Monday, March 19, 2012

የዝቋላ ጉዳይ



  • ዋልድባ ሲመታዝቋላ አለቀሰ፣
    እኔ አላማረኝም-ይሄ አገር ፈረሰ።
    ዋልድባ ሲታመስ-ዝቋላም ነደደ፣
    እኔ ፈርቻለሁ- ይሄ አገር ታረደ።

    ---------
    ደረጀ ሀብተወልድ
    (11፡14 ሰዓት ):-
    የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ያሰማራው ኀይለ ግብር የተዳፈነው እሳት አሁን ካለበት የባሰ እንዳይዛመት እሳተ ከላ(Fire Break) በግንድ፣ በቅጠሉ መሥራት እንደ ተሻለ አማራጭ ውስዶ እየተረባረበ ነው፡፡ ቃጠሎውን ለመከላከል የሚመጡ ምእመናንም የዝቋላን አቀበት ተቋቁመው ወጥተው በምንጣሮ፣ በቁፋሮ፣ በሸክም ለመራዳት የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡(ደጀ ሰላም)
  • (10፡44 ሰዓት ):- ከደቂቃ በፊት በገዳሙ ከሚገኙት ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ከአደጋ መከላከል የቅድመ አደጋ ዝግጁነት ምክትል ኃላፊ አቶ ታደሰ በቀለ ጋር የእሳት አደጋው እና ተዛማጅ ችግሮች ስላሉበት ሁኔታ ተነጋግረው በአስቸኳይ ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል ለመጨመር ቃል የገቡ ሲሆን በሥፍራው ለሚገኙ ሁሉ ለምግብ የሚሆኑ ብስኩቶች፣ ተምርና የሚጠጣ ውሃ እንደተላከና በተጨማሪም እንደሚላክላቸው ቃል ገብተውላቸዋል፡፡ ሌባና እሳት መነሻው/መግቢያው አይታወቅምና በንቃት በመከታተል ፍጹም መጥፋቱን እስክናረጋግጥ ድረስ መረጃ እናንተው ዘንድ ከማድረስ አንቦዝንም፤(ከቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ)

 ዝቋላ ትላንት እንዲህ ነበር

  • (ትላንት ቦታው ላይ የነበረ ሰው የሰጠው ቃል ) ሰኞ ከቀኑ 1100 ሰዓት አካባቢ ከዝቋላ ገዳም በምስራቅ በኩል በቁጥጥር ስር የዋለው እሳት ከምሽቱ 100 ገደማ አስቸጋሪ ከሆነው የምዕራብ አቅጣጫ ሲነሳ፡፡ በዚህ ወቅት እኛ ካለንበት በግምት ወደ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እሳቱ በመነሳቱና ወደ እሳቱ ለመቅረብ እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ በደኑ መካከል ጋብ የመፍጠር ስራ በህብረት እየሰራን የእሳቱን ታምራዊ ቃጠሎ እያየን ነበር፡፡ እሳቱን ቀርበን ለማጥፋት ባለመቻላችን ከሁሉም ወጣቶች ላይ የብስጭትና የቁጭት ገጽታ ይነበብ ነበር፡፡ የቻሉ ደግሞ በሰልክ የእሳቱን አስቸጋሪነት ሲገልፁ ነበር፡፡ይህ የእሳት ቃጠሎ እሰከ ንጋቱ ድረስ ማንም ወደ አጠገቡ መድረስ ባለመቻሉ ያገኘውን ደን ሁሉ ሲበላ አድሯል፡፡
  • (የአንድ ሰው አስተያየት) የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት የሲናን በረሀ ሀሩር ሙቀት በደመና ጋርዶ ሙቀቱን ወደ ቅዝቃዜ የለወጠ በገዳማችን በዝቋላም እነዲሁ ያድርግልን፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ይራዳን። እሳቱን ለማጥፋት ከእግዚአብሔር ጋር እየታገላችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እግዚአብሔር ይርዳችሁ፣ ያበርታችሁ። የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን እግዚአብሔር ይጠብቀን። ሌላ ምን እንላለን። ባለንበት እያዘንን ነው። ቸር ወሬ ያሰማን።ዝቋላ 
  • (10 ሰዓት ) ከደቂዎች በፊት ቤተክህነት አዳራሽ ኄደን ነበር መግቢያ በሩ ከወትሮ በተለየ መልኩ አራት የአዲስ አበባ ፖሊሶች ከዘወትር የበር ዘቦች ጋር እየጠበቁ መሆኑን ተመለከትን ፤ ፎቶ ለማንሳት ፈልገን ነገር መፈለግ ይሆናል በማለት ትተነዋል ፤ ይሄ ነው የሚባል ነገርም ለመመልከት አልቻልንም ፤ የተሰበሰቡት ወጣቶች ተበትነው ደርሰን ሊሆን ይችላል ፤ ከሰዓት ተጨማሪ አውቶቡሶች ወደ ቦታው አምርተዋል ፤ 
  • §   (8፡55ሰዓት ) የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ ቃጠሎው ከተነሣ ከአራት ቀናት በኋላ ዛሬ ወደ ዝቋላ እንዲሄዱ ታዘዋል፡፡(ጅብ ከሄደ ውሻ…..)
(8፡50ሰዓት )...(Dejeselam)
  1. የዝቋላን ገዳም ቃጠሎ ለመከላከል የተሰማሩ ወጣቶች በጠቅላይ ቤተ ክህነት ናቸው - ተቃውሟቸውን ለመግለጽ፣ ጥያቄያቸውንም ለማቅረብ፡፡ ፖሊስ ወጣቶቹ እንዲበተኑ እያዘዘ ነው፡፡
  2. §  ቃጠሎውን ጨርሶ ለማጥፋት የግል አውሮፕላን ከአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት በኪራይ ተገኝቷል ተብሏል፤ ውድ የሆነውና በመንግሥት ዘንድ ብቻ የሚገኘው ኬሚካል ግን ቸግሯል፡፡
  3. §  በየቦታው የተከማቸው የቃጠሎ ፍሕም በጣም ብዙ ነው፤ በተደጋጋሚ ቃጠሎ የመቀስቀስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

  • (8፡20ሰዓት ) እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምናእሳቱን የማጥፋት ሥራ ስኬታማ ሆኗል፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ገዳማውያኑና ምዕመናኑ በገዳሙ ውስጥ ቅዳሴ ሰዓት ላይ ይገኛሉ፡፡ በቦታው እሳት በማጥፋት ላይ ያሉ ምዕመናንም በታላቅ ደስታና ተቆርቋሪነት በየጫካው እየተዘዋወሩ እሳቱን እንዳያዳግም ለማጥፋት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ እምነት ያለ ምግባር ከንቱ ነው እና ዛሬም ወደፊትም ክርስትናችንን በምግባር መግለጥ አለብን፡፡ አሁንም እስከመጨረሻው እሳቱ ይጠፋ ዘንድ በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቅ፡፡ አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡
  • (8፡20ሰዓት ) የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ወደ አካባቢው አንድ የልዑካን ቡድን አሠማርቶ እገዛ እያደረገ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ኮሚሽኑ ጉዳዩን በንቃት እየተከታተለው ሲሆን በአካባቢው ለሚገኙ ሰዎች አስፈላጊ የሆነውን ርዳታ ለማድረግም ወደ አካባቢውተነቃንቋል፡፡ የአየር ኃይል አባላት ገዳሙን ከሚደርሰው አደጋ ለመጠበቅ በተራራው ላይ በንቃት እየጠበቁ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
  • (7፡08ሰዓት ) በክፍለ ሀገር የሚገኙ ምእመኖች ይህ መረጃ እንደደረሳቸው  የቻሉትን ያህል ገንዘብ  እየሰበሰቡ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡(የተሰበሰበውን የብር መጠን በኋላ ቆይተን እንገልጻለን)
  • (6፡05 ሰዓት )ከደቂቃዎች በፊት መስቀል አደባባይ ተገኝቼ ነበር ፤ ቦታው ላይ ያሉትን አስተባባሪዎችን ማግኝት ችዬ ነበር ፤ በደረስኩበት ሰዓት 5 ትላልቅ አውቶቦሶች እሳቱን ለማጥፋት ፍቃደኛ የሆነ ሰዎችን ይዘው መሄዳቸውን ለማወቅ ችያለሁ ፤ ጥቂት ሰዎችም የግል መኪናቸውን ይዘው በመገኝት በቤት መኪና ጉዞ ወደ ዝቋላ ሊያደርጉ ሲሉ አግኝቻቸዋለሁ ፤ እንደነገሩኝ መረጃ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሁለት ትልልቅ መኪኖች ለመሄድ ተዘጋጅተዋል ፤ መሄድ የምትችሉ በቦታው ብትገኙ የማትችሉ ደግሞ ጄሪካን ፤ ዳቦ ያልያ መግዥ ብር ብታደርሱላቸው መልካም ነው ፡፡(የሚቀጥለውን ስልክ ተጠቀሙ 0911-015623 (ወጣት ያሬድ) እና 0911-752970(ቴዲ) ብላችሁ ማግኝት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፤ 0912163180(የሰብሳቢው ስልክ)
  •  (6፡05 ሰዓት)   ‹‹ቅዱሳን አምባ›› በመባል በሚታወቀው ‹‹አጣብቂኙ ድንጋይ›› በስተጀርባ የሚገኘው በገደሉ ላይ የሚገኘውን እሳት ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ ሲሆን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለመከላከል የሚያስችል ተስፋ እንዳለ አባ ጥላሁን ከገዳሙ አስረድተውናል፡፡
  • (6፡05 ሰዓት)  በዝቋላ አከባቢ ተነስቶ የነበረው እሳተ ሰደድ በቅጥጥር ስር ውሏል ሲል ፋና 93.1 300 ሰዓቱ ዜና ገለጸ፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆን እሳቱን ለማጥፋት ወደ ሥፍራው ያቀኑት ምዕመናንና እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ትክክለኛውን መረጃ ወደ ሥፍራው ካቀኑት ሕዝበ ክርስቲያን እንጠብቃለን፡፡ (እንደ እኛ መረጃ ገና ነው፤ ይህን የሚያስብል ሰዓት ላይ አልተደረሰም)
  • +++“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ ቢኖር የአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ሀሳብ ነው”+++ ፪ቆሮ.፲፩፡፳፷
  • (6፡05  ሰዓት )  አየር ሃይል ሄሊኮፕተር እንዲሰጥ መጀመርያ የኦሮምያ ክልል ጽ/ቤት መፍቀድ ስላለበት ይህን ማድረግ ማስፈቀድ የምትችሉ ወገኖች ትብብራችሁን በእግዚአብሔር ስም ትጠየቃላችሁ፡፡
  • የእርዳታ ጥሪ!!!
    የዝቋላ ገዳምን መርዳት የምትፈልጉ ሁሉ የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
    ኅብረት ባንክ ቁጥር= 930
    ንግድ ባንክ ቁጥር= 90432
    አዋሽ ባንክ, ቁጥር= 0130366595700 (ደጆችስ አይዘጉ) ብላች መላክ ትችላላችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!! 

  • (5:50  ሰዓት ) ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጉዳዩን የሚመለከት አንድ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ የኮሚቴው አባላት ወደ ዝቋላ ገዳም ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ አካላት እንደገለጹት እሳቱ ገደል ውስጥ በመግባቱ በሰው ኃይል ፈጽሞ ለማቆም አይቻልም፡፡ አሁን ብቸኛው አማራጭ በሄሊኮፕተር በኬሚካል ማጥፋት ነው፡፡ የኬሚካል ርጭቱ ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቅ በመሆኑ የሁላችንንም ርብርብ ሳይፈልግ አይቀርም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአየር ላይ እሳትን ለማጥፋት የሚያስችለው መሣርያ እንደሌለ የሚናገሩ ወገኖችም አሉ፡፡አሁን በዚህ ሰዓት በገዳሙ ሆነው እሳቱን እየተከላከሉ ለሚገኙ ወገኖች የምግብ ርዳታ ለማድረግ ምእመናን እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች በዚያ ቦታ ላይ ለአራተኛ ቀን ያለምግብ እና ዕንቅልፍ በመጋደል ላይ ናቸው፡፡http://www.danielkibret.com/2012/03/blog-post_9833.html?spref=fb

  • (4:00  ሰዓት ) አሁን በደረሰን መረጃ እሳቱን ለማጥፋት ዛሬ ከሰዓት መሄድ የምትፈልጉ ምእመናን ጄሪካን ፤ እና የሚቀመስ ነገር(ዳቦ) በመያዝ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ መስቀል አደባባይ መገኝት የምትችሉ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ (አቅም ያለው በጉልበቱ ፤ ገንዘብ ያለው እሳቱን ለማጥፋት አስፈላጊ ናቸው የተባሉትን ነገሮች በማሟላት ፤ በጊዜው መገኝት ያልቻላችሁ በጸሎት አስቡን የሚል መልእክት ተላልፏል) 



(አንድ አድርገን መጋቢት 11 ፤ 2004ዓ.ም )፡- (2:00 ሰዓት)ከመንግስት ከፍተኛ እርዳታ እስካላገኝን ድረስ ገዳሙ ነበር የምንልበት ጊዜ እየተቃረበ ያለ ይመስለናል ፤ መንግስት ጉዳዬ ብሎ በአውሮፕላን የማጥፋት ዘመቻ እስካላካሄደ ድረስ በሰው ሀይል ከቦታው መልከ ምድራዊ አቀማመጥ አኳያ እሳቱን የማጥፋት ሂደቱን አዳጋች አድርጎታል ፤ እሳቱ ከአቅምም በላይ ሆኗል ፤ እሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖች መኖራቸው ግድ እየሆነ መጥቷል፡፡ 
በአሁኑ ሰአት  ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር  ጉዞ ወደ ዝቋላ አቦ አስፈላጊውን መሳሪያ  ይዞ ዛሬ ከሰአት በኋላ ጉዛን ማድረግ ይጀምራል፡፡በጉዞውም መሳተፍ የምትፈልጉ የጉዞውን አስተባባሪ አቶ አሻግር በስልክ ቁጥር 0912163180 ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ አውሮፕላን እንዴት ተከራይተን ማጥፋት እንደምንችል መረጃ ያላችሁ ሰዎች  0912163180 ደውላችሁ መረጃ ስጡን ፤ ስለ ኪራዩ አታስቡ መረጃውን ብቻ ስጡን፡

    • የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ኦርቶዶክስ ተማሪዎች ሰደደ እሳቱን ለማጥፋት ለመሄድ ቢወስኑም በመኪና እጦት መሄድ አልቻልንም የጭነት መኪና ተልኮ ትራፊክ መጫን እንደማይችል በማስገደዱ መኪናው ባዶዉን ተመልሷኣል፡ እባካችሁ መኪና ሊልክልን ወይም ሊተባበር የፈለገ ይንገረን መላው የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ኦርቶዶክስ ተማሪ ለመሄድ ዝግጁ ነው ዝቌላን እንታደግ እባካችሁ መኪና ያላችሁ በመኪና ሌሎቻችን ደሞ በጸሎት እንትጋ ፡
    ·        ከተለያዩ ከተሞች ወደ ገዳሙ የዘለቁት ምእመናን ሌሊት እና ቀን ያለ ዕረፍት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ምግብ እና ውኃ በማቅረብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በጸሎት እንድናግዛቸው ጥሪ ቀርቧል፡፡

    ·        አደጋው  አልፎ አልፎ የመቀነስ ከዚያም የመባስ ሁኔታ ይታይበታል፡፡ እሳቱ ግን ገና ፈጽሞ አልጠፋም፡፡ እናም ይበልጥ ተረባርበን ችግሩን እንዳይመለስ አድርገን መፍታት አለብን፡፡ እያንዳንዷ ሰዓት የራስዋ ዋጋ አላትና፡፡

    ·        ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየተቃጠለ የሚገኘው የዝቋላ ገዳም በቁጥጥ ስር እንደዋለ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን( ሚድያ) ማምሻውን ገልጾዋል(ኢቲቪን ያመነ ጉም የዘገነ ነው ነገሩ፤ ምዕመኑ እንዳይረባረብ የሚያደርግ የውሸት ዘገባ ነው) :: ከጉዳዩ ባለቤት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ግን ምንም የተባለ ነገር የለም:: ያው እንደሚታወቀው ጠቅላይ ቤተ ክህነት አለቆቻቸው የመንግስት ባለ ስልጣናት እስኪተነፍሱ ድረስ እየጠበቁ ናቸው::

    ·        ይህንን ጽሑፍ ስጽፍ እሳቱ ከተከላካዮች ዐቅም በላይ ሆኖ ወደ ገዳሙ በመዝለቅ ላይ ይገኛል፡፡ እሳቱ ገዳሙን ከወደ ሐይቁ በኩል እያጠቃው ነው፡፡ ከአዲስ አበባ እና ከደብረ ዘይት ተጉዘው በመከላከል ላይ የተሠማሩት ወገኖች ከዐቅማቸው በላይ እየሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ካልረዳን ከሰዓታት በኋላ ታላቁን ገዳም እናጣዋለን የሚል ፍራቻም አለ፡፡

    ·        ውኃውን ከወንበር ማርያም ወደ ተራራው ለማውጣት መንግሥት የኡራል መኪኖችን እንዲተባበር የገዳሙ አበ ምኔት እየጠየቁ ነው፡፡ በስልክ ያገኘሁት እና በመከላከል ተግባሩ ላይ የተሠማራው ወንድም «አሁን ልንሸነፍ ነው፤ ታላቁንም ገዳም ልናጣው ነው፣ እሳቱ ፊት ለፊቴ እየመጣ ነው፡፡ እኛ መሸሽ እንችላለን፣ ገዳሙን ግን ምን እናደርገዋለን» ብሎኛል፡፡

    ·        ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትዋህዶ ገዳማት ይገደናል የምትሉ ሁሉ የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም (ዝቋላ) በተመለከተ ቤተክህነት ሄደን አባቶቻችንን እንጠይቅ ዛሬ ምክንያቱም ከቦታው ካሉት የአይን እማኞች ባገኘነው መርጃ መሰረት እሳቱ ትልቁ ደን (ፀበሉ) ጋር ሊድርስ የሰዓታት እድሜ ነው ያለው ስለዚህ አባቶቻችን መፍትሄ እንጠይቅ፡፡
    • ትናንትና ማታ አካባቢ ከ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ትንሽ ጋብ ያለ መስሎ የነበረ ቢሆንም ከለሊቱ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ግን እንደገና በከፍተኛ ሁኔታ በመቀስቀሱ ደወል በመደወል እንደገና ህዝቡ እንዲሰበሰብ በማድረግ ለሊቱን ሙሉ ለማጥፋት ጥረት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም በተለይ አሁን ወደ ጠዋት ላይ ጠፍቶባቸዋል በተባሉ ቦታዎች ሳይቀር ሳይታሰብ እሳቱ ተቀስቅሶ እየተስፋፋ ነው፡፡ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ከተለያዩ ቦታዎች ወደቦታው ቁጥራቸው የበዛ ምዕመናን እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡ ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ በያለንበት በመሆን ልንጸልይ እግዚአብሔርን ልንጠይቅ ያስፈልጋል፡፡ 
    • አሁን አማራጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ የዝቋላን ገዳም ከማጣታችን በፊት ያለንን ነገር ሁሉ ይዘን በተገኘው ትራንስፖርት ወደ ዝቋላ መትመም ብቻ፡፡ ወንበር ማርያም ድረስ የውኃ ቦቴዎቹ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ባገኘነው ዕቃ ሁሉ ውኃውን ይዘን በመውጣት መረባረብ፡፡ ያለበለዚያ ግን የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ ታሪክነት ይቀየራል፡፡ እነሆ ክርስትናችን የሚፈተንበት፣ ኢትዮጵያዊነታችንም የሚለካበት ጊዜ መጣ፣ በእሳት ተቃጥለው ያቆዩትን ገዳም ከእሳት ማዳን ካልቻልን እንግዲህ የኛ መኖር ትርጉሙ ምንድን ነው? መኪኖች ያሏችሁ አንቀሳቅሱ፣ ጉልበት ያላችሁ ተንቀሳቀሱ፣ ሌላም አማራጭ ያላችሁ በፍጥነት ተጓዙ፣እሳቱን በእምነት እንቅደመው፡፡(Deakon Daniel Kibret)
    ትላንት በደጀ ሰላም 
    ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 10/2004 .ም፤ ማርች 19/2012)እሳቱ በአንድ አካባቢ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ በሌላ ሥፍራ ድንገት እየተቀሰቀሰ የመከላከሉን ጥረት አድካሚና ግራ አጋቢ አድርጎታል፡፡

    "በምዕራብ ስናጠፋው በምሥራቅ እየዞረ፣ በምሥራቅ ስናጠፋው በምዕራብ እየዞረ፣ በተለይም ዐርብ ረቡዕ በሚባለው የተራራው ገጽ በኩል፣ ጠበል ሜዳ (ጠበሉ የሚገኝበትን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ) እየከበበ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከገዳሙ በማእከላዊ ግምት 300 - 400 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡"
    • በእሳት አጥፊ አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር በሚረጭ ኬሚካል ካልሆነ በቀር ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ባፈር በቅጠሉ በሚደረገው የነፍስ ወከፍ መከላከል ጥረት ጨርሶ ሊጠፋ ወይም መጥፋቱ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ 
    • እሳቱ ጠበሉ ወደሚገኝበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ከገባ ገዳሙ የነበር ታሪክ ይሆናል፡፡
    •  የተወሰኑ የአየር ኀይል እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምእመናኑና ገዳማውያኑ ከሚያደርጉት ውጭ የተለየ መከላከል ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡
    •  ዛሬ ቀን ላይ በሦስት መኪኖች ከአዲስ አበባ ተጉዘው ከስፍራው በመድረስ በተለይም እሳቱ አስቀድሞ በተነሣበት ምሥራቃዊ አቅጣጫ (አዱላላ) ጥረት ሲያደርጉ ያመሹት ቁጥራቸው እስከ 300 የሚገምቱ በበጎ ፈቃድ የተሰበሰቡ የሰንበት /ቤት፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና በተለይም የአውቶቡስ ተራ አካባቢ ወጣቶች ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ ወጣቶቹ፣ "ቃጠሎው በአንድ ቦታ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ ባልታሰበ ሌላ አቅጣጫ ድንገት የመቀስቀስ ግራ አጋቢ እና ተኣምራዊ ጠባይዕ ያለው ነው፤" ብለዋል፡፡
    • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ /ቤት ለመንግሥት ደብዳቤ መጻፉ ተሰምቷል፡፡ ደብዳቤው ቃጠሎውን ለመከላከል መንግሥት እገዛ እንዲያደርግና መንሥኤው እንዲጠና የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡
    • የውኃ እጥረት እና የተራራው አቀበትነት ትግሉን አስቸጋሪ አድርጎታል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥንታውያን ገዳሞቻችን ህልውና እና ክብር ላይ እየተጋረጠ በሚገኘው አደጋ በቂ ወይም ምንም ጥረት እንዳላደረጉ እየተወቀሱ የሚገኙት ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ነገ፣ መጋቢት 11 ቀን 2004 .ም፣ በይፋ እንደሚፈጸም በሚጠበቀው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117 ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሲኖዳ የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት ዛሬ ማምሻውን ወደ ግብጽ እንደሚጓዙ ተዘግቧል፡፡ ከፓትርያርኩ ጋራ አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሌሎች ሁለት የፓትርያርኩ ፕሮቶኮል ሰዎች አብረዋቸው ይጓዛሉ፡፡
    ቸር ወሬ ያሰማን
    አሜን

    15 comments:

    1. ere mihila eniyaz?aleqoch zim bilu hizbu ena deg kahinat mihila meyaz aychilim ende???

      ReplyDelete
    2. Ohh almlahe kidusan ejihin zergalin. minim ayisanihimina bemihiret eyenh temelket.

      ReplyDelete
    3. Abyssinia Flight service 0116620622

      ReplyDelete
    4. ebakachehu abune zebesemayat belen beyalenebet endgem amlakachen bemehretu endyaseben !

      ReplyDelete
    5. amlake ytadegen beyalenebet abune zebesemayat endgem ebakachehu

      ReplyDelete
    6. 0116620622-24 Fax no.0116620620

      ReplyDelete
      Replies
      1. Hello there, what do you want us to do with this number

        Delete
    7. WOOOOW......andandirgen...you are very best.....you are our BBC AND CNN for our orthodox tewahdo lijoche..Bertu......Dengel k enante gar tehun......

      ReplyDelete
    8. Thanks Andadirgen, Amilak yirdan. Silly comment, on the top of the page it says Monday, March 19, 2012. I think it should be Tuesday March 20, 2012, date in Ethiopia, right? Can you correct that.

      ReplyDelete
    9. አንድ አድርገን እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ለምእመናን ወቅታዊ የሆነ መረጃ በማድረስና በመቀስቀስ እየሰራችሁት ያለው ስራ ይበል የሚያሰኝ ነውና በርቱ። የእምትችሉ ከቦታው በመሄድ አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን እያገኙት ከላው በረከት እንድትሳተፉ፣ ያልቻልን ደግሞ በጸሎት እናስባቸው። የቅዱሳን አባቶቻችን አባት እግዚአብሄር ይርዳን። ቸር ወሬ ያሰማን።

      ReplyDelete
    10. You have mentioned statement by ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ: Is the whole paragraph his message or only the last message. Please make it clear.

      GOD thank you for giving us a bit of relief.

      ReplyDelete
      Replies
      1. እንደምን አላችሁ አንድ አድርገኖች እኔ ግራ እያጋባኝ ያልው የዋልድባን መሰረታዊ ጉዳይ አሰቦትን በማቃጠል ለመሸፋፈን መሞከር አሳዛኝ አሳፋሪ እና አሳፋሪም ጭምር ነው ይህንን እናንተም ይህን መገንዘብ ይጠበቅባችሁዋል ፡፡ ስለዚህ ወቅታዊ መረጃ፣ እኛም ማድረግ ያለብንን ነገሮች፣ እስከመስዋዕትነት ድረስ መረጃዎችን ልታካፍሉን ይገባል አለበልዛ ሰው የሰውኛውን ሳይሰራ ሁሉንም ለመድሃኔዓለም ማሳለፍ አግባብ አደለም እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ፡፡

        Delete
    11. በተለያዩ ሁኔታ በፖሊሶች በጥይት የተመቱ ሰዎች እንዳሉ በቦታው የነበሩ ሰዎች ሲገልፁ የተለያየ የተቀረፁ ነገሮች እንዳይወጡ እየተመቱና እየተፈተሹ ይገኛሉ፡፡ እባካችሁ አሁን እንኳን ፖለቲካውን እንተወውና ሀገርንና ነፍስን እናድን፡፡ ሌላውን ጥያቄ ወደፊት እንደርስባታለን፡፡

      ReplyDelete
    12. Yasazinal yehagerachin, yebetekrstiyanachin ... Gudayi !!! Esat enatifa balu bepolice betiyit medebdeb !!! Betam yasazinal. Lemanignawum esat liyatefu kehedut temariwochi huletu bepolice tiyit temetewal :: eninika kezih belay....?!

      ReplyDelete
    13. Egziabher hoy ende sewoch sira sayhon ende mihiretih yihinen ESAT kemidre ZIQUALA GEDAM atfalin ETHIOPIAn bemihret aynochih ena bekal kidaneh tebkiln .......AMEN

      ReplyDelete