Friday, March 9, 2012

ከወደ ስልጤ ዞን ደስ የሚል ዜና ሰምተናል



(አንድ አድርገን የካቲት 30  2004ዓ.ም)፡- በትላንትናው እለት ከወደ ስልጤ አካባቢ መልካም ዜና ሰምተናል ፤ ከወራት በፊት በአካባቢ አክራሪ ሙስሊሞች  አማካኝነት የተቃጠለችው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስያን ጉዳይ ከዞኑ ባለስልጣናት እና ከመንግሰት ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሳይሰጥ ተንከባሎ እስከ አሁን መድረሱ ይታወቃል ፤ ባለፈው 17/06/2004 ዓ.ም እርቀ ሰላም ሊከናወን ታስቦ የክልሉ ጸጥታ ጉዳይ አቶ አሰፋ አብዮ ባለመኖራቸው እና የሚመለከታቸው የመንግስት ሀላፊዎች ተደራራቢ ጉዳይ ስላጋጠማቸው የእርቀ ሰላሙን ቀን ለአንድ ሳምንት እንዳራዘሙት መዘገባችን ይታወሳል ፤ ባለፈው እሁድ እኝህው ባለስልጣን ሳይገኙ እርቀ ሰላሙ የተከናወነ ሲሆን በስተመጨረሻ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድሞቻችን አዲስ ሀሳብ በማንሳታቸው ጉባኤው ሳይስማማ ከረዥም ሰዓታት ስብሰባ በኋላ ሊበተን ችሏል፤ ነገር ግን ያለመታከት ከቤተክርስትያናችን የተወከሉ አባቶች ፤ እና የአካባቢው ያሉት ክርስትያኖች ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት በ28/06/2004ዓ.ም  አቶ አሰፋ አብዮ ባሉበት በተደረገው የእርቀ ሰላም ጉባኤ ለቤተክርስትያናችን መልካም የሆነ ነገር ፤ ለህዝበ ክርስትያኑ በጎ ዜና ይዞ የመጣ ስብሰባ ተከናውኖ በአቋም መግለጫ እርቀ ሰላሙ ግቡን መቶ በሰላም ሊጠናቀቅ ችሏል ፡፡ ከስብሰባው በኋላ ሁሉም በሚቀጥሉት ነጥቦች ላይ ጉባኤው ሙሉ ስምምነት ላይ የደረሱ መሆናቸውን ከቦታው የደረሰን የውስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ ያመለክታል፡፡

1.     ጉባኤው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን መስሪያ የሚሆን ሶስት ከበፊት ይዞታ የሚበልጡ በአማራጭነት አቅርቧል ፤ ከቀረቡት አማራጮች የዞኑ መስተዳድር ከበፊቱ ይዞታ ቦታ ላይ 100 ሜትር በማይርቅ ቦታ ላይ ሰፊ ቦታ ለአርሴማ ቤተክርስትያን መስሪያ ቦታ ሲሰጥ ፤ ቤተክርስትያኗ በአንድ ቀን ውስጥ ሙሉ መሬቱንና የግንባታ ፍቃድ አግኝታለች ፤ በትላንትናው እለት 29/06/2004 ዓ.ም የቦታ ማረጋገጫ ካርታ ይሰጣታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
2.    በዞኑ መስተዳደር ቤተክርስትያኒቷ የምትጠቀምበትን የጥምቀት ቦታ በአግባቡ ተከብሮ ሙስሊሞች እንዳይደርሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
3.    ከ 2 ወር በፊት ቤተክርስትያኒቷ ስትቃጠል ለጠፋው ንብረት የወረዳና የዞኑ አስተዳደሮች ሀላፊነቱን በመውሰድ ማህበረሰቡን በማስተባበር በብር ወይንም በቁስ መልክ ለቤተክርስትያኒቷ እንዲያስመልስ የክልሉ መንግስት አቅጣጫ አመላክቶታል ፤ እነሱም ሊተገብሩት ቃል ገብተዋል
4.    ንብረቱን ያቃጠሉ ሰዎች በስምም ሆነ በአካል በማህበረሰቡም ሆነ በወረዳው አስተዳዳሪዎች የሚታወቁ ሲሆኑ ጉዳያቸው በእርቀ ሰላም ካለቀ የዞኑ መስተዳደር ሊተዋቸው ያለበለዚያ ላጠፉት ጥፋት ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት ለማስቀጣት ፍርድ ቤት እንደሚያቆማቸው ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡(የእነዘህ ሰዎች ጉዳይ ከቀናት በኋላ በአባቶቻችን እና በሙስሊም ሽማግሌዎች መካከል ይመከርበታል ተብሎ ይጠበቃል)
5.    በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ ሙስሊም ማህበረሰቡ ቤተክርስትየኗን ከክርስትና አማኞች ጋር አንድ ላይ በብር ፤ በጉልበት እና በቁሳቁስ እርዳታ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርተው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል፡፡
ኦ አምላከ ቅዱሳን ተመስገን ፤ አምላካችንን ምን ብለን እናመስግነው ፤ የአካባቢ ክርስትያኖች እንባ እግዚአብሄር ዘንድ ደርሷል ተገቢ መልስም አግኝተዋል ፤ የራሄልን እንባ የተመለከተ አምላክ የስልጤ ክርስትያኖችንም እንባ አልዘነጋም ፤ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ በአካባቢው ያሉ ክርስትያኖችን ጽናታቸውን ሳናደንቅ አናልፍም ፤ ይህ ለኛ ብዙ ትምህርት ይሰጠናል ፤ ይህ ጉዳይ  የቅድስተ አርሴማን ቤተክርስትያን ብቻ የሚመለከትም አይደለም ፤ የአንድ አካባቢም ምዕመን ጉዳይ ብቻም አይደለም ፤ ይህ ሁላችንንም የሚመለከት ጉዳይ ነው ፡፡ የክልሉን መንግስትም ሆነ የዞኑን አስተዳደር ለዚህ የበሰለ አካሄዳቸው ምስጋና እናቀርባለን ፤ እነዚህን የመሰሉ ሰዎች ለሌላ ክልልም ሆነ ዞን ስራቸው አስተማሪ ነው ብለን እናምናለን ፤ በሰከነ እና በተረጋጋ ሁኔታ ጊዜ ወስዳችሁ ሁሉን ያማከለ ስራ ሰርታችሁ ሁሉም የሚግባባበት ነጥብ ላይ ህዝቡን ማድረስ ቀላል የሚባል ስራ አይደለም ፤ መስተዳድሩ ነገሮችን በጉልበት ማህበረሰቡ ላይ ላለመጫን ብዙ መንገዶችን ተመልክቷል ፤ ሁሉንም የሚያስማማ ሁሉም የደገፈው የስምምነት ነጥብ ላይ አድርሷቸዋል፤ ይህ ስራው ብቻ ያስመሰግነዋል፡፡ መንግስትና ህዝብን እጅ ለእጅ እንዲያያዙ የሚያደርግ ስራ ስለሰራችሁ ፤ ህዝብና መንግስትም የጣለባችሁን ሀላፊነት መወጣት በመቻላችሁ ፤ ነገ ላይ አብሮ ለሚበላው አብሮ ለሚጠጣውን ማህበረሰብ አብሮ የመኖርን ፤ የመቻቻልን በር ስለከፈራችሁ እግዚአብሔር ያክብርልን ብለናል፡፡

በየቦታው ቤተክርስትያን እየተቸገረች ያለችው እሳቱን ለማጥፋት የሚከለሰው ውሀ ቤንዚል እየሆነባት ነገሮችን ገድጡ ወደ ማጡ እያደረጉባት ስለሚገኙ ነው ፤ የስልጤ አካባቢ ክርስትያኖች ያስተማሩን  በፈተና ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ምን ያህል መፅናት እንደሚያስፈልግ ፤ ስለ ቤተክርስትያን ተቆርቋሪነት ፤ ያለውን ችግር ጫፍ ድረስ ይዞ ሄዶ መፍትሄ ለመሻት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ፤  ችግርንና መከራን መጋፈጥን ነው ፡፡  ሌሎችንም  ብዙ ነገሮች ለእኛ አስተምረውናል፡፡ይህ ስለቤተክርስትያን ያላቸው ቅናት  ብዙ መስዋትነትን አስከፍሏቸዋል ፤ ዝም ብለው ቤታቸው እንዳይቀጡም አድርጓቸዋል ፡፡ በአሁን ዘመን  ከተነሱ አጽራረ ቤተክርስያን ጋርም አንገት ላንገት አስተናንቋቸዋል  ፤ ክርስትያን በህይወቱ በአምላኩ የማይቀና ከሆነ ውሀ የፈሰሰበት እንጨት ነው ፡፡ ስለቤተክርስትያን መጎዳት ግድ የማይለው ከሆነ ፤ ቤተክርስትያን ላይ የሚደርሰው አደጋ እሱ ላይ ቤተሰቡ ላይ የተቃጣ አድርጎ ካልወሰደው ገና ክርስትናው በአግባቡ አልገባውም ፡፡ ውሀ የፈሰሰበት እንጨት አንድም ካልደረቀ አለዚያ ቤንዚል ካልተርከፈከፈበት እንደማይቀጣጠል የመንፈስ ቅዱስ እሳት በበረከቱ የማይጎበኝው ተዘልሎ የተቀመጠ ክርስትያንም ስሙን ስለያዘ ብቻ ምንም አይነት በረከት የሚያሰጥ የፅድቅ ፍሬን የሚያፈራ ስራን መስራት አይቻለውም ፡፡ ቅናት አባታችን እዮብን ፍጹም ቅን እግዚአብሔርን የሚፈራ ከክፉ የራቀ ሰው አድርጎታል (እዮብ 1፤8) እግዚአብሔር ስለ እዮብ መስክሮለታል ፡፡  ቅናት ጻድቃንን ወደ ገዳም ሰማእታትን ወደ ደም ይመራል፡፤ በመሆኑም የቤተክርስትያን ቅናት እግዚአብሔር ለወደዳቸው የሚሰጠው ታላቅ ሀብት ነው፡፡ እነዚህም የስልጤ አካባቢ ክርስትያኖች ስለ ቤቱ ግድ ያላቸው ፤ የቤቱ ቅናት የበላቸው ናቸው ፡፡ ቤተክርስትያን ለእነርሱ ብዙ ነገራቸው ናት ፤ ለዚህም ነው ነገሩን ነገራቸው አድርገው መሄድ የሚገባቸውን ያህል ርቀት ተጉዘው ይህን መፍትሄ ማግኝት የቻሉት ፤

አንድ አድርገን ይህን ሁኔታ ችግሩ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስታ እስከ መፍትሄው ድረስ በሀገር ውስጥ ምዕመኖች እና ከሀገር ውጪ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉንም ነገር በጊዜው እንዲያውቁት የመፍተሄ አካልም እንዲሆኑ በቅርበት በመከታተል እናንተው ዘንድ ስታደርስ ቆታለች ፤ ይህን መስማት ለእኛ እንደ አሸናፊነት እንቆጥረዋለን ፤ አሁንም ቤተክርስትያኗን ለመስራት ከቀድሞ ይዞታዋ በተሸለ ሁኔታ ለማነጽ መንገድ ጀመርን እንጂ አልጨረስንም ፤ የፈረሰውን ቤታችንን ሁላችንም በድህረ ገጽ ከማንበብ እና በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ከመስማት ውጪ አሻራችንን የማኖር ክርስያናዊ ግዴታው አለብን ፡፡

ቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያንን ለመስራት ቡታ ጅራ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር 3907 ዝግ አካውንት በመክፈት ምእመኑ እና ሰበካ ጉባኤው ስራውን ጀምሯል፡፡ ይህችን ቤተክርስትያን መርዳት ለምትፈልጉ ሰዎች በዚህ አካውንት ተጠቅማችሁ ሀላፊነታችሁን መወጣት እንደምትችሉ ለማሳሰብ እንወዳለን ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ የተሰጠውን ቦታ ስፋት ፤ የቦታውን ፎቶ ግራፍ ፤ ለመስራት የታቀደውን የቤተክርስትያን ዲዛይን እናንተው ዘንድ እናደርሳለን ፡፡ የቤተክርትያኗን ለውጥም በየጊዜው እናቀርባለን ፤ ሁሉ ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜም ሩቅ እንደማይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ባለ ሙሉ ተስፈኞች ነን፡፡ አሁን ለሁላችን የስራ ጊዜ ነውና እንዴት መርዳት እንዳለብን እናስብ ፡፡ ቸር ሰንብቱ 


23 comments:

  1. Egziabher yetemesegene yihun. Amen!

    ReplyDelete
  2. Egziabher yimesgen!!le silte akababi metedadir akalat ena shimaglewoch misgana akerbaleku!!Egzer yistilin!!

    ReplyDelete
  3. Egziabher yetemesegene yihun. Amen!

    ReplyDelete
  4. If you have any contact person please provide the info fo me/us. I want to give a my word of contribution) to the contact person.

    ReplyDelete
  5. ይህን ውጤት ያመጣ እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን አብሮ የመኖር ችግር የለብንም ፡፡ የዋህ ህዝብ እንደ መሆናችን መጠን በታላላቆች የተነገረውን በሙሉ አሜን ብለን የመቀበል ልማድ አለን ፡፡ ይህን ጥቃትና በደል ያደረሱትም ግለሰቦች በሆነ ምክንያት ተገፋፍተው መሆን አለበት እንጅ ፣ ከዚህ ያለፈ በራሳቸው የተነሳሱበት ልዩ ተልዕኮ ይኖራቸዋል ብዬ እነሱን እንደ ወንጀለኛ አላይም ፡፡ በቅርብ ጊዜ የተቃጠለችውም የአርሴማ ቤተ ክርስቲያን ብቻ አይደለችም ፤ ይልቁንም ለሌሎቹ የጐንደር አብነት ት/ቤትና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን /ምንጭ - ግብረ ሄር /ቃጠሎ ምክንያት ተጣርቶ አስፈላጊው መፍትሄ ቢሰጥ ህዝበ ክርስቲያኑ ይደሰታል ፤ የገዳማቱም ቃጠሎና የማፍረስ ተግባር ሁሉ አግባብ ባለው መንገድ መፍታት ይገባዋል ፡፡ ይህን አርአያነት ፣ ሁሎችም አመራሮች ቢከተሉት እጅግ መልካም ይመስለኛል ፡፡ ሁላችን እናልፋለን ፤ የማታልፍ ቤተ እምነትን ጐድት ማለፍ ግን ትልቅ ስህተትና በደል ነው ፤ እግዚአብሔርም አንድ ቀን ይፈርዳል ፡፡ ድሉም የእግዚአብሔር ይሆናል ፡፡

    ReplyDelete
  6. This action could be repeated in other areas in which true christains are suffering. The government officials could know the time in which they are in, it is time of democracy and globalization, so please try to analyze things in rational way like this. Thanks for ur immidiat info.as usual

    ReplyDelete
  7. ejeg des yemil meserach new amlak mechereshawen yasamerelen

    ReplyDelete
    Replies
    1. ለብጹ አቡነቀለሚጦስ ረጅም ያገልግሎ ዘመን እና እድሚን ይስጥልን

      Delete
  8. Well done!!! Bertu. We will do our best to help build the church.

    Chala

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yihin Yaderege Ye Kidist Arsema Amlak Yimesgen !!!

      Delete
  9. Bertu des yemile zena new!!!

    ReplyDelete
  10. Egzeabher yimesgen lenatem Egzeabher biratatun yistachu amen

    ReplyDelete
  11. silmayineger sitotaw egiziabher yimesgen! mekerana kibr kibrna mekara ayileyayum!!! yeqidusan abewun tsinatina birtat lehulachinim yadilen AMEN!!!

    ReplyDelete
  12. Egziabher Yimesgen

    ReplyDelete
  13. enedakagtelu enesun ketel yaderegachw egeziabehir bekelu n yebekelelen lemanegawm egeziabehir mechereshawn yasamerelen amen+++

    ReplyDelete
  14. E/G yemesegane des yemil zana new ,yeha lebelete neger yanesasanale

    ReplyDelete
  15. yimesgen yikber amlake ethiopia na kristian

    ReplyDelete
  16. እግዚአብሔር ለ
    አባቶቻችን የሰጠውን ቃል አይረሳምና፦ የፈረሱትን የሚሰራ፤ የወደቁትን የሚያነሳ፤የተጨነቁትን የሚያረጋጋ፤ የአዘኑትን የሚያጽናና ᎐᎐᎐᎐አምላክ ነውና፤ እንኳን ደስአላችሁ(ለን)።አሁንም እግዚአብሔር በምህረቱ፤በቸርነቱ፤በመግቦቱ አይለየን አሜን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

    ReplyDelete
  17. እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የሰጠውን ቃል ኪዳን አይረሳምና፦ የፈረሱትን የሚሰራ፤ የወደቁትን የሚያነሳ፤ የአዘኑትን ያሚያጽናና፤የተጨነቁትን የሚያረጋጋ᎐᎐᎐᎐᎐ አምላክ ስላለን ደስይበለን(ላችሁ)። አሁንም እግዚአብሔር በምህረቱ፤ በቸርነቱ፤ በመግቦቱ አይለየን አሜን። ምስጋና ይሁን ለእግዚአብሔር።

    ReplyDelete
  18. Yee Enatacen Qedest Aresema Celote ,Yee Qedusan celote Eceen Haymanot Eceen Ewnatga ortoduckes Tewaedon Yetabqatal.

    ReplyDelete
  19. Bizegeyim Yemikekedmihi Yelem...misgana LEAB LEWOLD LEMENFESKIDUS!

    ReplyDelete
  20. እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የሰጠውን ቃል አይረሳምና፦ የፈረሱትን የሚሰራ፤ የወደቁትን የሚያነሳ፤የተጨነቁትን የሚያረጋጋ፤ የአዘኑትን የሚያጽናና አምላክ ነውና፤ እንኳን ደስአላችሁ(ለን)።አሁንም እግዚአብሔር በምህረቱ፤በቸርነቱ፤በመግቦቱ አይለየን አሜን።አሁንም እግዚአብሔር አምላክ በቤተክርስቲያንአችን ፡በአባቶቻችን ላይ የመጣውን መከራና ስቃይ ዘምበል ብሎ ይመልከት፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

    ReplyDelete
  21. egziabher melkam new !!!

    ReplyDelete