Friday, March 23, 2012

‹‹ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ ›› ይህን ስላቅ ምን ይሉታል ?


(አንድ አድርገን መጋቢት 14 2004 ዓ.ም)፡- ቤተክህነቱ ዋልድባ ገዳምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝበ ክርስትያኑን ጨጓራውን ያሰረረ ነበር ፤ መንግስት እንኳን ከጥቅሙ አኳያ ስኳር ፋብሪካ እገነባለው ቢል መጀመሪያ መቃወም ያለበት ቤተክህነት ሆኖ ሳለ ከመንግስት ጋርም ወግኖ መንቀሳቀሱ ቤተክርስትያኗ ደህና የሚባል መንግስትን የሚቃወም አካል እደሌላት በግልፅ ያሳያል ፤ በመጀመሪያ የዋልድባ አባቶች ገዳማቸው ሳይታረስባቸው ታረሰብን አይሉም ፤ ሳይነካባቸው ተነካብንም ለማለት አይደፍሩም ፤ የመንግስት ባለስልጣናትን የታረሰው ቦታ ላይ ኑ እና እንወያይ መጀመሪያ ስራችሁን እዩት ሲሏቸው ቀድመው የሰሩትን ስራ ያውቁታልና ሽሬ ላይ ካልሆነ ብለው ባለስልጣናቱ እምቢ አሉ ፤ አባቶችም በቃ የሰራችሁትን ስራ ላለማመን እና አላደረግንም ለማለት ስለሆነ በምትጠሩት ስብሰባ ላይ አንገኝም ብለው በአንድነት ተነስተው ወጡ ፤ መንግስት ደግሞ እያለ ያለው የፖለቲካ አላማ ያላቸው የገዳሙ መነኮሳት ብሎ አስተያየት በኢቲቪ ሲሰጥ ስመለከት በጣም ተበሳጨው ፤ ሰው የፖለቲካ አላማ ለማረመድ ገዳም ምን ሊሰራ ይገባል ? የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እኮ ከተማ ነው ተመራጭ ፤ እንዴት እደሚያስቡ ራሱ ግራ የሚገባ ነገር ነው ፤


ቤተክህነት እኛን ወክሎ ወደ ዋልድባ ያቀናው ሰው እና የመንግስት ስኳር ኮርፖሬሽን ሀላፊ አባይ ጸሀዬ  ሁለት አይነት መልስ መስጠታቸውም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ፤ አቦይ ስብሀት የሚነሳ መቃብር አለ ፤ እሱን ሌላ ቦታ ላይ የማስፈር ስራ ይሰራል ፤ በቤተክርስትያን አባቶች ቦታው ተባርኮ የነበሩትን አስከሬኖች በማንሳት ቦታ የመለወጥ ስራ ይሰራል ብለው አስተያየት ሲሰጡ ፤ አቶ ተስፋዬ  የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ደግሞ ምንም ነገር እንዳልተከናወነ እና የስኳር ልማቱ እና ገዳሙ በጣም የተራራቁ መሆናቸውን ገልጸዋል ፤ በነገራችን ላይ ይህ ሰው ከጀነራል ዊንጌት ኤሌክትሪሲቲ ዲፕሎማ እንዲሁም በገበያ ጥናት አስተናደር ሌላ ዲፕሎማ ያለው ሲሆን አሁን ከሚሰራበት ቦታ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው አቡነ ጳውሎስ ቢመልሱ መልካ ነው ፤ ባይሆን እንደኛ ሀሳብ የገበያ ጥናቱ ትምህርት የዋልድባን መሬት ከመንግስት ጋር በመደራደር ለመሸጥ የረዳው ይመስለናል ፤ ባለን መረጃ መሰረት ለዋልድባ ገዳም አባቶች ሀሳባቸውን በአግባቡ እንዳይገልጡ  እንደ እርጎ ዝንብ እየገባ ሲበጠብጣቸው የነበረውም ይህ ሰው ነው ፡፡ ገዳሙ ከግድቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አማራጭ እንዳለውም ገልጿል ፤ በተጨማሪ በጣም የገረመን አስተያየት የሸንኮራ ልማቱ ሲካሄድ በሚገደበው 138 ሜትር ግድብ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ የሚል አስተያየት መስጠቱም ጭምር ነው ፤ ቋርፍ የሚባል ገዳሙ የሚጠቀምበት ተክልም ብሎ ዘባርቋል ፡፡ ይህ ሰው በዚህ ብቃቱ እዚህ ቦታ ላይ መቀመጥ ይገባዋል ብለው ያስባሉ ?  እኛ እንደምናስበው ይህ ቦታ የቤተክርስትያኒቱን አማኞች ለመምራት በመንፈሳዊ ሆነም በአስተዳደራዊ ትምህርቶች ለቦታው የሚመጥን ሰው መሆን አለበት የሚል አስተያየት አለን ፤ አሁን የኛ ትልቁ ችግር የማይገባቸው ሰዎች ቦታን በዘመድም ይሁን በገንዘብ ይቆናጠጡታል ፤ ኋላ የሚመጣውን የቤተክርስትያን ችግር ሲመጣ ደግሞ ቤተክርስትያኒቷን አሳልፈው ይሰጧታል ፤ትክክለኛው ሰው ትክክለኛ ቦታ ላይ ቢቀመጥ ግን ይህን የመሰለ ችግር ለመፍታት መንፈሳዊ ሆነ አስተዳደራዊ ብቃት ስለሚኖረው ችግሮችን ሊጋፈጥ እና መፍትሄ ሊያመጣ የመጀመሪያው ሰው ይሆናል ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው የተገላቢጦሽ ነው ፡፡

እኛ የአሳ ናፍቆት የለብንም ፤ እኛ ርስታችንን አትንኩ ነው የምንለው ፤ አሳ ለማግኝት በመኪና ሀዋሳ መውረድ ይቻላል ፤ የአባቶችን ርስት ፤ መቃብር በዶዘር አትፈንቅሉብን ነው የምንለው ፤ አቶ አቦይ ስብሀት ስለ ሚያነሱት አፅም በቂ እውቀት ላይኖራቸው ይችላል ይህ ግን ከቤተክህነት ተወክሎ የሄደ ሰው ከሰውየው ዘቅጦ መገኝቱ ያሳፍራል፡፡ ልሳነ ዘተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ በየወሩ የምትታተም መፅሄት ላይ የ2004 ዓ.ም የአብይ ፆም እትም አቡነ ጳውሎስ ይህን ሰው ከፍተኛ ብቃት ያለው ሰው በማለት አሁን ላለበት ቦታ ሹመውታል፡፡

እኛም እንደ አባቶች ይግባኝ ለክርስቶስ ብለናል ፤ ቅን ፈራጅ እሱ ስለሆነ ለእሱ አሳፈናል ፤ ቤተክርትያን ጦር ሲነሳባት አብረው ከውስጥ ለሚወጓት ሰዎች ጊዜው ሲደርስ ባለቤቱ ይፋረዳቸው ፤ የአባቶችን ጸሎት አምላካችን ይሰማል ፤ በፍርድ ቀን መጽሀፉ እንዲህ ይላል ‹‹እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤›› ማቴዎስ ወንጌል 12 ፤36 እናንተም ስለ ስራችሁ ትጠየቁበታላችሁ ፤ የአምላካችን ቃል አይታበይም ፡፡

የኢቲቪ ዜና ይህን ይመስላል
የልማት ፕሮጀክቱ የዋልድባ ገዳም ህልውና የማይነካ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወች

በምዕራብ ትግራይ ወልቃይት ወረዳ የሚካሄደው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በሚገኘው የዋልድባ ገዳም ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። በቤተክርስተያኗ የተቋቋመው አጣሪ ቡድን በሰጠው መግለጫ የልማት ፕሮጀክቱ የገዳሙን ህልውና የማይነካና የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ የሚከናወንበት ቦታና ግድቡ የሚገነባበት ስፍራ የማይገናኙ ናቸው ብሏል። ግድቡ የዛሪማ ወንዝ የሚጠቀምና ሲፈስ እንኳን ወደ ምዕራብ ትግራይ እንጂ ሽቅብ ወደ ገዳሙ እንደማይወጣ ከገዳሙ መነኩሳት፣ ከፕሮጀክቱ ኃላፊዎችና ከአካባቢው አስተዳድር አካላት ጋር በተደረጉ ውይይቶች መረዳት ተችሏል ነው ያለው አጣሪ ቡድኑ። ገዳሙ ከግድቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አማራጭ እንዳለውም ተገልጿል።በገዳሙ ውስጥ የሚያልፍ መንገድም ሆነ ፓርክ እንደሌለ አጣሪ ቡድኑ ማረጋገጥ ችሏል። ገዳሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ መነኮሳት የሚሰጡት መረጃ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚያከናውኑት ተግባር ነውም ብሏል። እነዚህ አካላት ለሚያነሱት ሀሳብ ላይ ለመወያየት በተደጋጋሚ የተደረገው ጥረትም በእነሱ በኩል ፈቃደኝነትን ሊያገኝ እንዳልቻለ አጣሪ ቡድኑ ገልጿል። (ሪፖርተር ደባሱ ባይለልኝ)


33 comments:

  1. I thank you for your timely information. You are trying to do your best but we slept and the government is using this as a good chance to attack our church. By the way Meles and his followers don't know what we are asking. They only give attantion to something when they fear that it is danjerous for their power otherwise the issue of democracy, poeple's suffer, Country's history, religion etc are nothing for them. I think Meles doesn't have any ethics, moral and humanity. So what he fears is the gun b/c he knows that very well since he comes to position from "shita" position. So this gays are useless for this country, they could be avoided. By the way I decided to fight not only peacefully but with gun b/c that is what meaningful for them.

    ReplyDelete
  2. The sugar corporation guy is not Aboy Sibhat. He is "Abay Tsehaye". Please correct your news.

    ReplyDelete
  3. I feel that they couldn't analyze things properly; They have a mission to sell the Church. I think they are explaining the situation by considering only the building boundary of the Monastery. Which is the circle of the Game.

    ReplyDelete
  4. Is Paster.... preach about importance of Monasteries (by saying they are not important to get in heaven), is that a mission from Gov to achieve today's mission?

    ReplyDelete
  5. በነገራችን ላይ ይህ ሰው ከጀነራል ዊንጌት ኤሌክትሪሲቲ ዲፕሎማ እንዲሁም በገበያ ጥናት አስተናደር ሌላ ዲፕሎማ ያለው ሲሆን አሁን ከሚሰራበት ቦታ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው አቡነ ጳውሎስ ቢመልሱ መልካ ነው ፤ Please Andadirgen, don't be like other bloggers. Tell us what each authorities doing, but stop telling us about personal profile unless you have really a reason for that. Whether he has a degree in academics or from spiritual aspect what matters is he doing his duties properly? If yes, that it great, if not show us why he is not doing his duties properly. We, readers, can take it from there.

    The reason why I am commenting like this is because I am tired of blogs where they only write about the personal profile (he has a diploma,.. he is a graduate of trinity school) bla bla and all is not positively rather disgrace the person. Why is such, can't they including you Andadirgen be straight to the message. Example, if there is corruption, unfair decision, we only want that not his/her education background or personal life (but there are points you may need to mention education background).

    Amilak yirdan hulachininim.

    ReplyDelete
    Replies
    1. I think you stop reading that sentence only the answer is already there:
      አሁን የኛ ትልቁ ችግር የማይገባቸው ሰዎች ቦታን በዘመድም ይሁን በገንዘብ ይቆናጠጡታል ፤ ኋላ የሚመጣውን የቤተክርስትያን ችግር ሲመጣ ደግሞ ቤተክርስትያኒቷን አሳልፈው ይሰጧታል ፤ትክክለኛው ሰው ትክክለኛ ቦታ ላይ ቢቀመጥ ግን ይህን የመሰለ ችግር ለመፍታት መንፈሳዊ ሆነ አስተዳደራዊ ብቃት ስለሚኖረው ችግሮችን ሊጋፈጥ እና መፍትሄ ሊያመጣ የመጀመሪያው ሰው ይሆናል ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው የተገላቢጦሽ ነው ፡፡

      Delete
  6. Yemedia were andem ewnet yelewm,gen Bewnet kirstos ferdun kante entebkalen

    ReplyDelete
  7. ሃይለማርያምMarch 23, 2012 at 1:07 PM

    መልካም ነው! አሁን ስራው መሰራት ያለበት ከራሳችን ቤት በመሆኑ እርሱ ላይ እንረባረብ!!!
    ሁለት ሌባ አንዱ ከውጭ ሌላው ከውስጥ ሆነው ሲቀባበሏት ፈዘን ማየት የለብንም!!

    ReplyDelete
  8. እኛ እንደምናስበው ይህ ቦታ የቤተክርስትያኒቱን አማኞች ለመምራት በመንፈሳዊ ሆነም በአስተዳደራዊ ትምህርቶች ለቦታው የሚመጥን ሰው መሆን አለበት የሚል አስተያየት አለን ፤ አሁን የኛ ትልቁ ችግር የማይገባቸው ሰዎች ቦታን በዘመድም ይሁን በገንዘብ ይቆናጠጡታል
    ትክክል፡ብላችሁዋል፡፡አንድ፡ማወቅ፡ያለብን፡ነገር፡እነኚህ፡ሰዎች፡ገንዘብ፡ለመዝረፍ፡ብቻ፡ሳይሆን፡አውቀው፡ሃይማኖት፡ለማጥፋት፡እንደተሰገሰጉ፡ነው፡፡እነሱንም፡የሚሰገስጓቸው፡በሹመት፡የተቀመጡ፡መናፍቃን፡ተሐድሶ፡ምንም፡እንበላቸው፡የዲያቢሎስን፡ዓላማ፡አራማጆች፡ናቸው፡፡ከቅርብ፡ጊዜ፡ጀምሮ፡በተነሱት፡ችግሮች፡ምክንያት፡መረዳት፡ያለብን፡ቤተ፡ክህነትም፡ቅዱስ፡ሲኖዶስም፡ለቤተ፡ክርስትያኗ፡ግድ፡እንደሌላቸው፡ነው፡፡ግድ፡አለመኖር፡ብቻ፡ሳይሆን፡ብዙዎቹ፡ጥፋቷን፡ሲመኙና፡ለጥፋቷ፡ሲተጉ፡ጥቂቶቹ፡የሚቆረቆሩት፡በፍራቻም፡ይሁን፡በስንፍና፡ጆሮ፡ዳባ፡ልበስ፡ብለው፡ተቀምጠዋል፡፡አሁንም፡ምእመኑ፡ባይኖር፡ከዚህ፡በከፋ፡በተቸገርን፡ነበር፡፡እባካችሁ፡በፀሎት፡እንትጋ፡፡በየገዳማቱ፡በየበረሃው፡በየጫካው፡ያሉትን፡አባቶቻችንን፡እናቶቻችንን፡ይጠብቅልን፡ያጽናልን፡ያበርታልን!!!
    መድሃኔአለም፡በምህረቱ፡ይጎብኘን!!!
    ወላዲተ፡አምላክ፡በምልጃዋ፡ትጠብቀን!

    ReplyDelete
  9. you guys seems to me book smart.

    ReplyDelete
  10. ሰው የፖለቲካ አላማ ለማረመድ ገዳም ምን ሊሰራ ይገባል ?
    ይህን የጠየቅህ ሰው በእውነትም ተላላ ነህ ፡፡ እነሱ እኮ የራሳቸውን ታሪክ እየነገሩህ ነው ፡፡ ደርግን ሲዋጉ ከመደምሰስ የተረፉት በየገዳማቱ ውስጥ ተሸሽገው ነው የሚል ታሪክ አለ /ኢህአፓ ፣ ኢዲዩ ፣ ቲፒኤልኤፍ/፡፡ ምናልባት ያን የታሪክ ትዝታ ተንተርሰው ፣ ሁሉም ተቃዋሚ ወደ ገዳም ሄዶ ገብቷል ብለው አስበው እንዳይሆን ፡፡ ከተማ ውስጥ የረባ ተቀናቃኝ የላቸውማ ፡፡ ታድያ የት ገባ ይበሉህ ?
    እናንተ ይኸን ታወራላችሁ ፣ እኔን ግራ የገባኝ የሰማይ ቁጣ የመጣ ይመስል ይሄ በየቦታው እነደ ወረርሽኝ የተነሳውን የገዳም ቃጠሎ መነሾ ምክንያት ነው ፡፡ ገዳም ስለተቃጠለ ምንኩስናና ክርስትና ይቆማል ብሎ የሚያስብ ሰው አይደለም እንሰሳስ ይኖር ይሆን ?

    እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን እንዲጠበቅ ፣ ገዳማቱን እነዲያድን ጸሎት ያስፈልገናል ፣ ጸሎት ያስፈልገናል

    ReplyDelete
  11. በጣም የገረመን አስተያየት የሸንኮራ ልማቱ ሲካሄድ በሚገደበው 138 ሜትር ግድብ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ የሚል አስተያየት መስጠቱም ጭምር ነው ፤ ቋርፍ የሚባል ገዳሙ የሚጠቀምበት ተክልም ብሎ ዘባርቋል

    ReplyDelete
  12. Abetu amlakachin betin lematifat yetaselafutin eskameche nawu yemititagesawu??? Ahun hulum gilts yewata yimaslagnal patriariku betakirstinuan eyatafuat newu yih endiho eyefakadnilachewu nawu silazih yetarik tewokash keminihu beka yaminilibet seat ahun newu kehagere sibkat jemiro eska worada dires 10 persent gabi bemakalkal cimirm behon genazab binisetachewu makina gezubet vila aserubet betakirstiyanuan lematifat tetakamubet yih hulu sihon zim belanal silezih.....

    ReplyDelete
  13. ሁሌም የኦርቶዶክስ እምነት መጨቆን የበዛበት ለምን ይመስላችዋል ???

    ReplyDelete
    Replies
    1. እውነት ስለሆነች ነዋ!!!

      Delete
    2. tikikilegna, ketitegna ena ewnet yalebat yekedemechiw hayimanot silehonechi

      Delete
  14. ቤተክህነት የቤተክርስቲያን ወይስ የመንግስት?…አልገባኝም!!! እግዚአብሄር ይጠብቀን

    ReplyDelete
  15. የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማሪያም የአደራ ልጆች ቤተክርስቲያናችንን እንዲጠብቅልን ሁላችሁም በፆም በፀሎት እምላካችንን ጠይቁ የቻላችሁትን ተጋድሎም ፈጽሙ እንደእርሱ ፈቃድ እንጂ፣ እግዚአብሔር እኮ ቸርነቱ የማያልቅበት አምላክ መጨረሻቸውን ልየው ምንአልባት ይፀፀቱና ንስሃ ይገቡ ይሆናል ብሎ ስለሚጠብቃቸው ነው፣ እያለ እንደሌለ የቆጠሩት፤፤ አንድ ቀን ግን ይህ ምህረት ወደ ቁጣ የተቀየረ ለት ግን አዎ የነበረውን እንዳልነበረ ማድረግ ያውቅበታል እናም የእግዚአብሔር ቀን እስከሚደርስ ወይም እነሱ እስከሚፀፀቱ ህዝበክርስቲያኑ በቻላችሁት መጠን ማድረግ ያለባችሁን አድርጉ የቤተ ክህነት ሰው ምናምን ማለታችሁን ትታችሁ ሁሉም ክርስቲያን እራሱ በሚችለው መጠን የሚችለውን ያድርግ ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት ለእርሱ ለባለቤቱ ይስጥ ሁሉም በጊዜው ይሆናልና፤፤

    ReplyDelete
  16. minewu abatochs bezmita sefenu?

    ReplyDelete
  17. Ye kiristos lijoch kezih belay min medafer ale? Betekinetunm hone lielochn ersu wagachewun yisetachewal! Be alem lay yal hisbe kiristian bedenb yetegna yimeslegnal, minew zim alu?

    ReplyDelete
  18. ወይ መቃጠል!ተቃጥዬ ማለቄ ነው ምን ይሻለኛል? ምን የማንረባ ፍጥረት ነን ግን? በቃ ቤተክርስቲያኒቱን ነጋደዎች ሲቀራመቷት ዝም ብለን ነው የምናየው? ኧረ ጌታ ሆይ ከምኑ ትውልድ ፈጠርከኝ? ስለ ሰማእታት ማውራት ብቻ ዋጋ ያለው ይመስል የቀደሙት ስለ ክርስቶስ መከራን ተቀበሉ እያልን እንዘባርቅ ሰማእትነት እስከ መቀበል ዋጋ አንክፈልና.....

    ReplyDelete
    Replies
    1. BAY THE NAME OF THE FATHER,THE SON AND THE HOLY SPIRIT ONE GOD AMEN!!!
      WENIDIME Yemitilew hulu gilits new gin simetawinet yitayibetal. Yehe neger eko kebetekihinet jamiro tifat yetazezebet bemehonu enji beteregaga menifes binasibibetina menigisitim libun kefito biyadaniten bekelalu mefetat yichillal. hulachinim lehagerachinina lebetekristiyanachin Eyasebin mehonun mejemeriya biniredada tiru new. beseyif memotachin bichawun min yifeyidilinal? Bizu menigedich alina. gedamu sayneka Yehagerachinim limat sayidenakef betebeber mesiratina fire mafirat enichilalen. Tiliku chigir Alemedemametachinina alemenegagerachin yimesilegnal. menigist Ene Yalikut kalihone bilo Ende derek enchet mehonun akumo Egnam yerasachinin Menigist ende baed menigist sanikotir memekaker yeminichilibetin meniged Binamechach tiru new.
      Wenidime bizih miretihna menesasatih esti kelibih beeniba wede fetariyachi alikis. Getachin eko Ayine sewur behonew sew bedelegnawun kaelin yetebekele new. minim bedelegnoch binihon Esu Yesewun eniba chel ayilimina Litikebelew yefelegikewun semaetinet beeniba tekebel. Hulachinim sanikatel keriten ayidelem gin behasab mekatel bicha sayihon ende HIZIKIYAS hayil endelelen hayilachin esu mehonun bemegilets abetutachinin leamilakachin enakirib. Yan gize yemayiseman kehone yesu fekad yehonewun enekebelalenina Enikilif bematat besigidetina betsom eneleminew.
      Cherinetun Ayarikibin Amen!!!!!

      Delete
  19. Woy shufet enanteye! lemehon Yehayimanot Sew negn bilo bemerinet ketekemete sew Siletsidik sil Ehil kemebilat rasun lekelekele sew Asa Bemebilat yetekemal tebilo yinegeral? Enezih krisitiyan sayihonu besim bich rasachewun kofisew yetekemetu minim yeteleke ewuket yelelachew "BESIM EKUL BEGIBIR SINKUL" Yehonu sewoch Sewun sayafiru Egziabiherin sayakebiru hodachewun lememulat silu betekristiyanin asalifew Eyesetuat new eko. Wegenoche Ebakachihu Kelibachin honen Beeniba wede Feraju Getachin Enechuh. Esu Betun asalifo ayisetatimina Hulachihim Enechuh. "SEYTAN ENDE GELEBA LIYABETIRACHIHU TEYEKE ENE GIN SILE ENANTE MALEDIHU" YALE GETA zarem asalifo ayisetenimina gidelachihum eneleminew. LEGNA AYIDELEM LESIMU SIL SIRAWUN YISERALINA EGNA BICHA ENIMELES ENALIKIS. Senakiremin Yawarede, Nabukedenetsorin kemetabeyu yetenesa wede asamanet yelewetena lenisiha yabeka esu zarem besilitanachew, betorachewuna besigawi kibrachew temekitew menifesawiwun neger chilla bemalet betekrstiyanachinin lematifat berekeke silit yetenesutin hulu esu baweke BBEBELEAM FIT YELAKEWUN MELAK LIKO ENDIGETSITSACHEW BETEKRISTIYANACHINIM KETIFAT ENDITEBIKILIN. tegiten enileminew. hizikiasin yesema zarem ale. Selesitu dekikin yetadege zarem ale. Ethiopiachinin keITALY werari yetadege zarem ale. AYIZON TESFA YEMINADERIGEW AMILAK BEWESENEW KEN HAILUN YANESAL YIGELITAL. BICHA EGNA SEW ENIHUN. AMILAK LIMENACHININ YESIMALIN KEHULUM BELAY SILE SIMU KIBIR SIL FETINO YITADEGEN. AMEN!!!!!!!

    ReplyDelete
  20. ALEMETADEL HONO BETE KIHINETUN YETEKOTATERUT KEMENGISTI YETEBERERU KADIREWOCHI LEMISALE ESKINDIR G/KIRISTOS ,DAWIT OROMO /TADESE/ TESFAYENA YEMESASELUTI NACHEWI PATRIYARIKU YELEBA WEDAJI HUNU MINIYIDEREGI

    ReplyDelete
    Replies
    1. ante maneh ortodocs betekristianachin endih bla atastemrm gn ante ande politics ande hymanot talka tgebelk kemanm belay egziabiher now ketlo mengt ligodan syhon emibegen yawkal. ante ortodocs kehonk tselot adrgeh tegna egziabiher hulu neger yawkal. ante gn ande meles mnamn mnamn

      Delete
  21. ተ ክህነቱ ም/ስራ አስኪያጅ የተባለው አቶ ተስፋዬ እንዴት አድርጎ በዚህ ውሸቱ ቤቱን ሊመራ ይችላል? ሲጀመር አባ ጳውሎስ በቤተ ክህነቱ የቦዘኔና የተሀድሶ ጉሩፕ በማደራጅት ቤተ ክርስቲያኒቱን እንድትውድቅ እያደረጉ ነው
    ለመሆኑ ተስፋዬ በምን መስፈርት ነው እዚህ ሊደርስ የቻለው? መልሱ ሁለት ነው ካድሬ በመሆኑና አባ ጳውሎስ እንደልቡ ለሚቸረችረው የቤተ ክርስቲያኒቱ ቤት ዋና አመቻች በመሆኑ ነው። ሲጀመር የአስተዳደር ልምድ የለው የፋብሪካ ወዘደር ሆኖ ነውቤተ ክህነቱ ማተሚያ ቤት የስራው ትልቁ ልምዱ ደግሞ የአንድ ወረዳ የኢህዲግ ምርጫ ታዛቢ ሆኖ መስራቱ ነው። አቡኑም ይህን ክሬዲት እና አባቶች በተደበደቡ ጊዜ ከአቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስና ከኤልዘቤል ጋር ያደረገውን ተሰትፎ ቆጥረውለት ነው። እባካችሁ ቤተ ክርስቲያኒቱ በዚህ ሰው አመራር ተዋረደችአስተውሉ መናፍቅ ስብከተ ወንጌል መምርያ፤ ጴንጤ መዝገብ ቤት፤ሲገራ አጫሽ ህዝብግኑኝነት መሬት ሸጦ ቤተ ክህነት የተደበቀ ሙስኛ ፕሮቶኮል አቤቱ አድነን

    ReplyDelete
  22. leba hula gezeawe yetebeqe...atalaye

    ReplyDelete
    Replies
    1. what is the use of talking here and there and in every direction why don't we have some time to pray (EGIZIOYTA) even if the top position's religious persons are keeping their silent. Blogs has to be the way of seeking for good (positive) things. Please don't be gossip giver. GOD BLESS ETHIOPIA

      Delete
    2. betam ygermal eko Etiopia kedinetua lemewtat betekirstian mafres alebat? mebeltsegna mekber ende china bemesrat new gin enihin sewoch Amlak aylekachewm yferdibachewal lizegey gin ychilal ayresam

      Delete
  23. በፍርድ ቀን መጽሀፉ እንዲህ ይላል ‹‹እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤›› ማቴዎስ ወንጌል 12 ፤36 እናንተም ስለ ስራችሁ ትጠየቁበታላችሁ ፤ የአምላካችን ቃል አይታበይም ፡፡

    ReplyDelete
  24. Abetu yihen gif temeliket, they take the land from Gondar and they make ethinic federalism and take resources and hurt mama Ethiopia, one day the truth will reveal

    ReplyDelete
  25. oho my God i have seen this Guy(Ato Tsfaye) YETENSAE at Slassie Church, he wear as presit, he can not speak and not talk well, he can not speak properly and we were hurted by his speech as there are may GUYs at addis who can speak and teach the community of the church.

    ReplyDelete