Tuesday, March 27, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ ስብሰባ ጠራ

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 19/2004 .ም፤)· ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት /ቤት፣ ከዋልድባ ገዳም ተወክለዋል የተባሉ መነኰሳት፣ ከጎንደር ከተማ የተመረጡ ምእመናንና በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት ነገ፣ መጋቢት 19 ቀን 2004 .ም፣ የመንግሥት ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ስለ ደቀነው ስጋት፣ በተጨባጭም ስለታየው መጋፋት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ስብሰባውን የጠራውን ብአዴን/ኢሕአዴግ ሲሆን የሚካሄደውም በጎንደር ከተማ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በስብሰባው ላይ የፕሮጀክቱ ስፍራ ድረስ በመሄድ የግድቡን ግንባታ ከሚያካሂደው ተቋራጭ (ሱር ኮንስትራክሽን) ባለሞያና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋራ የቀጥታ ውይይት አካሂደዋል የተባሉ ግለሰቦች በስብሰባው ላይ ሪፖርት ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ እኒህ ግለሰቦች ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን ዘገባ ላይ የግድቡ ግንባታ፣ የሸንኮራ ልማቱንና ስኳር ፋብሪካው ከገዳሙ ክልል ጋራ ግንኙነት እንደሌለው፣ ይልቁንም ልማቱ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሆኑ እንደሚደግፉት ሲገልጹ የተሰሙት ናቸው፡፡

የዜናው ምንጮች እንደሚገልጹት በኢ.ቴቪ ዜና ዘገባ ላይ ቀርበው እንዲህ ዐይነቱን አስተያየት የሰጡት ወገኖች ተጨማሪ ሹመት ሽልማት የሚፈልጉ፣ ሁሉንም የገዳሙን ማኅበር አባላት የማይወክሉ፣ ለድርጅቱ እንደ ካድሬ ሆነው የሚያገለግሉ በመሆኑ ሪፖርታቸው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል፡-
  • የሰሜን ጎንደር /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳመ ዋልድባ ችግር ከተሰማበት ዕለት አንሥቶ ጸሎተ እንዲያዝ ዐውጀው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ይኹንና ‹‹እንዴት ጸሎት ያውጃሉ፤ ዐመፅ ለመቀስቀስ ነው ወይ?›› በሚል በአንድ የዞኑ ባለሥልጣን በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ጸሎት እንዳላውጅ ማን ይከለክለኛል?›› ብለው መልሰዋል፡፡ የዞኑ ሓላፊም ማንኛውም ሰው ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ሄዶ ግድቡ ለገዳሙ ጉዳት እንደሌለው ማረጋገጥ እንደሚችል በገለጸው መሠረት ሰዎች ተመርጠው ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ለመሄድ ሲዘጋጁ ግን እንዳይሄዱ ተከልክለዋል፡፡
  • በምትኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን በጎን ተልከው ባወጡት መግለጫ ምእመኑ ክፉኛ ማዘኑ ተመልክቷል፡፡ የግድቡ ውኃ የሚሸፍናቸው በገዳሙ ክልል የሚገኙ አራት አብያተ ክርስቲያን እንደሚፈርሱ ግልጽ ሆኖ እያለ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መግለጫና በኢ.ቴቪ ዘገባ የገዳሙ ድንበር እንዳልተደፈረ የተላለፈው ዘገባ ከእውነቱ የራቀ መሆኑም ተገልጧል፡፡ ይኸው ዘገባ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የገዳሙን ህልውና እና ክብር ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ቢያሳርፍም ‹‹የኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀብት የሆነው ገዳመ ዋልድባ ዕድል በቀላጤ/ቅጥረኛ ሓላፊዎች መግለጫ ሊወሰን አይችልም፤›› ተብሏል፡፡
  • አባ ነፃ በተባለው የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር የፈለሰበትና፣ የሙዝ ቋርፍ የሚዘጋጅበት የገዳሙ የአትክልት ቦታ የታረሰ በመሆኑ ‹‹ለቋርፍ ተለዋጭ መሬትና በጠፋውም የቋርፍ ተክል ምትክ በስድስት ወር የሚደርስ የሙዝ ዘር እንሰጣችኋለን፤›› ቢባልም ማኅበረ መነኰሳቱ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተዘግቧል፡፡ የሙታን ዐፅም ከተቀበረበት መፍለሱን ያመኑት የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ‹‹የፈለሰው ግን የቅዱሳን ዐፅም አይደለም›› ለማለት መሞከራቸው ባልተጣቸው ሥልጣን መግባታቸውን ያሳያል፡፡
  • · ከአራቱ የገዳሙ አብያተ ክርስቲያን መነሣት ውጭ የቀሪዎቹ 14 የገጠር አብያተ ክርስቲያን መነሣት በተመለከተ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በጎንደር ከተማ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋራ በተፈጠረ አለመግባባት ሙስሊሞቹ ከቦታው ሲነሡ መስጊዱ ግን እስከ አሁን ተጠብቆ የቆየበት ሁኔታ በምሳሌነት ቀርቧል፡፡ ከዚህ አኳያ ሕዝቡ ሲነሣ ማኅበራዊ ተቋሞቹ አብረው ይነሣሉ በሚል 14 አብያተ ክርስቲያን እንደሚፈርሱ መገለጹ ፍትሐዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም፡፡
ይህ በዝምታ ከታለፈ ነገ በከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያን ሳይቀሩ በስመ ልማት ይፍረሱ የማይባልበት ጊዜ ሩቅ ባለመሆኑ መንግሥት የክርስቲያኑን ጩኸትና አቤቱታ አድምጦ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ ጸንቶ መታገል እንደሚያስፈልግ የዜናው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል በዓዲ አርቃይ፣ በማይ ፀብሪ እና በሽሬ ተመሳሳይ ውይይት ስለመካሄዱ በመንግሥት ባለሥልጣናትና ብዙኀን መገናኛዎች መገለጹ ይታወሳል፡፡
አሜን፡፡

11 comments:

  1. የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳመ ዋልድባ ችግር ከተሰማበት ዕለት አንሥቶ ጸሎተ እንዲያዝ ዐውጀው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ይኹንና ‹‹እንዴት ጸሎት ያውጃሉ፤ ዐመፅ ለመቀስቀስ ነው ወይ?›› በሚል በአንድ የዞኑ ባለሥልጣን በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ጸሎት እንዳላውጅ ማን ይከለክለኛል?›› ብለው መልሰዋል፡፡ የዞኑ ሓላፊም ማንኛውም ሰው ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ሄዶ ግድቡ ለገዳሙ ጉዳት እንደሌለው ማረጋገጥ እንደሚችል በገለጸው መሠረት ሰዎች ተመርጠው ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ለመሄድ ሲዘጋጁ ግን እንዳይሄዱ ተከልክለዋል፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Haile Michael zemerahe berhanatMarch 28, 2012 at 12:05 AM

      እንደ እኔ እምነት በተለያየ ሚዲያ አውርተን ወዲያው ዝም ማለታችንና ተገቢውን ጥያቄ በተገቢ መልክ ለመጠየቅ አለመንቀሳቀሳችን ለመንግ ሥትና ለአጽራረ ቤተክርስቲያን የልብ ልብ እንድሰማቸው ያደረገ ይመስለኛል:: እንዲህ አውርተን ፈሪዎች መሆናችንን ከሚናስመሰክር ዝም ብንል ይሻላል ::ምክንያቱም ዝም ብንል ቢያንስ ከሰሙ ………….. እየተባለ እንዲህ በንቀትና በግልጽ በድፍረትም በቤተክርስቲያን አይዘበትም ነበረ::ከተነጋገርን ከሰማን ካየን ወደ መፍትሔ እንሂድ ወይ አናውራ ዝም እንበል::አሁን የቤቱ ግድግዳው ተበልቶ አልቆአል ::የቀረው እያንዳንዳችንን ማተብ በጥስ ሃይማኖት ለውጥ የሚል አዋጅ የጣሪያው መቃጠል ነው፡፡በ

      ስለዚህ ብንዘገይም የባሰ ሳይመጣ አሁን ወደ መፍትሔ እንሂድ:-

      1) አባቶቻችን ካህናት ይህን ሁሉ ጥፋት ላያዉቁ ይችላሉ፡ ቢያዉቁም አቡነ ጳውሎስና መንግሥት እጅና ጉዋንት ስለሆኑ (ለመንግሥት ህልውና ቅድሚያ ስለሚሰጡ) ካህናቱም በብዛት ቤተሰብአቸውን የሚመሩት ከቤተክርሰቲያን ከሚያገኙት ገቢ ስለሆነ ከፊት መሆን ልከብዳቸው ይችላል::

      2) ስለዚህ በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት በአባልነት ያለን በተላይም ዲያቆናት እንቀሳቀስ ::

      3) እስካሁን ያዩትና የሰሙት ከበቂ በላይ ቢሆንም መረጃ ለመእመናን በማዳረስ ረገድ በርትተን እንሥራ: ይህንንም መረጃ በቀላሉ ልዳረስ በሚችልባቸው አከባቢዎች በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች በኮልጆች በቴክኒክና ሙያ ተቁዋማት እናተኩር ::

      ነገሩ ወደ ውጤት ከመምጣቱ በፊት ለማስፈራራት እንዳይጠቀሙት ጥያቄያችንን በአንድነት እስከምናቀርብበት ቀን ድረስ በጥንቃቄ እንሥራ ይህንንም እስካሁን በቤተክርስቲያን ላይ በመንግሥት በአጽራረ ቤተክርስቲያን የደረሱ ግፎችን በመረጃ በማጠናከርና በመላክ የሰሙትም እንዲሰሙና የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅነት ግድታቸውን እንድወጡ በማሳሰብ በfacebook እናስታውቅ በemail እንላክ::

      በቤተከርስቲያን ላይ እስካሁን የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የጥፋት ሤራ በመረጃና በዝርዝረ በማስቀመጥ መፍትሔ በፍጥነት እንድሰጥባቸው ቢያንስ ፈርማ ለማሰባሰብ እንቀሳቀስ፡፡ይሀንንም በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት እንጀምር፡፡ ምክንያቱም የሰበካ ጉባኤ አባል ያልሆነ ቤተሰብ የለምና፡፡ የሰበካ ጉባኤ አመራር አባላትም ከምእመናን ከሰንበት ትምህርት ቤት ከካህናት የተወጣጡ ናቸውና ፡፡

      ይህን ስንል ፖለቲካ የሚመስላቸው ልኖሩ ይችላሉ: በእርግጥ በፖለቲካው ዐይን ካዩ ፖለቲካ ልሆንባቸውም ይችላል::

      እሱማ ዐራት ኪሎ ጠቅላይ ቤተክህነት ለተለያየ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ትንሽ ብዛት ያለው ሰው ከተገኘ ሁሉ ለመንግሥት ፖለቲካ መምሰል ከጀመረ ቆይቶአል::

      “.....

      ታስታ

      ውቅ ከደረቱዋ ትታጠቅ’” እንዲሉ :: እዉነት ፍትሕ ካለ ይህን ያህል ምን አስፈረው: መንግሥትን!?

      መንግሥት መጣብን እነጂ እኛ አልሄድንበት::

      ከጸሎት ባሻገር ሰማዕትነትን

      እነደ አግባቡ መክፈል ተገቢ ባይሆን ኖሮማ የዋልድባ መነኮሳት”…….. የሚትሠሩት በእኛ መቃብር ላይ ነው::” በማለት ስብሰባ ረግጠው ባልወጡም ነበር ::መቼም ከመነኮሳቱ በላይ መንፈሳዉያን ነን እንደማንል እርግጠኛ ነኝ::

      እኛ በፋሽስት ጣሊያን ጊዜ የነበርን ቢሆን “አይ እግዚአብሔር ከሰማይ መቅሰፍት አውርዶ እስኪያጠፋቸወ ዝም እንበል” ሳንል አንቀርም ::

      “ እግዚኦ እግዚእነ ኢታርዕየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲያን”

      Delete
  2. ahunem egzehabher yerdan!!!

    ReplyDelete
  3. Haile Michael zemerahe berhanatMarch 27, 2012 at 11:58 PM

    መነግሥት በየውይይት መድረኩ ባለፉት ሥርዓቶች ተጠቃሚ የነበረ ሃይማኖት ነው እያለ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት ለማስደፋት በማያገባውና በማያውቀው ስዘባርቅ ከነበረው ይሀንንም አቶ ተፈራ ዋልዋ በ1997 ዓ/ም ቤተክርሰቲያንን በይፋ ከተሳደቡበት ፡ከወያኔ መሥራች አንዱ የሆኑት አረጋዊ በርሔ የወያኔን ታሪክ በጻፉበት ወያኔ ትግራይን ለመገንጠል የኢትዮጵያን ሕዝብ በብዙ ነገር አስተሳስራ ያለችውንና ብሔራዊ መንፈስን የሚታስተምረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በቅድሚያ ማዳከም እንዳለበት አቅዋም ይዞ መነሳቱን (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ፡ Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims፡“A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult …the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag – an act also regularly observed …’ page 244

    “The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. …there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause” page 245) እና በተለያዩ አካላት በቤተክርስቲያን የሚፈጸመውን ተጽእኖ ስናይ ይህ ሁሉ የሚፈጸመው በመንግሥት ይሁንታ እነደሆነ እናረጋግጣለን፡፡

    በዝህም ብቻም አያበቃም የወያኔ ሤራ ፡፡ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ይህን አጀነዳ እነደያዙ በቤተክርስቲያን መዋቅር በቀጥታ መሳተፍም ጀምረዋል፡፡

    በቅርቡ የአድዋ ድል የትግራይ ሕዝብ ብቻ እንደ ነበረ ጽፈው በትግራይ ክልል ወጣቱ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያለው አመለካከት እንድለወጥ(To Brainwash) ያሰራጩትንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቁትን ገብረ ኪዳን ደስታን መጥቀስ ይቻላል::

    እነደ ጩሉሌ ነጣቂ አስመሳይ መነኮሳት መብዛታቸው ከተሐዲሶ መናፍቃን ባሻገር የዚህ ሤራ አካል ሳይሆን አይቀርም::ሰሞኑን ዋልዲባ ገዳምን አስመልክቶ የተሰጠው የቤተክህነቱና የቤተመንግሥቱ መግለጫ “የዐይጥ ምስክር ድንቢጥ” ዓይነትና ከእውነት የራቀ የሆነው አንዱ የዚህ ሤራ ይመስለኛል::

    እስኪ አቡነ ጳውሎስና ጋሻ ጀግሬዎቻቸው እስካሁን ከቤተክርስቲያን የዘረፉትን ገንዘብ ገምቱ: የት እየሄደ ነው ?

    ReplyDelete
  4. “የዐይጥ ምስክር ድንቢጥ”

    ReplyDelete
    Replies
    1. Haile Michael zemerahe berhanatMarch 28, 2012 at 5:07 AM

      የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶከሳዉያን:-

      በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚደርሰው ተጽእኖ በዓይነቱ ከኅቡእነት ወደ ግልጽነትና ንቀት ወደ ተሞላበት :መንግሥት እስካሁን ሰድቦ ለሰዳቢ ስሰጥ ከነበረበትና በሃይማኖታችን ላይ በተለያዩ አካላትና በባለሥልጣናቱ ለሚደርሰው ተጽእኖ ጆሮ ዳባ ልበስ እያለ ከሚያፍንበት ራሱ በግልጽ ገዳማቱንና አብያተክርስቲያናቱን ወደ ማፍረስ በተሸጋገረበት በብዛት ደግሞ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የተቀናጀ ኃይል ተልእኮውን በግልጽ እየፈጸመ ባለበት የቤተክርስቲያንን ሕልውና ለማስቀጠል "ምን እናድርግ ? "ማለት ግድ ይሆናል::

      በግፍ የተገደለን አንድ ሕጻን መረጃ ለማጥፋት አስከሬን ሳይመረመር “ቅበሩት!” ማለት ምን ማለት ነው?(http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=906:2012-03-21-14-41-35&catid=1:-&Itemid=18)ወዴት እየሔድን እንደሆነ እስኪ አስቡት:: ይህ ሁሉ ግፍስ በአጋጣሚ ብቻ የሚከሰት ይመስላችሁዋል ወይስ የሚሳበበው የውጭ አክራሪ እስልምና ብቻ ይማስላችሁዋል?

      ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አፍሪካን ወክለው ስለ ካርቦን ልቀት እንዳልደሰኮሩ ችግኝ ተከላ እየተባለ እንዳልተለፈፈ የዝቁዋላ ገዳም ደን ሰቃጠል መንግሥት እሳቱን ለማጥፋት እንደ መተባበር ለቅድስት ቤተክርስቲያን ካለው ጥላቻና ንቀት ብዛት የሚቀጠለው ደን መሆኑ እንኩዋ ጠፍቶት የማጥፋት ሥራውን እሳቱ ሳይጠፋ ጠፍል በማለትና ለማጥፋት የሚሄዱትንም በማስተጉዋጎል ለደኑ መቃጠል አስተዋጽኦ እንዳደረገ ያስተውሉዋል:: በቤቱዋ ቀጋ በውጭ አልጋ እነዲሉ:: “ኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ታሪክ ነው ያላት የ3000 ዓመታት ታሪክ አላት የሚባለው ውሸት ነው”ያሉትን እነደ ዝቁዋላ ያሉ ሕያው አሻራዎችን በማጥፋት ለመጭው ትውልድ እውነት አስመስሎ ለማስተላለፍ ይሆን እንዴ ሤራው?

      በቅርቡ በስልጢ ዞን ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ “እስከ ላይ ተነጋግረን ጨርሰናል አፍርሱ” ተብለው በትእዛዝ አይደል ያፈረሱብን?

      ነገሩ አጋጣሚ ወይም የተወሰኑ ሰዎች ችግር ብሆንማ ቤተክርስቲያኑን ለማፍረስ የመንግሥትን ሥልጣን ተገን ያደረጉት ከ3 ባላነሱ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት ቆመው ባየን ነበረ 1)ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም 2)ወንጀል በመሥራት 3) ሕዝብን በሕዝብ ላይ በማነሳሳት 4) የሃይማኖት ነጻነት በመጋፋት::

      ዳሩ ግን ወደ አዲስ አበባ ተዛወሩ እነጂ ለእርሳቸው ሕግ ሚሠራ አይደለም::

      እሰኪ የአራዳው ምድብ ችሎት በመምህር ዘመድኩን ላይ ያስተላለፈውን ብያኔ ተመልከቱ ::ነገ አንድ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወይም አስመሳይ በቤተክርስቲያን መድረክ እንግዳ የሆነ ትምህርት ቢያስተምር ብንቃወም ጳጳስ ካልሆንን ዘብጢያ እንወርዳለን ማለት ነው::በጋሻው የሃይማኖት ችግር ከሌለበት እዉነተኝነቱን መረጋገጥ የሃይማኖት ጉዳይ ነው ፡፡ከዚያ ባለፈ የሃይማኖት ነጻነትን ተጋፍታሃል የሚለው የአራዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሌላ ጉዳይ ነው ::(ልብ በሉልኝ የቦሌ ምድብ ችሎት ዳኛን እያልኩ አይደለሁም )፡፡

      Delete
    2. የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶከሳዉያን:-

    3. እነዚህ ደም ጠጪዎች አቡነ መለኬ ጼዴቅንና ሌሎች አባቶችን እንደ ገደሉ አባታችን አቡነ ኤልያስንና ሌሎችንም አባቶች በስውር እንዳይገድሉብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል::

      Delete
  5. እር ጎንደሮች………/…….
    እረ ጎንደሮቸ በሲሲኒወስ ዘመን የተሰውቱ ሰማእታት አፅም እንዳይወቅሳችሁ ስለእውነት ቁሙ ስለ

    ReplyDelete
  6. It is not good dession.

    ReplyDelete