Monday, March 26, 2012

የዋልድባ ገዳም መብት ለማስከበረ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ



(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2004ዓ.ም)፡-26/03/2012 ዓ.ም  በአሜሪካን ሀገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አማኞች  ዋልድባ ገዳም ላይ መንግስት ሊሰራው  ያሰበውን የስኳር ልማት በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል ፡ ሰላማዊ ሰልፉን እንዲሳተፉ ለብዙ ሰንበት ተማሪዎች ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ለአባቶች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት በአባቶች ጸሎት ተጀምሯል ፣ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ 450 ሰዎች የፈረሙበትን የህዝብ ድምጽ አያይዘው አቤቱታቸውን አቅርበዋል ፡ የኢምባሲው ሰራተኛ ነኝ የሚሉ አንድ ሰው ነገ ተመልሰው እንዲመጡ አሳስበዋቸዋል ፣ በፊት በተለያዩ ሲኖዶሶች ሲተዳደሩ የነበሩት ክርስትያኖች ይህ ጉዳይ አንድ ያደርገናል እንጂ ሊለየንም አይችልም በሚል ሀሳብ ተስማምተው በአንድነት ሰላማዊ ሰልፉን በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት አድርገዋል ።  በጊዜውም
ሀይል የእግዚአብሔር ነው
ማዳን የእግዚአብሔር
ጥበብ የእግዚአብሔር
አንመካም በጉልበታችን
እግዚአብሔር ነው የኛ ሀይላችን
እያሉ ሲዘምሩ ተደምጠዋል። እውነት ነው «ሀይል የእግዚአብሔር ነው» እኛ ጉልበት ኖሮን ለውጥ ላናመጣ እንችላለን ፣ ጉልበት ግን የእግዚአብሔር ነው ፡ ኃይል ግን የእግዚአብሔር ነው  ። የእግዚአብሔርን እጅ እንጠብቃለን ፣ ከ420 ዓመት በኋላ እስራኤልን ከባርነት ያወጣ አምላክ እኛንም አይተወንም ፡ አይረሳንም ። እኛን የሚጎነኝበት ለጥያቄያችን መልስ የሚሰጥበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በተስፋ እንጠብቃል ።



(ከአሐቲ ተዋሕዶ):-
የአባቶቻችን ርስት እና ቅርስ ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍየሚል መሪ ቃል ያለው የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካን መንግስት መቀመጫ በሆነችው በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ መጋቢት 172004 / በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር 9am ላይ ተካሄዶዋል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ በቦታው የተገኙ አባቶች በጸሎት አስጀምረዋል:: በሰልፉም ከአንድ ሺህ በላይ ክርስቲያኖች እንደተገኙ በአካባቢው የነበሩ ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉም በአስተዳደር ምክንያት የተለያዩ ወገኖች በአንድነት የቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚፈታተኑን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል:: ለአራት ሰዓታት ያህል የቆየው የአቤቶታው ሰልፍ በተለያዩ መዝሙራት የታጀበ ነበረ:: ተሳታፊዎቹም ጥያቄዎቻቸውን በእንባ እና በጩኸት ለኤምባሲው አሰምተዋል:: 

የጠቅላይ ሚንስተሩ /ቤት ከዋልድባ ገዳም በተወከለቱ የገዳሙ አባቶቻችን ላይ ያሳየውን ንቀት የዋሽንግተን ዲሲው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለአቤቶታ በወጡ ክርስቲያኖች ላይ ንቀቱን ደግሞታል:: አቤቶታ አቅራቢዎች ለሦስት ሰዓታት ተኩል ያህል በኤምባሲው በር ላይ መብታችውን ሲጠይቁ ከኤምባሲው ማንንም ምንም የመንግስት ተወካይ ወጥቶ ሊያናግራቸው አልቻለም ነበር:: በመጨረሻም አንድ ተላላኪ ወጥቶዛሬ ሳይሆን ነገ እናግራችኋለንበማለት አሳፋሪ ምላሽ እንደሰጣቸው ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል:: መንግስት በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ እያደረገ ያለውን ንቀት በዋሽንግተን ዲሲ ባስቀመጣቸው ተወካዮቹ ጭምር ደግሞታል:: ታድያ ንቀቱ እስከ መቼ ድረስ ይሆን? 


ክርስቲያኖች በአላውያን ነገስታት ወይም በእምነት የለሽ ገዢዎቻቸው ጭቆና ሲበዛባቸው በጸሎት አምላካቸውን ከመማጸን በተጨማሪ ድምጻቸውን ለመንግስታት ማሰማት በአሐት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የተለመደ ነው:: የግብጽ፣ የአርመን እና የሶርያ ክርስቲያን ወንድሞቻችን በተለያዩ ጊዜያት በገዢዎቻቸው ጭቆና ሲደርስባቸው ለዓለም መንግስታት እና ለራሳቸውም መንግስታት በአቤቱታ ሰላማዊ ሰልፍ ጩኸታቸውን እንደሚያሰሙ በተለያዩ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ሲዘግቡ እንሰማለን:: በሕገ ክርስትና በኢ-አማኞች ጭቆና ሲደርባችሁ የአቤቱታ ሰላማዊ ሰልፍ አትውጡ የሚል ነገር የለም:: ስለዚህ ክርስቲያኖች የአቤቱታ ሰላማዊ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታችው ተገቢ ነው:: 

አቤቱታን ለዓለም መንግስታት ማቅረብ በአሐት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እንደተለመደው ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን ዘንደም መለመድ አለበት በማለት የሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆቹ በቦታው ለተገኙ ዘጋቢዎቻን ገልጸውላቸዋል:: 


በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያ ከአርባ ዓመት ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት ክርስቲያኖች ሲታረዱ፣አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለወህኒ ወርደው በግፍ ሲገደሉ እንደሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ድምጻቸውን ለዓለም መንግስታት አላሰሙም ነበረ:: ይህ ዛሬ የተካሄደው የአቤቱታ ሰላማዊ ሰልፍ ከእንግዲህ ወዲህ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችዝምታው በቃን ድምጻችን እናሰማለንበማለት የተጀመረ ይመስላል:: ስለዚህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ጨምሮ በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ የተዋሕዶ ልጆች በጥታውያን ገዳማቶቻችን እየደረሰ ያለውን ጥፋት ለማስቆም የአቤቱታ ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ ለማካሄድ የዛሬው አቤቱታ መልካም ጅምር ነው:: በሰላማዊ ሰልፉ የተነሱ ጥያቄዎች እንደሚከተለው ቀርቧል:: 
  • · ክርስቲያኖች ዋልድባን ነጻ ያወጣሉ፣ 
  • · በዋልድባ ጉዳይ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት እንቆማለን፣ 
  • · ጳጳሳት ውሳኔያችሁ ይሰማ፣ 
  • · የአባቶቻችን ርስት ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ፣ 
  • · የገዳማት አባቶቻችን መብት ይጠበቅ፣ 
  • · ዋልድባ ነጻ ትውጣ፣ መንግስት የመነኮሳቱ ድምጽ ይስማ፣ 
  • · ዋልድባ የቅዱሳን እንጂ የኢንቨስተር አይደለችም፣ 
  • · አባቶቻችን ያስቀመጡልን ገዳማት ሲፈርሱ ዝም አንልም፣ 
  • · የቤተ ክርስቲያን መሪ አባቶች ዝምታችሁ ይብቃ፣ 
  • · ገዳማትን የሚያፈርስ መንግስት አንፈልግም፣ 
  • · የስልጣኔ ምንጭ የሆነች ቅድስ ቤተ ክርስቲያን መብቷ ይከበር፣ 
  • · ገዳማት የጸሎት ቦታ እንጂ የመዝናኛ ቦታ አይደሉም፣ 
  • · ክርስቲያኖች የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ 
  • · አድባራትንና ገዳማትን ማጥፋት ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው፣ 
  • · የአባቶቻችን ተረፈ አጽማቸው ይከበር፣ አጽማቸው ቆፍሮ ማውጣት ይቁም 
  • · ልማት ገዳማትን በማፍረስ አይመጣም፣ 
  • · ሃይማኖታችን የማንነታችን መገለጫ ናት ስለዚህ መንግስት ይህንን ያክብር፣ 
  • · ሃይማኖት ከሌለ ሀገር አይኖርም፣ 
  • · ገዳማት የሚያፈርስ መንግስት ተቀባይነት የለውም፣ 
  • · አብያተ ክርስቲያናት ያቃጠሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ 
  • · ቅዱስ ሲኖድ የገዳማትን ይዞታ የማስከበረ ግዴታ አለበት፣ 
  • · ገዳማትን ማጥፋት በታሪክ ያስጠይቃል፣ 
  • · ገዳማቱ እንዲከበሩ እንፈልጋለን፣ 
  • · ገዳማትን የሚያፈርሱ አይከበሩም፣ 
  • · ዋልድባን ለማጥፋት የሚሞክሩ ይጠፋሉ፣ 
  • · ገዳማቶቻችን ታሪካችን ናቸው፣ 
  • · የአብነት ተማሪው ናታንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ 
  • · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሃይማኖታቸው ዝም አይሉም፣ 
  • · መንግስት ሃይማኖታችን ከማጥፋት ይቆጠብ፣ 
  • · አጥፊዎች ለፍርድ ይቅረቡ፣ 

የሚሉ ናቸው:: የጥንታውያን ገዳማት ህልውና ማስጠበቅ የቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ማስጠበቅ ነውና በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ የተዋሕዶ ልጆች በአጠቃላይ የፖለቲካ እና የዘር ልዩነታቸውን ትተው የአንድነት ድምጻቸውን ለሚመለከተው ሁሉ እንዲያሰሙ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች አደራ ብለዋል:: አሐቲ ተዋሕዶ ይህንን የአደራ ቃል ለምእመኑ ሁሉ እንዲዳረስ የበኩሏን ጥረት ታደርጋለች::

እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!! 
ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ

11 comments:

  1. Let the will of God be with our church!

    ReplyDelete
  2. ABETU ALEMAMENACHINEN EREDAW,,,,, YEWALDIBAN NEGERM ADERA !!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሆድን ያቃጥላል፣ሆድን ይበላል !!! ልብን ይሰብራል!!!ያሳዝናል!!!የአይን እምባ ያጎርፋል !!!የቤተ ክርስትያን ልጅ ሁሉ አንድነቱ ልያሳይ ፤ሆ!!! ሆ!!!ሆ!!!እንዲልና እውነተኛ የክርስቶስ አካል መሆኑ የምያሳይበት ፤በጾም፡ በጸሎት የሚተጋበት፡እየሰገደ የምያለቅስበት ፡በመሪዎቻችን አድሮ ቤተ ክሪስቲያን ለማጥፋት የተነሳው ዲያብሎስ የምናሸንፍበት ለኛ የተሰጠ በረከት የያዘ ፈተና ነው። እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ክርስቲያን በዚህ ነገር "የ እግዚአብሔር የተባለ እቃ ሁሉ ለብሶ ከተነሳ " እንደ አባቶቻችን ጸጋ እናገኝበት አለን ።

      Delete
  3. ሃይማኖታችን የማንነታችን መገለጫ ናት ስለዚህ መንግስት ይህንን ያክብር፣
    · ሃይማኖት ከሌለ ሀገር አይኖርም፣
    · ገዳማት የሚያፈርስ መንግስት ተቀባይነት የለውም፣
    · አብያተ ክርስቲያናት ያቃጠሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣
    · ቅዱስ ሲኖድ የገዳማትን ይዞታ የማስከበረ ግዴታ አለበት፣
    · ገዳማትን ማጥፋት በታሪክ ያስጠይቃል፣
    · ገዳማቱ እንዲከበሩ እንፈልጋለን፣
    · ገዳማትን የሚያፈርሱ አይከበሩም፣
    · ዋልድባን ለማጥፋት የሚሞክሩ ይጠፋሉ፣
    · ገዳማቶቻችን ታሪካችን ናቸው፣
    · የአብነት ተማሪው ናታንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣
    · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሃይማኖታቸው ዝም አይሉም፣
    · መንግስት ሃይማኖታችን ከማጥፋት ይቆጠብ፣
    · አጥፊዎች ለፍርድ ይቅረቡ፣

    ReplyDelete
  4. egziabher dimtsachinin yisma

    ReplyDelete
  5. ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም

    ReplyDelete
  6. EGNA BEMIDIR ENICHOHALERNINA GETA HOY KESEMAYAT SIMA YEMADANIHIM SIRA YIGELETS. YEBETIH TELATOCH AMED YIKAMU. WEDAJOCHIHIM BEMADANIH HASET YADIRIGU AMEN!

    ReplyDelete
  7. እኔ እንደሚመስለጘ አሁን ያለዉ የቤተክርስቲያን ችግር ሊያበቃ የሚችለዉ ክርስቲያኖች የራሳችዉን መንግስት ሲያቁዋቁሙ ብች ነዉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ለ20 አመታት ስንፈራ የነበረዉ የመገነጣጠል ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ክርስቲያኖች እኔ መገነጣጠልን ወዽጃለሁ፡፡ እናንትስ???

    ReplyDelete
    Replies
    1. Bete kirestyan yandnet enji yemelyaya bota aydelechimna, serat biniyiz.!!!

      Delete
  8. ene me megentel yemilew neger aygebagnem. yehulacen amlak wub adrgo fetronal enam behibret enenoralen betekrstianachinenm entebkalen

    ReplyDelete
  9. ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም
    ስለ ጽዮን ዝም አልልም

    ReplyDelete