብረ አበሮችህ ልጠይቅ፡፡ ከቃለ መጠይቁ እንደሰማሁት እና ባልደረቦችህም እንደሚያደርጉት  ቃለ መጠይቅ የምታደርግልህን እህት ጌታ ይባርክሽ ስትል ሰምቻለሁ፡፡ ቅዱሳን አንዱ ለሌላው አይጸልዩም፣ አያማልዱም እያልክ አንተ የትኛው ቅዱስ ሆነህ ነው ጌታን ጠይቀህ ጌታ እንዲባርካት ማድረግ የምትችለው፡፡ አንተም ለራስህ ጌታ ባርከኝ፤ እርሷም ለራሷ ጌታ ባርከኝ ትበል እንጂ ፤ ይኸ አይደል አንዱ ክህደትህ፡፡ አንተ ከሰይጣን መናፍሰት ጋር ተዋርሰህ፣ ማህበር ገብተህ ከሰይጣን ጋር እየኖርክ ሌላዋን ጌታ ይባርክሽ የምትል አንተ ማነህና ?  አንተ መቼ ተባረክና ?  ኑሮህ ከሰይጣን ጋር፡፡ አንተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባልም አልነበርክም አባልነትህ ከሰይጣን ነበር፡፡ አስራት በኩራት የምትከፍለው ለሰይጣን ነበር፡፡ በግልህ ሰይጣንን ከምታመልክበት በጋራ ሰይጣን ወደ ሚመለክበት ቦታ ነው የተዘዋወርከው፡፡ የቀየርከው ቦታ ብቻ ነው፡፡  ሀይማኖትህ መስሎህ ነው እንጂ አንድ ነው፡፡ ምን እያጣህ እንደሆን ግን ተረድተኸዋል? በምድር ሞገስን፣ ክብርን አጥተሀል፡፡ በሰማይ ደግሞ ገነት መንግሰተ ሰማያትን ታጣለህ፡፡ ቅዱሳንን ተሳድበህ ክብር ያለህ መስሎህ እንደ ቃየል ስትቅበዘበዝ፣ ይኸ መናፍቅ ከሃዲ እተባልክ እንገትህን ስትደፋ ነው የምትኖረው፡፡ ስንቶች በአንድ ወቅት በዘሩት የክህደት እንክርዳድ አልቅሰው ንስሃ መግባት ሲገባቸው ምድራዊ ክብርን ሽተው በስራቸው አፍረው ሀገር ቀይረዋል፣ ስማቸውን ሀይማኖታቸውን ለውጠዋል፣ በአደባባይ እንደ በፊቱ መታየት አቁመዋል፡፡ የሰው ሁሉ መጠቋቆሚያ ሆነዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ይሰውረን፡፡

እኔ ግን ይኸን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ነገር በቤተክርስቲያናችን ላይ ጥፋት ታስከትላለህ ፣ በጎችን ጠቦቶችን ትነጥቃለህ ብዩ አስቤ አይደለም፡፡ ግን የተናገርካቸው እንቆቅልሾች ውስጤን ስለጠዘዙት እና ምን ያህል አስመሳይ የሆንክ ሰው መሆንክን ስለተረዳሁ ነው፡፡ ደግሞ እኔ ወንበር ዘርግቼ ተማሪ ማስተማር አልፈልግም ነበር አልክ፡፡ ደሮውንስ ከአንተ ምን አይነት ደቀ መዝሙር ነበር ተምሮ የሚወጣው፡፡ አንተ እኮ መሪ-ጌታ ሳይሆን መሪ-ሰይጣን  ነበርክ፡፡ የሰይጣንን መንገድ እኮ ነው ስትመራ የኖርከው፡፡ እና አንተ እንዴት መሪ-ሰይጣን ሆነህ ሳለ እራስህን መሪ-ጌታ ብለህ ትጠራለህ፡፡  አሁንም አንተ ብቻ ሳትሆን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ባወቀ ከአዝመራው እየነቀለ ያወጣችሁ የቤተክርስቲያን አረሞች የነበራችሁ አሁን በተለያየ የዕምነት ድርጅት የምትገኙ ሰዎች እባካችሁ እዚህ የነበራችሁ መሪጌታ፣ ቄስ፣ አባ ትባሉ የነበራችሁ ስማችሁ እርሱ ጋር ለቦታው የሚስማማ ስላልሆነ ሀይማኖታችሁን ብቻ ሰይሆን ስማችሁን ማለትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰጠቻችሁን ማዕረግ ቀይሩት፡፡ እርሱ የሚሰራው እኛ ጋር ብቻ ነው ፡፡
          በመጨረሻ ለአንተና ለግብረ አበሮችህ ልልህ የምፈልገው ነገር ፡-
1.      የገባህበት ድርጅት መሪ-ጌታ የሚለው ቃል ስለማይስማማውና  ስለማይገልጸው ስምህን እንደ ወንድሞችህ ፓስተር ሙሴ ብለህ ብታስተካክል፡፡ ምክንያቱም መሪ-ጌታ  የሚለው ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀይማኖት ለሚያስተምሩ ለእውነተኛ  የኢሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ፡-ቅዱሳንን፣ሰማዕታትን፣ ሊቃውንትን፣ በአጠቃላይ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሄርን በላሟሎች ለሚያገለግሉና እግዚአብሔርን ለሚያመልኩ ሰዎች ብቻ የሚሰጥ ማዕረግ ስለሆነ፡፡ አንተ ደግሞ ይህ በአጠቃላይ የማይመለከትህና የማታምንበት ስለሆነ፡፡
2.     ግዕዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀይማኖታዊ ቋንቋ ነው፡፡ በገባህበት የሀይማኖት ድርጅት  አዳራሽ ከአውሮፓ ተገዝቶ የመጣውን የራሳችሁን ቋንቋ ብትጠቀም፡፡ ግዕዝ የመላዕክት ንቋ ነው፡፡ መላዕክት ደግሞ በአነተና በግብረ አበሮችህ ዘንድ ቦታና ክብር የላቸውም፡፡ እንዴት የማትወዳቸውንና የማታከብራቸውን የቅዱሳን መላዕክትን ቋንቋ ትጠቀማለህ፡፡
3.     ከአዋልድ መጻህፍት አንዳንዱን እየጠቀስኩ አስተምራለሁ ብለሃል፡፡ ይኸ አስተሳሰብ እኮ የዘመዶቸህ እምነት ነው፡፡ አንተ የተሻልከው እንዳንዶችን እንደ ማጣቀሻ እጠቀማለሁ ማለትህ ነው? ወይ ሀይማኖት! ይገርማል፡፡ ቆይ እንጂ የማታምንበትንና የማትከተለውን ሀይማኖት ቅዱሳት መጽሀፍት ማጣቀሻ እንዴት ታደርጋለህ፡፡ ለነገሩ ድርጅታችሁ የተመሰረተው ከግለሰቦች በተውጣጡ ሀሳቦችና ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰኑትን ብቻ እንደ ማጣቀሻ በመጠቀም አይደል፡፡ ብትችል ከእነ ሉተር፣ ንስጥሮስ እና መሰሎቻቸው መጻህፍት መጣቀሻ ብትጠቀም፡፡
4.     አንተ የገባህበት ድርጅት በቅዱስ ያሬድ ዜማ አያምንም፤ በነ ሞዛርት ቅኝት እንጂ፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀብትና የቅዱሳን መላዕክት የምስጋና ዜማ ስለሆነ አንተን አይመለከትህም፡፡ ሁሉንም የአንተ ያልሆነውን ነገር እርግፍ አድርገህ ብትተወው፡፡
ሀይማኖት ካለህ እውቀት ይሰጥሀል፡፡ እውቀት ያለው ሰው ሁሉ ግን ሀይማኖት ለውም፡፡ ዛሬ ቤተክርስቲያን ትታደስ እያሉ ያሉ ጸረ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን እንቅስቃሴ የሚያደርጉት ሰዎች እውቀት አለን ብለው የሚያስቡ ሐይማኖት ግን የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አንድ ቀን ሲያስተምሩ የተናሩትን አስታወሰኝ፡፡ ‘ሐይማኖት ከማይኖርህ እውቀት ባይኖርህ ሻልሀል፡፡” ሐይማኖት ያለው ሰው እንጂ እውቀት ያለው ሰው አይጸድቅም፡፡ ሐይማኖት ካለህ እውቀትህን እግዚአብሄር ይገልጸልሀል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን መጀመሪያ ሐያማኖት ነበረው፡፡ በሐይማኖት ውስጥ ሆኖ እግዚአብሄርን እውቀት ለመነ፡፡ ተሰጠውም፡፡ ዛሬ አንዳንድ ነገር እሰማለሁ፡፡ ይኸም ምንድን ነው፡፡ ዛሬ በቤተክርስቲን አውደ ምህረት እንዳይሰብኩ በሲኖዶስ የተከለከሉ ሰዎች ብዙ ይናገራሉ፡፡ እኛ ብዙ ህዝብ ወደ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ስለሰበሰብን፣ በዝማሬ ስላቀለጥነው፣ የጠጠር መጣያ እስኪ ጠፋ ድረስ መንገድ ዘግተን ስላስተማርን ቀንተው ነው ስማችንን የሚያጠፉት ይላሉ፡፡ ብዙ ባንነጋገር ይሻላል፡፡ቆይ እስቲ በዚያ መንገድ ዘግታቸሁ ሰፊ ህዝብ ሰብስባቸሁ በአስተማራችሁበት አውደ ምህረት ምን ያህል ሰው ወደ ንስሀ ህይወት እንዲመለስ አደረጋችሁ?፣ ስንቱ ሰው ስጋ ወደሙ ተቀበለ?፣ ማነው በእናንተ ትምህርት በሰርዓተ ቤተክርስቲያን ጋብቻውን የፈጠመው?፣ የእናንተን ትምህርት ተምሮ ማነው ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር የሰጠው?፣ቅዱሳን አባቶቻችንን፣ ጳጳሳትን፣ ካህናትን፣ ዲያቆናትን ያከበረው ማን ነው?  አላውቅም፡፡ እናንተው መልሱት፡፡ እንደ እውነቱስ ከሆነ ዛሬ ሁሉም ሰው ይመስክር በዝማሬ የሚቀልጥበት ጊዜ ነው?  ምን ተገኘ፡፡ የሰው ልጅ የሀጢአት ስራን የዕለት ከእለት ስራው፣ ነውር የነበረው ነገር ሁሉ በአዋጅ የሚፈጸምበት፣ ሀይማኖት እንደ አሸን በሚፈላበት፣ ክህደት በበዛበት፣ መተማመን በጠፋበት፣ አለም በጦርነት፣ በሽብርተኝነት እና በተለያዩ ነገሮች እርስ በእርስ አየተጠፋፋ ባለበት ዘመን፣ ለሰው ልጆች ዳቦ ለመስራት ሳይሆን ኒውክሊየር  ቦምብ ለመገንባት እሽቅድምድም  በሚደረግበት፣ እግዚአብሔር የለም የሚል አስተሳሰብ በነገሰበት፣ ቅዱሳን ሀዋርያት፣ ጻድቃን ሰማእታት፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በማይሰጥበት፣ረሀብ፣ስደት፣ ድርቅ፣ በሽታ፣ የሙቀት መጨመር፣ የዝናብ እጥረት ብቻ ምን አለፋችሁ በጣም የብዙ ብዙ መከራዎች በዓለም ላይ በሰፊው በነገሰበት በዚህ ዘመን ሀዘን፣ ልቅሶ፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት እንጂ እንዴት ዳንኪራ ይስማማዋል፡፡ ሆኖም እናንተ፡-
1.    በአደባባይ በቤትክርስቲያን አውደ ምህረት ምን እግዚአብሔር እግዚአብሔር ትላላችሁ ኢየሱስ በሉ እንጂ አላችሁ፡፡ ምን ይበል ይህ ምዕመን፡፡ አዲስ ነገር ሆነበት እኮ፡፡ ድሮ መናፍቃን አዳራሽ ነበር ኢየሱስ በሉ እግዚአብሄር አትበሉ የሚባለው፡፡ አሁን ግን በቀጥታ በእንደራሲያቸው በኩል ኢየሱስ እንጂ እግዚአብሔር አትበሉ በማለት ተናገራችሁ፡፡ ይህ ህዝብ ሀይማኖት ያለው ህዝብ ነው፡፡ ምንም  መሬት ላይ ተቀምጦ በትህትና ቢማር የማያውቅ እየመሰላቸው የተጫኑትን እያመጡ ሲደፉ የለም ይህ ስህተት ነው፡፡ ይህን አንቀበለውም፡፡ አያችሁ ሀይማኖት እንደዚህ ነው፡፡ እንግዲያ ትክክል ብትሆኑ ኖሮ ያ ሁሉ ተሰብስቦ ይሰማችሁ የነበረ ህዝብ ዛሬ የት ሄደ፡፡  ያ ይሰማችሁ የነበረው ሰው እናንተ የሰበሰባችሁት እኮ ነው ዛሬ አይ እናንተ በትክክል የእግዚአብሔርን ቃል አይደለም የምታስተምሩት ያለው፡፡ ይህ ምእመን እኮ ከልጅነቱ ጀምሮ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ተምሯል፡፡  ኧረ እንዲያውም ምን ከ7 ዓመት፤ ክርስትና ከተነሳ ጀምሮ እንጂ፡፡ ከእናቱ ጋር በአንቀልባ እየታዘለ እየመጣ እኮ ገና በ40 በ80 ቀኑ ነው ቅዳሴ ማስቀደስ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት የጀመረው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የማይጠገብና ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ቃል ደጋግመው ሲሰሙት ስለማይሰለች እኮ ነው  ፤ እየመጣ አውደ ምህረት ቁጭ ብሎ የሚማረው፡፡ የነፍስ ምግብ ቃለ እግዚአብሔር ስለሆነ እኮ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ስለሀይማኖቱ የማያውቅ እንዳይመስላችሁ፡፡ እናንት ገና የመጀመሪውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መናገር ስትጀምሩ ምእመኑ እኮ መደምደሚያውን ያውቀዋል፡፡
2.        ድንግል ማርያም አታስፈልግም መዳን በአንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚል ቁንጽል ሀሳብ ብትናገር ማን ይሰማሀል። ምን እንደሆነ ታውቃለህ፡፡ ድንግል ማርያም ብዙ ነገር ያደረገችለት ህዝብ እኮ ነው፡፡ ድንግል ማርያም  ውለታ የልዋለችለት ማን አለ ? ስራ ያልሰጠችው፣ በጸበሏ ያልፈወሰችው ፣ በሀዘን ጊዜ የላጽናናችው፣ በብቸኝነት ጊዜ አብራው ያልሆነች፣ በስደት ጊዜ አብራው ያለተሰደደች፣ በምጥ ጊዜ ያልደረሰችላት እናት ማን አለች? ከፈተና ያላወጣችው፣ ከመከራ ያልታደገችው ማን አለ ?  አንተ አታስፈልገኝም የምትለውም እኮ ባታውቀው ነው እንጂ አንተ እየጠላሀት፣ አታስፈልገኝም እያልካት አሁንም ጌታ ሆይ ልቦና ስጥልኝ ፣ ማርልኝ ብላ እኮ ትጸልይልሀለች/ትጸልይልሻለች። እና እንግዲህ እንዴት ነው ይህን ሁላ ውለታ የዋለችለትን ህዝብ ከደም ስሩ ጋር የተዋሀደችውን እናት እንዴት አታስፈልግም ብለህ ብትነግረው ይቀበልሀል? ሀይማኖትና እውቀት የተለያየ ነገር ነው ያልኳችሁ ለዚያ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ሀይማኖት አለው፡፡ በሀይማኖቱ ጽናት የተነሳም ቅዱሳን ብዙ ነገር አድርገውለታል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ከስደቷ ጀምሮ ልጇ ጌታችን መድሀኒታችን ኢሱስ ክርሰቶስን ወደ ኢተዮጵያ ይዛ በመምጣት ኢትዮጵን ባርካለች በልጇም አስባርካለች፡፡ ዛሬም ድንቅ ድንቅ ታምራት እየሰራች ትገኛለች፡፡ በቅርብ እንኳን በኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ እንጦጦ ሀመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን እያደረገች ያለውን ፈውሰ ስጋና ፈውሰ ነፍስ ማየት በቂ ነው፡፡
3.     ዛሬ  በኢትዮጵያ እንኳን በከተማው በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ብንጓዝ በጣም የሚገርም ሀይማኖት እኮ ነው ያለው፡፡  አርሶ አደሩ የተጣራውን ምርቱን ከጎተራው አውጥቶ በሜዳ ሲዘራ አደራውን ለአምላኩ ለፈጠረው ለእግዚአብሔር  ለወዳጆቹ ለቅዱሳን ሰጥቶ ነው፡፡ ተክለ ሀይማኖት አንተ ታውቃለህ እኮ ነው የሚለው፡፡ የዚህን ያህል እምነት አለን እኛ፡፡እና ይህ አርሶ አደር አልተማረም ማለት ይቻላል? በእውነት ምሁር ነው፡፡ፍጹም የሆነ እምነት ነው ያለው፡፡ የሀገራችን አርሶ አደር እኮ በሌሊት ተነስቶ ሞፈር ቀንበር ተሸክሞ፣ በሬዎቹን በጠኋት  ጠምዶ በዚያ ከባድ እና አድካሚ ስራ ውስጥ ሆኖ እስከ 11 ሰዓት ጀምበር ግባት ድረስ ነው የሚጾመው። የትኛው አርሶ አደር ነው በመጸሙ ምክንያት ከአድካሚ ስራ ጋር ጨጔራህ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ተብሎ ዶክተሩ ሪፈር የጸፈለት? ማን ነው? ማንም የለም፡፡ አሁን ይህን አርሶ አደር ጾም አያስፈልግህም ብትለው ይሰማሀል፡፡ ምክንያቱም ጥቅሙን እርሱ ያውቃል፡፡ ጉዳቱንም እርሱ ያውቃል፡፡ እዚህ ጋ ግን እስቲ እናንተን ልጠይቃችሁ፡፡ ጾም በመሻራችሁ ያገኛችሁትን ጥቅም ብታስረዱን፡፡ በጠዋት ተነስተን በመመገባችን አባቶቻችን የስቀመጡትን ስርዓት በመሻራችን ይህን አግኝተናል በሉን እስቲ፡፡ ምንም መልስ እንደሌላችሁ አውቃለሁ፡፡
4.     መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ሀሳብ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም እጅ የወጣ ከሰው ልብ መውጣቱ አይቀርም፡፡ ይህችን በልባችን ውስጥ የነገሰችውን፣ ከደም ስራችን የተዋሀደችውን እናት ከልቡ ያስወጣ አይደለም ከምእመናን ልብ ከመንግስተ ሰማያት ይወጣል፡፡ እባካችሁ ምእመናንና ምእመናት ከምእመናን ልብ እንዳትወጡ፣ ከእግዚአብሔር አንድነት እንዳትለዩ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔርን እንደ ሀዋርያት እምነት ጨምርልን ብላችሁ ለምኑት፡፡  አለበለዚያ በምድር በስጋ በክብር ማነስ፣ በሰማይ ከመንግስተ ሰማያት መለየት አለ፡፡ዛሬ ብዙ ሰዎች አሉ ለተወሰነ ጊዜ አንቱ ተብለው አባ አባ መምህር መምህር ሲባሉ ቆይተው ምዕመናን አሁን እኒህን ሰዎች አይደለም ከመምህርነት ማእረግ በምእመን ደረጃ እንኳ የማይመለከቱት ክብራቸውን ያጡ ሰዎች አሉ፡፡ ክርስትናን የጀመረ ሳይሆን የጨረሰ ነውና ገነት መንግስተ ሳማያት የሚገባው ክብራችን ሳይቀንስ የሀይማኖት ጉድለት ሳይገኝብን  እንደ ጅማሬያችን  እስከ ፍጸሜያችን ጸንተን  የማታልፈዋን የእግዚአብሔርን መንግስት እንድንወርስ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
5.     ራዕ(፪፥፬) ‘ነገር ግን አንተን የምነቅፍበት ነገር አለኝ፡፡’’ ከወዴት እንደወደቅህ አስብ፡፡ ሌሎችን ለማዳን ፣ ወንጌልን በዓለም ሁሉ ለማዳረስ የምትተጉ ወንድሞቸና አባቶቼ እንዲሁም እናቶቼና እህቶቼ  ከክብር እንዳታንሱ ለራሳችሁም ሳትሆኑ እንዳትቀሩ እራሳችሁን ዞር እያላችሁ እያያችሁ፣ አንዳንዴም መምህር ብቻ ሳይሆን እንደ ምእመናን መሬት ላይ ተቀምጣችሁ ሌሎች ወንድሞቻችሁ ሲሰብኩ እየሰማችሁ እየተማራችሁ አሁን ያለሁት በትክክለኛው የህይወት መስመር ውስጥ ነው አይደለም እያላችሁ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ እራሳችሁን እየመረመራችሁ ቢሆን መልካም ነው፡፡ ምዕመናንንም በደንብ በተግባር የሚለውጣቸው እናንተ መድረክ ላይ ቆማችሁ ባስተማራችሁት ብቻ ሳይሆን እንደ ኢሱስ ክርስቶስ አላዋቂ መስላችሁ ቁጭ ብላችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ ከምእመናን ጋር ቃለ ወንጌልን ስትሰሙም ጭምር ነው፡፡ እኔ እኮ አንዳንዱ መምህር ይገርመኛል፡፡ አንዱ ደቀ መዝሙር የሌላውን ደቀ መዝሙር ስብከት የማይሰማበትም ጊዜ አለ፡፡ ለመማር ሳይሆን ለማስተማር ብቻ  የሚመጡ አሉ። የራሱን ተራ ካሰተማረ በኋላ ትምህርተ ወንጌሉ በአባቶች ቃለ ምዕዳንና ጸሎት ሳይዘጋ ተነስተው ውልቅ ሲሉ እናያለን፡፡ እዚህ ጋ ግን ማቴ(፱፥፴፯)”መከሩስ ብዙ ነው ሰራተኛው ግን ጥቂት ነው” እንደሚል እውነተኛ የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት አገልጋዮች ከማነሳቸው የተነሳ በአንድ ቀን የሰርክ ጉባዔ ከአንድ በላይ አገልግሎት ቦታ ፕረፐግራም ያላቸው ደቀመዛሙርት እንዳሉና እነርሱንም እንደማይጨምር ለመግለጽ እፈልጋለሁ፡፡  ይህ መልዕክት ከዚህ ውጭ ላሉትና ከጉባዔ በኋላ ሌላ አገልግሎት ለሌላቸው ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ ደቀመዛሙርት እርስ በእርስ እንድ ሀዋርያት እንደ ሊቃውንት አባቶቻችን ልምድ መለዋወጥ መማማር አለባቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ግን እኮ እናንተም የእግዚአብሔር ቃል የስፈልጋችኋል፡፡ ማስተማር መማር መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ቁጭ ብሎ እንደ መማር አይደለም፡፡ ስለዚህ የተከበራችሁ የጌታችን የመድሀኒታችን የኢሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ይኸን ብትለምዱ መልካም ነው የሚል የልጅነት ምክሬን እለግሳችኋለሁ፡፡ ቁጭ ብሎ አውደ ምህረት ላይ የሚማር ምዕመን በእውነት ከአገልጋዮች ብዙ ይታዘባል፡፡ ማን ትልቅ ማን ትንሽ እንደሆነ ያውቃል፡፡  ከምእመናን ውስጥ እኮ ለዘመናት ቃለ ወንጌልን የሰሙ፣ ያስቀደሱ፣ ኪዳን የሚያስደርሱ፣ ማህሌት የሚያድሩ የሚሰሙ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈራረቁ የተለያዩ አባቶች የህይወት ልምድ የወሰዱ፣ እንደ ደቀ መዛሙርት ሰርትፊኬት የሌላቸው ነገር ግን የሚገርም የቤተክርስቲያን እውቀትና መንፈሳዊ ህይወት ያላቸው በጣም ታላላቅ እናቶችና አባቶች ከአውደምህረት ስር ቁጭ ብለው ከሚማሩት ጋር አብረው እንዳሉ መረዳት በልህነትና አስተዋይነት ነው፡፡ ይሁ(፩፥፫)”ለቅዱሳን የተሰጠችውንም ሃይማኖት ትጋደሉላት ዘንድ እማልዳችኋለሁ’’ እንዳለ አሁን እየደረሰ ያለው ለቅዱሳን ለተሰጠችወ ሃይማኖት ላይ የሚዘራውን እንክርዳድ መልቀም፣ እንዳይዘራ መከላከል ምእመናን መጠበቅ በዋናነት የእናንተ ድርሻ ነውና ከፊት ይልቅ በተጋድሎ እንድትተጉ ምክሬን እለግሳችኋለሁ፡፡ በማቴዎስ በንጌል(፳፫፥፫) እንደተገለጸው ‘’የሚያስተምሩትን አይሰሩትም’’ ተብሎ ከተነገረው የወንጌል ቃል ይጠብቃችሁ፡፡

አሁን ጊዜው ክርስቶስን የመቀበል ያለመቀበል ጉዳይ አይደለም፡፡ ክርስቶስንማ ዓለም እይጠላቸውም ቢሆን ጥንት ነው በከብቶች በረት የተቀበለችው፡፡ የሚያስፈልገው በክርስቶስ እምላክነት ማመን የለማመን ጉዳይ ነው፡፡ እስራኤላውን ክርስቶስን ተቀብለውታል አወንታዊ ባልሆነ መንገድ፡፡ የጎደላቸው ነገር በክርስቶስ አምላክነት ያለማመን ጉዳይ ነው፡፡ ክርስቶስን መቀበልና በክርስቶስ ማመን ፍጹም የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡

ከመሬት ተነስቶ እከሌ የሚባል ማህበር፣ እከሌ የሚባለው መምህር፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቤተክርስቲያን አስወጡኘ፣ ከህዝብ ልብ አራቁኝ ብሎ ቢናገር ሁሉም ስራው እራሱ እያጋለጠው በራሱ በሰራው እያፈረ፣ ዳግመኛ ይህን ህዝብ እንዴት እንዲህ አይነት የክህደት ትምህርት አስተምሬ በእነርሱ ፊት እታያለሁ እያለ በገዛ ፈቃዱ ይፈረጥጣል እንጂ ማንም ማንንም አላባረረም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤትየሰ በተ ጸሎት ትሰመይ እንዳለው ለቤቱ ቅናት ስላለው ቤቱ ዋዘኞች የዓለምን እንቶ ፈንቶ እንዲያወሩበት፣ ዳንኪራ እንዲመቱበት ስለማይፈቅድ እግዚአብሔር ባወቀ ለተወሰነ ጊዜ በሰርጎ ገብነት እንክርዳድ ይዘራሉ፡፡ ኋላ የተዘራው እንክርዳድ ዘር በቅሎ ከአደገ በኋላ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምርቱ እንዳይነቀል ጥንቃቄ በማድረግ አረሙን እንደ ፓስተር ሙሴ እየነቀለ ይጥላል፡፡ እስካሁን ብዙ አረሞች ተነቅለዋል፡፡ የቀሩትም ጊዜያቸውን እየጠበቁ ይነቀላሉ፡፡ እመኑኝ ይእግዚአብሄር ልጆች ይህ ግድ አይቀርም፡፡ የሚቆዩት እስከ መከር ብቻ ነው፡፡ ከፍሬው ጋር እንክርዳዱ በእርግጠኝነት ወደ ጎተራ አይገባም፡፡ እንደ ፓስተር ሙሴ ተበጥሮ ይጣላል፡፡ ማቴ(፫፥፲)’’መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል፡፡’’ ቤተክርስቲያናችን እንደሆነች አንዲት፣ ቅድስት፣ እንተ ላዕለ ኩሉ፣ ሐዋርያዊታ፣ ሰማያዊት ናት፡፡

ሌላው አባ ሰላማ በሚል ስም ድህረ ገጽ ከፍታቸሁ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ስም የምትንግዱ ግለሰቦች ጊዜው አልቋልና ስለማያዋጣችሁ ሌላ ስራ በጊዜ ብትፈልጉ መልካም ነገር ይመስለኛል፡፡ የምትከተሉት ሀይማኖት ፕሮቴስታንት፤ የምታስተላልፉት መልዕክት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን አማኞች፡፡ ቆይ ከመቸ ወዲህ ነው አንዱ የእምነት ድርጅት የራሱን እምነት ተከታዮች ማስተማር ትቶ በሌሎች ሀይማኖቶች ስም የሀይማኖት ትምህርት የሚያሰተላልፈው፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን አትታደስም፤ እርሷ ሁልጊዜም በክርስቶስ አዲስ ናት፡፡ እንደ እናንተ የሀይማኖት ድርጅት በፊርማ አልተመሰረተችም፡፡ ሰውም ህጓን አላረቀቀላትም፡፡ የሀይማኖቷን ስርዓት የደነገገላት እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት ደግሞ መጀመሪያ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሀዋርያት በቃልና በተግባር ሲየስተምራቸው ስህተት ነበረበት እነደ ማለት ይቆጠራል፡፡ ሎቱ ስብሃት፡፡ ይህ ደግሞ ድፍረት ነው፡፡ እዚያው እንደለመዳችሁት የመሰረታችሁትን የእናንተውን ድርጅት በየጊዜው እያደሳችሁ፣ እያሻሻላችሁ፣ የማይመቻችሁን አየቀነሳችሁና እየጨመራችሁ እስከምትዘጉት ድረሰ ተከተሉት፡፡ የኛን ሀይማኖት መቀየር ለምን አሰፈለጋችሁ? ተሰባሰቡና ይኸ ይኸ  ትክክል ነው፤ ይኸ ደግሞ ስህተት ነው ብላችሁ ተፈራረሙና የራሳችሁን የእምነተ ድርጅት በፍትህ ሚኒስተር አስመዝግባቸሁ የራሳችሁን እምነት ተከተሉ፡፡ እኛ ጋ ምን አጣላችሁ፡፡ ካልተመቻችሁ፣ ከአላመናችሁበት ማን በግድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲንን ተከተሉ አላችሁ፡፡ አሁን ደግሞ ምን ችግር አለ፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን ሀይማኖት መከተል እንደሚችል በህገ መንግስት ደረጃም ተደንግጎላችኋል፡፡ በኛ ስም መነገዳችሁን ትታችሁ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት የራሳችሁን የእምነት ድርጅት አቋቋሙ፡፡ በእናንተ አልተጀመረ፡፡ 

በእውነት ነው የምላችሁ አባ ሰላማዎች ሰው እየሳቀባችሁ ነው፡፡ ምን አገባችሁ ስለሌላ ሀይማኖት፡፡ እኔ በእናንተ ድህረ ገጽ የሚተላለፉ መልእክቶችን ብዙ ጊዜ አይቻቸዋለሁ፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲንን አይወክሉም፡፡
·         ጾም አያስፈልግም፣
·         ቅድስት ድንግል ማርያም ኣታስፈልግም፣
·         ቅዱሳን አያስፈልጉም፣
·         ታቦታት አያስፈልጉም፣
·         ቤተክርስቲያን አያስፈልግም፣
·         ጳጳሳት አያስፈልጉም፣
·         ቀሳውስት ዲያቆናት አያስፈልጉም፣
·         መላክት አያስፈልጉም፣
·         ከበሮ ጸናጽን አያስፈልግም፣
·          የቅዱስ ያሬድ ዜማ አያስፈልግም፣
·         ቅዳሴው ማህሌቱ ሰዓታቱ ኪዳኑ አያስፈልግም፣
·         ጸሎተ ፍትሀት አያስፈልግም፣
·   መስቀል ጥምቀት አያስፈልግም፡፡ ይቅርታ አያስፈልግም የምትሉት ብዙ ነገር እንዳለ አውቃለሁ፡፡ግን የተወሰነውን ለአብነት ከጠቀስኩ ይበቃኛል፡፡ ስለዚህ ይህን ያህል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ጋር ልዩነት እያላችሁ እዚህ ምን ትሰራላችሁ፡፡ ምንም እኮ አንድ የሚያደርገን ነገር የለም፡፡  ቶሎ ሂዱና እንደ ፓስትር ሙሴ ኢየሱስን ተቀበሉ እንጂ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን እነዚህ ከላይ አያስፈልጉም ያላችኋቸውን ነገሮች ዛሬ የፈጠረቻቸው ነገሮች አይደሉም፡፡ ዘመናትን የስቆጠረ ከመሰረቱም የነበረ ነው፡፡

አባ ሰላማ በሚባለው ድህረ ገጽ የሚተላለፈው መልዕክት የፈሪሳውያንና የሰዱቃውን እርሾ ነው፡፡ ኣባ ሰላማውያን እነ ከሌ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸው ተብለው ይህን ይህል ጊዜ ተፈረደባቸው፡፡ እነ ከሌ ደግሞ ሊቀጡ ነው ብላችኁ ብትናገሩ ብዙም አይገርምም፡፡ ሀዋርያት ታስረዋል፡፡ ብዙ ቅዱሳን አባቶቻችን በዓለማዊው ወህኒ ቤት ታጉሮባቸው ታሰረው ነበር፡፡ እስከ ሞትም ድረስ ደርሰዋል፡፡ ትልቁ ጉዳት አእምሮ ሲታሰር እንጂ ስጋ ሲታሰር አይደለም፡፡  ይኸ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ተነግሯል፡፡ በዓለማዊ ዳኝነት እንኳን እነ መምህር እገሌ  ኢየሱስ ክርስቶስም ወንጀለኛ ነህ፣ ህግ ተላለፈሀል ተብሎ በወንበዴዎች መካከል እንዲሰቀል ተደርጓል፡፡ ትልቁ ነገር በእግዚአብሔር የዳኝነት ወነበር ሲፈረድብህ ነው፡፡ ከሳሾች እኮ ከተከሳሾች ቀድሞ በእግዚአብሔር ዳኝነት ተፈርዶባቸው ከቤተክርስቲን ዓውደ ምህረት ከተለዩ ብዙ ጊዜ ሆኗቸወል፡፡  ይህን ብያኔ ለምን አላስተላለፋችሁትም፡፡ ስጋን ሳይሆን ነፍስን ከሚገድሉት መጠበቅ ነው ትልቁ ነገር፡፡ ለሀይማኖታቸው ሲታገሉ ዓለም እንደ ኢሱስ ክርስቶስ በውሸት እየከሰሰች በዓለም ምድራዊ ወህኒ ቤት የገቡ ሰዎች ለክርስትና መጠናከር እንጂ መድከም አንድም ቀን አስተዋጽኦ አድርጎ አያውቅም፡፡ በዚህ ጉዳይ ምግቢያ ቀዳዳ የሚያጡት ሁልጊዜም ከሳሾች ናቸው፡፡ በቤትክርስቲን ላይ ጉዳት ማድረስ ለሰው ቤተክርስቲያንን ማጥፋት ይመስለዋል፡፡ ግን አሁንም ከምተገፋው በላይ እየሰፋች፣ እየበዛች፣ እያበበች ትገኛለች፡፡

በአጠቃላይ ከላይ እንደገለጽኩት አሁንም በድጋሚ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር(፵፬፥፲፩) ‘ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ’’ በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱሉሽ እንዳለው ዛሬም ለየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚሰሩ፣ የሚተጉ ልጆች በአባቶች ፈንታ ተወልደዋል፡፡ አንተም ሆነ ለመውጣት እያኮበኮባችሁ ያላችሁ ውሉደ ይሁዳውያን፣ አርዮሳውያን፣ ንስጥሮሳውያን፣ ሉተራውያን አትድከሙ ቤተክርስቲያንን አትችሏትም፡፡ እንደ እናንተ በግለሰቦች ፊርማ አልተመሰረተችም፡፡በሀዋርያት አለትነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው የተመሰረተችው፡፡ ብትችሉ የምትቆፍሩትን ጉድጓድ ባታርቁት መልካም ነው፡፡ ኋላ መውጫው ይከብዳችኋል፡፡ ዛሬ ቅድስት ድንግል ማርምን አላከበረችሁልኝምና እሰይ መስጋና ይገባችኋል የሚላችሁ የመስላችኋል ልጇ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ፡፡ በእውነተ ምን አይነት ሞኝነት ነው፡፡ እኛ ክርስቶስን እንዴት ከእናንተ እንቀበል፡፡ እንደ ደብዳቤ ቅብብሎሽ እኮ አደረጋችሁት፡፡ ና ክርስቶስን ላስተዋውቅህ፤ ወይ አለማፈር፡፡ ቆይ እንጂ ከማን የተወለደውን ክርስቶስን ነው የምታስተዋውቁን?  ብቻ ተውት፡፡ህዝብ ይሳለቅባችኋል እንጂ የእናንተን ቅጥፈት ሰምቶ ማንም እንደ ፓስተር ሙሴ በዳቦ አይቀይርም፡፡ የፈለከው እርሱ ነበር ተሳክቶልሀል፡፡  እንኳን ደስ አለህ፡፡ ሌሎች ወንድሞችህም እናንተ ጋ ነን እናንተ ጋ አይደለንም እያሉ ግራ ከሚያጋቡ አብረውህ ከአንተ ጋር የአቋም መግለጫ ይስጡ፡፡ ወይ ልቦና ከሰጣቸውና እውነት የጌታችን የመድሀኒታችን የኢሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀማዛሙርት ከሆኑ፣ የቅዱሳን ወዳጆች የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የአስራት የቃል ኪዳን ልጆች ከሆናችሁ ፤ በሀይማኖት ውስጥ እራስን ዝቅ ማድረግ እንጂ ትዕቢትና ክብር ይገባናል የሚል አስተሳሰብ ስለሌለ አዎ አጥፍተናል፣ ቅዱሳንን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተሳድበናል፣ለቅድስት ድንግል መርያም የሚገባትን ያህል ክብር አልሰጠንም፣የክህደት እንክርዳድ ትምህርት ከመናፍቃንና ከዲያብሎስ አምጥተን በቤተክርስቲያን ላይ ዘርተናል፣ አጥፍተናል እግዚአብሔር ሆይ ወደ ልባችን ተመልሰናል ብለው ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ቢጠይቁ ሁልጊዜም ቤተክርስቲን የይቅርታ ባለቤት ናት፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የስተምራል እንጂ ማንንም አስገድዶ አያድንም፡፡ የነጻነት አምላክ ነው፡፡ ዬሐ(፭፥፮)’’ልትድን ተወዳለህን?” ብሎ ይጠይቃችኋል፡፡ አይ መዳን አንፈልግም ካላችሁ እንደ ፈለጋችሁ፡፡ ቤትክርስቲያን የሁልጊዜም ጥያቄዋ ልትድኑ ትፈልጋላችሁ? ነው፡፡ አዎ ብለው መልስ ለሚሰጧት እንግዲያውስ የኢየሱስን አምላክነት እመኑ፣ ባለሟሎቹን አክብሩ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ፣ ስገዱ፣ ከዓለም እርኩሰት ተለዩ፣ ንስሃ ግቡ፣ስጋ ወደሙን ተቀበሉ ትላለች፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆን ማርያምን ካለ አይመለስም፤እግዚአብሄርን፣ሚካኤልን፣ ገብርኤልም ካለ ወደ ኋላ አይልም፡፡ እኛ እኮ የእግዚአብሔር ባለሞሎች ብለን እንጂ በሌላ በምንም አይደለም ቅዱሳንን የምናከብራቸው፡፡ እንዴት የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርም አትከበር፡፡ ማነው እንደ እመቤታችን የስጋ እና የህሊና ንጽህና የተገኘበት፡፡ ማንም፡፡ አሁንም ልላችሁ የምፈልገው እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን አማኞች እግዞአብሔርን እናመልካለን፡፡ ባለሟሎችን እንደ ተሰጣቸው ጸጋ መጠን እናከብራለን፤ እናዘክራለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቤት በባለሟሎቹ ስም መታሰቢያ አድርገን እንሰራለን፡፡ መጽሀፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ፡፡ በዚህም አልተሳሳትንም፡፡ ጥንትም ነበር፤ ዛሬም አለ፤ ወደፊትም እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ይኖራል፡፡  በመሆኑም አባ ሰላማዎች የምትሰሩት ስራ የከሰረና ጊዜው ያለፈበት ስለሆነ አትድከሙ፡፡ ቶሎ ወደሚያዋጣችሁ ተቀላቀሉ፡፡ ተቀላቀሉ ስላችሁ በይፋ እንደ ፓስተር ሙሴ እንጂ በድብቅ ከማን ጋር እንደሆናችሁማ ማንም የተዋህዶ ልጅ ያውቃል፡፡ ፍሬያችሁ ያስታውቃልና፡፡  ሲራ(፳፰፥፲) ‘በእንጨቱ ልክ የእሳቱ ነዲድ ይበዛል’’ እንዳለው አሁንም እንጨት ብትጨምሩ በራሳችሁ ላይ የሚነደው እሳት ነው የሚጨምረው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን ዘንድ እንደ ሆነ እናንተ የምትሰሩት የክህደት ስራ ኢምንት ነው፡፡ ለብዙ ዘመናት ከዚህ የበለጠ ፈተና አሳልፋለች፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬስ ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ እንዲል ቅዱስ ዳዊት በሁለት ሰይፍ የተሳለ በጥበብ ስጋዊ በጥበብ መንፈሳዊ የተካነ ለሀይማኖቱ ቀናኢ የሆነ እንክርዳድ በቤተክርስቲያን ላይ እንዲዘራ የማይፈቅድና ለዚህም ቦታ የመይሰጥ አዲስ ልጆች በአባቶች ፈንታ ተወልደዋል፡፡ ወይ ፍንክች፡፡ አትድከሙ፡፡ ምንም በሉ ምን ይህ ተውልድ ቤተክርስቲያንን ለጠላት አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ዬሐ(፲፬፥፲፪) ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የምሰራውን ሥራ የሚሰራ እርሱም ይሰራል፤ ከዚያም የበለጠ ይሰራል፡፡’’ ሰይጣን መቸም የማይቀናበት ቦታ የለም፡፡ አያችሁት አይደል የጥምቀት ዕለት ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ተነስተው  እስከ ሚያርፉበት ድረስ አስፋልቱ ታጥቦ፣ ስጋጃ ተነጥፎላቸው የነበረውን የወጣቱን ትጋት፡፡ ይኸ ለሰይጣንና ታቦታት አያስፈልጉም ለምትሉ ለእናንተ ታላቅ ሀፍረትና አንገትን ያስደፋ ስራ ነበር፡፡ ለነገሩ ባትቀኑ ነበር የሚገርመው፡፡ ገና ብዙ ይደረጋል፡፡ ይህ ትውልድ ታሪክ ይሰራል፡፡ ይህ ትውልድ በእውነት በእናንተ ዲስኩር ሀይማኖቱን የሚቀይርና ቤተክርስቲንን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ ይመስላችኋል?  እራሳችሁ ፈቅዳችሁ የቋቋማችሁት ድርጅት እጅ እጅ ሲላችሁ ስለሰው ሀይማኖት ታወራላቸሁ፡፡ ይኸ ቅናት ነው ሌላ ምንም አይባልም፡፡ ለነገሩ እንኳን እናንተ ድሮ የቤተክርስቲን ልጆች የነበራችሁ ቀርቶ ሌሎች ከጥንትም የእኛ ያልነበሩ ኢአማንያን ተደብቀው መጥተው እኮ ጥምቀትን መስቀልን ከእኛ ጋር ነው የሚያከብሩት፡፡ማቴ (፲፱፥፴) ‘ብዙዎችም ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ ፤ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ’’ እንደሚል ሌሎች እውነተኛ ሐይማኖት መሆኑ የገባቸው እየተጠመቁ የተዋህዶ ልጆች ይሆናሉ፡፡ እንደ እናንተ አይነቱ ደግሞ በ11ኛው ሰዓት ሀይማኖቱን እየካደ ወደ ሰይጣን ማህበር ይገባል፡፡ ጊዜ ይወስዳል እንጂ እናንተም ነገ አይታችሁት እነደማያዋጣችሁ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ሲነግራችሁ ተመልሳችሁ ነስሃ ገብታችሁ እንደመትመለሱ ተስፋ አድረጋለሁ፡፡ ዬሐ(፲፫፥፲፰) ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’’ ለሚለው የጌታ ቃል መፈጸሚያ ብቻ ነው የሆናችሁት፡፡

በተረፈ ይህን መልዕክት የምታነቡ እናቶች አባቶች፣ እህቶችና ወንድሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳንድ የቤተክርስቲያንን ቋንቋ እየተናገሩ የክህደት ስራ እየሰሩ የሚገኙ፣ ከሰይጣን ጋር ማህበርተኛ የሆኑ የዲያብሎስ ልጆችን ብትመለከቱ በክርስትና ውስጥ ይህ አዲስ ነገር አለመሆኑን እንድትገነዘቡ አሳስባለሁ፡፡ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የ5 ገበያ የሚያህል ህዝብ ይከተለው ነበር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው፡፡  ይኸ ሁሉ ግን ድህነትን ፈልጎ አልነበረም፡፡ እንደ ፓስተር ሙሴ ለሆዳቸው ሲሉ ሲያስተምር ውሎ ማታ ላይ እህል አበርክቶ ይመግባቸው ሰለነበር  ለስጋቸው ሲሉ የሚከተሉትም ነበሩ፡፡ ዛሬም እነዚህ ሰዎች አሉ፡፡ደሞዜ ቀረብኝ፣ ስልጣኔ ተነካብኝ፣ ጥቅሜ ቀረብኝ፣ ከአውደ ምህረት ተክለከልኩ ብለው እንደ ይሁዳ በ30 ብር ሀይማኖት የሚቀይሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች መጀመሪም የኛ አልነበሩም፡፡ ስለዚህ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ እከሌ እንደዚህ ነበረ፡፡ እገሊት ዘማሪት ነበረች፡፡ አያስገርምም፡፡ መስበክ፣ መዘመር ሌላ ሀይማኖት ሌላ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የተማረ ማንኛውን ፈረንጅ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ይችላል፡፡ ስነ ቃል መደርደር የሚችል በይም የድምጽ ተሰጥኦ ያለው ሰው መዝፈን፣ መዘመር ይችል ይሆናል፡፡ ከሀይማኖት ጋር ግን ምንም አይነት ዝምድና የለውም፡፡ አባቶቻችንን እኮ ይኸን ያህል የምናከብራቸው በመስበካቸው፣ በመዘመራቸው አይደለም፡፡ በመንፈሳዊ ህይወታቸው፣በትህትናቸው፣በጾማቸው፣ በጸሎታቸው፣ በትዕግስታቸው፣ በታማኝነታቸው፣ በየዋህነታቸው፡፡ በአጠቃላይ የመንፈስ ፍሬዎች የሚባሉትን በሚገባ በማፍራተቸው ነው፡፡ ‘ልብ ላይ የተጻፈ ደብዳቤ ፊት ላይ ይነበባል’’ እንዲሉ አባቶቻችን በስራ የተገለጠ፣ የሚታይ ስራና ጸጋ ነበራቸው፡፡ ውድ የተዋህዶ ልጆች ሁላችንም ለቤተክርስቲያን ችግር የመፍትሄ አካል መሆን ይጠበቅብናል፡፡ የቤተክርስቲያን ችግር ያለመስዋዕትነት ዳር ሆኖ በማየት ሊፈታ አይችልም። ሙሉ ተዋናይ መሆን ያስፈልጋል። ምሳሌ ብንወስድ በእግር ኳስ ጨዋታ ህግ ዳር ቆመው የሚመለከቱት ቲፎዞዎች ከጨዋታ በኋላ በሚኖረው ሽልማት ወይም ጥቅም ላይ መጋራት የሚያስችል መብት የላቸውም፡፡ መሀል ገብተው የተጫወቱትና ላባቸው በፊታቸው እስኪዎርድ የተቻወቱት፣ የታገሉት፣ ጉዳቱ የደረሰባቸው ብቻ ናቸው፡፡ የቤተክርስቲያን ጉዳይም ከዚህ አይለይም፡፡ በመጀመሪያ ለራሳችን ምን ሰራችሁ የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ እነ ከሌ እያሉ የሚለው አያዋጣም ያ ለእነርሱ ነው ካንተም የሚጠበቅ አለ፡፡ የምግባር ህጸጹን እየታገስን፣ የሀይማኖት ህጸጹን ግን እየታገልን መስራት ይጠበቅብናል፡፡ አባ ሲዞስ የሚባሉ አበው ‘ዝናው ከሥራው በላይ የገነነበት ሠው ያልታደለ ነው፡፡’’ እንዳሉት ለዝና ሳይሆን ሁልጊዜም አቤቱ ጋታዬ ምግባር የጎደለኝ ሀጠአተኛ ልጅህን ለሐዋርያት እምነት እንደ ቸመርክላቸው ልእኔም ጨምርልኝ በሉት፡፡  ምዕመናንና ምዕመናት ወገኖቼ የፀኑትንና ያለፉትን ቅዱሳን አባቶቻችንን፣ ቅዱሳን አንስትን አብነት አድርገን የመምህራችንን የጌታችንን የመድሀኒታችንን የኢሱስ ክርስቶስን ፈለግ ተከትለን የመንግስቱ ወራሾች የክብሩ ቀዳሾች እንድንሆን እግዚአብሔር አምላካችን ይፍቀድልን፡፡ እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን፡፡ አጽራረ ቤተክርስቲያንን የስታግስልን፡፡ ልቦና ይስጣቸው፡፡ ወደ እውነተኛዋ አማናዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የንስሀ እድሜ ስጥቶ ይመልሳቸው፡፡ ለመሄድ በማኮብኮብ ላይ ያሉ እግራቸው ቤተክርስቲያን ፤ ልባቸው መናፍቃን አደራሽ ያሉትን በቤቱ ያጽናቸው፡፡ ያሉትን ይጠብቃቸው፡፡ በተለይ በተለይ ወጣቱን ትውልድ ለቤተክርስያን ዋጋ እየከፈለ ነውና እግዚአብሄር በጎ ምኞታቸውን ሁሉ እንደየፍላጎታቸው ይፈጽምላቸው፡፡ የጻድቃን የሰማዕታት የቅዱሳን መላዕክት ረድኤትና ጥበቃ አይለየን፡፡ ይቆየን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
ዲ/ን ያሬድ ጥዑመልሳን




24 comments:

  1. nice view...betekekele asetewelehale...egizihare yestehe...menafeqe menafeqe newe..metefo serane be seme lemedegefe aba selama belewe yeseralu ayaferum?

    egiziabehere ethiopian ...tewahidone yetebeqelene

    ReplyDelete
  2. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
    Replies
    1. am sure it is my comment has been removed,but i have told you the truth.

      Delete
  3. Dn.Tiuemelisan Egziabeher Tsegan abizito Yichemirilih. Benezih Yetehadisona Yemenafikan "BLOGOCH" laye beminayewuna beminanebew neger betam eyazenen bihonim yeseytanin andebet esu kalizegaw beker egna zim kemalet yalefe neger aladereginim. Gin endih yale meseretawi melise betekristiyanachin eyalat zimitaw eskemeche new? egna zim bemaletachin sinit yewahan begoch eyeteneteku letekula keleb eyehonu mehonun lib yemanilew leminidin new? Bebetekristiyan bewusit lesilitan,legenzeb,lesigawi kibir,lezer hareg etc... eyeteset yalew tikuret wede menfesawiwu ageligilot yemizorew meche yihon?
    Lehulum neger fetariyachin yekidusanun limena semito mihiretun endiyadilen kidus fekadu yihunilin Amen.

    ReplyDelete
  4. betam des yemelna beteley bemekenyat yetdegefe asteyayte selesethe betam tedeschalew!menem enkwa tshufhe rejem behonem alslechegnem neber betam astemarina ena anekake new bezhu ketelbete!
    egiziabehere hagerachenen ena haymanotachen yetebeqelen

    ReplyDelete
  5. እንግዲህ እንዴት ነው ይህን ሁላ ውለታ የዋለችለትን ህዝብ ከደም ስሩ ጋር የተዋሀደችውን እናት እንዴት አታስፈልግም ብለህ ብትነግረው ይቀበልሀል? kal hiwot yasemalen, mengsete semayate yawarselen!

    ReplyDelete
  6. it is nice veiew!!!!berta

    ReplyDelete
  7. ተሃድሶ እኔ አለሁ እያለ " አባሰላማ " ብሎግ:: እንዴት ተሃድሶ የለም ይባላል::
    በተለይ ከላይ የተጠቀሰው ግለ ሰብ ድሮም ለገንዘብ አድሮ ያጋንንት ነበረ:: ዛሬም ያጋንንት ነው:: ልዩነቱ ገበሬ ለወተት የሚጠቀምባት ላም መሥና ለሥጋ ተዋጾ እንደማድለብ ነው:: ገበሬው ሁለቱንም ጊዜ ባለቤቷ ነው:: ፓስተር ሙሴ ይሁን ቃልቻው ሙሴ የዲያብሎስ ስለነበረ እና ሥለሆነ መቼውንም የአምላክ ሆኖ አያውቅም::ይሁዳም ከሐዋሪያት መካክል ቢሆንም አንዴም ከጌታዉ ከገንዘብ ውጭ የእግዚአብሔር አልነበረም::

    ብዙ የሚደንቀኝ ግን ተሃድሶ የለም የሚሉ ወገኖች ናቸዉ:: አውቀው ነው እንጂ " አባሰላማ " ብሎግ እንኳን በቂ አይደለም ::ጠበቃ የቆመው
    ለማን እንደሆነ ከማ ወገን እንደተሰለፍ በማን አለብኝነት ይናገሩየለ::
    1 ቅዱሳን በተለይ እመቤታችንን ታምሯን
    2 ጻድቁ ተክለሃይማኖትን
    3 ቅዱስ ሚካኤልን
    በተለያዩ ጊዜ የጻፏቸው ነቀፋዎች ማንንም ያሳምናሉ ብዬ ግምት ባይኖረኝም ግን ግን የነሱን ማንነት ከውስጥ ከነማን ጋር እንደሚሠሩ
    ተረዳሁ::ድምዳሜዬም ተሃድሶ አለ:: ስለዚህ አባቶቻችን እኛም ቤተክርስቲያንን ሲያቃጥሉ እሳት ልናቀብላቸው አይገባም::

    ሀሰት እራሷን ገልጻለችና እኛም እናስተውል:: ተሃድሶ ቤተክርስቲያንን ሊያፈርስ እምነታችንን ሊያጠፋ እየሠራነው::
    ምናልባት በገንዘብ ፍቅር በሥልጣንና ለዝና የምትከተል ካለህ ንቃ እግዚአብሔር ያልሰጠን ሁሉም ከንቱነው::

    እናስተውል::

    ቸሩ እግዚአብሄር ይጠብቀን!
    አሜን

    ReplyDelete
  8. እግዚአብሔር ይባርክ ፣ ሰላሙን ፣ ፍቅሩን ፣ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡
    እግዚአብሔር ቤቱንና እኛን ልጆችን ይጠብቅ።

    ReplyDelete
  9. የቅዱሳን አምላክ ቃል ህይወት ያሰማልን መንግስተ ሰማያት ያዋርስልን። በጣም ደስ የሚል መልዕክት ነው። የኢትዩዽያ ኦርቶዶክስ ዕምነትና አስትምሮ ካልተመቻችው ስለምን ለቀቅ አድርገውን የራሳቸውን መንገድ አይከተሉም።

    ReplyDelete
  10. HULUM LIMELEKETEW YEMIGEBA TEKAMI MEREJA ENA YEMANKIA DEWIL!!! http://www.youtube.com/watch?v=aFqOJrx10DQ

    ReplyDelete
  11. andit sare temeza betewedeq besewa mekniyat betu weset zenab ayegebam neger gen lesuwa lerasua gudwa fela b/c esat newa yemitebeqat

    ReplyDelete
  12. kal hiwot yasemalen

    ReplyDelete
  13. Egziabher Ybarkh! Tsegawnm Abzto Yisth!!!
    Yibel bilenal!!! DES yemil orthodoxawi mels!!!!

    ReplyDelete
  14. Kale Hiywot Yasemalin Wendimachin D Yared

    You just wrote what the real tewahedo lige response May GOD bless u and ur family. Excellent response not only response it is a course. It is a DOCUMENT.
    በግልህ ሰይጣንን ከምታመልክበት በጋራ ሰይጣን ወደ ሚመለክበት ቦታ ነው የተዘዋወርከው፡፡ የቀየርከው ቦታ ብቻ ነው፡፡ ሀይማኖትህ መስሎህ ነው እንጂ አንድ ነው፡፡

    ReplyDelete
  15. ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት ደግሞ መጀመሪያ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሀዋርያት በቃልና በተግባር ሲየስተምራቸው ስህተት ነበረበት እነደ ማለት ይቆጠራል፡፡ ሎቱ ስብሃት፡፡ ይህ ደግሞ ድፍረት ነው፡፡ እዚያው እንደለመዳችሁት የመሰረታችሁትን የእናንተውን ድርጅት በየጊዜው እያደሳችሁ፣ እያሻሻላችሁ፣ የማይመቻችሁን አየቀነሳችሁና እየጨመራችሁ እስከምትዘጉት ድረሰ ተከተሉት፡፡ የኛን ሀይማኖት መቀየር ለምን አሰፈለጋችሁ? ተሰባሰቡና ይኸ ይኸ ትክክል ነው፤ ይኸ ደግሞ ስህተት ነው ብላችሁ ተፈራረሙና የራሳችሁን የእምነተ ድርጅት በፍትህ ሚኒስተር አስመዝግባቸሁ የራሳችሁን እምነት ተከተሉ፡፡ እኛ ጋ ምን አጣላችሁ፡፡ ካልተመቻችሁ፣ ከአላመናችሁበት ማን በግድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲንን ተከተሉ አላችሁ፡፡ አሁን ደግሞ ምን ችግር አለ፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን ሀይማኖት መከተል እንደሚችል በህገ መንግስት ደረጃም ተደንግጎላችኋል፡፡ በኛ ስም መነገዳችሁን ትታችሁ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት የራሳችሁን የእምነት ድርጅት አቋቋሙ፡፡ በእናንተ አልተጀመረ፡፡ thank you d/n yared God ke kedest betekrestian ayeleyeh....berta yekurt ken ye betkerestian lej ...berta..

    ReplyDelete
  16. ቃለ ህይወት ያሰማልን አንተንም ልቦናህን አይቀይርብን ሁሌም እግዚያብሄር ካንተ ጋር ይሁን!!!

    ReplyDelete
  17. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ይህ ጉዳይ የሁሉም የተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የወቅቱ ፈተና ነው፡፡ ለጊዜያዊና ብልጭልጭ ነገሮች ብለው ሃይማኖታቸውን በሚቀይሩና በሚክዱ ሰዎች ምክንያት የቤተክርስትያናችን አማኝ ይናወፃል የሚል ግምትም ዕምነትም የለኝም፡፡ ነገር ግን እነርሱ ያተረፉ መስሏቸው በተለያዩ ሚዲያዎቻቸው መሪጌታ እገሌ አባ እገሌ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ወደኛ መጡ እያሉ ያሳያሉ ያስነብባሉ እንዲሁም ያሰማሉ፡፡ ሆኖም በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የታተመች ቅድስት የምትሆን ቤተክርስትያናችን አትናወፅም፡፡ ለኛ ሃይማኖታችንን ማንም አይነግረንም ሐዋርያት ነግረውናልና፡፡ ማንም አይሰብክልንም ቅዱሳን በሥራቸው አሳይተውናልና፡፡ ስለዚህ በቅዱስ አባታችን በከሳቴ ብርሃን ሰላማ ስም ለሳቸው በማይስማማ ክህደት የከፈታችሁትን የጥፋት መንገድ ትታችሁ ዲያቆን ያሬድ እንዳላችሁ ጎራችሁን ለዩና ወዳባቶቻችሁ አዳራሽ ግቡና ጨፍሩ ካሻችሁ ደግሞ ተነፋረቁ፡፡ እኛ ለእንጀራ ብለው የሚያገለግሉ አገልጋዮች የሉንም ስለመንግስቱ ብለው ራሳቸውን የሚሰጡ እንጂ፡፡ በብዙ አበያተክርስትያኖቻችን እየታወቀባችሁ በጠንካራ ምእመናንና ሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶች በእግዚአብሔር ቸርነትና በቅዱሳን ምልጃ ከኣውደ ምህረቱ ላይ ወርዳችሁልናል፡፡ በዚህም ብዙ ዝላያችሁንና ኑፋቄያችሁን እንዳናይና እንዳንሰማ ተጠብቀናል፡፡ አሁንም ግን በአንዳንድ አውደምህረቶች ላይ ብቅ ማለታቸሁን አልተዋችሁም፡፡ በተለይም አቃቂ መድሃኒዓለምና ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያናት፡፡ ከዛም ጌታ በፈቀደ ቀን እንደምትቀሩ ተስፋዬ ነው፡፡

    ReplyDelete
  18. ቀድሞውንም የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላት ነበርክ እንጂ የእግዚአብሔርን መንግስት የምትሰብክ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር አልነበርክም፡፡

    ReplyDelete
  19. ቃለ ህይወት ያሰማልኝ
    መግለጫው ዘገየ እንጅ እጅግ በጣም ጥሩ ነው ፡፡ አሁንም እየተከታተላችሁ ለሚነዙት የሃሰት ትምህርት ከቤተ ክርስቲያናችን ትምህርትና አቋም አኳያ በወቅቱ መልስ መስጠት ይገባችኋል ፡፡ ወንጌልን በንጹህ ከማስተማር ይልቅ የምእመኑን አምልኮ ለመበረዝ ፣ የሉተርን ትምህርት ለማስረጽ ታጥቀውና ተደራጅተው እየሠሩ ነው ፡፡ ቀዳሚ መንገዳቸው ደግሞ ለሆዳቸው ያደሩትን ቀሳውስትና ካህናት በመጠቀም ፣ ምእመን እስከማይደርስበት የሚገቡትን ውስጥ አዋቂዎች ፣ ለኦርቶዶክስ እምነታችን ምልክት የሆነውን ቋንቋ ግዕዝ ተናጋሪን በመጠቀም ነው ፡፡ ህዝቡን ማስተማር ያስፈልጋል ፤ ከዚሁ ጐን ለጐን ደግሞ ካህናቱንም እንዲያስተውል መቀስቀስ ያስፈልጋል ፡፡ ግዕዝ የሚናገር ሁሉ አንድ እምነት የለውም ፤ የተለየ ትምህርትና አቋም ያለውን መለየት መቻል ይገባል ፡፡
    በጎችን ለመጠበቅ አደራ የተሰጣችሁ ሁሉ ተግታችሁ መሥራት ይጠበቅባችኋል

    ReplyDelete
  20. ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ በሁላችንም ህሊና የሚመላለሰውን ሀሳብ ነው አውጥተህ የተናገርከው፡፡ አንጀቴን ነው ያራስከው፡፡ አዎ በጣም ትክክል ነህ እስካሁን በጣም ብዙ አረሞች ከቤተክርስትያናችን ላይ ተነቅለው ወጥተዋል፡፡ የቀሩትም ጊዜያቸውን እየጠበቁ ነገ ይነቀላሉ፡፡ አሁን ከውስጥ ሆናችሁ ቤተክርስቲያናችንን እየመረዛችሁ ያላችሁ የጭቃ ላይ እሾሆች መርዛችሁን እየተፋችሁ አባቶቻችን የሰሩትን ድንበር ባታፈርሱ መልካም ነው፡፡

    ReplyDelete
  21. emberhan edmana tenawen tesethe ....

    ReplyDelete
  22. kale hiwot yasemalen.

    ReplyDelete
  23. ቃለ ህይወት ያሰማልኝ
    መግለጫው ዘገየ እንጅ እጅግ በጣም ጥሩ ነው ፡፡ አሁንም እየተከታተላችሁ ለሚነዙት የሃሰት ትምህርት ከቤተ ክርስቲያናችን ትምህርትና አቋም አኳያ በወቅቱ መልስ መስጠት ይገባችኋል ፡፡ ወንጌልን በንጹህ ከማስተማር ይልቅ የምእመኑን አምልኮ ለመበረዝ፣የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን እየፈጠሩ ህብረተሰቡን ማጠራጠር ፣ከቤተክርስቲያን መለየት፣ መንፈሳዊ ህይዎቱን ማዳከም ማለትም ዳ/ን ዳንአል በስብከቱ " እግዚአብሔር ሰው አለው "በሚለው ስብከቱ ላይ እከሌ እንደዚህ ከሆነ እኔ ማነኝ የሚሉ አሉና እባካቺሁ ሳትሰለቹ እውነተኛውን መረጃ አሰሙን፡፡ ቀዳሚ መንገዳቸው ደግሞ ለሆዳቸው ያደሩትን ቀሳውስትና ካህናት በመጠቀም ፣ ምእመን እስከማይደርስበት የሚገቡትን ውስጥ አዋቂዎች ፣ ለኦርቶዶክስ እምነታችን ምልክት የሆነውን ቋንቋ ግዕዝ ተናጋሪን በመጠቀም ነው ፡፡

    ReplyDelete